2 months ago
የወልቂጤ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭት ተቋረጠ
#ethiopia | በደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ስር የሚገኘው የወልቂጤ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች፣ ከመስከረም 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የነበረበት የደመወዝ ማሻሻያ አልተደረገልንም በሚል መጋቢት 16 ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን አስታወቁ።
ሠራተኞቹ በጻፉት ደብዳቤ፤ "ሌሎች አቻ ቅርንጫፎች ጥቅማጥቅሙ ተከብሮላቸው እኛ ጋር ግን ምላሽ የሚሰጥ አካል ጠፋ" ብለዋል።
በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት እስከማስወጣት መገደዳቸውንና ማህበራዊ ሕይወታቸው መቃወሱን በምሬት ገልጸዋል።
በአማርኛ፣ በቀቤንሲኛ፣ በየሚኛ፣ በጉራግኛና በማረቂኛ ቋንቋዎች የሚተላለፈው ስርጭት ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ተቋርጦ እንደሚቆይ ሠራተኞቹ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
#ኢትዮጵያ #ወልቂጤ #ደቡብ_ሬድዮና_ቴሌቪዥን #የደመወዝ_ማሻሻያ #የሠራተኞች_መብት #getu_temesgen #ዜና #gurage #wolkite

4 months ago
#ethiopia | አጋዝ ገብረየሱስ ኃይለማሪያም ጉራጌ አቀፍ የምርምርና የድርሰር ስራዎች እንዲሁም ''የሚሊኒየሙ መሸኛና መቀበያ'' ፎቶግራፎችን ለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በስጦታ አበረከቱ።
የደራሲ ገብረየሱስ ኃይለማርያም ከ28 ዓመት በፊት (በፈረንጆቹ ሚሊኒየም የመጨረሻው ለሊት እና ንጋት) ወደ ወጨጫ ተራራ በመጓዝ ያነሷቸው የሚሊኒየሙ ጀንበር መሸኛና መቀበያ ፎቶግራፎችን ጨምሮ የጫሙት ሽካ፣ ተኬትነት አጂነት/አገኪ፣ ነሁቸርና The Gurage and their Culture የተሰኙ የድርሰት ሥራዎቻቸውን ለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አስረክበዋል።
ለጉራጌ በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበረሰብ ልማት ዘርፎች ያበረከቷቸው የሕይወት ዘመን አገልግሎቶች "አጋዝ" የሚል ባህላዊ ስያሜ የተሰጣቸው አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃይለማርያም በጉራግኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን ጽፈዋል።
ለጉራጌ ባህልና ቋንቋ ልማት ካበረከቱት አስተዋጽኦ ባሻገር የጉራጌ ባህል ማእከል እና የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅትን (ጉህራልድ) በምስረታ ሂደት ላይ ላቅ ያለ ሚና ነበራቸው። በሌሎች ሀገራዊና ዓለምአቀፍ ተቋማትም አሻራቸውን አኑረዋል።
በዚሁ ወቅት የብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተ መፅሀፍት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ኅላፊ አቶ አባተ ካሣው እንደተናገሩት ደራሲገብረየሱስ በኢትዮጵያ በብሔረሰቦች ቋንቋ ድርሰት መጽሐፍ ከጀመሩት ውስጥ ናቸው ያሉ ሲሆን ታሪካዊ ሰነዶችን ለወመዘከወር በማስረከባቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልፃለን ብለዋል።
