14 days ago
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን AHEFT ሽልማትን ተቀበለ
#ethiopia | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን የተዘጋጀውን Africa Higher Education for Transformation (AHEFT) Prize በመጀመሪያው ዙር ከተሸለሙ አምስት የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ሆኖ ተቀብሏል።
ሽልማቱ በተቋማዊ ደረጃ ዘላቂ ለውጥ በማምጣት ላይ ያሉ የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሽልማቱን ያገኘው በምርምርና ፈጠራ ዘርፍ ባሳየው ተቋማዊ ለውጥና እድገት ነው።
ዩኒቨርሲቲው ሽልማቱን መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. በጋና አክራ በተካሄደው የመጀመሪያው Higher Education Transformation Convening ላይ ተቀብሏል። መድረኩ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮችን፣ የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮችን፣ የመንግሥት ተቋማትን፣ የፋይናንስና የግል ዘርፍ አጋሮችን፣ የልማት አጋሮችን እና ወጣቶችን አሰባስቧል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የቡርኪና ፋሶው International Institute of Water and Environmental Engineering፣ የጋናው Kwame Nkrumah University of Science and Technology፣ የዩጋንዳው Muni University እና University of Rwanda የ2026 የAHEFT Prize ተሸላሚዎች ሆነዋል።
እያንዳንዱ ተሸላሚ ተቋም ለወጣቶች የትምህርት ዕድሎችን ለማስፋትና ተቋማዊ ለውጥን ለማጠናከር ሥራዎቹን እንዲያስፋፋ 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ያገኛል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመድረኩ በተቀዳ የቪዲዮ መልዕክት የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ወጣቶችን ለወደፊቱ ዓለም ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊቱን ዓለም እንዲቀርጹ የማስቻል ኃላፊነት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።
የAHEFT ሽልማት በመማርና ማስተማር፣ በምርምርና ፈጠራ፣ ተማሪዎችን ወደ ሥራ ዓለም በማሸጋገር እና በጤና ውጤቶች ላይ ዘላቂ ተቋማዊ ለውጥ እያመጡ ያሉ የአፍሪካ ተቋማትን ለመደገፍ የተጀመረ ዓመታዊ ሽልማት ነው።
በ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተደገፈው መርሐ ግብሩ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ቢያንስ 150 የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እውቅና ለመስጠት ያለመ ነው።
በአክራው መድረክ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት፣ የምርምር፣ የፈጠራ እና የችግር ፈቺ ሐሳቦች ማዕከላት ሆነው ሊያበረክቱ ስለሚችሉት ሚና ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱም በተለይ በከፍተኛ ትምህርት፣ በኢንዱስትሪና በማኅበረሰብ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር፣ ወጣቶችን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፈጣሪና መሪ እንዲሆኑ ማስቻል እና ምርምርን ወደ ኢንዱስትሪና ማኅበረሰብ ማድረስ ላይ አተኩሯል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያዎቹ የAHEFT Prize ተሸላሚዎች አንዱ መሆኑ፣ በመማርና ማስተማር፣ በምርምርና ፈጠራ፣ በአጋርነት እና ለወጣቶች ዕድል በመፍጠር የሚያከናውናቸውን ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎች ለማጠናከር የሚያግዝ እውቅና ሆኗል።
#aau #education #africa #aheft #mastercardfoundation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

21 days ago
47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የዳግም ምዝገባ መስፈርት አላሟሉም ተባለ‼️
ራስ ገዝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የዳግም ምዝገባ መስፈርት አለማሟላታቸውን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ።
የባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ሥራ አስፈጻሚ ጀንበሩ ዓለማየሁ፣ ተቋማቱ በሰነድ ያቀረቡትን መረጃ መሠረት በማድረግ በሰኔ 2018 ዓ.ም. ግምገማ መደረጉንና ሁሉም ዝቅተኛውን መስፈርት አለማሟላታቸው መረጋገጡን ተናግረዋል።
ተቋማቱ ተጨማሪ 40 ቀናት እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰነዶቻቸውን እንዲያስገቡ ጊዜ መሰጠቱም ተገልጿል።
በዳግም ምዝገባው ሂደት ልዩ አደረጃጀት የተሰጠው ፕብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ብቻ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል።
Seledadotio

