Logo
Getu Temesgen
☕️ የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሊካሄድ ነው! 🇪🇹✨
#ethiopia | ​ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ ለዓለም ልዩ የሆነ የቡና ሥነ-ሥርዓት ባህል ያበረከተች ሀገር ናት።

ይህንን የቆየ ማህበራዊ መስተጋብራችንን ለማክበርና ይበልጥ ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው ታላቁ ፌስቲቫል ለ2ኛ ጊዜ ሊካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።

​የፌስቲቫሉ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​📅 ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም.
​📍 በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም
​👥 ከ2 ሺህ 5 መቶ እስከ 3 ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

​🎯 ዓላማው፦ የቡና ሥነ-ሥርዓት ባህላችንን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ፣ ለዓለም ለማስተዋወቅና በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ግፊት ለማድረግ ነው።

​የዋርካ ቡና ኃ/የተ/የግል ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ ይህ ፌስቲቫል ቡና ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ያለውን ጥልቅ ማህበራዊ ትስስር የሚያሳይ ነው።

​በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በመታደም የኢትዮጵያን የቡና ባህል እንዲያደምቅ ጥሪ ቀርቧል።

​ኑ! የጥቁር ወርቃችንን ሽታና የሥነ-ሥርዓቱን ውበት አብረን እናጣጥም! ☕️🌿

​#ethiopiancoffee #coffeeculturefestival #unesco #warkacoffee #adwamuseum #addisababa #ethiopia #coffeeceremony #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.