ለደራሲ ገብረየሱስም ከወመዘክር የተዘጋጀ የእውቅናና ምስጋና የምስክር ወረቀት ሰርተፊኬት ሰጥተዋል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሠረት አመርጋ በበኩላቸው እንዲህ አይነት ታሪካዊ ስራዎች በሰነድነት ታስበው የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ መዘጋጀቱ ለሀገር ትልቅ ነገር ነው ብለዋል።
ደራሲ አጋዝ ገብረየሱስ ሀይለማርያም በበኩላቸው ስራዎቹን ሳከናውን እዚህ ይደርሳል ብዬ ባይሆንም የበርካታ ታሪክና ባለታሪኮች ሰነድ መገኛ የሆነው ወመዘክ ፎቶግራፎቼንና የድርሰት ስራዎቼን በአሻራነት መሰነድ በመቻሉ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።
ዝግጅቱ ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከሶዶ ለማ ሚድያ ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።
ዓለም አቀፍ የጉራጌ ማህበር - International Gurage Association - IGA

5 months ago
🍽️ ክትፎን ጨምሮ አራት የጉራጌ ዕሴቶች ወደ ዩኔስኮ (UNESCO) ሊያመሩ ነው
#ethiopia | የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ ታዋቂውን የጉራጌ ክትፎን ጨምሮ አራት የጉራጌ ባህላዊ እሴቶችን በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ ጥናት መጀመሩን አስታወቀ።
🥩 ክትፎ፦ ከምግብነት በላይ የሆነ የማንነት መገለጫ
የጉራጌ ክትፎ በዩኔስኮ ቅድሚያ ከተሰጣቸው እሴቶች መካከል ቀዳሚው ነው። ክትፎ ለጉራጌ ማህበረሰብ ምግብ ብቻ ሳይሆን የእንግዳ መቀበያ፣ የማህበራዊ ትስስር እና የጥበብ መገለጫ ነው። በአሁኑ ወቅት የክትፎ አዘገጃጀት፣ ከቆጮ፣ ከሚጥሚጣ እና ከንጥር ቅቤ ጋር ያለው ቁርኝት በጥልቀት እየተጠና ይገኛል።
📜 ሊመዘገቡ የታጩት አራት የኩራት ምንጮች፦
* የክትፎ አዘገጃጀት ጥበብ፦ ልዩ የሆነው የማክተፍ፣ የቅመማ ቅመም አጠቃቀምና የማቅረብ ስነስርዓት።
* ባህላዊ የክብ ቤት አሰራር፦ ያለ ሚስማር የሚገነባውና ለዘመናት የሚቆየው፣ የምህንድስና ጥበብ የታየበት የቤት አሰራር።
* የጎርደና የዳኝነት ስርአት፦ ለማህበራዊ ሰላምና ፍትህ የሚጠቀሙበት ጥንታዊና ውጤታማ የዳኝነት ስርዓት።
* የጀፎረ (መንደር) አወቃቀር፦ ለጋራ መስተጋብር በሚመች መልኩ የሚሰሩ ሰፋፊ መንገዶችና ማራኪ የመንደር አቀማመጥ።
📍 የጥናቱ ሂደት ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመረጋ እንደገለጹት፣ ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል። ጥናቱ እንደተጠናቀቀ ሰነዱ በቀጥታ በፈረንሳይ ፓሪስ ለሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መስሪያ ቤት ለውሳኔ ይላካል።
ከዚህ በተጨማሪ በዞኑ የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ መስጂዶች፣ ጥንታዊ ኪታቦች፣ ገዳማትና ታሪካዊ ዋሻዎች ለቱሪስት መስህብነት እንዲውሉ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ጉራጌ #ክትፎ #ዩኔስኮ #ቅርስ #ኢትዮጵያ #ባህል #ቱሪዝም #የጉራጌባህል #gurage #kitfo #unesco #ethiopianheritage #tourismethiopia

አዝማች ይርጋ ገብሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
አዝማች ይርጋ ገብሬ ትውልድ እና እድገታቸው አዲስ አበባ ሲሆን ባለ ትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በቀድሞ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዪኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በሀገረ አሜሪካ ተከታትለዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይም ዲፕሎማዎችን እና እውቅናዎችን አግኝተዋል፡፡
በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች እና በባህር ማዶ በመዘዋወር በመምህርነት እና ተዛማጅ ዘርፎች እንዲሁም በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ጥንቅቅ ያሉ ተመራማሪ፣ ባለሙያ እና መሪ ነበሩ፡፡
በጠቅላይ ሚንስቴር ቢሮ የኦዲት እና ኡንስቴክሽን ሀላፊ፣ በጉራጌ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት ከአባልነት እስከ ከፍተኛ አመራር ሆነው አገልግለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሀገር በቀል እውቀትን በመጠቀም ሰላም ለመፍጠር የሚያስችሉ ምርምሮችና ጥናት ማካሔድ እና ማማከር፣ በአለም ባንክ ፋይናንስ ለተደረጉ የጤና፣ የትምህርት፣የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ፕሮጀክቶች ጥናት ማካሔድ እና ማማከር እንዲሁም ከ13 በላይ ሀገራዊ ተቋማት ላይ በስራ አስፈጻሚነት፣ በቦርድ ሰብሳቢነት እና በአማካሪነት መስራታቸው ብቻ ለአብነት የሚጠቀሱ ነው፡፡
በሀገራችን የኢኮኖሚው ዘርፍ በዘመናዊ መንገድ እንዲመራ እና ስኬታማ በሆኑ ግዙፍ አክሲዎኖች ውስጥ ንቁ ተሳታፊ በመሆንም ይታወቃሉ፡፡ ለአብነትም አልፋ ትምህርት እና ስልጠናዎች አክሲዮን ማህበር፣ አልፋ አታሚዎች፣ ሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ንብ ባንክ እና ንብ ኢንሹራንስ ውስጥ ያላቸው ሚና እጅግ ግዙፍ ነው፡፡
ባለ ብዙ መልክ የሆኑት አባት እድሜ ልካቸውን ያገለገሉዋት ሰፊውን ሀገራችንን ብቻ ሳይሆን ከምንጩ ለተቀዱበት የጉራጌ ማህበረሰብም ብዙ ብዙ ግልጋሎቶችን ሰጥተዋል፡፡
በመብት ትግል ውስጥ በደርግም ሆነ በኢሀዲግ መንበረ ስልጣን ውስጥ የማህበረሰቡ መብቶች እንዲከበሩለት ፊት ለፊት ተጋፍጠዋል፡፡ እንዲሁም በኢትዮጲያ የጎልማሶች ትምህርት መምሪያ በነበሩበት ወቅት ለጉራግኛ ቋንቋ ፊደል ቀረጻ እና በጉራግኛ ቋንቋ መጽሐፍት እንዲታተሙ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡
የስዊድን ተራድኦ ድርጅት በማስተባበር የቋንጤ ትምህርት ሲመሰረት የእሳቸው ጥረት ፍሬ አፍርቷል፡፡ የሙጎ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምስረታ እና የጉፐና ትምህርት ቤት በአዲስ መልክ ሲደራጅ በገንዘብ በእውቀት እና የአመራርነት ሚና በመውሰድ ለአካባቢው ዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ፈር ቀዳጅ ሆነዋል፡፡
እንዲሁም ጉርዳ ሊንክ በተባለ ድርጅት ባህር ማዶ በሚኖሩ የቤተ ጉራጌ ተወላጆች በአሜሪካ አቋቁመው በጉራጌ ዞን እና በሌሎች አካባቢዎች ልዩ ፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገንባት ሚያስችል ፕሮጀክት ለማስፈጸም በኢትዮጲያ ተወካይ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ሰርተዋል፡፡
በተጨማሪም በባህላዊ የግጭት አፈታት ስርአት በመጠቀም ብዙ ችግሮችን መቅረፋቸውን እና እየቀረፉ በመሆኑ ለሀገራችን የሽምግልና ስርአት ሞዴል ናቸው፡፡
የጆካ ቂጫ ወደ ጹሁፍ ህግ ሲቀየር ንቁ ተሳታፉ የነበሩ እና የጉራጌ ባህል ማእከል እና የጉራጌ መንገድ ስራ ድርጅትን ከመሠረቱና ከመሩ ሰዎች መሀከልም አንደኛው ናቸው፡፡ በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ለአካባቢው ማህበረሰብ ለአስተዳደር ስራዎች ምቹ ሲደረግ የነበራቸው ሚና ከፍተኛ ነበር፡፡
