ለአለም ስልጣኔ ያስተማረችዉ ሀገር !
" ዛን ዜንዲጊ አዛዲ ሴት ህይወት ነፃነት "/ኢራናውያን /
በሰዉ ልጆች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታል ገንብታ ማከም የጀመረች ።
#ethiopia | በአልጀህብራን ቀመር ሂሳብ አስልታ ለአለም ያስተማረች ። ኬሚካል በማዋሀድ የጥበብ የተራቀቀች ። በአርክቴክቸር ሳይንስና ዲፕሎማሲ በመካከለኛው ምስራቅ አሀዱ ያለች ።በጠቢባን ልጆቿ በቀጠናው ለመጀመሪያ ጊዜ ድሮን አምርታ ለገበያ ያቀረበች የሴቶችን የመማር ነፃነት በመስጠት 70 % ሴቶች በዲግሪ ደረጃ ያስመረቀች ። ሴቶችን ማስተማር እንብዛም ባልሆነበት ቀጠኒ 25% የሀገሪቱን የኒኩሊየር ሳይንቲስቶች ለሴት ልጆቿ የሰጠች ።በፕላኔታችን በምዕራባውያን ማዕቀብ ብዛት ቀዳሚ የሆነች የአለም ፖለቲካ የወሬ ማጣፈጫ ሀገረ ኢራን ።
እነሆ በዛሬው አለምን እንወቅ ዝግጂታችን ወገንተኛዉ የአዉሮጳዉያን ሚዲያዎች ክፉዋን ብቻ እየጠቀሱ የሚነግሩን ጥንታዊቷን ኢራንን ልንጎበኝ ወድደናል ።
አብራችሁን ስትዘልቁ ቀደምት ኢትዮጵያዊን ሀበሾች መኖርያ የሆነችዉን በባህል ከእኛ ጋር የምትመሳሰለዉን ከእግር እስከ እራሷ እየቃኘን ስለሀገሪቱ ሰምታችሁት የማታዉቁትን ታሪክ እንነግራችኋለንና ከፓለቲካ ምልከታ ገለል ብላችሁ ሌላ ገፅታዋን ለማየት አብራችሁን ዝለቁ ።
መቼም እኛ ኢትዮጵያዊያን ከምንታወቅበት አንዱ መግደርደርና እንብላ እንጠጣ የሚል ሰወኛ ግብዣችን ነዉ ታዲያ ይህ ባህል በእኛ ብቻ አይደለም ኢራንም ዉስጥ ወላ በሬስቶራን ወይም በካፌ እንብላ እንጠጣ መባባል ። እየፈለጉም ቢሆን መግደርደርን ከእነ ሙሉ ክብሩ እናገኘዋለን ።
ደግሞ ሌላ መቼም እንግዳ በቤት ለማስተናገድ ቡና ማፍላት የተለመደ ነዉ እነሱም ታሮፍ በሚሉት የእኛን መሰል ባህል ሻይ አፍልተዉ እግር አጥበው አልጋ ለቀው ያስተናግዳሉ ።
እንደ ታሪክ አዋቂዎች ከሆነ በኢራን ከሚገኙ በርካታ ዝርያዎች መካከል በደቡባዊ ኢራን ሆርሙዝጋን ግዛት የሚኖሩት ከ4 ክፍለዘመን ጀምሮ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ጉዳይ የሚሳተፉ መነሻቸው ከኢትዮጵያ እንደሆነ የሚነገርላቸው በአሴርያዉያን ስርዎ መንግስት ጎልተዉ የነበሩ ከሀበሻ የሄዱ አፍሮ ኢራናውያን አስተምረዋቸዉ ይሆናል ።
ወጋችን ከተገረምኩበት ጉዳይ ልሰልስ
