5 days ago
በአንድ ቦታ 10 ሺህ ስኒ ቡና መጠጣቱን ተከትሎ የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ተመዘገበ
#ethiopia | በአዲስ አበባ 10 ሺህ ስኒ ቡና በአንድ ቦታ በማዘጋጀትና በማጠጣት የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ተመዘገበ
በአዲስ አበባ 10 ሺህ ስኒ ቡና በአንድ ቦታ በማዘጋጀትና በማጠጣት የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ መመዝገቡ ተገለጸ።
የቡና ጠጡ ሥነ-ሥርዓቱ በኢስት አፍሪካ ቢዝነስ ግሩፕ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓልንና የዓለም የቡና ቀንን በማስመልከት መካሄዱ ታውቋል።
በዝግጅቱ 100 ኪሎ ግራም ቡና እና 10 ሺህ የቡና ስኒዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። ለዚህም 200 ሊትር የሚይዝ ትልቅ ጀበና እና 18 ሜትር ዙሪያ ያለው ረከቦት ተዘጋጅቷል።
10 ሺህ ስኒ ቡና መጠጣቱም በሶፍትዌር በተደገፈ የቆጠራ ሥርዓት መረጋገጡ ተገልጿል።
በተለይም የቡና ጠጡ ሥነ-ሥርዓቱ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔን በዓል ለማክበር ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶችን በባህላዊ የቡና ሥነ-ሥርዓት ለመቀበልና ቡና እንዲጠጡ ለመጋበዝ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
አዘጋጆቹ ዝግጅቱ የኢትዮጵያን የቡና ባህልና ቅርስ ለአፍሪካና ለዓለም ማስተዋወቅ፣ የቡና ባህሉንም በሰፊው ማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
#ethiopia #ethiopiancoffee #coffeeceremony #coffeeculture #africanrecord #guinnessrecord #addisababa #irreecha #horafinfinne #worldcoffeeday #ethiopianculture #coffeelovers

8 months ago
☕️ የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሊካሄድ ነው!
✨
#ethiopia | ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ ለዓለም ልዩ የሆነ የቡና ሥነ-ሥርዓት ባህል ያበረከተች ሀገር ናት።
ይህንን የቆየ ማህበራዊ መስተጋብራችንን ለማክበርና ይበልጥ ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው ታላቁ ፌስቲቫል ለ2ኛ ጊዜ ሊካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።
የፌስቲቫሉ ዋና ዋና ነጥቦች፦
📅 ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም
👥 ከ2 ሺህ 5 መቶ እስከ 3 ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
🎯 ዓላማው፦ የቡና ሥነ-ሥርዓት ባህላችንን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ፣ ለዓለም ለማስተዋወቅና በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ግፊት ለማድረግ ነው።
የዋርካ ቡና ኃ/የተ/የግል ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ ይህ ፌስቲቫል ቡና ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ያለውን ጥልቅ ማህበራዊ ትስስር የሚያሳይ ነው።
በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በመታደም የኢትዮጵያን የቡና ባህል እንዲያደምቅ ጥሪ ቀርቧል።
ኑ! የጥቁር ወርቃችንን ሽታና የሥነ-ሥርዓቱን ውበት አብረን እናጣጥም! ☕️🌿
#ethiopiancoffee #coffeeculturefestival #unesco #warkacoffee #adwamuseum #addisababa #ethiopia #coffeeceremony #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments