Logo
Getu Temesgen
የሹዋሊድ በዓል
በፍቅር ከተማ ሐረር
#ethiopia | ​ለዘመናት በኩራት ለዘለቀውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የሹዋሊድ በዓል ተከብሯል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እንደተናገሩት የሐረሪ ሕዝብ ካሉት በርካታ ድንቅ ባህላዊ እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው ብለዋል።

ሹዋሊድ ከረመዳን ጾም መጠናቀቅ በኋላ የሚከበር የደስታ፣ የፍቅር እና የማኅበራዊ ትስስር መገለጫ ነው።

ሚኒስትሯ በዓሉ ኢትዮጵያ ያላትን ጥንታዊ ሥልጣኔና ለዓለም ያበረከተችውን ድንቅ የባህል ሀብት በኩራት ያስታወሰ ነውም ሲሉ ተናግረዋል።

​የሹዋሊድ በዓል ለቱሪዝም ዘርፋችን ትልቅ አቅም ይዞ የመጣ ብርቅዬ ሀብታችን ነው።

በታሪካዊቷ የሐረር ጀጎል ግንብ ውስጥ የተከበረው ይህ ደማቅ በዓል፣ በባህላዊ ጭፈራዎች፣ ውብ በሆኑ አልባሳትና የሐረሪ ሕዝብ የእንግዳ ተቀባይነት ሥነ-ሥርዓቶች የታጀበ በመሆኑ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቀልብ የሳበ ነበር።

የቱሪዝም ሚኒስትር ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ ቅርስ ለዓለም በማስተዋወቅ፣ ሐረርን ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።

​በመጨረሻም፣ ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ ታላቅ ቅርስ የመጠበቅ፣ የመንከባከብና ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት የሁላችንም ነው።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በኩላቸው
የሸዋሊድ በአል ባህላዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የኢትዮዽያዊነትና የጋራ ማንነታችንን በሚያጎላ መልኩ በታላቅ ድምቀት እንዲከበር አድርገናል ብለዋል።

ይህ በመሆኑም በርካቶች የሚታደሙበት የሰላም የፍቅርና የአብሮነት አውድማ እየሆነ መጥቷል።

ሁለቱም ስራዎቻችን በቱሪዝም ዘርፉ የተሰናሰሉ እና በሀረሪ ክልል ፈጣን የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ ሀረርን ወደ ቀድሞው ክብሯና ገናና ታሪኳ መልሰናል ሲሉም ገልጸዋል።

የዘንድሮ የሹዋሊድ በዓል የጎዳና ላይ ሩጫ በማድረግ ተጠናቋል።

በዚህም የ'ቪዚት ሐረር' የጎዳና ላይ ሩጫ በታሪካዊቷ ፈረስ መጋላ ተደርጓል"::

የሹዋሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ "ቪዚት ሐረር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና መነሻና መድረሻውን ታሪካዊው ፈረስ መጋላ ላይ ያደረገው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ፌስቲቫል፤ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ አትሌቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)

​#getutemesgen

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.