የፊቼ ጨምበላላ በዓል በነገው እለት በአዲስ አበባ ይከበራል
የፊቼ ጨምበላላ በዓል በነገው እለት በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ በድምቀት እንደሚከበር የሲዳማ ኮሚኒቲ ማህበር አስታወቀ።
የአዲስ አበባ የሲዳማ ኮሚኒቲ ማህበር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ፕሬዚዳንት አቶ ሚኤሶ እርቤሳ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንዳብራሩት፤ ማህበሩ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበውን የፊቼ ጨምበላላ በዓል ለሰባተኛ ጊዜ እያከበረ ይገኛል።
በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ከተመዘገበ 11ኛ ዓመት የሆነውን ይህን በዓል ከሌሎች ወንድም ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመዲናዋ በጋራ ለማክበር ዝግጅቱ መጠናቀቁንም ተናግረዋል።
በዓሉ የሰላም እና የእርቅ ነው ያሉት አቶ ሚኤሶ፤ ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም ጭምር ሰላምን የሚመኝ እሴት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመግለጫው ላይ ንግግር ያደረጉት የባህል ጥናት ባለሙያው አቶ ስለሺ ወርቅነህ በበኩላቸው፤ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከዘመን መለወጫነቱ ባለፈ ጥልቅ የሆኑ የሲዳማ ነባር እውቀቶችና እሴቶች መገለጫ መሆኑን አስረድተዋል።
“ፊቼ ጨምበላላ የሰላም፣ የእርቅና የአንድነት ተምሳሌት ነው” ያሉት ባለሙያው፣ በዓሉ ከመከበሩ በፊት “አራራ ካራ” (እርቅ እናውርድ) በሚባለው ስርዓት በሰዎች መካከል እርቅ መውረድ እንዳለበትና ሰላም ሳይሰፍን በዓሉ እንደማይከበር ገልጸዋል።
በዓሉ ቱሪዝምን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አቶ ስለሺ ገልጸዋል።
በዓሉ ነገ በዕለተ አርብ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በወዳጅነት አደባባይ እንደሚከበር ተመላክቷል።
በዮሐንስ መልካሙ

2 months ago