ከሰሞኑ አንዳንዶቹ የኢራንን 1 ዶላር በሚሊዮን ተመነዘረ የሚል የገንዘብ ጉዳይ አንስተው ሙድ ለመያዝ ሲሞክሩ አይቻለሁ ። በእርግጥ ማዕቀቡ ጉዳት ቢኖረውም የኢራን የገንዘብ ቁጥር የሚጀምረው ከአምስት ሽህ ሪያል ነዉ ማለትም የእኛ አስር ሳንቲም እንደማለት ። ለማንኛውም ኢራን የብር ኖቶ በቁጥር ሲሰማ ቢያስደነግጥም የ ሁለት ሚሊዮን ድረስ ኖቶች አሉ ።
ከአሜሪካ ጋር በገባችበት እሰጣ ገባ ያልተጣለባት የማዕቀብ ናዳ የለም ። ምናልባት ሀገሪቱ ኢራን ባትሆን ኑሮ የማዕቀቦቹን ናዳ የሚሸከም ጫንቃ ሊኖራት አይችልም ።
ይህ ማዕቀብ ያላጎበጣት ኢራን ምንም ጥሬ እቃ ከዉጭ ማስገባት ባትችልም 50 ዶላር ባልሞላ ወጭ ተምዘግዛጊ ሰዉ አልባ ድሮኖች ። ሰማይ ሰንጣቂ ሚሳኤሎች ቀላልና ከባድ መሳርያዎች ተሻግራ 60% የተብላላ ኒኩሊየር ባለቤት መሆን ችላለች ።
የአያቶላሆቹ በራስ መቆም ምሳሌዎች ናቸዉ ። ዘጠና ከመቶ የመኪናውን ክፍል በራሷ የምትሰራቸዉ የጭነት የትራንስፖርት ሞተርና የግል "ኢራን ኮድሮ" ሳይፓ "ፋርስ ኮድሮ " የመኪና ብራንዶችን በአመት 1 ሚሊዮን መኪኖች አምርታ ትሸጣለች ።
ሀገሪቱ ትላንቷን አጥብቃ ትወዳለች ። ዋና ከተማዋ ታሪክን ከባህል ዘመናዊነትን ከፓለቲካ ጋር ያጣመረች ከተማ ናት ። ከእነዚህም መካከል የከተማዋ እንብርትና የሀገሪቱ የእርቀት ስሌት ዜሮ ዜሮ ተብሎ የሚጀመርበት የፋርስን ስልጣኔ ለማስታወስ የተገነባው አዛዲ ታወር የአለማችን ስድስተኛው ረጂሙ ታወር ሚላት ታወር ጨምሮ ማንነቷን ገላጭ አርክቴክቸር ዉጤቶች ። ከ400 አመታት በላይ እድሜ ያለዉ የግራንድ ባዛር ዛሬም በድምቀት የፋርስ ምንጣፎችን የሀገር በቀል ምርቶች ይሸጡበታል ።
ከ60 በላይ ዩንቨርስቲዎች መገኛ የሆነችው ቴህራን በመካከለኛው ምስራቅ ትልቅ እንደሆነ የሚነገርለት ሜትሮ ዘመናዊ ትራንስፖርት በከረሜላ መግዣ ዋጋ ለህዝብ አገልግሎት ይሰጣል ።
የዱባይን ዱባይ ሞል የቻይናውን ሳዉዝ ቻይና ሞል በመብለጥ የአለማችን ትልቁ የገበያ ሞል በኢራን ይገኛል 2ሚሊዮን ካሬ ይሰፋል ።
በቴህራን የፐርሺያን ስልጣኔ 2050 አመት መታሰቢያ ባከበረችበት ወቅት በ24 አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ንድፉ የተሰራ የነፃነት ሀዉልት የከተማዋ ግርማ ነዉ በየቀኑ አምስት ሚሊዮን ተሳፋሪዎች የሚያስተናግደው ዘመናዊ የምድር ዉስጥ ባቡርና ሜትሮ አገልግሎት በመስጠት ከጎረቤቶቿ ትለያለች ።
