ውበት ሞልቶ እየፈሰሳት ነው
#ethiopia | በፍቅሯና በሰላሟ የምትታወቀው ሐረር ከተማ ዛሬ ደግሞ ውበት ሞልቶ እየፈሰሳት ትገኛለች።
በዩኔስኮ ሁለት ቅርሶችን በማስመዝገብ ቀዳሚ የሆነችው ሐረሪ ክልል አመታዊው የሹዋሊድ በዓል እያከበረች ትገኛለች።
በዓሉን የሚያከብሩ የክልሉ እንደዚሁም በአሉን ለመታደም ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ የመጡ እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ በአለም ቅርስነት መዝገብ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶቸ መካከል የሹዋሊድ በዓል አንደኛው ነው።
ይህ ኢትዮጵያን በአለም የሚያስተዋውቀው ድንቅ በዓል ታሪኩን በሚመጥን መንገድ በየአመቱ እየተከበረ ይገኛል።
እናም ዛሬ እየተከበረ በሚገኘው በዚሁ በአል ላይ ሐረሪ የውበት አክሊል አላብሷታል።
በአሉን አስመልክቶ የሀረሪ ክልል መንግስት ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፏል።
በዓሉ የክልሉን ህዝቦች የመቻቻል፣ የአብሮነትና የሰላም እሴት በማጉላትና የቱሪዝም ዘርፉን በማጎልበት ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጿል።
በዓሉ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እንዲሁም የክልሉን ልማትና ዕድገት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችል መልኩ በደማቅ ዝግጅት እየተከበረ ይገኛል።
የሸዋሊድ በዓል በተሳካ መልኩ ለማክበር የተለያዩ ኮሜቴዎች ተዋቅረው ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን፥ የሐረርን ታሪክ፣ እሴትና ባህል የሚያስተዋውቁ ሁነቶች ለታዳሚዎች እንደሚቀርቡ ነው የተገለጸው፡፡
የክልሉ መንግስት ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በዓሉ አብሮነት፣ ፍቅር፣ ሰላምና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#getutemesgen

2 months ago