6 hours ago
የኢትዮጵያ ትንሳኤ !
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብስራት አድማስ እና የዓለም ዓይኖች ማረፊያ እየሆነች ትገኛለች።
እሷ የታሪክ እምብርት፣ የሰው ዘር መገኛ እና የነፃነት ማኅተም ናት። ዛሬ ደግሞ በልጆቿ ጽናት እና በማይበገረው ህዝባዊ ወኔያቸው አዲስ የትንሳኤ ምዕራፍ እየተቀኘች ትገኛለች።
ይህ የትንሳኤ ብርሃን ለራሷ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ጥቁር ህዝብ እና ለአፍሪካ አህጉር አዲስ የብስራት አድማስ እየቀደደ ነው።
የዚህች ታላቅ ሀገር ትንሳኤ ከባዶ የተነሳ ሳይሆን፣ ከጥንታዊው የክብር ሥርዓቷ እና ካልተደፈረው ማንነቷ የተቀዳ ነው። አፍሪካ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር በነበረችበት የጨለማ ዘመን፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ብቸኛ ፋኖስ ሆና እንዳበራች ሁሉ፣ ዛሬም ያ የወርቃማ ታሪክ በዘመናዊው ትውልድ ልብ ውስጥ እንደገና እየተቀጣጠለ ይገኛል።
በመሆኑም ይህች የአናብስት ምድር የገጠሟትን ዘመናዊ ፈተናዎች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎች እና ማህበራዊ ውጣ ውረዶች በራሷ ልጆች ጥረት እና ጥንካሬ እያሸነፈች ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ህዝብ ታታሪነቱ፣ ለነጻነት ቀናኢነቱ፣ የማይበገረው ፅናቱ እና ለሀገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር አዲሱን የትንሳኤ መንገድ እያቀናው ነው።
በዚህ ጽናት ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ትንሳኤ የመላው አፍሪካም ትንሳኤ ነው። አፍሪካ ለዘመናት የድህነት፣ የጦርነት እና የተስፋ መቁረጥ ምድር ተደርጋ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስትሳል ብትኖርም፤ ኢትዮጵያ ይህንን የተሳሳተ ትረካ በተግባር እየቀየረችው ትገኛለች።
ከኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እስከ ቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶቿ፣ በአረንጓዴ ዐሻራዋ እና በኢኮኖሚ መነቃቃቷ አህጉራዊ ተምሳሌትነቷን በማደስ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም ማደግ፣ መበልጸግ እና የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ የሚያሳይ ትልቅ የብስራት አድማስ ሆኖ፣ አህጉሪቱ ወደ አዲስ የነፃነት እና የብልጽግና ምዕራፍ እንድትሻገር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው።
በዚህም የምክንያት ዛሬ የዓለም ዓይኖች ወደ እሷ እየተመለከቱ ነው። በዓለም ከሚታወቁት ግዙፍ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው የአሜሪካው ሲኤንኤን የሰሞኑ ዘገባው ይህን ያመለክታል። ይህ ዘገባ የአድናቆት እና የግርምት እይታ ነው።
በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በአቪየሽን እንዲሁም አጠቃላይ በልማት እያስመዘገበቸው ያለውን ዕምርታ በጥልቀት የዳሰሰው ሚዲያው የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ ያሳዬ ነበር፡፡ በዚህም ሀገራችን የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን እና ቱሪስቶች ቀልብ ስባለች።
ሰፊው የገበያ እምቅ አቅሟ እና ስትራቴጂካዊ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ የዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል እያደረጋት ሲሆን ፤ ከተፈጥሮ ውበቷ እስከ ጥንታዊ ስልጣኔዎቿ፣ ከላሊበላ እስከ አክሱም ዘመናትን የተሸገሩ ቅርሶቿ ደግሞ ዓለምን ማስደመማቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሩቅ ህልም ሳይሆን የዕለት ተዕለት እውነታ እየሆነ የመጣ ተጨባጭ ክስተት ነው። በራሷ ውስጣዊ ዕምቅ አቅም፣ በህዝቦቿ ላብ እና ጥረት የምታስመዘግበው ስኬት የዓለምን መድረክ እየማረከ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ትናንት የነፃነት ምልክት እንደነበረች ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ የብልጽግና እና የብስራት አድማስ ሆና በዓለም ፊት በኩራት ቆማለች ።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

13 hours ago
ከቡና ባሻገር፦ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ትኩረት ውስጥ
#ethiopia | የአሜሪካው ዓለም አቀፍ የዜና አውታር CNN በ«Connecting Africa» ፕሮግራሙ ላይ ኢትዮጵያ ከቡና ባሻገር እየገነባችው ስላለው አዲስ የኢኮኖሚ አቅጣጫ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል።
ዘገባው የቡና ታሪካዊ ሚናን በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ ዛሬ በወርቅ፣ በኃይል ልማት፣ በአቪዬሽን እና በግዙፍ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ እየከፈተች መሆኑን ያሳያል።
በዘመናዊ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ታሪክ ለብዙ ዓመታት ቡና ዋናው የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ነበር። ይሁን እንጂ ባለፈው ዓመት ወርቅ በውጭ ገቢ ቡናን በመብለጥ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱ የኢኮኖሚው እየተለዋወጠ መምጣቱን ያመለክታል።
ወርቅ፤ አዲሱ የውጭ ምንዛሬ ኃይል
የሲኤንኤን ዘጋቢ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚገኘውን የኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት ጎብኝታለች። ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የፈሰሰበት ይህ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ትልልቅ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ሲሆን፣ በዓመት 9 ቶን ወርቅ የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል። ፕሮጀክቱ በዓመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።
ይህ እድገት ሌሎች ዓለም አቀፍ የማዕድን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ እምነት እየፈጠረ መሆኑም ተጠቅሷል።
የህዳሴ ግድብ፤ የኃይልና የክልላዊ ትስስር ማዕከል
CNN በዘገባው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በስፋት አስተውሏል። ግድቡ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን በማሳደግ ኢንዱስትሪን ለማጠናከር፣ ወደ ጎረቤት ሀገራት ኃይል በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት እና የክልል ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ቁልፍ ሚና እንዳለው አመልክቷል።
ቢሾፍቱ አዲሱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ዘገባው በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለውን ግዙፍ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያም በሰፊው ያቀረበ ሲሆን፣ ይህ ፕሮጀክት 12.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የአፍሪካ ትልቁ የአቪዬሽን መሠረተ ልማት እንደሆነ ገልጿል። የመጀመሪያ ደረጃው 60 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን በዓመት የሚያስተናግድ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 110 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን በዓመት የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋና የአቪዬሽን ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚሉት
ከCNN ባሻገር ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ኢትዮጵያ በወርቅ፣ በኃይል፣ በአቪዬሽን እና በመሠረተ ልማት እያደረገች ያለውን ለውጥ በተደጋጋሚ እየዘገቡ ነው። ትኩረታቸውም ኢትዮጵያ ከባህላዊ የቡና ኢኮኖሚ ወደ የተለያዩ የገቢ ምንጮች የተመሰረተ ኢኮኖሚ እየተሸጋገረች መሆኗን ያሳያል።
መደምደሚያ
ቡና አሁንም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መለያ ሆኖ ቢቀጥልም፣ የወርቅ ማዕድን፣ የህዳሴ ግድብ፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ አዲስ አቅጣጫ እየመሩት እንደሆነ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እያመለከቱ ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቁ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣ የአቪዬሽን እና የኃይል ማዕከል የመሆን እድሏን የበለጠ ታጠናክራለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

1 day ago
ቱሪዝም - የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጫ አንዱ መሳሪያ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቱሪዝም ዘርፉ ከዋና ዋናዎቹ የክፍለ ኢኮኖሚው ምሰሶዎች ዝርዝር በመግባቱ ለዘርፉ በርካታ መሰረተ ልማቶች ተሰርተዋል፡፡
ኢትዮጵያም ለሌሎችም የሚተርፍ ገቢን መፍጠር የሚያስችል እምቅ የቱሪዝም ሃብት ቢኖራትም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሚገባው ልክ አልተጠቀመችበትም ነበር።
ዘርፉ እንዲያንሰራራ ፖሊሲ የማውጣት፣ ተቋማትን የማዋቀር፣ አዳዲስ ልማቶችን የማከናወን ሥራ ተከናውኗል፡፡
ከለውጡ ወዲህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ቅርሶችን ከመጠገን ባለፈ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ተገንብተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ እመርታ በማሳየት የሀገሪቱ ዋና የኢኮኖሚ ምንጭ እየሆነ መጥቷል።
የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ከነበረበት መዘናጋት በማውጣት የሀገሪቱን ብልጽግና ከሚያረጋግጡ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
መንግሥት ዘርፉን እንደ አንድ ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ ምሰሶ አድርጎ በመቅረጽ፣ አዳዲስ ግዙፍ መዳረሻዎችን በመገንባት እና ነባር የባህል፣ የታሪክና የተፈጥሮ ጸጋዎችን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
ቱሪዝምን ከተፈጥሮ ጥበቃ እና ከማህበረሰብ ልማት ጋር ያቀናጁ የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ሜጋ ፕሮጀክቶችን መቅረጽና መተግበር ነው።
በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን በመሳብ ለሀገሪቱ ገቢና የስራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
ለዘርፉ እድገት መንግሥት በሰጠው ትኩረት አዳዲስ መዳረሻዎችና መሠረተ ልማቶች ተገንብተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ እና በሌሎችም የሀገሪቱ ከተሞች የተከናወኑት የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበት በማጎልበት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ቱሪዝሙን ማነቃቃት ተችሏል፡፡
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የፋሲለደስ ግንብ እና የጁገል ግንብ የመሳሰሉ አንጋፋ ቅርሶችን የመጠበቅና የዕድሳት ሥራዎች በስፋት ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡
ከውጭ ጎብኚዎች ባለፈ፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ከፍተኛ እድገት እያሳየ ሲሆን፤ ዜጎች ሀገራቸውን እንዲያውቁና እንዲጎበኙ በማድረግ፤ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን አጠናክሯል።
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ የሀገሪቱን አወንታዊ ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ ረገድ የማይተካ ሚና አለው።
የቱሪዝም መዳረሻዎችን በዘመናዊ መንገድ የማልማትና አገልግሎቶችን የማዘመን ሥራዎችም በስፋት እየተሰሩ ነው፡፡
ኢኮኖሚው በብዝሃ ዘርፍ ላይ እንዲመሰረት መደረጉ በቱሪዝም ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ይበልጥ መጠቀም የሚያስችል ዕድል ፈጥሯል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ

"Why Are You Not Here?"
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአማዞን ፕራይም ቪዲዮ ፕሪሚየር!
#ethiopia | "Why Are You Not Here?" የተሰኘው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ የቴሌቪዥን ተከታታይ ሲሪዝ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ይመረቃል።
ይህ በአማዞን ፕራይም ቪዲዮ ለዓለም አቀፍ ተመልካቾች የሚቀርበው ሥራ፣ የኢትዮጵያን ውበት፣ ባህል፣ ቅርስ እና የሕዝቧን እንግዳ ተቀባይነት በልዩ መንገድ ያሳያል።
ታሪኩ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ አፍሪካዊ-አሜሪካዊ ገጣሚ በሀገሪቱ፣ በባህሏ፣ በቅርሶቿ እና በሕዝቧ ፍቅር እንዴት እንደተማረከ የሚተርክ ነው።
በምርቃቱ ላይ ሲገኙ
✅ በነፃ ይታደማሉ
✅ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ይጎበኛሉ
✅ ከአገር ውስጥና ከውጭ እንግዶች ጋር የመተዋወቅ ዕድል ያገኛሉ
ቦታ: ዓድዋ ድል መታሰቢያ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. (August 8, 2026)
ከቀኑ 9:00 (3:00 PM) ሰዓት
መግቢያ: በነፃ
ቀድመው ይመዝገቡ: EthiopianRSVP.com
ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ፤ ይህን ልዩ የፊልም ምርቃት እንዳያመልጥዎ ለወዳጆችዎም ያጋሩ!
#whyareyounothere #amazonprimevideo #moviepremiere #visitethiopia #addisababa #ethiopiancinema #getutemesgen #ጌጡተመስገን

