Logo
Getu Temesgen
🌼 የፍቅርና የምስጋና ስጦታ የሆነው የጌዴኦ ህዝብ "ዳራሮ" በዓል በሸራተን አዲስ ደመቀ!
#ethiopia | ​"ወደ ዩኔስኮ ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው"
​በጌዴኦ ማህበረሰብ ዘንድ እንደ አዲስ ዓመት እና የዘመን መለወጫ የሚከበረው ታላቁ “ዳራሮ” በዓል፤ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል በድምቀት ተከብሯል።

​ዳራሮ ምንድን ነው?
✅ የጌዴኦ ህዝብ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገሩን የሚያበስርበት፣

✅ ማህበረሰቡ ለአባ ገዳዎች ስጦታ ይዞ በመቅረብ ምርቃት የሚቀበልበት፣

✅ ለፈጣሪ ምስጋና እና ለቀጣይ ዘመን ምርት ጸሎት የሚደረግበት፣

✅ የሰላም፣ የስጦታ እና የምስጋና በዓል ነው።

​በሸራተን አዲስ በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ፤ በዓሉ በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ አስፈላጊው የመረጃ ማደራጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

​ዋናው በዓል የፊታችን አርብ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዲላ ከተማ በድምቀት ይከበራል።

​እንኳን አደረሳችሁ!

​#dararo #gedeo #newyear #culture #sheratonaddis #unesco #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.