የጉራጌ አባት፣ ነገር አዋቂ፣ አንደበተ ዕርቱው፣ የሀገር ሽማግሌ፣ በተለያዩ ተቋማት አንቱታን ያተረፉ ባለሙያ፣ ህግ አዋቂ እና በተለያየ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እና መሪ የሆኑት አዝማች ይርጋ የፖለቲካ ተሳትፎዋቸውም የሚደንቅ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ኢህአፓ፣ ኢሰፓ፣ ጉህዴግ፣ በቅንጅት እና ኢዜማ ውስጥ በመሳተፍ ለሀገራችን ዲሞክራሲያዊ እድገት በሰላማዊ መንገዶች እንዲመጣ ብዙ ጥረዋል፡፡
አዝማች ይርጋ ገብሬ በአደባባይ ሰውነታቸው የሰሩትን ስራ ብቻ ሳይሆን የሚደነቀው የሚኖሩበት መንደር እና ቀዬ ውስጥ (አዲስ አበባ ጌጃ ሰፈር ውስጥ ባሉ መንደሮች) መኖርያ መንደሩ ምቹ ለማድረግ በውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ በሰላም እና ደህንነት፣ በጤናና እና ማህበራዊ ዘርፎች ማን እንደሳቸው የተባለላቸው የህዝብ አገልጋይ ነበሩ፡፡
ለመላው የጉራጌ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን 😭
ነፍስ ይማር

9 months ago
የጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ
ለቱሪስቶቸ ምቹ ስፍራ
#ethiopia | መስቀልን በጉራጌ ለማክበር ለምትመጡ እንግዶቻችን የጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ እንድትጎበኙ ስንጋብዛችሁ በወፍ በረር ስለ ፓርኩ መረጃ እንስጦ
ጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ውስጥ ይገኛል።
ፓርኩ በዞኑ ከሚገኙ አራት ወረዳዎች ማለትም አበሽጌ፣ ቸሃ፣ እኖር እና እኖር ኤነር መገር ወረዳዎች ውስጥ ባሉ 24 ቀበሌዎች ያዋስኑታል።
የብሄራዊ ፓርኩ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 360 ስኴር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ፓርኩ ከመዲናችን አዲስ አበባ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ 178 ኪ.ሜ እንዲሁም ከወልቂጤ ከተማ 18ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
የፓርኩ ጂኦግራፊያዊ አቅጣጫ መገኛ ከ05 25'N ወደ 06 15'N እና 35 24'E ወደ 3600 ንፍቀ ክበብ ያመለክታል።
ከፍታው ከ1050-1835 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ይገኛል።
የፓርኩ አመታዊ የዝናብ መጠኑ በአማካኝ ከ900 እስከ 1400ሚ.ሜ ይሸፍናል።
በውስጡ የሚገኙ የአፈር አይነቶች አሸዋማ ፣ አለቶች፣ ግራጫ፣ ጥቁር አፈር እና ከፍተኛ የሆኑ ሚነራሎች ይገኙበታል።
በብሄራዊ ፓርኩ የሚገኙ በርካታ የቱሪስት መስህብ ወስጥ
ትላልቅ አጥቢ የዱር እንስሳት ዝርያዎች ፓርኩ በውስጡ ከ20 በላይ ትልልቅ የዱር እንስሳት ዝርያዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥአጋዘን፣ ጉማሬ፣ ነብር፣ ጉሬዛ፣ ከርከሮ፣ አቦ ሸማኔ፣ ድኩላ ተጠቃሽ ናቸው።
የአእዋፋት ዝርያዎች በፓርኩ እስካሁን በተደረገ ጥናት የተለያዩ ብርቅዬ የአእዋፍ ዝርያዎች እንዳሉ ያመላክታል ለአብነት ነጭ የቋጥኝ ወፍ፣ጋጋኖ፣የሀሩስድ ቆቅ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው።
በውሃ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት በፓርኩ ውስጥ በውሃ ውስጥ ብቻ የሚኖሩ በርካታ የዱር እንስሳት ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አዞ፣ ጉማሬ፣ ዘንዶ እንዲሁም ከአምስት በላይ የዓሳ ዝርይዎች ይገኙበታል።
