Logo
FBC
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገራዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፡-

👉 ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በከፍተኛ ወታደራዊና የመንግሥት አመራሮች ላይ የተፈጸመው ግድያ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትምምን ውስጥ ጠባሳ ፈጥሯል፡፡

👉 የፖለቲካ መተማመን በጣም እንዲቀዘቅዝ አድርጓል፣ በሰዎች መካከል አብረህ እየኖርክ፤ እየሰራህ፤ እየተሰበሰብክ የመተማመን ዝንባሌው በእጅጉ እንዲቀንስ አደርጓል፡፡

👉 አብረህ ስለ ሀገር ከምትመክረው ሰው አደጋ ያጋጥመኛል ብለህ እያሰብክ መምከር በእጅጉ ትምምንን የሚቀንስ ጉዳይ ስለሆነ እንደ አንድ ጠባሳ የሚታይ ክስተት ነው፡፡

👉 ክስተቱ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል አበላሽቶታል፤ ከንግግር ከውይይት ይልቅ በመሳሪያና በጉልበት ግለሰቦችን በማፈንና በመግደል ስልጣን የመጎናጸፍ ልምምድን የሚያስቀጥል ጠባሳ ሆኗል፡፡

👉 ገዳይንም፣ ሟችንም ሁለቱንም ወገኖች በጀግንነት ያወሳ የፖለቲካ ትርክት የታየበት ክስተት ነው፤ ይህንን አሁንም ቆም ብለን ማየት ይገባናል፡፡

👉 ታሪክን እየመረጥን፣ እያንሻፈፍን እና በፈለግነው መንገድ የማቆየት የትርክት ስብራት ጉዳይ አሁን ላለንበት አጠቃላይ ውጥንቅጥ ዋናው መሰረት ነው፡፡

👉 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እስካሁን ከሚስተዋለው ከዚህ ውጥንቅጥ ወጥተን፤ ታሪክን እንዳለ አስቀምጠን ከመልካሙም ከስህተቱም መማር ይገባናል፡፡

👉 አሁን እዚህ እንደ ዋዛ በብሄርተኝነት ስሜት በአውራጃዊነት ስሜት ታሪክን አንሻፍፈን ብንጽፍ፣ ብንናገር ነገ ልጆቻችንን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ማሰብ አለመቻል ደግሞ ያሳዝነኛል፡፡

👉 ይሄ ጉዳይ እንዳለ ታሪኩን አስቀምጠህ ከተቀመጠው ታሪክ ተነስተህ በሚኖረው ትንተና የፈለግከውን ነገር ወደ ቀኝ ወደ ግራ ወስደህ መማር ትችላለህ፡፡

👉 ታሪክን ማዛባት ግን እምብዛም ጠቃሚ አይደለም፤ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም ዋጋ ያስከፍላል፣ ትውልድ ዋጋ ይከፍልበታል፡፡

👉 እኛ በህይወት እያለን የምናውቀውን ጉዳይ በተንሸዋረረ የታሪክ አረዳድ የምናስቀምጥ ከሆነ እኛ በማንኖርበት ሰዓት የሚኖረው ትወልድ እንዴት እንደሚወስደው አሁን ባለው የኢትዮጵያ ታሪክ መመልከት ይቻላል፡፡

👉 አሁን ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ የዚህ የተንሸዋረረ የፖለቲካ ትርክት ውጤት ነው፡፡

👉 ታሪክን እንዳለ ማስቀመጥ ሳይሆን አዛብተን በማስቀመጣችን ምክንያት የሚፈጠር ችግር ነው፤ ከዚያም ሻገር ሲል የፖለቲካ ሴራ ተንታኞች መጠቀሚያም ሆኗል፡፡

👉 ያ ክስተት በተፈጠረበት ወቅት አሚኮን ጠርተን ለሕዝቡ መግለጫ የሰጠነው እዚሁ አዲስ አበባ መሆኑን ታውቃለህ፥ በኋላ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህር ዳር ሆነው መግለጫ ሰጡ በሚል የሴራ ተንታኔ ተቀይሯል፡፡

👉 እንደዚህ ያለ ከእውነት የተፋታ፤ ለዛሬም ለነገም የማይበጅ፤ የሚሸነገል የሚዋሽ ነገር ጥፋት ብቻ ነው የሚያመጣው፡፡

👉 ክስተቱ እንደ ጥቁር ጠባሳ የሚወሰድ መጥፎ ክስተት ነው፡፡

በአቤል ነዋይ

4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.