Logo
YenetaTube
ፍቼ ጫምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ

የሰላም፣ የመከባበርና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነው የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ ጫምበላላ ዛሬ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ለሰባተኛ ጊዜ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

​በበዓሉ አከባበር ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በምርቃት ተጀምሯል።

​የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፍቼ ጫምበላላ የፍቅርና የአዲስ ተስፋ መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ የጨረቃንና የከዋክብትን ዑደት የቀመረ ጥልቅ ሀገር በቀል እውቀት የሚታይበት የአለም ህዝብ ቅርስ ነው ብለዋል።

​የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዓሉ የሲዳማ አባቶች ያላቸውን ጥልቅ የሥነ-ፈለክ ዕውቀት ለዓለም ያስተዋወቀ የታሪክና የባህል ማንነት መገለጫ መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል።

​በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ በዓሉ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና የከተማዋን ብዝኀነት ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

​የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ይህ በዓል እሴቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍና የቱሪዝም ዘርፉን እንዲያነቃቃ ከክልሉ መንግሥት ጋር በትኩረት እንደሚሠራ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.