ከቴህራን ወጣ ስንል ደግሞ የኢራንን መንፈሳዊ ከተማ ማሻድን እናገኘዋለን ። በአመት 25 ሚሊዮን ጎብኝዎችነ የምታስተናግድ ከምድራችን ትላልቅ የእምነት ስፍራዎች አንዱ የሆነዉን መስጊድ የያዘች በሽአ አማኞች ቅድስት የተባለች ከተማ ናት ።
ኢስፋሀን ደግሞ የሀይማኖት መቻቻል የሚታይባት የአይሁዶች ቤተ እምነት የክርስትያን አብያተክርስቲያናት መሳጂዶች ጎን ለጎን የሚገኙባት ዩኔስኮ በቅርስነት የመዘገባት ከተማ ናት ።
የአያቶላሆቹ ሀገር በሀገርነት ሽህ አመት የሚለው ቁጥር ከሚያዉቁት ጥቂቶች አንዷ ከጫካ ወጥቶ ቤት ቀልሶ መኖር የጀመረባት የመግስታዊ ስርአት አስተዳደር በመስኖ ማረስ ከቃል አልፎ በፅሁፍ መግባባት መነሻው ከዚሁ ነዉ ።
አለማችን ላይ ለዘመናት የራሷን የቀን አቆጣጠር እስካሁን የምትጠቀም የራሷ ካላንደር ያላት ባህልን ከታሪክ በራስ የመቆም መቻልን ከዘመናዊነት በማዋሀድ እልፍ የቱሪስት መዳረሻዎች የያዘች ብትሆንም የአለም ስርአት በጣለባት ማዕቀብ ተጠቃሚ አልሆነችም
ለማሳረግያ አንድ ታሪክ እናካፍላችሁ ።
እስራኤል እና ኢራን የዛሬን አያድርገው እና ወዳጅ ሀገራት ነበሩ ያዉም የአሜሪካዉን ሲአይኤ ያልደረሰበት ምስጢር የተጋሩ ወዳጆች ።
ዛሬ ካልተጋደልን የሚሉት ሁለቱ ፍቅራቸዉ ለአይታ ያስቀና ነበር እስራኤል ዙርያውን ያሉ የአረብ ሀገራት ነዳጅ አንሸጥም ባሏት ወቅት ኢራን በሯን ከፍታ ከመስጠት ባሻገር ከአሜሪካ ተደብቀው ፕሮጀክት ፍላወር የተባለ የአሜሪካን ሚሳኤሎች እስራኤላውያን በእዉቀት ኢራን በገንዘብ ተባብረው ያመርቱም ነበር ።
ከአራት አስርታት ዓመታት በፊት እስራኤል ሀገር ለመሆን እና በአንድ እግሯ ለመቆም ስትጣጣር በነበረበት ወቅት ለእስራኤል የሀገርነት እውቅና ለመስጠት ቀዳሚ ከነበሩ ሁለት የእስልምና እምነት ተከታይ ሀገራት መካከል ኢራን አንዷ ነበረች።
ኢራን የአየር መቃወሚያ መርከቦች ራዳሮች ሌሎችም መሳርያዎች በእስራኤል በኩል ይቀርብላት ነበር ዛሬ ላይ የሁለቱ ሀገራት ግጭት መንስኤ የሆነው ኒኩሊየር እንድታመርትም የእስራኤል ተሳትፎ አለበት ።
ሞሳድ በመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራትን የሚሰልልበት ቢሮዉ ቴህራን ላይ ነበረው በአሁኑ ጊዜ በቴህራን ከ30 ሽህ በላይ እስራኤላዉያን ይኖራሉ ትላንት ተመልካችና ሰሚ የሚቀናባቸዉ ሁለቱ ሀገራት በሀይማኖት የተጀቦነ ፖለቲካ ነጠላቸዉ እንጂ ህዝብ ለህዝብስ ጥላቻ የለባቸውም ። ማን ያዉቃል ነገ ደግሞ ፍቅራቸው ሊመለስ ይችላል ።
ታዴ የማመይ ልጅ

8 months ago