2 days ago
ሲኤንኤን (CNN) በ‘ኮኔክቲንግ አፍሪካ’ (Connecting Africa) ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን አዲሱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በዝርዝር ዳስሷል #ebc #etv #ebcdotstream #cnninternational
2 days ago
የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በአቪየሽን ዘርፍ መሪነቷን እንደታጠናክር ያስችላታል - ሲኤንኤን
***********************
የዓለማችን ታዋቂው የዜና መረብ ሲኤንኤን (CNN) "ኮኔክቲንግ አፍሪካ" በተሰኘው ዝነኛ ፕሮግራሙ፣ የአፍሪካ የአቪዬሽን መሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየመራው ያለውን ታላቅ የመሠረተ ልማት፣ የኢኮኖሚ እና የቱሪዝም እምርታ በሰፊው ዳስሷል።
ዘገባው እንደ አመላከተው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአህጉሪቱ ምሳሌ የሚሆን የዕድገት ሞተር ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ ትስስር ማዕከል በማድረግ ረገድ ወደ አዲስ እየተሸጋገረ ይገኛል።
ዘገባው ኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፏን ዘመናዊ በማድረግ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣናን (AfCFTA) ተግባራዊነት በማፋጠን እና የተፈጥሮ ሀብቶቿን ለዓለም አስተዋውቃ የቱሪዝም አቅሟን በመገንባት በኩል እያከናወነቻቸው ያሉትን ዐበይት ተግባራት በስፋት አሳይቷል።
በዘገባው ጎልተው ከተካተቱት ዐበይት ጉዳዮች መካከል በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግንባታው የተጀመረው እና በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሜጋ ፕሮጀክት ቀዳሚው ነው።
ይህ ዘመናዊ የአቪዬሽን መንደር የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 60 ሚሊዮን፣ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ደግሞ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ እና 4 ሚሊዮን ቶን ካርጎ የማጓጓዝ ከፍተኛ አቅም ይኖረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ከሲኤንኤን ዘጋቢ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ አፍሪካውያንን እርስ በእርስ በማስተሳሰር ረገድ የመሪነት ሚናውን እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በተጨማሪም አየር መንገዱ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣናን ስኬታማ ለማድረግ እና አህጉራዊ የንግድ ትስስርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ቁልፍ ሞተር መሆኑን አስረድተዋል።
በዘገባው ላይ እንደተጠቆመው የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቶች ለዓለም አቀፍ እና ለአህጉራችን ጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ ዘመናዊ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የማረፊያ ስፍራዎች እና አዳዲስ የመንገድ ዝርጋታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ይህም ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ የምታገኘውን የኢኮኖሚ ጥቅም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው።
የሲኤንኤን ዘገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ዘርፍ እያመጣ ያለውን ብሩህ ተስፋ እና በአቪዬሽን መሠረተ ልማት አህጉራዊ መሪነቷን በጽኑ የምታረጋግጥበትን የልማት ጉዞ በግልጽ ያሳየ ነው።
የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀገራችን የአህጉሪቱ ዋና የንግድ፣ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ መገናኛ ማዕከል በማድረግ ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #bishoftuairport #ethiopianairlines #connectingafrica #cnn

በአረንጓዴ ዐሻራ ወደ ዓለም አቀፍ እውቅና የተሻገረችው ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀልበስ ያለመው ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ፤ ዛሬ በአንድ ጀንበር ከ800 ሚሊየን በላይ ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሃ ግብሩን በስኬት እያከናወነ ይገኛል።
የዘንድሮውን ሀገራዊ የችግኝ ተከላ እና የደረሰበትን ምዕራፍ አስመልክቶ የብሔራዊ አረንጓዴ አሻራ ቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ አረንጓዴ አሻራ በሀገር ውስጥ ካመጣው ሥነ-ምህዳራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ባሻገር ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል እያስገኘ ነው ብለዋል፡፡
ከስምንት ዓመታት በፊት በከፍተኛ ሁኔታ የሙቀት መጨመር፣ የደን ሽፋን መመናመን፣ የዱር እንስሳት ስደት እና የግብርና ምርታማነት መቀነስ የመሳሰሉ ችግሮች እየጨመሩ መጥተው ነበር፡፡ ይህን አሳሳቢ ሁኔታ ለመቀልበስ የተጀመረው አረንጓዴ ዐሻራ፤ እስካሁን ባለው ሂደት ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን ዶ/ር አደፍርስ ገልጸዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሁሉም ዜጋ እና ተቋማት በአንድነት በተሳተፉበት በዚህ ንቅናቄ፤ አሳሳቢ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 23.6 መድረስ ችሏል።
ኢትዮጵያ ባከናወነችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከዚህ ቀደም በየዓመቱ እስከ 92 ሺህ ሄክታር ይደርስ የነበረው የደን ጭፍጨፋ አሁን ላይ ወደ 27 ሺህ ሄክታር ዝቅ እንዲል ማድረግ ተችሏል።
በመርሃ ግብሩም የደን፣ የፍራፍሬ፣ የእንስሳት መኖ እና ልዩ ልዩ ችግኞችን በማፍላት እና በመንከባከብ ሂደት ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል።
ይህም ለዜጎች የገቢ ምንጭ ከመሆኑም በላይ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመር አስችሏል።
በአረንጓዴ ዐሻራ የመጣው ድምር ሥነ-ምህዳራዊ ውጤት፤ እንደ ሐረማያ እና አቢጃታ-ሻላ ያሉ የደረቁ እና መጠናቸው በከፍኛ ሁኔታ የቀነሱ ሐይቆች ዳግም እንዲያንሰራሩ ጭምር ትልቅ ሚና መጫወቱን ዶክተር አደፍርስ ወርቁ አብራርተዋል።
እንደ ዶ/ር አደፍርስ ማብራሪያ፣ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ሲጀመር በተለይም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ጥርጣሬ ነበረ።
ነገር ግን ኢትዮጵያ ከእቅዷ በላይ በመትከል እና አጽድቃ በማሳየት ይህንን ትርክት መቀየር ችላለች ብለዋል።
አሁን ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለ አየር ንብረት ለውጥ በንድፈ ሀሳብ ከመወያየት ባለፈ፤ የኢትዮጵያን ተግባራዊ ስራዎች እና ውጤቶች በማየት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት ጀምሯል።
ይሄም ሀገሪቱ በዲፕሎማሲው መስክ ትልቅ ትሩፋት እንድታገኝ እና ስሟ በበጎ እንዲነሳ ማድረጉ አስተባባሪው ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) እንድታዘጋጅ መመረጧ የዚሁ ጥረት ውጤት መሆኑንና፤ ጉባኤውም ትክክለኛው የአፍሪካ ኮፕ እንደሚሆን ዶክተር አደፍርስ አብራርተዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ አርሶ አደሩን እና አርብቶ አደሩን ከሚያጋጥመው የድርቅ ፈተና ከመታደግ ባለፈ፣ ኢትዮጵያ የዓለምን የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን በመቀልበስ ረገድ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
በዓለምሰገድ አሳዬ

Sponsored by
Surafel
2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል የተፈረመው የ1.616 ቢሊዮን ዶላር የሕዝብ ጤና ትብብር ስምምነት፣ የሀገሪቱን የፖሊሲ ነፃነት፣ ግልፅነት እና እውነተኛ አፈፃፀም አስመልክቶ አዳዲስ ሂሳዊ ጥያቄዎችን ማስነሳቱን አንድ አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ። በእንግሊዙ ብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ በጤና ኢኮኖሚክስ እና ፖሊሲ ትንተና ባለሙያ የቀረበው ይህ ጥናት፣ ስምምነቱ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ያጠናክራል ተብሎ ቢነገርለትም፣ ከጎረቤት ሀገራት ተሞክሮ እና ከሀገር ውስጥ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ በርካታ የትኩረት ክፍተቶች እንዳሉበት አመልክቷል።
የስምምነቱ ዝርዝር እና የኬንያ ንፅፅር
በታህሳስ 2018 (ዲሴምበር 2025) በጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ በፋይናንስ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና በአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ መካከል የተፈረመው ይህ ስምምነት፣ አሜሪካ እስከ 1.166 ቢሊዮን ዶላር (ተጨማሪ የብቃት ድጋፍን ጨምሮ) እና ኢትዮጵያ 450 ሚሊዮን ዶላር በሀገር ውስጥ የሚሸፍኑበት ነው። ነገር ግን ጥናቱ እንደሚያሳየው፣ አጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ የኢትዮጵያን ግማሽ ያህል የምትሆነው ጎረቤት ሀገር ኬንያ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራርማለች።
የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት እጅግ የበዛ ሆኖ እያለ፣ ለምን ከኬንያ በእጅጉ ያነሰ የፋይናንስ ድጋፍ ለመቀበል ተስማማች የሚለው ጥያቄ የሙያተኞችን ትኩረት ስቧል። የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ከህዝብ ብዛታቸው አኳያ ከኬንያ እጥፍ ወይም እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ድጋፍ ለምን አልጠየቁም የሚለውም ተነስቷል። ከዚህ በተጨማሪም በኬንያ የተደረገው ስምምነት በከፍተኛው ፍርድ ቤት እና በፓርላማ በግልፅነት፣ በህዝብ ተሳትፎ እና በጤና መረጃ ጥበቃ በኩል ተገቢው ምርመራ እንዲደረግበት መታገዱን የሚያስታውሰው ጥናት፣ የኢትዮጵያ ስምምነት በምን ያህል የፓርላማ እና የህግ ባለሙያዎች ምርመራና ይሁንታ አለፈ የሚለውን ይጠይቃል።
የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት እና የህዝብ ተቋማት እውነታ
ሌላው በጥናቱ የተነሳው አሳሳቢ ጉዳይ የመድኃኒት አቅርቦት እና የሀገር ውስጥ ምርት እውነታ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሐምሌ ወር ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት አቅም የሀገሪቱን 44 በመቶ ፍላጎት መሸፈን መቻሉን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ በጥናቱ እንደተመላከተው፣ ይህ ቁጥር በወረቀት ላይ የሚታይ እንጂ በህዝብ የጤና ተቋማት ውስጥ ያለውን የመድኃኒት እጥረት አይገልጽም።
በጥራዝ ነጠቅ መረጃዎች እና በህሙማን ቅሬታዎች እንደታየው፣ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ክፍያ የሚከፍሉ ወደ 32 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በመንግስት ሆስፒታሎች መድኃኒት በማጣታቸው ምክንያት ከኪሳቸው ተጨማሪ ገንዘብ አውጥተው ከግል ፋርማሲዎች ለመግዛት ይገደዳሉ። ይህም የመንግስት የሀገር ውስጥ ምርት አድጓል የሚለው መረጃ እና በምድር ላይ ያለው እውነታ አለመጣጣሙን ያሳያል።
የመልካም አስተዳደር እና የታማኝነት ጥያቄዎች
ጥናቱ ሲያጠቃልል ደግሞ የጤና ዘርፍ አመራር እና ስኬት መመዘን ያለበት በሚያምሩ ንግግሮች ወይም ስምምነቶች በመፈራረም ሳይሆን በዜጎች ህይወት ላይ በሚያመጣው ተጨባጭ ለውጥ መሆኑን ያሰምርበታል። የጤና ሚኒስቴር ለፓርላማ እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርባቸው የቁጥር ሪፖርቶች እውነተኝነት በገለልተኛ አካል ሊረጋገጥ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን፣ የመድኃኒት አቅርቦት እጥረትን ለማስወገድ እና በህዝብ የጤና ተቋማት ላይ እምነትን ለመመለስ ግልፅ አሰራር እና ቁጥጥር ሊኖር እንደሚገባ በጥናቱ አሳስቧል።

805.3 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር፤ የኢትዮጵያውያን ተአምራዊ ውሎ
*********************
ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአንድ ልብ እና በአንድ መንፈስ በመንቀሳቀስ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።
ኢትዮጵያውያን የዕድሜ ልዩነት ሳይበግራቸው ከሕፃናት እስከ አዛውንት ከአካል ጉዳተኞች እስከ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች በጋራ በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። ይህ የነቃ ተሳትፎም የማህበረሰቡን አንድነትና ለአካባቢ ጥበቃ ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ነው።
ይህ መርሃ ግብር ልጆችን በማሳተፍ ስለ አካባቢ ጥበቃ አስፈላጊነት በተግባር የሚማሩበት ልዩ መድረክ ሆኗል። ህፃናት ከወዲሁ የችግኝ እንክብካቤን እንደ ባህል እንዲለምዱና የነገዋን አረንጓዴ አገር የመረከብ ሃላፊነታቸውን ገና በሕፃንነታቸው እንዲረዱ ያግዛል።
በተጨማሪም ሀገራዊ አንድነትን በተግባር ከመግለጹ በላይ ለአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ ፈተናዎች ምላሽ ለመስጠትና የኢትዮጵያን የመጻኢ ዘመን ዕጣ ፈንታ በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ ንቅናቄ ነው።
ይህ የተቀናጀ ሀገራዊ ርብርብ የትናንቱ የአድዋ ድል የነፃነት አርበኝነት በተፈጥሮ ጥበቃ የሚደገምበት የዘመናችን የጀግንነት ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።
ቀደምት አባቶች በአድዋ ተራሮች ላይ ልዩነቶቻቸውን አክስመው ለሀገር ነፃነት እንደቆሙ ሁሉ የዛሬው ትውልድም ድህነትንና የተፈጥሮ መራቆትን ለማሸነፍ ዕውቀቱን ጉልበቱንና ፍቅሩን አስተባብሮ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ የተራቆቱ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ የአፈር መሸርሸርና የጎርፍ አደጋዎች እንዲቀንሱ እንዲሁም የከርሰ ምድር ውሃ እንዲበለጽግ በማድረግ ረገድ ትልቁን ድርሻ ታበረክታለች።
ከአካባቢ ጥበቃ ፋይዳው ባሻገር መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት የሚያነቃቃ ታላቅ ዕድል ፈጥሯል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በችግኝ ማፍላት በጉድጓድ ዝግጅትና በተከላ ሥራዎች በመሰማራት ሰፊ የሥራ ዕድል ያገኙ ሲሆን በተለይም እንደ ቡና፣ አቮካዶና ማንጎ ያሉ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ተክሎች ትኩረት ማግኘታቸው ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረት ጥሏል።
በተጨማሪም ይህ ሀገራዊ ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት መዛባትን ለመቋቋም የሚረዳና ኢትዮጵያ ለዓለም አረንጓዴ ልማት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሕያው ውርስ ነው።
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቅድመ ዝግጅት ከተያዘው እቅድ በላይ በመፈጸም በዛሬዉ ዕለት ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን 26.2 ሚሊየን ሰዎች ተሳትፈዋል በዚህም 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት መሸፈን ተችሏል በዚህም ታሪካዊ ስኬት ተመዝግቧል።
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው አገራዊ የችግኝ ተከላ ዘመቻ የህዝባችንን የተቀናጀ የተቀናጀ ጥረት እና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት በአለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ ሁነት ሆኖ አልፏል።
በዘንድሮው አመት እስካሁን ባለው ጊዜ ከ6.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው የተገለጸ ሲሆን የተያዘውን አጠቃላይ እቅድ ለማጠናቀቅ ቀሪ የሆኑት 1.5 ቢሊዮን ችግኞች ደግሞ በሚቀጥሉት ወራት ተተክለው የሚጠናቀቁ ይሆናል።
የዚህ ታሪካዊ ዘመቻ እውነተኛ ስኬት የሚለካው በተከላው ሂደት ብቻ ሳይሆን ከተከላ በኋላ በሚደረግ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤና ጥበቃ በመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ የተከላቸውን ችግኞች ተንከባክቦ ለፍሬ የማብቃት አደራ አለበት።
በብሌን ደምበሎ

3 days ago
መልካም ጉዞ...
ተፃፈ በመሐሪ ነጋሽ
(የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሚኒኬሽን )
#ethiopia | ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድናችንን በከፍተኛ ኩራትና በመልካም ምኞት ወደ አሜሪካ ኦሪገን ሸኝተናል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቻችን በተሟላ ዝግጅት ወደ ሻምፒዮናው እንዲያቀኑ ሱሉልታ በሚገኘው የጀግናው ኦሊምፒያን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሆቴል በማሳረፍ አስፈላጊውን ድጋፍ፣ ክትትልና ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
የቀነኒሳ በቀለ ሆቴልም አትሌቶቻችንን እንደቤተሰቦቹ በመቀበል፣ በፍቅር፣ በአክብሮትና በልዩ እንክብካቤ እስከ ሽኝታቸው ድረስ አግዟቸዋል።
ለዚህ ውድ አስተዋፅኦ ከልብ የመነጨ ምስጋና ተቀበሉ
ዓለም የሚጠብቀው ሻምፒዮና 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (World Athletics U20 Championships) ሻምፒዮና ....
በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው ሄይዋርድ ፊልድ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ይካሄዳል።
ከ1,700 በላይ ወጣት አትሌቶች ከ190 የሚጠጉ አገራት በ44 የውድድር ዓይነቶች ላይ ይፎካከራሉ።
ዩጂን ከተማ በግምት 180,000 የሚጠጋ ህዝብ ያላት ብትሆንም፣ በዓለም ላይ "Track Town USA" በሚል ስም የምትታወቅ የአትሌቲክስ ዋና መዲና ናት።
የሻምፒዮናው ትኬቶች በፍጥነት እየተሸጡ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፣ ውድድሩም በብዙ የዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ኔትወርኮች፣ ዲጂታል መድረኮች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የስፖርት ጋዜጠኞች ይሸፈናል። የዚህ ውድድር ቀደምት እትሞች በ140 በላይ አገራት በቴሌቪዥን ተሰራጭተው 16 ሚሊዮን በላይ የተጠራቀመ የቲቪ ተመልካች ደርሰው ነበር።
በ2024 በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሐስ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ በአጠቃላይ 9 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በዓለም 2ኛ ደረጃን ማስመዝገቧ ይታወሳል።
ዘንድሮም አትሌቶቻችን በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር፣ 3000 ሜትር መሰናክል፣ 400 ሜትር እና በርምጃ ውድድሮች ላይ የኢትዮጵያን ስም በክብር ለማስጠራት ዝግጁ ናቸው።
ለጀግኖቻችን...
ውድ አትሌቶቻችን!
ከእናንተ ጋር የሚጓዘው የኢትዮጵያ 60 ዓመታትን ያስቆጠረ የድል ታሪክ ነው፤ የአበበ ቢቂላ ጨምሮ
የብዙ ጀግኖች የድል አሻራ ነው።
ኢትዮጵያውያን ልብ ከእናንተ ጋር ነው። በእግራችሁ የምትሮጡት ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችሁ፣ ለሕዝባችሁ እና ለመጪው ትውልድ ነው።
መልካም ጉዞ!
መልካም ውድድር!
መልካም ዕድል! 🇪🇹❤️

የአረንጓዴ ዐሻራ የሰባት ዓመታት ሰባት አንኳር ስኬቶች
*************
አረንጓዴ ዐሻራ በኢትዮጵያ ምድር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ ሀገራችንን ከአፈር መሸርሸር እና ከበረሃማነት የመታደግ ሀገራዊ ራዕይ ብቻ ሳይሆን፤ የምድርን ሕይወት የሚያድስ፣ የዜጎችን ሥነ-ልቦናዊ አስተሳሰብ የሚቀርጽ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም የሚገነባ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሆኖ ዘልቋል።
ይህ ሀገራዊ የሕልውና ጥረት ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስትራቴጂዎች ጋር ተናብቦ ባለፉት ሰባት ዓመታት ያስመዘገባቸው ሰባት ዋና ዋና ተጨባጭ ስኬቶች እንደሚከተለው ተተንትነዋል።
1. የችግኝ ብዛትን ከጽድቀት ምጣኔ ጋር ያጣመረ አዲስ ታሪካዊ ሽግግር
ባለፉት ሰባት ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው ብቻ ሳይሆን፣ የተከላው ዋና ትኩረት ወደ ጥራት እና ድኅረ-ተከላ እንክብካቤ በማደጉ የችግኞች ጽድቀት ምጣኔ ከ80 በመቶ በላይ ማደግ ችሏል።
ይህም ቀደም ሲል የነበረውን "መተከል እንጂ አለመጽደቅ" የሚል የብክነት ታሪክን በመቀየር በቆላ እና በደጋ አካባቢዎች የተጎዱ መሬቶች በፍጥነት አረንጓዴ እንዲለብሱ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ሚዛን እንዲጠበቅ አድርጓል።
2. ከአካባቢ ጥበቃ ወደ የምግብ ዋስትና የተደረገ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር
አረንጓዴ ዐሻራ ከተፈጥሮ የደን ዛፎች ባሻገር እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አፕል እና ቡና ያሉ ፍሬያማ ተክሎችን በስፋት አካትቷል።
ይህ ስትራቴጂያዊ እርምጃ ፕሮጀክቱን ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ እና አባወራዎችን የገበያ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ብሎም የሀገራችን የግብርና ምርት የወጪ ንግድ የሚያሳድግ የኢኮኖሚ ሞተር አድርጎታል።
ይህም የአካባቢ ጥበቃን ከዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ማሻሻል ግብ ጋር በማስተሳሰር ዘላቂነቱ የተረጋገጠ የልማት ምሰሶ እንዲሆን አስችሎታል።
3. የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ
በመላ ሀገራችን የተቋቋሙት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ለብዙ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች እና ለሴቶች አዲስ እና ዘላቂ የገቢ ምንጭ ሆነዋል።
ችግኝ ማፍላት፣ መንከባከብ እና ለገበያ ማቅረብ በራሱ አዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የሀገራችንን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጅማሮ በጠንካራ መሠረት ላይ አኑሮታል።
ችግኞች ከተተከሉ በኋላ የሚደረገው ጥበቃ እና ክብካቤም በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ቋሚ የሥራ ዘርፍ መሆን ችሏል።
4. የውኃ ሀብት እና የታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ዋስትና
በስፋት የተከናወነው የደን ልማት እና የአፈር ጥበቃ ሥራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራዊ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች በደለል እንዳይሞሉ የመከላከል ታሪካዊ ሚና ተጫውቷል።
በተጨማሪም የከርሰ ምድር ውኃ መጠን እንዲያገግም እና የደረቁ የምንጭ ውኃዎች መልሰው እንዲፈልቁ በማድረግ አስተማማኝ የውኃ ዋስትናን እያረጋገጠ ይገኛል።
ይህ ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የመጠበቅ አቅም ለኢትዮጵያ ብልጽግና ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን የውኃ ምንጭ ለሆነችላቸው የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ትልቅ ትሩፋት ነው።
5. አረንጓዴ ዲፕሎማሲ እና የቀጣናዊ ትሥሥር ማጠናከሪያ
ኢትዮጵያ ያዘጋጀቻቸውን ችግኞች እንደ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ላሉት ጎረቤት ሀገራት በማጋራት፣ የምሥራቅ አፍሪካን እና የአፍሪካ ቀንድን የቀጣና አየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት በጋራ የመከላከል መሪነት ሚናዋን በተግባር አሳይታለች።
ይህም አረንጓዴ ዐሻራን የድንበር ተሻጋሪ ዲፕሎማሲ፣ የቀጠናው ሰላም እና የጋራ ልማት መሣሪያ አድርጎታል።
በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል የአረንጓዴ ልማትን በሀገሮቻቸው እያስፋፉ ይገኛሉ።
ከዚህ ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ባመጣቻቸው ተጨባጭ ስኬቶች “ዘላቂ የደን ልማት አያያዝ እና አጠቃቀም” በሚል ዘርፍ ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) ከፍተኛ እውቅናን አግኝታለች።
6. የከተሞች ሥነ-ምኅዳር መታደስ እና የኮሪደር ልማት ውበት
አረንጓዴ ዐሻራ በገጠር ተራራዎች ብቻ ተወስኖ ሳይቀር ወደ ከተሞች በመግባት የዘመናዊ ፓርኮች ግንባታ፣ የከተማ አረንጓዴ ልማት እና አሁን ላይ በስፋት እየተተገበረ ላለው የኮሪደር ልማት ዋነኛ አካል ሆኗል።
ይህም የከተሞችን የአየር ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩም በላይ፣ የሥነ-ሕይወት ስብጥርን ወደ ነበረበት በመመለስ እና ለዜጎች ምቹ የመዝናኛ እና የኑሮ አካባቢን በመፍጠር የከተሞቻችንን ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመለወጥ ላይ ይገኛል።
7. ሕዝባዊ ንቅናቄ እና የዜግነት አገልግሎት ባህል ግንባታ
በአንድ ጀምበር በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ችግኝ የመተከል ልምዳቸው፣ የአካባቢ ጥበቃን ከዘመቻነት አውጥቶ የባህል እና የዜግነት ግዴታ አካል አድርጎታል።
ይህም የሕዝባዊ ወንድማማችነትን ያጠናከረ እና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤን በማሳደግ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር እጅግ ግዙፍ ማኅበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ስኬት ነው።
በአጠቃላይ አረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተፈጥሮ ሀብታችንን ከመመለስ አልፎ ሀገራዊ አንድነትን ያጠናከረ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ አቅማችንን የገነባ እና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ አቅራቢ ሀገር ያደረገ አንጸባራቂ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #climateaction #greendiplomacy #greeneconomy

