"ይህች በእርግጥ ምድር ነች?"፦ ከምድር ውጪ ሌላ ፕላኔት የሚመስለው አስደናቂው የተፈጥሮ ጥበብ 'ዳሎል'
********************
ኢትዮጵያ በተፈጥሮና በታሪክ ሀብቷ ከሚጠቀሱ የዓለማችን እምቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዷ ስትሆን፣ የዚህ ዘርፍ ትልቅ አምባሳደር ከሆኑት ድንቅ ስፍራዎች መካከል ደግሞ ዳሎል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የሚገኘው ይህ የዳሎል ሃይድሮተርማል ሥርዓት፣ ሀገራችን በቱሪዝም ዘርፉ ያላትን ልዩ ሀብት ለዓለም የሚያሳይና ማንኛውንም ተመልካች በእውነት ይህ በምድር ላይ ያለ ስፍራ ነው? የሚያስብል ድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ ነው።
ከእይታ ውበቱ ባሻገር ዳሎል በሳይንሳዊ እና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ እጅግ አስገራሚ እውነታዎችን የያዘ ነው።
ይህ ስፍራ የሚገኘው በዳናኪል ዝቅታ ቦታ ውስጥ ሲሆን፣ ከባሕር ጠለል በታች 130 ሜትር ያህል ዝቅ ብሎ በመገኘቱ በዓለማችን ላይ ካሉ እጅግ ዝቅተኛ ቦታዎች አንዱ ያደርገዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ዳሎል በምድር ላይ ካሉ እጅግ ሞቃታማ ስፍራዎች ተርታ የሚመደብ ሲሆን፣ የሙቀት መጠኑም በቀን ውስጥ በአማካይ ከ34 እስከ 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እና ከዚያም በላይ ይደርሳል።
በስፍራው ጎልተው የሚታዩትና የጎበኙትን ሁሉ የሚያስመሙት ደማቅ የቢጫ፣ የአረንጓዴ፣ የብርቱካናማ እና የነጭ ህያው ቀለሞች እንዲሁ በዘፈቀደ የተፈጠሩ አይደሉም።
እነዚህ ማራኪ ቀለማት የሰልፈር፣ የብረት ኦክሳይድ፣ የጨው እና እጅግ አሲዳማ የሆኑ የሙቀት ምንጮች ኬሚካላዊ ውህደት ውጤቶች ናቸው። በሚፍለቀለቁት የሙቀት ምንጮች እና በሚደንቁት የማዕድን ክርስታሎች የተሸፈነው ይህ ቦታ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሳቢነት ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግራል።
ይህ ልዩ አካባቢ ባለው እጅግ ከፍተኛ ሙቀት፣ አሲዳማነት እና የጨው ክምችት የተነሳ ምንም ዓይነት የሕይወት ዘር የማይኖርበት አካባቢ በመሆኑ፣ ስፍራው በእርግጥም ከምድር ውጪ ያለች ሌላ ፕላኔትን ምስል በአዕምሯችን ይስላል።
ለዚህም ነው ይህን ልዩ የተፈጥሮ ጥበብ በዓይናቸው ለማየትና በካሜራቸው ለማስቀረት ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተጓዦች እና ፎቶግራፍ አንሺዎች በየዓመቱ ወደ ስፍራው የሚጎርፉት። የዳሎልን አስደናቂ ገጽታ በአካል የተመለከተ ማንኛውም ሰው የተፈጥሮን ድንቅ የፈጠራ ጥበብ እያደነቀ ማለፉ አይቀሬ ነው።
በስምረት ገዛኸኝ
#dallol #ethiopia #danakildepression #travelethiopia #naturephotography

5 days ago