19 days ago
ከአቧራ ወደ ዐሻራ፤ ከቅርስ ወደ ቁርስ
*************
በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ከተራ የኢኮኖሚ ምንጭነት ባለፈ ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም፣ ለብዝኃነትና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ አድርጋ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።
ሀገራችን በታሪክ፣ በባሕልና በተፈጥሮ ያላትን እምቅ ባለጠግነት ለመጠቀም ቱሪዝምን ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ ያደረገች ሲሆን፣ ይህም መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት፣ ገቢን ለማሳደግና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መሠረት ሆኗል።
መንግሥት የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅትን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመምራት፣ ቱሪዝም የጋራ ታሪክን የሚያሳይና ብሔራዊ ማንነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እንዲሆን እያደረገ ነው።
ይህን ዘርፍ ለማሳደግ ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ በሚኒስቴር ደረጃ እንዲደራጅ መደረጉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን አሳድጎታል።
በተጨማሪም የስብሰባ፣ የጉዞ፣ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን (MICE) ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን፣ የአሠራር ሥርዓቱን ለማዘመን የኢ-ቪዛና የዲጂታል አሠራሮች ተዘርግተው የቱሪስት ፍሰቱን አቀላጥፈዋል።
እንደ “ገበታ ለሀገር”፣ “ገበታ ለሸገር” እና “ኮሪደር ልማት” ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሀብትን ከልማት ጋር በማስተሳሰር ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
እነዚህ ተቋማዊ ጥረቶች እንደ እንጦጦ፣ ወንጪ፣ ሃላላ ኬላ እና ኮይሻ ያሉ መዳረሻዎችን ወደ ሥራ በማስገባት የቱሪስቶች ቁጥር ከ781 ሺህ ወደ 1.3 ሚሊዮን እንዲያድግ ማድረጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ይህም የውጭ ምንዛሪ ገቢን በከፍተኛ መጠን ከማሳደጉም በላይ በሆቴልና በአስጎብኚ ዘርፎች ለሺዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ኢትዮጵያ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት እንድትሸለም ከማድረጉም ባሻገር፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ የታሪክ ክብረ-ወሰን እንድታስመዘግብ አስችሏታል።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋናና በዓለም የተመረጠች መዳረሻ በማድረግ የቱሪስት ፍሰቱን እስከ 7.3 ሚሊዮን ለማድረስ ሰፊ ራዕይ ተቀምጧል።
ይህንን ለማሳካት አዳዲስ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎችን ማስፋፋት፣ የታሪካዊ ቅርሶች ጥገናን ማዘመን፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማበረታታትና የመሠረተ ልማት አውታሮችን ማሻሻል በትኩረት እየተከናወነ ነው።
በቀጣይም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎቱን ማዘመንና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ተጨማሪ የሥራ ዕድል መፍጠር የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት ሲሆን፣ ይህም ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች የኑሮ ደረጃ መሻሻል ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopiantourism #landoforigins #visitethiopia #miceethiopia

Comments