4 days ago
የውኃ ሉዓላዊነታችን በተግባር፡ ከ18 ዓመታት የእንቅልፍ ዘመን የነቃው የመገጭ ግድብ
****************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ በአማራ ክልል እየተከናወኑ ያሉ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከእነዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን የረዥም ዘመን የመጠጥ ውኃ ጥያቄ የሚመልሰው እና ሰፊ የመስኖ ልማት አቅም ያለው የመገጭ ግድብ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡
ግንባታው በ2001 ዓ.ም. የተጀመረው ይህ ግድብ፣ ላለፉት 18 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፕሮጀክት አመራር ድክመት ተጓትቶ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ በ2017 በጀት ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጥተኛ አመራር፣ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ የነበረው ተቋራጭ ከፕሮጀክቱ እንዲወጣ ተደርጎ ሥራው ለሀገር በቀል ተቋራጭ ተሰጥቷል፡፡
የውጭ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተጋብዘው የመሬት መንሸራተት ችግሩ በጥናት እንዲፈታ መደረጉ፣ እንዲሁም ሥራው በቀን እና በሌሊት ፈረቃ እንዲከናወን መወሰኑ ፕሮጀክቱን ከእንቅልፉ ቀስቅሶ ወደ ጤናማ እና ፈጣን የአፈጻጸም ምዕራፍ አሸጋግሮታል፡፡
በዚህም የግንባታው ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በቅርቡ ለፍሬ እንደሚበቃ ይጠበቃል፡፡
የመገጭ ግድብ ከግንባታ ባለፈ የኢትዮጵያውያን የልማት ፅናት ማሳያ ነው፡፡ አጠቃላይ የውኃ መያዝ አቅሙ 185 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 116 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚሆነው ለመስኖ ልማት የሚውል ነው፡፡
ይህም 17 ሺህ ሔክታር መሬትን በመስኖ በማልማት የጎንደር ከተማን እንዲሁም የምሥራቅ እና የምዕራብ ደምቢያ አካባቢ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ክልሉ ያለውን ሰፊ የውኃ እና የመሬት ሀብት አቀናጅቶ ለመጠቀም እየተገነቡ ካሉ ሰፋፊ የመስኖ አውታሮች አንዱ የሆነው ይህ ፕሮጀክት፣ የሀገራችን የግብርና ትራንስፎርሜሽን እና የምግብ ዋስትና ራዕይ በጉልህ የሚያሳካ የዘመን ትሩፋት ነው፡፡
ይህ የኢትዮጵያ የማይቆም የልማት እርምጃ እንደተለመደው የግብፅ ሚዲያዎችን ሰላም ነስቷል፡፡
የመገጭ ግድብ በጣና ሐይቅ ገባር ወንዝ ላይ የሚገነባ መካከለኛ ፕሮጀክት ቢሆንም፣ የግብፅ ሚዲያዎች ፕሮጀክቱን በተመለከተ ሰሞኑን እያስተጋቡት ያለው ጩኸት ሀገሪቱ ከያዘችው የቆየ እና ራስ ወዳድ የውኃ ፖሊሲ የሚመነጭ ነው፡፡
ግብፅ ኢትዮጵያ የውኃ ሀብቷን እንዳትጠቀም የማስፈራራት ፖሊሲን ብትከተልም፣ ኢትዮጵያ ግን ታላቁን የሕዳሴ ግድብ አጠናቅቃ ልማቷን የሚያፋጥኑ እንደ መገጭ ያሉ ግድቦችን መቀጠ "ኢትዮጵያ አትጨበጥም" የሚል ድንጋጤ ፈጥሮባቸዋል፡፡
ግብፅ አሁንም ጊዜ ያለፈባቸውን የቅኝ ግዛት ውሎች እያነሳች የትኛውም የኢትዮጵያ ልማት ግብርናዋን እንደሚጎዳ በማስመሰል ከእውነት የራቀ ኢ-ፍትሐዊ ትርክት ታራምዳለች፡፡
ኢትዮጵያ ግን ፍትሐዊና ምክንያታዊ የውኃ አጠቃቀም መርህን (CFA) በመከተል ሕዝቧን ለመመገብ የገዛ ሀብቷን የማልማት ተፈጥሯዊና ሕጋዊ መብቷን እያስከበረች ትገኛለች፡፡
ከዚህም ባሻገር እንደ መገጭ ባሉ የኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች ግድብ መሥራት የውኃ ትነትን እጅግ የሚቀንስ መሆኑ የኢትዮጵያ ልማት ማንንም የማይጎዳ ለመሆኑ ሳይንሳዊ ማረጋገጫ ነው፡፡
እውነታው ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ምዕራፍ ከትላንቱ በእጅጉ የተለየ መሆኑ ነው፡፡ ሀገራችን የዜጎቿን ሕይወት ለመለወጥ እና ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን የልማት ጉዞ በማንኛውም የውጭ ኃይል እጅ ጥምዘዛ የማታቆምበት ታሪካዊ ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡
የመገጭ ግድብም ሆነ ሌሎች በሀገራችን እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የዚሁ ሉዓላዊ መብት አካል ናቸው፡፡
ማንም ይጩህ ማን፣ ኢትዮጵያ በራሷ ሀብት፣ በራሷ አቅም እና በራሷ ጊዜ የጀመረቻቸውን የልማት ሥራዎች ከዳር በማድረስ ታሪኳን በአዲስ መልክ መጻፏን አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡
መንግሥትም በቀጣይ የመገጭ ግድብ ቀሪ ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ፣ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችን በማጠናከር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የዲፕሎማሲ ሥራውን በማስፋት የኢትዮጵያን ብልጽግና ያረጋግጣል፡፡
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #megechdam #nile #development #amhararegion

(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) የሶማሌላንድ የሀገርነት ጥያቄ እና አለም አቀፍ እውቅና የማግኘት ፍላጎት በዋናነት የተመሰረተው በቅኝ ግዛት ወቅት በነበራት ግልጽ ድንበር፣ እ.ኤ.አ. በ1960 ለተወሰኑ ቀናት አግኝታው በነበረው ነጻነት እና በ1991 ያወጀችው ነጻነት አዲስ የመገንጠል ጥያቄ ሳይሆን የነበረን ሉዓላዊነት የመመለስ እርምጃ ነው በሚለው መከራከሪያ ላይ ነው። እንግሊዝ ከ1884 እስከ 1886 በሰሜን ሶማሊያ ከሚገኙ የጎሳ መሪዎች ጋር ባደረገችው የስምምነት ውል መሰረት የሶማሌላንድን ግዛት የመሰረተች ሲሆን፣ የውጭ ድንበሮቿም ከፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ኢትዮጵያ ጋር በተደረጉ አለም አቀፍ ስምምነቶች የተከለሉ ነበሩ። ሰኔ 26 ቀን 1960 ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን የተቀዳጀችው ሶማሌላንድ፣ ከአምስት ቀናት በኋላ በፈቃደኝነት ከጣሊያን ሶማሊያ ጋር በመዋሃድ የሶማሊያ ሪፐብሊክን መስርታለች። ይሁን እንጂ የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስት በ1991 መውደቁን ተከትሎ፣ ሶማሌላንድ ከውህደቱ በፊት ወደ ነበራት ነጻነት መመለሷን በማወጅ የ1960ዋን ግዛቷን ይዛለች።
የሶማሌላንድ ዋነኛ የህግ መከራከሪያ አዲስ ነጻ የሚወጡ ሀገራት በቅኝ ግዛት ወቅት የነበራቸውን ድንበር ጠብቀው ሊቀጥሉ ይገባል የሚለው መርህ ነው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ1964ቱ የካይሮ ውሳኔው እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የመመስረቻ ሰነዱ ላይ አባል ሀገራት በነጻነት ጊዜ የነበራቸውን ድንበር ሊያከብሩ እንደሚገባ አስፍረዋል። በመሆኑም ሶማሌላንድ አለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷ የቅኝ ግዛት ድንበርን ከመጠበቅ ባለፈ አዲስ ድንበር የማካለል ስራ አይደለም በማለት ትከራከራለች። አቋሟም ከዚህ ቀደም ሉዓላዊ ሀገር እንደነበረች፣ የ1960ውን ውህደት በራሷ ፈቃድ እንደፈጸመች እና የ1991ዱ እርምጃዋም የከሸፈን ውህደት ማፍረስ እንጂ አዲስ ግዛትን ከሶማሊያ መገንጠል አይደለም በሚሉ ሶስት ምሶሶዎች ላይ የቆመ ነው። ይህ አቀራረብ ሶማሌላንድን ምንም አይነት የቅኝ ግዛት ወይም አለም አቀፍ ድንበር መሰረት ከሌላቸው የመገንጠል ጥያቄዎች የተለየች ያደርጋታል።
የሶማሌላንድን ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ማነጻጸር የጉዳዩን የዲፕሎማሲ ውስብስብነት በደንብ ያሳያል። ሁለቱም ግዛቶች የተለየ የቅኝ ግዛት ታሪክ፣ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር የተደረገ የትጥቅ ትግል እና ከ1991 በኋላ ውጤታማ የሆነ ራስን በራስ የማስተዳደር ልምድ አላቸው። ይሁን እንጂ የኤርትራ የነጻነት ጥያቄ የኢትዮጵያን የሽግግር መንግስት ፈቃድ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህዝበ ውሳኔ ታዛቢነትን በማግኘቱ ፈጣን አለም አቀፍ እውቅናን ሊያጎናጽፋት ችሏል። በሶማሌላንድ በኩል ግን ጠንካራ ተቋማትን መገንባት እና ህዝበ ውሳኔ ማካሄድ ብትችልም፣ ከሶማሊያ መንግስት የተገኘ ስምምነትም ሆነ እንደ ኤርትራው አይነት አለም አቀፍ ድጋፍ ባለማግኘቷ የዲፕሎማሲ እውቅናው ሊዘገይባት ችሏል። ይህ የሚያሳየው ውጤታማ አስተዳደር እና ታሪካዊ ድንበር መኖር ብቻውን በቂ እንዳልሆነ እና እውቅና ማግኘት በስምምነት፣ በቀጠናዊ ፖለቲካ እና በዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ላይ በእጅጉ የተመሰረተ መሆኑን ነው።
የአፍሪካ ህብረት በ2005 ወደ አካባቢው አጣሪ ቡድን ልኮ የሶማሌላንድ ጥያቄ በቅኝ ግዛት ድንበር እና በቀድሞ ነጻነቷ ላይ የተመሰረተ ታሪካዊ መነሻ እንዳለው ቢገነዘብም፣ አሁንም ድረስ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ቅድሚያ መስጠትን መርጧል። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሶማሌላንድን እውቅና መስጠት በሌሎች አካባቢዎች የመገንጠል ጥያቄዎችን ሊያነሳሳ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ሶማሌላንድ በበኩሏ የድሮውን ድንበር መመለስ እንጂ አዲስ ድንበር መፍጠር አይደለም ስትል ምላሽ ትሰጣለች።
ሶማሌላንድ በቅኝ ግዛት ድንበር እና በቀድሞ ነጻነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የህግ መከራከሪያ ብታቀርብም፣ የኤርትራን ተሞክሮ ስንመለከት የህግ ትንታኔ ብቻውን እውቅናን እንደማያመጣ መገንዘብ ይቻላል። ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ጋር የደረሰችበት ምንም አይነት ስምምነት ባለመኖሩ፣ የእውቅና ጉዳይ አሁንም ድረስ አለም አቀፍ ተቋማት የድሮዋን ሉዓላዊ ሀገር ዳግም መመለስ አድርገው ይቀበሉታል ወይስ የሶማሊያን የግዛት አንድነት የሚፈታተን ድርጊት አድርገው ይቆጥሩታል የሚለው ጉዳይ የፈተና መድረክ ሆኖ ቀጥሏል።

የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና፤ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በደማቅ ሥነ-ስርዓት ተሸኘ
#ethiopia | በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት በሚገኘው ታሪካዊው Hayward Field ከነሐሴ 5 እስከ 9 ቀን 2026 (ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም.) የሚካሄደውን 21ኛውን የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ የሚያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ልዑክ ቡድን በአዲስ አበባ ደማቅ የሽኝት ሥነ-ስርዓት ተካሂዶለታል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ አሠልጣኞች፣ ቤተሰቦች እና የስፖርት ደጋፊዎች በመገኘት ለወጣት አትሌቶቹ የስኬት ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ቡድን በመካከለኛና ረጅም ርቀት ሩጫዎች፣ በእንቅፋት ሩጫ እና በተወሰኑ የሜዳ ውድድሮች ጠንካራ ተስፋ ተጥሎበታል።
የሻምፒዮናው መድረክ የዓለም የወደፊት የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮኖች የሚፈጠሩበት እንደሆነ ይታወቃል፤ በቀደሙት ውድድሮችም በርካታ ታዋቂ አትሌቶች ከዚህ መድረክ ተነስተው ዓለም አቀፍ ስኬት አስመዝግበዋል።
ዘንድሮ በኦሪገን የሚካሄደው ሻምፒዮና ከ135 በላይ አገራትና ከ1,700 በላይ ወጣት አትሌቶችን በአንድ ስፍራ ያሰባስባል። ይህም የዓለም ወጣት አትሌቶች ከፍተኛ የውድድር መድረክ በመሆኑ ለተሳታፊዎች ትልቅ የልምድና የስኬት ዕድል ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ በወጣቶች አትሌቲክስ መድረክ የበርካታ የዓለም ሻምፒዮኖችን በማፍራት የታወቀች ሲሆን፣ የዘንድሮውም ቡድን ያንን ታሪክ ለመቀጠል በከፍተኛ ዝግጅት ወደ ውድድሩ እያቀና ነው።
የስፖርት ቤተሰቡም ወጣት አትሌቶቹ የኢትዮጵያን ስም በክብር እንዲያስጠሩ ምኞቱን ገልጿል።
መልካም ዕድል!

5 days ago
«ከለውጡ በኋላ የነበረውን የመታፈን ስሜት ለማናፈስ በተደረገው ጥረት ውስጥ የተቀላቀሉ ቢምቢዎች ነበሩ»- ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ ጉዞንና ከዚያ በኋላ በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የታዩትን ኩነቶች አስመልክተው ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ በሰጡት ማብራሪያ፣ የዐማራ ሕዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለለውጥና ለዕድገት ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጉን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ ከለውጡ ማግሥት የነበረው ጉዞ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ተስፋ የተሞላበት፣ «በዚህ ለውጥ እሠራለሁ፣ አተርፋለሁ፣ ሀገር አጠናለሁ» የሚል ሕልም በሰፊው የተገለጸበት ወቅት ነበር። ከለውጡ በፊት በነበረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ የመዘጋትና የመታፈን ምልክቶች እንደነበሩ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የተዘጋን ቤት መስኮት ከፍቶ እንደማናፈስ ሁሉ ፖለቲካውንም ማናፈስ አስፈላጊ ነበር ብለዋል።
ሆኖም መስኮቶች ሲከፈቱ ንጹሕ አየር ብቻ ሳይሆን «ቢምቢዎችና ትንኞችም» አብረው እንደሚገቡ በመግለጽ፣ በፖለቲካው ምህዳር መከፈት ምክንያት አጋጣሚውን በመጠቀም ሁኔታዎችን ወደ ሥጋትና ድንግዝግዝነት ለመቀየር የሞከሩ አካላት እንደነበሩ አስረድተዋል።
«ቢምቢ በሳይዟ በጣም ትንሽ ናት፤ ነገር ግን ድምፅ በማሰማት እንዳትተኛ ታውክሃለች። ሁለተኛውና ከዚያ የሚከፋው ደግሞ በመንደፍ ደምን መምጠጧና በሽታ ማምጣቷ ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዓውድ ውስጥም ከፍተኛ ድምፅ በማሰማት ለማወክ የሚሞክሩ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማደናቀፍና ህልውናዋን ለመገዳደር ከሚፈልጉ ኃይሎች ጋር እስከመሰለፍ የሄዱ አካላት ነበሩ።»
በወቅቱ በተፈጠሩት ነገሮች ምክንያት በሕዝቡ ዘንድ ምንድን ነው የመጣብን ሥጋት ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም፣ ነገሮች እያዋሉ እያደሩ ሲመጡ ግን የ«መደመር» መንገድ ብቸኛው አማራጭ መሆኑንና ለመበልጸግ የሚደረገው ጥረት ተገቢ መሆኑን ሕዝቡ ማመኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም፣ ሕዝቡ ይህንን እምነቱን በምርጫ ማረጋገጡን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብቸኛው ኢትዮጵያን የማጽኛ መንገድ ታሪካዊውን ውህደትና እህትነት በሚያርቅ፣ በሚያድስና በሚያሰፋ መንገድ መሄድ፣ ተከባብሮና ተዋዶ በጋራ በመስራት ሀገርን ማጽናት ብቻ መሆኑን አብራርተዋል።
Seledadotio