የእፅዋት ዝርያዎች በብሄራዊ ፓርኩ ውስጥ በርካታ ዝርያ እድሜ ጠገብ ዛፎችና ሌሎች በመካከለኛና አነስተኛ የዛፍ ፤ቁጥቋጦና የሳር ዝርያዎች የተሸፈነ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ጥቅጥቅ ባለ በአረንጓዴ የተሸፈነ ጫካ እና በሁለት ረዣዥም ወንዞች ዳርቻ የተጠቀጠቀ ጫካ (Riverine forest)
ሆኖ ይገኛል።
በፓርኩ የሚገኙ የዕፅዋት ዝርያዎች ለአብነት አርሙኮ(acacia policanta)፣ነጭ ዋጮ(acacia seyal) አቢሲካ ግራር(acacia Abysinica) ፤ቶርቶሊስ ግራር(acacia tortolis) ነጭ ሴባ(combratum cleinum) የእጣን ዛፍ(poswellia paperifera) ክትክታ፣ቀውት ፣ደሬ ይጠቀሳሉ።
ሌሎች የቱሪዝም መስህቦች በብሔራዊ ፓርኩ አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች ለእይታ ማራኪ መልከዓ ምድር ለአብነት ዶባ መቅደላ መንደር፤ ሉቆ ሲቆራ፣ ናይካም ወንዝ፣ ናይካም ፏፏቴ፣ ቋሽቋሽ ፏፏቴ ፣ጃቱ ፍል ውሃ፣ ሉቄ ፍል ውሃ ፣ጓንታና ዋሻ እና ሄሬሪኬ ዋሻ ተጠቃሽ ናቸው።
#visit Gibe Valley National Park #visit Gurage #ethiopia
© Mesfin Teka

11 months ago
ወልቂጤ : የምስጋና እና የክብር ፕሮግራም
#ethiopia | ለአንጋፋው ለጉራጊኛ ድምፃዊ ደምሴ ተካ የምስጋና እና የክብር ፕሮግራም በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ
አርቲስት ደምሴ ተካ በግጥም እና ዜማ ድርሰቶቹ እንዲሁም በጉራጊኛ 10 አልበሞች እና በርካታ ነጠላ ሙዚቃዎችን የሰራ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔረሰዊ ቴአትር የረጅም ጊዜ የባህል ድምጻዊ በመሆን እየሰራ ይገኛል።
የምስጋና ፕሮግራሙ በአትነት የጉራጌ አርቲስቶች ማህበር፣ በጉራጌ ዞንና በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በጋራ በጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተዘጋጅቷል።
በመርሀ ግብሩ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ፣የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሠረት አመርጋ ፣የወልቂጤ ከተማ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ ፣አትነት የጉራጌ አርቲስቶች ማህበር አባላት ፣የዞንና ከተማ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣የከተማ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሀ -ግብር ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዓለም አቀፍ የጉራጌ ማህበር
- International Gurage Association - IGA

Sponsored by
Surafel
11 months ago
የተከዳው የጥበብ ዋርካ ሰብ ኸንከም በዛ አፈር ትትነብር ጥፉወ አትህን በገጋኸ ይሰብር ፣ ወሄነት ተሰብ ዋረም ያድር ወሄ ህን ዘር ተጡር ይነብር•••• ህይወቱን ሙሉ ሰጥቶ ሸርተት ሲል የተከዳው የጥበብ ዋርካ (ጀማል መሀመድ) #ethiopia | ጀማል መሀመድ ከውልደት እስከ እርጅና ህዝብና ሀገር በማገልገል ዘመኑን የጨረሰ ሰው ነው። ሰው ስለሆንን ሄደን ሄደን በዱኒያ ጉዳይ ልንዝል መቻላችን ሰውኛ ነው። እሱንም የገጠመው ይኸው ነው። ከአመታት በፊት ተዳፍኖ ከቀረበት ተስፋ የሚባል ልጅ ወደ ህዝብ አምጥቶት ለማንሰራራት ቢሞክርም በቋሚነት መቆም አልቻለም። ተደጋጋሚ የገንዘብ ስብራት ገጠመው። ያኔ ተስፋ ህዝብ አስተባብሮ የተከፈተው ሱቅም በኮሪደር ምክንያት ፈረሰ። ይባስ ብሎም ጤናው ታውኮ የነርቭና የዲስክ መንሸራተት ሰለባ ሆኖዋል። ጀማል መሀመድ ዛሬ እኛ በፅሁፍ በሌላ ቋንቋ(አነጋገር) የምናወራቸውን የጉራጌን ችግሮች አስቀድሞ ያየውን በምስክርነት የፈራውን በትንበያ አስቀምጧል። ጀማል ችግሮቻችንን ብቻ ሳይሆን መፍትሄያቸውንም ጭምር በሚገርም ኪነጥበባዊ ቋንቋ አመላክቷል። ዛሬ ጠፍንጎ የያዘን መንደርተኝን ጨምሮ። ስለደግነት፣ስለ ቤተሰብ፣ስለአንድነት፣ስለ አረፋና መስቀር፣ ስለአገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ መሰዋእት... ወዘተ ጀማል ማህበራዊ ስሪቶቻችንን በሙሉ በማይሰለቸው ድምፁ በተራ በተራ እያነሳ አዝናንቶ አስተምሮናል። "እንዴ እማት ህሮ ሰበና፣ወፈንቻ አትመዝሮ በዘና: ቸሀ እኖሩ ጌታ ትንብነ፣እንጭመታ አተረ ሸመነ..." ከጀማል በዘመን አቧራ የማይሸፈኑ ወርቃማ ሀሳቦች ውስጥ ነው። ጀማል የጉራጌን ባህልና ኪነጥበብን እንዳይወርድና እንዳይነካ ከፍ አድርጎ ከሰቀለው በኋላ በክብሩና በዝናው ሳይታበይ ተከታዮችንም በቅንነት አፍርቷል። የጉራጌ ባህል፣ ማንነት፣ ስነልቦና፣ ማ/ሰባዊ ፍልስፍና ከማህበሰባችን አልፎ ለመላው ኢትዮጵያውያን አድርሷል። ያለ ምንም ልዩነት በአገር ደረጃ የሚወደድ የጥበብ ሰው! ዛሬ ታሞ፣ ስራ ፈትቶ እያለ የሱን ጉዳይ የሚመለከተው ተስፋ ነዳ ብቻ መሆኑ ያሳዝናል። በመሆኑም የሚከተሉትን የመፍትሄ ሀሳቦች ማስቀመጥ ወደድኩኝ። 1. በባለሃብት ተብዬዎች በኢንቨስትመንት ስምና በቀድሞ ዘርማ ነን ባይ ፈርሴቡላዎች እየተቸበቸበ ካለው የጉራጌ መሬት በየቦታው ሰው እያንጓጠጣቸው ላሉት ለጀማልና ሌሎች የጉራጌ ባህልና ወግ እያስተዋወቁ ላሉት የጉራጊኛ ድምፃዊያን የቤት መስሪያ ቦታ በከተማዎቹ ወልቂጤና ቡታጅራ ወይም ሌላ አቻ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል። ለዚህም አትነት የጉራጌ አርቲስቶች ማህበርና የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ጫና ሊያደርጉ ይገባል። 2. በእኖር ወረዳ ዋና ከተማና በእኖር ኤነር መገር ወረዳ ዋና ከተሞች በሆኑት ጉንችሪየና ሚቄ ከተሞች ጀማል ለሰራቸው ስራዎች ባይመጥንም የቤት መስሪያ ቦታ በሁለቱም ከተሞች ሊሰጠው ይገባል። ለዚህም ከአካባቢው ተወላጆች ኮሚቴ በማዋቀር በፍጥነት ሊደረግለት ይገባል። 3. የትውልድ አካባቢው በሆነው እኖር ውስጥ በቁም እያለ በስሙ "ጀማል መሀመድ ጎዳና'' ሊሰየምለት ይገባል። ብናከብረው የምንከበረው እኛ በመሆናችን ይሄም ሊደረግለት ይገባል። በቁሙ እያየው ቢደሰት የሚገባው ነው። ለዚህም ከላይ አስቀድሜ ከወረዳው (አካባቢው) ተወላጅ ቢመሰረት ባልኩት ኮሚቴ ማስኬድ ይቻላል። 4. ለጉራጌ ባህል፣ልማትና ባህል የሚሰራው የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር እና የጉራጌ ዞን አስተዳደር ሁለቱ ለህክምና ሂደቱ ሀላፊነት ሊወስዱ ይገባል። 5. ጀማል በእርጅና ዘመኑ የገንዘብ ጉዳይ ሀሳብ እንዳይሆንበት እሱን የሚመጥን ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ልናደርግለት ይገባል። ለዚህም ወዳጆቹ፣ አትነት፣ የዞኑ መንግስት እና ጉልባማ ስራውን መስራት ይኖርባቸዋል። 6. የመሆኑ ነገር እርግጠኛ ባልሆንም በውትድርና ካገለገላት አገሩ አዲስ አበባ (ሻዋ) ላይ ቢያንስ ኮንዶሚኒየም እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ቢቻል። ይሄም መልካም ስምና ተፅእኖ ባላቸው ሰዎች ፕሮቶኮሉ ጠብቆ ከንቲባዋ ጋር ቢደርስ። በዚሁ አጋጣሚ በማናቸውም አስተባባሪ ኮሚቴዎች ውስጥ ገብቼ ለማገዝ ፈቃደኛ መሆኔን አስቀድሜ እገልፃለሁ። #unity #gurage
Comments