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገራዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፡-
👉 ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በከፍተኛ ወታደራዊና የመንግሥት አመራሮች ላይ የተፈጸመው ግድያ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትምምን ውስጥ ጠባሳ ፈጥሯል፡፡
👉 የፖለቲካ መተማመን በጣም እንዲቀዘቅዝ አድርጓል፣ በሰዎች መካከል አብረህ እየኖርክ፤ እየሰራህ፤ እየተሰበሰብክ የመተማመን ዝንባሌው በእጅጉ እንዲቀንስ አደርጓል፡፡
👉 አብረህ ስለ ሀገር ከምትመክረው ሰው አደጋ ያጋጥመኛል ብለህ እያሰብክ መምከር በእጅጉ ትምምንን የሚቀንስ ጉዳይ ስለሆነ እንደ አንድ ጠባሳ የሚታይ ክስተት ነው፡፡
👉 ክስተቱ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል አበላሽቶታል፤ ከንግግር ከውይይት ይልቅ በመሳሪያና በጉልበት ግለሰቦችን በማፈንና በመግደል ስልጣን የመጎናጸፍ ልምምድን የሚያስቀጥል ጠባሳ ሆኗል፡፡
👉 ገዳይንም፣ ሟችንም ሁለቱንም ወገኖች በጀግንነት ያወሳ የፖለቲካ ትርክት የታየበት ክስተት ነው፤ ይህንን አሁንም ቆም ብለን ማየት ይገባናል፡፡
👉 ታሪክን እየመረጥን፣ እያንሻፈፍን እና በፈለግነው መንገድ የማቆየት የትርክት ስብራት ጉዳይ አሁን ላለንበት አጠቃላይ ውጥንቅጥ ዋናው መሰረት ነው፡፡
👉 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እስካሁን ከሚስተዋለው ከዚህ ውጥንቅጥ ወጥተን፤ ታሪክን እንዳለ አስቀምጠን ከመልካሙም ከስህተቱም መማር ይገባናል፡፡
👉 አሁን እዚህ እንደ ዋዛ በብሄርተኝነት ስሜት በአውራጃዊነት ስሜት ታሪክን አንሻፍፈን ብንጽፍ፣ ብንናገር ነገ ልጆቻችንን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ማሰብ አለመቻል ደግሞ ያሳዝነኛል፡፡
👉 ይሄ ጉዳይ እንዳለ ታሪኩን አስቀምጠህ ከተቀመጠው ታሪክ ተነስተህ በሚኖረው ትንተና የፈለግከውን ነገር ወደ ቀኝ ወደ ግራ ወስደህ መማር ትችላለህ፡፡
👉 ታሪክን ማዛባት ግን እምብዛም ጠቃሚ አይደለም፤ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም ዋጋ ያስከፍላል፣ ትውልድ ዋጋ ይከፍልበታል፡፡
👉 እኛ በህይወት እያለን የምናውቀውን ጉዳይ በተንሸዋረረ የታሪክ አረዳድ የምናስቀምጥ ከሆነ እኛ በማንኖርበት ሰዓት የሚኖረው ትወልድ እንዴት እንደሚወስደው አሁን ባለው የኢትዮጵያ ታሪክ መመልከት ይቻላል፡፡
👉 አሁን ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ የዚህ የተንሸዋረረ የፖለቲካ ትርክት ውጤት ነው፡፡
👉 ታሪክን እንዳለ ማስቀመጥ ሳይሆን አዛብተን በማስቀመጣችን ምክንያት የሚፈጠር ችግር ነው፤ ከዚያም ሻገር ሲል የፖለቲካ ሴራ ተንታኞች መጠቀሚያም ሆኗል፡፡
👉 ያ ክስተት በተፈጠረበት ወቅት አሚኮን ጠርተን ለሕዝቡ መግለጫ የሰጠነው እዚሁ አዲስ አበባ መሆኑን ታውቃለህ፥ በኋላ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህር ዳር ሆነው መግለጫ ሰጡ በሚል የሴራ ተንታኔ ተቀይሯል፡፡
👉 እንደዚህ ያለ ከእውነት የተፋታ፤ ለዛሬም ለነገም የማይበጅ፤ የሚሸነገል የሚዋሽ ነገር ጥፋት ብቻ ነው የሚያመጣው፡፡
👉 ክስተቱ እንደ ጥቁር ጠባሳ የሚወሰድ መጥፎ ክስተት ነው፡፡
በአቤል ነዋይ

የሀገራዊ ለውጥ ጉዞ የአንድ ሰሞን ድግስ ሳይሆን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ሂደት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********************
የሀገራዊ ለውጥ ጉዞ የአንድ ሰሞን ድግስ ሳይሆን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ሂደት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ዜጎች ለወቅታዊ ፈተናዎች እጅ ሳይሰጡ ለሀገር ዘላቂ ጥቅም በጽናት ሊቆሙ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ እና የዘመኑን የመረጃ ፍሰት በአግባቡ መገንዘብ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት መረጃ በዋናነት በብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ብቻ ይገኝ የነበረ መሆኑን አስታውሰው፣ አሁን ላይ ግን የኢንተርኔትና የዳታ ስርጭት በመስፋፋቱ እንዲሁም በርካታ ትንታኔ ሰጪዎች በመፈጠራቸው ወቅቱን በጥንቃቄ መረዳት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።
ለውጥ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ ዜጎች ራሳቸውን እያስተማሩ እና ከሁኔታዎች ጋር እያስማሙ መጓዝ እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መክረዋል።
ጫናን መቋቋም አቅቷቸው ለጊዜያዊ ችግሮች ሸብረክ የሚሉ አካላት እንዳሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ለርካሽ እና ጊዜያዊ ነገር ሲባል ከትልቅ ሀገራዊ ቁም ነገር መጉደል እንደማይገባ በአጽንኦት ተናግረዋል።
ሁሉም አካል ታሪክ መሥራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ ማተኮር እንዳለበት፣ ይህ ካልተቻለ ደግሞ ቢያንስ ከታሪክ ቀኝ መቆም እንጂ በአቋም መዋዠቅ የሀገርን ጥቅም አደጋ ላይ መጣል እንደማይገባ አስገንዝበዋል።
እውነታው በሂደት እና በተጨባጭ ሥራዎች እየተገለጠ እንደሚመጣም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #pmabiyahmed #nationalinterest #ebc

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው ሀገራዊ የምክክር ሂደት አሁን ላይ ሀገሪቱን ክፉኛ ወደሚያወዛግቡ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች መግባቱን ተከትሎ፣ ታዋቂው የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ክቡር ገና የሂደቱን መነሻ ሀሳብ አጥብቀው ተቹ። አቶ ክቡር ዛሬ ባወጡት ጽሁፍ፣ ጉባኤው መጀመር የነበረበት "ኢትዮጵያውያን በጋራ መገንባት የሚፈልጉት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው?" በሚለው ጥያቄ ሆኖ ሳለ፣ ሂደቱ ግን "ኢትዮጵያውያንን የሚከፋፍላቸው ምንድን ነው?" በሚል የተሳሳተ የመነሻ ጥያቄ መጀመሩን አስምረውበታል።
የምክክር ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ፣ ምልክቶች፣ የወደፊቱን የህገ-መንግስት ቅርጽ፣ ፓርላማዊ ወይስ ፕሬዝዳንታዊ ስርዓት፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለቤትነት፣ የፌደራሊዝም፣ የማንነት፣ የታሪክ እና የስልጣን ጉዳዮችን ወደ ጠረጴዛ አምጥቷል። እነዚህ ጥያቄዎች እጅግ አስፈላጊ ቢሆኑም፣ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ደረጃ የማይግባቡባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አቶ ክቡር ያስረዳሉ።
የፖለቲካ ፍልስፍና እንደሚያሳየው፣ ሀገራት በህገ-መንግስት ወይም በሰንደቅ ዓላማ ብቻ በአንድነት ሊቆሙ አይችሉም። ይልቁንም ህዝቦች ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቁ ሆነው የጋራ መጻኢ ጊዜን ለመምረጥ ሲወስኑ ብቻ ነው ሀገራት ሊቀጥሉ የሚችሉት። ይህ ምርጫ ደግሞ ከህገ-መንግስት ቀረጻ በፊት ሊመጣ የሚገባው እንጂ በኋላ የሚመጣ አለመሆኑን ተንታኙ ይሞግታሉ። የምክክር ሂደቱ ግን ይህንን ተፈጥሯዊ ቅደም ተከተል የገለበጠው ይመስላል።
የምክክር ሂደቱ ዋነኛ ሀገራዊ ቅራኔዎችን በመለየት እና ተወካዮችን በማሰባሰብ መግባባት ላይ መድረስ ይቻላል የሚል ፍልስፍናን የተከተለ ይመስላል። ነገር ግን ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ሰዎች ከጥልቅ ቅራኔዎቻቸው በመነሳት አንድነትን ሲያገኙ አይታይም፤ ይልቁንም የየራሳቸውን አቋም በበለጠ ሁኔታ መከላከልን ነው የሚማሩት። በታሪክ አተረጓጎም ክርክር የሚጀምር ውይይት፣ በተሻለ የተብራራ የታሪክ ልዩነትን በማስገኘት ያበቃል። ተሳታፊዎች ይበልጥ ተማምነው ሳይሆን፣ እርስ በርስ በተሻለ ሁኔታ ተረድተው ብቻ ሊወጡ ይችላሉ። አቶ ክቡር እንደሚሉት፣ መደማመጥ ማለት ሀገር መገንባት ማለት አይደለም።
የምክክር ሂደቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የህዝብን ብሶት ከመሰብሰብ ይልቅ የህዝብን ምኞት ማሰባሰብ ነበረበት። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሀገር ለምን መቀጠል እንዳለባት፣ ለየብቻ ሊገነባ የማይችል ነገር ግን በጋራ ሊገነባ የሚችል የወደፊት ጊዜ ምን እንደሆነ፣ እንዲሁም ለዚህ የጋራ ዕጣ ፈንታ ለመጠየቅ ሳይሆን ለመሰዋት ዝግጁ የሆነው ምን እንደሆነ ቢጠየቅ ኖሮ አቅጣጫው በተቀየረ ነበር። እነዚህ ጥያቄዎች ቢነሱ ኖሮ ውይይቱ ከባለቤትነት ይልቅ ወደ ዓላማ፣ ከመብት ይልቅ ወደ ኃላፊነት እንዲሁም ከትናንት ይልቅ ወደ ነገ በተሸጋገረ ነበር።
የሂደቱን ተአማኒነት አደጋ ላይ የሚጥለው ሌላው ትልቅ ፈተና፣ መሳተፍ የነበረባቸው ወሳኝ አካላት በጉባኤው ውስጥ አለመኖራቸው ነው። ታዋቂ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች በእስር ላይ ይገኛሉ፣ አንዳንዶቹ በስደት ላይ ናቸው፣ ሌሎች ደግሞ በትጥቅ ትግል ውስጥ ተሳትፈዋል። ለኢትዮጵያ የተለየ ራዕይ ያላቸው በርካታ ተጽእኖ ፈጣሪ ምሁራን እና የፖለቲካ ተዋናዮች ሂደቱን እንደራሳቸው አድርገው አይመለከቱትም። ሰላም ብዙ ጊዜ የሚደራደረው አስቀድመው በሚግባቡ ሰዎች መካከል ሳይሆን፣ በመካከላቸው ጥልቅ ያለመተማመን ባለባቸው አካላት መካከል በመሆኑ፣ ወሳኝ ድምጽ ያላቸው አካላት ሁሉ በውጪ ከመቅረት ይልቅ በአዳራሹ ውስጥ መገኘታቸው እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጽሁፉ ያትታል።
ታሪክ የሚያስታውሰው ስንት ውይይቶች እንደተካሄዱ፣ ስንት አጀንዳዎች እንደተሰበሰቡ ወይም ስንት ሪፖርቶች እንደወጡ አይደለም። አቶ ክቡር ገና በመደምደሚያቸው እንዳሰፈሩት፣ ታሪክ የሚዘክረው "ምክክሩ የኢትዮጵያን የጋራ ብሔራዊ ማንነት አጠናክሯል ወይስ በቀላሉ የኢትዮጵያን አለመግባባቶች በተሻለ ሁኔታ አደራጅቷል?" የሚለውን ብቻ ነው። ተሳታፊዎች ከጉባኤው ሲወጡ "አሁን በጋራ ምን ዓይነት የወደፊት ጊዜ መገንባት እንችላለን?" ብለው ከጠየቁ፣ ሀገርን የመገን ባት እጅግ ወሳኝ ስራ ተጀምሯል ማለት ነው። ይህ ደግሞ የምክክር ጉባኤው ሊጀምርበት ይገባ የነበረው ትክክለኛው የመጀመሪያ ጥያቄ መሆን ነበረበት።

ነገ ሁለቱ ተጓዦች ይመጣሉ!”
ለጥበብ እና ለጉዞ ወዳጆች -ታላቅ የምስራች!
በዓመታዊው የንባብ ለሕይወት የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ፣ መድረኩን ለየት ባለ ጥበባዊ ድምቀት ሊያነዝሩት የተዘጋጁ ሁለት ታላላቅ ስሞች በአንድ መድረክ ይከሰታሉ!
የሀገራችንን ውበት በቃላትና በምስል እየቀመረ የጉዞን ጥበብ ያስተማረን ሄኖክ ስዩም...ከአንደበተ ርቱዑ እና ተወዳጁ የይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) ጋር በመሆን “ንባብና ቱሪዝም”ን በጥበብ መነጽር ያሳዩናል።እነዚህ ሁለቱ ተጓዦች ነገ ምን ይዘውልን ይከሰቱ ይሆን?በንባብ ዓለም ውስጥ የሚደረግ ረጅም ጉዞ፣የኢትዮጵያን ውበት በጥበብ የመቃኘት ጥልቅ እይታ፣የአእምሮ ስንቅ እና የማይረሱ ውብ ትዝታዎች!ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018፣ የዕውቀት እና የጥበብ ማዕድ ተካፋይ ለመሆን ቀጠሮዎን ከእኛ ጋር ያድርጉ። ይህ ድንቅ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ!
ቦታው ኤግዚቢሽን ማዕከል
ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018

6 days ago
በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሚታዩ የክህሎትና የመዋቅር ችግሮችን ለመቅረፍ አዲስ የጋራ ስምምነት ተደረገ!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሚታዩ መዋቅራዊና የክህሎት ችግሮችን ለመቅረፍ የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እና የአባ ለታ አክቲንግ አካዳሚ በጋራ ለመስራት በዛሬዉ እለት ተፈራረሙ።
በአዲሱ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር የሚገኙትን ብሔራዊ ቴአትር፣ ሀገርፍቅር ቴአትር፣ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም (ባህል አዳራሽ)፣ ራስ ቴአትር እና የሕፃናትና ወጣቶች ቴአትርን የሚያስተዳድረው ተቋሙ፤ ከግል ዘርፍ አጋሮች ጋር አብሮ ለመሥራት ባቀደው መሠረት ይፋዊ ስምምነቱን አድርጓል።
በስምምነቱ መሠረት የአስተዳደሩን የዘመናት የታሪክና የልምድ ክምችት ከአካዳሚው ዘመናዊና ፈጠራ የታከለበት የአሰልጠና ዘዴ ጋር በማዋሃድ በቴአትር፣ በሙዚቃ፣ በፊልምና ተዛማጅ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ሰፊ ስልጠናዎች በጋራ እንደሚሰጡ ተገልጿል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ወግ የሚያንፀባርቁ ጥበባዊ ሁነቶችንና ትላልቅ ፕሮዳክሽኖችን በጋራ በማዘጋጀት ለሕዝብ ለማቅረብ፣ እንዲሁም ከግጥም ምሽቶች እስከ ታላላቅ የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫሎች ድረስ ያሉ መድረኮችን ለማስፋፋት መታቀዱም ነዉ የተገለፀዉ።
የአባ ለታ አክቲንግ አካዳሚ ዋና መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሌንጮ ፍቅሩ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደገለጹት፤ አካዳሚው ከተመሠረተበት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ወጣትና ህጻናት
ተማሪዎችን አብቅቶ ያስመረቀ ሲሆን፣ በተለይም በልጆች አክቲንግ ዘርፍ አበራች አስተዋጽኦ አበርክቷል ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ሌንጮ አክለው እንደገለጹት፣ አካዳሚው እስካሁን በነበረው ጉዞ የቦታ፣ የሎኬሽን እና የትወና ቁሳቁሶች (Props) እጥረት ዋና ዋና ማነቆዎች እንደነበሩበት አስታውሰዋል።
ሆኖም ከአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ጋር የተደረገው ይህ ይፋዊ ስምምነት እነዚህን የሎጅስቲክስና የቦታ ችግሮች በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የሰለጠኑ አዳዲስ ከዋክብትን ወደ ታሪካዊ የቴአትር መድረኮች ለማውጣት ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

ከገጠር እርሻ ወደ ዓለም አቀፍ ዝና! ✨🇪🇹
የኤልሳቤጥ ደስታ ጉዞ የጽናት፣ የክብር፣ እና የማይደበዝዝ የኢትዮጵያ ውበት አስደናቂ ታሪክ ነው።
በተፈጥሯዊ ውብ ቆዳዋ፣ በልዩ ግርማዋ እና በራስ መተማመኗ፣ ኤልሳቤጥ የአዲሱን ትውልድ የኢትዮጵያ ሞዴሎች በኩራት ትወክላለች። በሁሉም የምትሳተፍባቸው የብራንድ ዘመቻዎች የኢትዮጵያን ባህል፣ ልዩነት እና ልቀት ለዓለም ታስተዋውቃለች፣ በስራዋም ብዙዎችን ታነሳሳለች።
ኤልሳቤጥ በBN Advertising & Talent Management Company ብቸኛ አስተዳደር ስር ያለች ተሰጥኦ ሲሆን፣ በታዋቂው በጎ አድራጊ ማስተር አብነት ከበደ ጋር በመተባበር ይህ ፕሮጀክት ተከናውኗል።
የግብይት አማካሪ: ናትናኤል ዘሪሁን | NZ Communications
ፎቶግራፍ: Miki Photo (Fitle Picture) 📸
ሜካፕ: Marzel 💄
ስታይሊስት እና አርት ዳይሬክተር: Hemen ✨
ውበትን ከዓላማ ጋር፣ ተሰጥኦን ከራዕይ ጋር፣ ኢትዮጵያንም በኩራት እናክብር። 🇪🇹❤️
#elsabet #ethiopianbeauty #brandmodel #madeinethiopia #africanbeauty #fashionphotography #bnadvertisingandevents #brooknews #masterabinetkebede #nzcommunications #mikiphoto #marzelmakeup #hemenstylist #portraitphotography #ethiopianmodels #beautywithpurpose #addisababa #proudlyethiopian

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በክለቦች የተጫዋቾች እና የቴክኒክ አባላት የደመወዝ ክፍያ ላይ ጥሎት የነበረውን ዓመታዊ የወጪ ጣሪያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታውቋል።
ባለፈው የውድድር ዘመን እያንዳንዱ ክለብ በዓመት ለደመወዝ ማውጣት የሚችለው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 70 ሚሊዮን ብር እንዲሆን ተወስኖ ነበር። ይህ የገንዘብ ጣሪያ አሰራሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲተገበር ከነበረው 50 ሚሊዮን ብር ከፍ ተደርጎ የተተገበረ ቢሆንም፣ አዲሱ የሊጉ ውሳኔ ግን ክለቦች ለ2026/27 የውድድር ዘመን ያለምንም የገንዘብ ገደብ የደመወዝ በጀታቸውን በራሳቸው እንዲወስኑ ሙሉ ነፃነት ይሰጣቸዋል።
ይህ የገንዘብ ጣሪያ በአንድ ተጫዋች ደመወዝ ላይ ሳይሆን ክለቦች በአጠቃላይ ለደመወዝ በሚያወጡት ወጪ ላይ የተጣለ ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማውም እያሻቀበ የመጣውን የደመወዝ ወጪ ለመቆጣጠር እና የተለያየ የፋይናንስ አቅም ባላቸው ክለቦች መካከል ያለውን የፋይናንስ ፉክክር ለማመጣጠን ነበር። ጣሪያው መነሳቱ በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር እና የውል ድርድር ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል፤ ምክንያቱም ክለቦች ከዚህ በኋላ ዓመታዊ የደመወዝ ወጪያቸውን ከ70 ሚሊዮን ብር በታች ለማድረግ አይገደዱም።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አሁንም ለህልውናቸው በክልል መንግስታት፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በመንግስት ተቋማት እና በልማት ድርጅቶች ዓመታዊ በጀት ላይ ጥገኛ በሆኑበት ወቅት ነው። ከስፖንሰርሺፕ፣ ከቴሌቪዥን ስርጭት መብት፣ ከቲኬት ሽያጭ፣ ከማልያ ሽያጭ እና ከመሳሰሉት የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚገኘው ገቢ አሁንም በመላው ሊጉ እጅግ አነስተኛ ሆኖ ቀጥሏል። የበርካታ ክለቦች ዋነኛ የፋይናንስ ምንጭ አመታዊ የበጀት ድልድል ሲሆን፣ በርካቶቹ የራሳቸው ስታዲየም፣ ቋሚ የመለማመጃ ሜዳ ወይም ቋሚ ገቢ የሚያስገኝ የንግድ ተቋም የላቸውም።
የስፖርት ተንታኙ ፈይሰል ዘኪር የደመወዝ ወጪን መጨመር ብቻውን የኢትዮጵያን እግር ኳስ መዋቅራዊ ችግር እንደማይፈታው ያስገነዝባል። "ብዙ ገንዘብ ማውጣት ምንም አዲስ ነገር አያመጣም፤ ይልቁንም ይኸው ገንዘብ ለክለቦች ስታዲየም ለመገንባት እና ትልቅ አቅም ያላቸውን ወጣት ተጫዋቾች ለማፍራት መዋል ነበረበት" በማለት ተችቷል። ክለቦች ወጪያቸውን ከማሳደጋቸው በፊት ዘላቂ የገቢ ምንጭ መፍጠር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባም አሳስቧል። አክሎም "በጀት አመዳደቡ የአጭር ጊዜ ውጤት ላይ ብቻ ያተኮረ ነው፤ ለዚህም ነው አንድ ክለብ በአንድ የውድድር ዘመን ከላይ አጠናቆ፣ በሚቀጥለው ዓመት በጀቱ ሲያልቅ ወደ ታች የሚወርደው" ሲል የችግሩን ስር-መሰረት አብራርቷል።
በአህጉር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የአፍሪካ ሊጎች በክለብ ወጪ እና በተጫዋቾች ክፍያ ላይ የተለያየ አሰራር አላቸው። ለምሳሌ ጋና የክለቦችን አጠቃላይ ወጪ ከመገደብ ይልቅ ለተጫዋቾች የሚከፈል አነስተኛ የደመወዝ እርከን በማውጣት ተጫዋቾችን ትጠብቃለች። ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ምንም ዓይነት የደመወዝ ጣሪያ ሳታስቀምጥ ክለቦች በስፖንሰር እና በቴሌቪዥን መብት በሚያገኙት ገቢ በነጻነት ይደራደራሉ። በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) በኩል ደግሞ የክለቦችን ወጪ ከሚያገኙት ገቢ ጋር የሚያስተሳስር የፋይናንስ ህግ ይተገበራል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተነሳውን የደመወዝ ጣሪያ በሌላ ከገቢ ጋር በተገናኘ የፋይናንስ ህግ ወይም የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስርዓት ስለመተካቱ እስካሁን ያሳወቀው ነገር የለም። የጣሪያው መነሳት ለክለቦች በዝውውር ገበያው ላይ ሰፊ ነፃነት ቢሰጥም፣ የደመወዝ ክፍያ ግዴታዎችን ማክበር እና የፋይናንስ አስተዳደር ኃላፊነትን ግን ሙሉ በሙሉ በእያንዳንዱ ክለብ ትከሻ ላይ ጥሎታል ያስብላል።

የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነት አለም አቀፍ አልበም በይፋ ተመረቀ
#ethiopia | የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነት የባህላዊ ሙዚቃ አልበም ትናንት በጎንደር ከተማ በተካሄደ ደማቅ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በይፋ ተመረቀ።
በሙዚቃዊ፣ በሰላም ኢትዮጵያ እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ትብብር የተዘጋጀው አልበም፣ የጎንደርን እና የአማራ ክልልን የባህል ሙዚቃ ለአለም አቀፍ አድማጮች ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግስት ተወካዮች፣ አርቲስቶች፣ የባህል ባለሙያዎች፣ አጋር ተቋማት፣ የሚዲያ ተወካዮችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተዋል። የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነትም የቀጥታ የሙዚቃና የውዝዋዜ ትርኢት በማቅረብ ታዳሚዎችን አስደስቷል።
በአልበሙ ውስጥ የቡድኑ ድምፃውያን ሕይወት እያሱ፣ እህተነሽ ፋንታ፣ ሰሎሞን ጥጋቤን ጨምሮ ሌሎች የቡድኑ አባላት ተሳትፈዋል።
የሙዚቃ ዳይሬክተርነቱንም ሙዚቀኛ ምሳሌ ለገሰ መርተዋል። አልበሙ በባህላዊ የኢትዮጵያ መሳሪያዎች የተቀናበረ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ተቀርጾ የድምፅ ማስተካከያውና ማስተሪንጉ በጣሊያን በሚገኘው ማክስሳውንድ ቫይብ ስቱዲዮ ተከናውኗል።
በዝግጅቱ ላይ የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ኪነትን ከ50 ዓመታት በላይ የሚያስቆጥር ታሪክ የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይም ለእንግዶች ቀርቧል። አውደ ርዕዩ የቡድኑን እድገት፣ ለኢትዮጵያ ሙዚቃና ትዕይንት ጥበባት ያበረከተውን አስተዋፅኦ እንዲሁም ያፈራቸውን ታዋቂ አርቲስቶች የሚያስታውሱ ታሪካዊ ፎቶግራፎችና ሰነዶችን አካቷል።
በዝግጅቱ ላይ የሙዚቃዊ ተወካይ ሲሳይ መንግስቴ፣ አልበሙ ከመደበኛ የሙዚቃ ስራ በላይ የኢትዮጵያን የባህል ሀብት ለማስጠበቅና ለአለም አቀፍ ተደራሽነት ለማብቃት የተደረገ ኢንቨስትመንት መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ስራ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ እና ለአዲስ ትውልድ ለማስተላለፍ ጠቃሚ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #gondarfasilidesculture #የጎንደርፋሲለደስባህልኪነት #ethiopianmusic #ethiopianculture #gondar #traditionalmusic #ethiopia

"ይህች በእርግጥ ምድር ነች?"፦ ከምድር ውጪ ሌላ ፕላኔት የሚመስለው አስደናቂው የተፈጥሮ ጥበብ 'ዳሎል'
********************
ኢትዮጵያ በተፈጥሮና በታሪክ ሀብቷ ከሚጠቀሱ የዓለማችን እምቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዷ ስትሆን፣ የዚህ ዘርፍ ትልቅ አምባሳደር ከሆኑት ድንቅ ስፍራዎች መካከል ደግሞ ዳሎል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የሚገኘው ይህ የዳሎል ሃይድሮተርማል ሥርዓት፣ ሀገራችን በቱሪዝም ዘርፉ ያላትን ልዩ ሀብት ለዓለም የሚያሳይና ማንኛውንም ተመልካች በእውነት ይህ በምድር ላይ ያለ ስፍራ ነው? የሚያስብል ድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ ነው።
ከእይታ ውበቱ ባሻገር ዳሎል በሳይንሳዊ እና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ እጅግ አስገራሚ እውነታዎችን የያዘ ነው።
ይህ ስፍራ የሚገኘው በዳናኪል ዝቅታ ቦታ ውስጥ ሲሆን፣ ከባሕር ጠለል በታች 130 ሜትር ያህል ዝቅ ብሎ በመገኘቱ በዓለማችን ላይ ካሉ እጅግ ዝቅተኛ ቦታዎች አንዱ ያደርገዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ዳሎል በምድር ላይ ካሉ እጅግ ሞቃታማ ስፍራዎች ተርታ የሚመደብ ሲሆን፣ የሙቀት መጠኑም በቀን ውስጥ በአማካይ ከ34 እስከ 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እና ከዚያም በላይ ይደርሳል።
በስፍራው ጎልተው የሚታዩትና የጎበኙትን ሁሉ የሚያስመሙት ደማቅ የቢጫ፣ የአረንጓዴ፣ የብርቱካናማ እና የነጭ ህያው ቀለሞች እንዲሁ በዘፈቀደ የተፈጠሩ አይደሉም።
እነዚህ ማራኪ ቀለማት የሰልፈር፣ የብረት ኦክሳይድ፣ የጨው እና እጅግ አሲዳማ የሆኑ የሙቀት ምንጮች ኬሚካላዊ ውህደት ውጤቶች ናቸው። በሚፍለቀለቁት የሙቀት ምንጮች እና በሚደንቁት የማዕድን ክርስታሎች የተሸፈነው ይህ ቦታ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሳቢነት ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግራል።
ይህ ልዩ አካባቢ ባለው እጅግ ከፍተኛ ሙቀት፣ አሲዳማነት እና የጨው ክምችት የተነሳ ምንም ዓይነት የሕይወት ዘር የማይኖርበት አካባቢ በመሆኑ፣ ስፍራው በእርግጥም ከምድር ውጪ ያለች ሌላ ፕላኔትን ምስል በአዕምሯችን ይስላል።
ለዚህም ነው ይህን ልዩ የተፈጥሮ ጥበብ በዓይናቸው ለማየትና በካሜራቸው ለማስቀረት ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተጓዦች እና ፎቶግራፍ አንሺዎች በየዓመቱ ወደ ስፍራው የሚጎርፉት። የዳሎልን አስደናቂ ገጽታ በአካል የተመለከተ ማንኛውም ሰው የተፈጥሮን ድንቅ የፈጠራ ጥበብ እያደነቀ ማለፉ አይቀሬ ነው።
በስምረት ገዛኸኝ
#dallol #ethiopia #danakildepression #travelethiopia #naturephotography

7 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ህገ-መንግስት ከጸደቀ 30 ዓመታት ቢቆጠሩም፣ ሀገሪቱ አሁንም የሰዎችን ህይወት ከሚቀጥፉ፣ ማህበረሰብን ከሚያፈናቅሉ እና የህዝብን አመኔታ ከሚሸረሽሩ ተደጋጋሚ ግጭቶች መላቀቅ አልቻለችም። አብዛኛዎቹ ሰዎች ለእነዚህ ችግሮች የብሔር ወይም የፖለቲካ ፉክክርን በዋነኛነት ቢወቅሱም፣ የፖለቲካ ትንታኔዎች ግን ዋነኛው እና ስር የሰደደው ችግር የፌደራል እና የክልል መንግስታት የጸጥታ ኃላፊነት ድንበር በህገ-መንግስቱ ላይ በግልጽ አለመቀመጡ መሆኑን ያመላክታሉ።
ይህ ግልጽነት የጎደለው አሰራር "የተበታተነ ሉዓላዊነት" ፈጥሯል። ይህም ማለት የተለያዩ የመንግስት እርከኖች በተደራረበ ህጋዊ ስልጣን እና እርስ በርስ በሚፎካከር ፖለቲካዊ ፍላጎት የጸጥታ ኃይልን ያዛሉ። በዚህም ምክንያት የፌደራል እና የክልል የጸጥታ መዋቅሮች ተደጋግፈው ከመስራት ይልቅ፣ አንዳንዴ በትይዩ አልያም በፉክክር መንፈስ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ፤ ይህም ግጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት አወሳስቦታል።
የዚህ አጣብቂኝ መነሻ ያለው እ.ኤ.አ. በ1995 በጸደቀው የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ውስጥ ነው። ህገ-መንግስቱ የሀገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስን ኃላፊነት ለፌደራል መንግስቱ በአንቀጽ 51(6) ስር ሲሰጥ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ክልሎች የራሳቸውን ፖሊስ ኃይል እንዲያቋቁሙ እና ጸጥታ እንዲያስከብሩ በአንቀጽ 52(2)(g) ላይ ስልጣን ይሰጣቸዋል። ይህ ድንጋጌ የክልሎችን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እና የሀገርን አንድነት ለማመጣጠን የታለመ ቢሆንም፣ የክልል የፖሊስ ስልጣን የት ላይ ያበቃል የፌደራል የጸጥታ ኃላፊነትስ የት ይጀምራል ለሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል።
በዚህም ምክንያት ሁለት ተቋማዊ ድክመቶች ተፈጥረዋል። የመጀመሪያው፣ ክልሎች የተሰጣቸውን የፖሊስ ኃይል የማቋቋም መብት በመጠቀም ከመደበኛ የፖሊስ ግዳጅ ባለፈ ወታደራዊ ቅርጽ እና ትጥቅ ያላቸውን የክልል ልዩ ኃይሎችን ማቋቋማቸው ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ በክልሎች መካከል የሚነሱ የድንበር እና የማንነት ጥያቄዎችን የሚፈታ ጠንካራ ተቋማዊ አሰራር ባለመኖሩ የክልል ፖሊስ ተቋማት የፖለቲካው አካል በመሆን ግጭቶችን ከማብረድ ይልቅ ተሳታፊ ወደ መሆን መሸጋገራቸው ነው።
ህገ-መንግስታዊ ክፍተት ብቻውን ብጥብጥ አያመጣም። ነገር ግን ፖለቲከኞች የጸጥታ ኃላፊነቶች በተደራረቡበት ስርዓት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አደገኛ ይሆናል። በኢትዮጵያ፣ አንዱ የመንግስት እርከን ለራሱ ደህንነት ሲል የሚወስደው ራስን የመከላከል እርምጃ፣ በሌላው ወገን እንደ ትንኮሳ እና ለጥቃት እንደመዘጋጀት ይቆጠራል።
ይህ ተለዋዋጭ ሁኔታ በሚያዝያ 2015 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት በወሰደው እርምጃ ወቅት በግልጽ ታይቷል። መንግስት እርምጃውን የተዋሃደ ሀገራዊ የጸጥታ መዋቅር ለመገንባት ያለመ መሆኑን ቢገልጽም፣ በተለይም በአማራ ክልል ከፍተኛ ፖለቲካዊ ተቃውሞን እና ቀጣይነት ያለውን ግጭት አስከትሏል። ይህ የሚያሳየው፣ የክልል መንግስታት የጸጥታ ተቋሞቻቸውን እንደ ህገ-መንግስታዊ የራስ ገዝ አስተዳደር መገለጫ አድርገው በሚያዩበት ፌደራላዊ ስርዓት ውስጥ፣ ኃይልን ማዕከላዊ ለማድረግ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ እንደ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት እንደሚቆጠር ነው።
መዋቅራዊ መፍትሄዎች፡ ኃይልን ብቻ ሳይሆን ህጉን ማስተካከል
የኢትዮጵያን ተደጋጋሚ የጸጥታ ቀውሶች በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ማድረግ የግድ ይላል። በቅድሚያ በአንቀጽ 51 እና በአንቀጽ 52 መካከል ያለውን የፌደራል እና የክልል የጸጥታ ኃላፊነቶች ግንኙነት በግልጽ በማብራራት የፌደራል መንግስት በምን ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ጣልቃ መግባት እንዳለበት ህጋዊ ድንበር ሊቀመጥ ይገባል። በተጨማሪም የክልልን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በማይጋፋ መልኩ፣ መረጃ የሚለዋወጡበት እና ግጭቶች ወደ ጦርነት ከማምራታቸው በፊት የሚፈቱበት ቋሚ የፌደራል እና የክልል የጸጥታ ማስተባበሪያ መዋቅር መገንባት ያስፈልጋል።
በሌላ በኩል የፖሊስ ተቋማት ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዱ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና በፖለቲካ የተነሳሱ የጸጥታ ጥሰቶችን የሚመረምር ገለልተኛ የቁጥጥር አካል በማቋቋም ተቋማዊ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ ነው። እንዲሁም የክልል ፖሊሶች ለክልል ፖለቲካዊ ፍላጎቶች ሳይሆን ለህገ-መንግስቱ እና ለህግ የበላይነት ታማኝ የሚሆኑበትን የጋራ ስልጠና እና ኦፕሬሽናል መርሆች በመተግበር የጋራ ፕሮፌሽናል አስተምህሮ ማዳበር ይገባል።
የኢትዮጵያ ተደጋጋሚ የጸጥታ ቀውሶች የሚያሳዩት "ህገ-መንግስታዊ ንድፍ ልክ እንደ ፖለቲካዊ አመራር ሁሉ እጅግ ወሳኝ መሆኑን" ነው። ዘላቂ ሰላም ጊዜያዊ ተኩስ አቁምን ወይም ወቅታዊ የጸጥታ ዘመቻዎችን ብቻ ተመርኩዞ ሊመጣ አይችልም። የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ጥያቄ የጸጥታ ማሻሻያ ያስፈልጋል ወይ የሚለው ሳይሆን፣ ማሻሻያው የችግሩን ውጫዊ ምልክቶች ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ እና ህገ-መንግስታዊ ስር-መሰረቱን ይፈታል ወይ የሚለው ነው።

ግብጾች የአባይን ውሃ ስለሚጠቀሙ ለኢትዮጵያ ሊከፍሉን ይገባል ዶክተር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ፣ ግብፅ የአባይን ውኃ በነፃ እየተጠቀመች አገሯን እያለማች በመሆኗ ለኢትዮጵያ ተገቢውን ክፍያ ልትፈጽም እንደሚገባ ገለጹ።
ሚኒስትሩ በቆይታቸው እንደጠቆሙት፤ ኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ በታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት—በተለይም በግብፅ ላይ እንዳይደርስ ከፍተኛ የክትትልና የእንክብካቤ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች።
ሆኖም አገራቱ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ያለምንም ክፍያ በመጠቀም አገራቸውን እያለሙ በመሆናቸው፣ ለሚጠቀሙበት ውኃ ለኢትዮጵያ ክፍያ ሊፈጽሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ከቀዩ አብዮት ወደ አረንጓዴው አብዮት፡ የትውልድ እና የተግባር ሽግግር
*********************
(የዕለቱ መልዕክት)
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ማህደር ገልጠን ስንመረምር፣ የ1960ዎቹ "ያ ትውልድ" ያቀጣጠለው ንቅናቄ በታሪክ ጎልቶ ይወጣል። ይህ አብዮተኛ ትውልድ ዘመናትን የተሻገረውን የንጉሣዊ ሥርዓት በታላቅ ህዝባዊ ማዕበል ለመገርሰስ ቢችልም፣ ያንን ለውጥ ወደ ተረጋጋ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ማሸጋገር ግን አቅቶት ነበር። ከጊዜ በኋላ ንቅናቄው ወደ አስከፊ የደም መፋሰስ ስላመራ፣ ያን የትናንት የታሪክ ምዕራፍ "ቀይ አብዮት" ብለን ልንጠራው እንችላለን። ቀይ አብዮት፥ ደም ያፋሰሰ፣ የተለየ ሀሳብን በጠብመንጃ ያዳፈነ፣ እና "አብዮት ልጆቿን ትበላለች" በሚል ጭካኔ የተሞላበት ዲስኮርስ ትውልድ ያመከነ የጥፋት ዘመን ነበር።
በዚህ የቀይ አብዮት አዙሪት ውስጥ፣ የአንድ ትውልድ አቅምና ሀገርን የመቀየር ጉጉት የነበረው ወጣት ኃይል እርስ በርሱ ተከፋፈለ፣ ተገዳደለ። በመደማመጥና በመተጋገዝ ሀገርን በጋራ ከመገንባት ይልቅ፣ አንዱ አብዮተኛ ሌላውን አብዮተኛ እያሳደደ በማጥፋቱ ምክንያት፣ የተረጋጋ መንግሥት መመስረት ሳይቻል ቀረ።
በዚህ ክፍተት ወታደራዊው ሥርዓት ስልጣኑን በኃይል ተቆጣጥሮ፣ ሀገሪቱን መውጫ ወደሌለው ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከተታት። ጦርነቱን ተከትሎ የዚያው ትውልድ አካል የነበሩ ኃይሎች መንግሥትን በኃይል በመገልበጣቸው፣ "የመጠፋፋት ፖለቲካ" ሥር ሰዶ ለዘመናት የዚህች ሀገር ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስብራት ሆኖ ቆይቷል።
ዛሬ ግን በዚህች ታላቅ ሀገር ምድር ላይ የተለየ ንጋት ፈንጥቋል። አዲሱ የመደመር ትውልድ የትናንቱን ቁርሾ የሚያብስ፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስብራትን የሚጠግን አዲስ ታሪክ እየጻፈ ይገኛል። ይህ ትውልድ ያስነሳው አብዮት፣ መንግሥትን በጉልበት ለመቀየር፣ ሥርዓትን አፈራርሶ በሌላ ለመተካት፣ ወይም የተለየ ሃሳብ ያለውን ለማጥፋት ያለመ አይደለም። ይህ አብዮት፣ ከቀይ አብዮት ወደ አረንጓዴ አብዮት የተደረገ የሰለጠነ የልዕልና ሽግግር ነው።
አረንጓዴ አብዮት የሕይወት፣ የልምላሜ እና የብልጽግና አብዮት ነው። ቀዩ አብዮት አንዱን በማግለልና በመጠፋፋት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ አረንጓዴው አብዮት ግን በመደመር፣ በትብብርና በአንድነት ላይ የቆመ ነው። ይህ አብዮት ለዘመናት የተራቆተችውን፣ በድርቅና በረሃብ ስትፈተን የኖረችውን እናት ሀገር፣ በተፈጥሮ ጸጋዋ ዳግም እንድታንሰራራ፣ ቁስሏ እንዲሽርና ወደ አረንጓዴ ምድርነት እንድትመለስ የሚያደርግ የሕልውና ትግል ነው። ዛሬ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዘር፣ በሃይማኖት፣ ወይም በፖለቲካ አመለካከት ሳይከፋፈል፣ በየአቅጣጫው ተሰልፎ እናት ሀገሩን ውብ አረንጓዴ ልብስ እያለበሳት ይገኛል።
ይህ የሕይወት አብዮት ዛሬ በሀገሪቱ ተቀጣጥሏል፣ ተፋፍሟልም። የዚህ ሥር-ነቀል አብዮት ማሳያ ደግሞ፣ የፊታችን ሐምሌ 27 በመላ ሀገሪቱ የሚተገበረው ታሪካዊ የክተት አዋጅ ነው። በዚህ ዕለት፣ አረንጓዴው አብዮተኛ ትውልድ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አብዮቱን ወደማይቀለበስ የታሪክ ከፍታ ያሸጋግረዋል።
በጥቅሉ፣ ያለፈው ትውልድ በቀይ አብዮት ባፈሰሰው ደምና ባመከነው ዘመን ፈንታ፣ የዛሬው የመደመር ትውልድ በአረንጓዴ አብዮት የትጋት ላቡን በማፍሰስ እና የሕይወት ችግኞችን በመትከል ሀገሩን እያንቆጠቆጠ ይገኛል። ሀገርን ከማፍረስ ይልቅ በመገንባት፣ ከመገዳደል ይልቅ የሕይወት ዘር በመዝራት የሚፋፋመው ይህ አረንጓዴ አብዮት፣ በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን የልዕልና ማማ ላይ የሚያስቀምጣት፣ ትውልድን አሻጋሪ ሕያው ንቅናቄ ነው!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
'እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል' አካሄድ
በአሁኑ ወቅት ከየአቅጣጫው የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ጠላቶች በመናበብ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለመጉዳት እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡
የሀገር ውስጥ ባዳዎች ልዩነታቸውን እና አጀንዳዎቻቸውን በሀሳብ ሜዳ አቅርቦ ለማሸነፍ አቅም የሌላቸው በመሆናቸው ወደ ግጭት ለመግባት የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ነው፡፡
ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን ውስጣዊ ልዩነቶቹን ጭምር በታሪኩ በውይይት ፈትቶ የማያውቅ ከመሆኑ ባሻገር የሃሳብ የበላይነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች በማሳደድና ደብዛ በማጥፋት ይታወቃል፡፡ በሃሳብ ያጡትን የበላይነት በጥይት በመሳሪያ በመቀልበስ ይታወቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በ1970ዎቹ ቀደምት መስራች የነበሩትን አረጋዊ በርኸ (ዶ/ር) እና ግደይ ዘርዓጺዮን ጭምር የተሻለ ሃሳብ በማንሳታቸው መባረራቸውን የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡
ህገ ወጡ ቡድን ለ27 ዓመታት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት እየጨመረ የመጣውን የህዝብ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ የበዛ ጭቆናና አፈና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ሙስናና ዘረፋን ሲያጧጡፍ ነበር፡፡
ለችግሮች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተሻለ ሃሳብ ማፍለቅ የተሳናቸው የህገ ወጡ ቡድን አባላት የህዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ ሳይታጠቁ ደረሰባቸው፡፡
በለውጥ ከመጣው መንግሥት ጋር ተቀምጦ ለመወያየትና ለመደራደር አቅም እንደሌላቸው ሲያውቁ የትግራይ ክልልን ህዝብ ወደ ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ከተቱት፡፡
የትግራይ ህዝብ ህገ ወጡ ቡድን ለ27 ዓመታት በስልጣን ላይ እያለም፣ ከደም አፋሳሹ የቅርቡ ግጭት በኋላም ለክልሉ ህዝብ ደንታ እንደሌለው እና ጥቂት ግለሰቦች ስልጣናቸውን ለማደላደል ብቻ እንደሆነ ተረድቷል፡፡
በትግራይ ህዝብ ዐይንህ ለአፈር የተባለው ይህ ህገ ወጥ ቡድን ወጣቱን አስገድዶ ወደ ጦርነት ለመክተት አፋኝ ህጎችን ማውጣት ጀምሯል።
ከዚህ በላይ የኢትዮጵያ ጠላት ከሆኑ የውጭ ኃይሎች ጋር በማበር ሰላምና ልማቷን ለማደናቀፍ እየሰራ ሲሆን የባንዳነት ባህርይው በግልፅ የታየበት ተግባር ነው፡፡
የኢትዮጵያን መልማት፣ መጠንከርና ሰላሟን የማይሹ የቀጣናው ሀገራትና ታጣቂ ቡድኖች በሀገር ውስጥ ያሉ ባንዳዎችን ተጠቅመው ለማደናቀፍ የሚያደርጉት መፍጨርጨር ከልማት ጉዟችን አንገታም፡፡
መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመሆን የነዚህን ባንዳዎች የቀቢጸ ተስፋ አካሄድ በቃ ሊላቸው እንደሚገባ እና በብሔራዊ ጥቅማችን የሉዓላዊነታችን ቀይ መስመር መሆኑን ማስረገጥ ያስፈልጋል፡፡

8 days ago
በጎቲያ ካፕ የተሳተፉ 20 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በስዊድን መሰወራቸው ተረጋገጠ
#ethiopia | በስዊድን ጎተንበርግ ከተማ በተካሄደው የ2026 የ«ጎቲያ ካፕ» ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር ላይ የተሳተፉ 20 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ተጫዋቾችና ቢያንስ አንድ የቡድን አመራር አባል ከውድድሩ በኋላ መሰወራቸውን የስዊድን ፖሊስ አረጋግጧል።
በስዊድን ፖሊስ መረጃ መሠረት፣ ቡድኑ ያረፈበትን ትምህርት ቤት ለቆ ያለማሳወቅ እንደወጣ ከታወቀ በኋላ ለፖሊስ ሪፖርት ተደርጓል። ፖሊስ እስካሁን የወንጀል፣ የሰው ዝውውር ወይም የግዳጅ ማስጠፋት ምልክት እንዳልተገኘ ገልጾ፣ ድርጊቱ በራሳቸው ፈቃድ የተፈጸመ እንደሚመስል አስታውቋል።
የጎቲያ ካፕ አዘጋጆች በበኩላቸው ከቡድኑ አንድ አመራር ጋር ግንኙነት እንዳደረጉ ገልጸው፣ ተጫዋቾቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውንና በደህና መሆናቸውን ቢናገርም፣ አሁን የሚገኙበት ቦታ እንደማይታወቅ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በኩል የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብርሃም ገብረማሪያም፣ የተሰራጨው መረጃ እውነት መሆኑን አረጋግጠው፣ ወደ ስዊድን የሄደው ቡድን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ወክሎ የተላከ ሳይሆን በግል አደረጃጀት የተሰባሰበ ቡድን መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መግለጫ እንደሚያወጣ አስታውቋል።
«ጎቲያ ካፕ» በዓለም ላይ ትልቁ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ውድድር ሲሆን፣ በ2026 ውድድሩ ከ78 አገራት የመጡ ከ45,000 በላይ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ተሳትፈዋል።
#ethiopia #gothiacup #sweden #sportsnews #getutemesgen #getunews

አረንጓዴ ዐሻራ፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ አዲስ የኅብረት እና የጋራ ዓላማ ባህልን የፈጠረ መርሐ-ግብር
**********************************
ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የጀመረችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዛሬ ላይ የኢትዮጵያን ገጽታ ከመስዋብ አልፎ የምግብ ዋስትና እና የዲፕሎማሲ አቅም የለወጠ ታላቅ ሀገራዊ እና አህጉራዊ ንቅናቄ ሆኖ ታይቷል።
ባለፉት ሰባት ዓመታት የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ላይ ያሳየችውን ተግባራዊ ምላሽ እና ያስመዘገበችውን ዘላቂ ፍሬ በጥልቀት የሚያስረዱ ናቸው።
ከሥነ ምህዳር እና ተፈጥሮ ጥበቃ አንጻር ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ ከ48 ቢሊዮኖች በላይ ችግኞችን በመትከል ምድርን ለማከም ተችሏል። ይህም የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በማስወጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ የደን ሽፋኗ እንዲያገግም አስችላል።
በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ዘመቻ የአፈር መሸርሸርን ከመቀነስ፣ የከርሰ ምድር ውኃን ከማጎልበት እና የተጎዱ የሥነ ምህዳር ክፍሎችን መልሶ ከመገንባት አንጻር እጅግ የጎላ ሚና ተጫውቷል።
ቀደም ሲል በድርቅ እና በአፈር መሸርሸር የተጠቁ አካባቢዎች ዛሬ ላይ አረንጓዴ ለብሰው በማገገም ይገኛሉ።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከተራ የተፈጥሮ ጥበቃ ባለፈ ወደ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ምንጭነት ተሸጋግሯል። በተለይም ባለፉት ዓመታት ትኩረት የተሰጣቸው የተቀናጁ የፍራፍሬ (አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን) እና የቡና ችግኞች ተከላ ዐበይት ውጤቶችን እያስገኙ ይገኛሉ።
ይህም ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ አባወራዎች አዲስ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩም በላይ በሀገር ውስጥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለውጭ ገበያ የሚላኩ ምርቶችን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማጠናከር ትልቅ መሠረት ጥሏል።
መርሐ-ግብሩ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አዲስ የኅብረት እና የጋራ ዓላማ ባህልን ፈጥሯል።
እድሜ፣ ጾታ፣ የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ሳይበግረው በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሚሊዮኖች ዜጎች በአንድ ጀምበር ወጥተው ችግኝ የመትከል ልምድን ማዳበራቸው ሀገራዊ አንድነትን እና የመረዳዳት መንፈስን አጠናክሮታል።
ይህም ኢትዮጵያውያን በትብብር ከተነሱ የማይሻገሩት ፈተና እንደሌለ በተግባር ያሳዩበት ታላቅ ማኅበራዊ ሀብት ሆኗል።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ የሀገር ወሰንን ተሻግሮ ለአጎራባች ሀገራት ችግኞችን በማካፈል የቀጣናዊ ትስስር እና የ አረንጓዴ ዲፕሎማሲ ማሳያ መሆን ችሏል።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመመከት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የፖለቲካ መሪዎች በሚታገሉበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በተግባር ያሳየችው ይህ ንቅናቄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሙገሳ እና ዕውቅና እንድታገኝ አድርጓታል።
ባለፉት 7 ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዞ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በምግብ እራስን መቻል፣ በሕዝባዊ አንድነት እና በዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ያስመዘገበችው ድል ነው።
ኢትዮጵያውያን ይህን የተተከለውን ተስፋ ጠብቀው በማሳደግ እና ወደ ተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ፣ የተረጋጋች እና የበለፀገች ሀገርን ለማስረከብ ተሰናድተዋል።
በሃና ምንዳሁን
#ebc #ethiopia #ebcdotstream #greenlegacy #greenethiopia #climateaction #ethiopiarising

Comments