23 days ago
ቀይ ባህር የኢትዮጵያን ጠንካራና አስተማማኝ ክንድ ይፈልጋል - የፖለቲካ ተንታኞች እና ምሁራን
************************
በአፍሪካ ቀንድና በሎጂስቲክስ መተላለፊያ መስመሮች ላይ እየተከሰቱ ያሉ የደህንነት ስጋቶች፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚና ሀገራዊ ህልውና በቀጥታ እየፈተኑት ይገኛሉ።
ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ያደርጉት የፖለቲካ ተንታኝ አፈወርቅ በደዊ፥ የቀይ ባህር አካባቢ ሁከት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት ቀጣናው አስተማማኝና ጠንካራ የሰላም ክንድ የሚፈልግበት ጊዜ ላይ መድረሱን ጠቁመው፣ ያም አስተማማኝ አቅም ያለው በኢትዮጵያ እጅ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ንግድ ከ90 በመቶ በላይ የሚከናወነው በባብ ኤል መንደብ እና በቀይ ባህር መተላለፊያ መስመር በኩል በመሆኑ፣ በቀጣናው የሚፈጠር ማንኛውም ዓይነት አለመረጋጋት በሀገራችን ህልውና ላይ ከፍተኛ አደጋ ይደቅናል ብለዋል።
ባለፉት አስርት ዓመታት የባህር ላይ ውንብድና፣ የህገ-ወጥ ሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውር እንዲሁም የሽብርተኞች እንቅስቃሴ እየተስፋፋ መምጣቱን ያነሱት ተንታኙ፤ እንደ አልሸባብና ሁቲ ያሉ ኃይሎች ቀጣናውን ለፖለቲካና ኢኮኖሚ ፍላጎቶቻቸው ማሳኪያ እያደረጉት ይገኛሉ ብለዋል።
በመሆኑም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሀገራት ሳይቀሩ ከኢትዮጵያ ጋር መስራታቸው ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማት ወሳኝ መሆኑን እንደሚረዱት አክለዋል።
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪው ተስፋዬ ጂማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ተሻግረው በደጃችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በባህሩ ዙሪያ የሚገኙ ሀገራት ብቻቸውን እነዚህን ታጣቂዎች ማስቆም እንደማይችሉ የተናገሩት ዶክተር ተስፋዬ፤ ኢትዮጵያ ባላት የህዝብ ብዛት፣ የኢኮኖሚ አቅም እና ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ታሪክ ቀይ ባህርን ብትጋራ የቀጣናውን ስጋት በመቀነስ ረገድ ትልቅ ድርሻ ማበርከት እንደምትችል ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ከታሪክ አጋጣሚዎች ጋር ተያይዞ የተነጠቀን መብት የመመለስ ጥያቄ በመሆኑ፣ ጉዳዩ በሰላማዊ ዲፕሎማሲና ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የሚሳካ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ "የፍትህ ጥያቄ" መሆኑን በማስመር፣ ሃገራችን ከተፈጥሮ ሃብቷ የምታገኘውን የኢኮኖሚ አቅም ተጠቅማ የዲፕሎማሲ ተደማጭነቷን እያደሰች እንደምትገኝ አስምረዋል።
የሱዊዝ ካናል ሰላምና የግብፅ ኢኮኖሚ ደህንነት የሚረጋገጠው በባብ ኤል መንደብ የሚያልፉ መርከቦች ሰላም ሲጠበቅ እንደሆነ ያብራሩት ተንታኙ፤ የቀይ ባህር ወጪና ስጋት እየጨመረ በሄደ ቁጥር ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶቿን እስከ መጨረሻው አቅሟ ለመጠቀም እንደምትገደድና ይሄንንም የቀጠናው ሀገራት ተረድተው በፍትሃዊ መንገድ ለመነጋገር ቁጭ ማለት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በኢንቲሃድ አብራር
#ebc #ebcnews #ethiopia #redsea #diplomacy #hornofafrica #economicgrowth #peaceandsecurity

“የሚጨሰው ጠረጴዛ” የተሰኘው የጥበብ ሥራ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለዕይታ ቀረበ
**************************
አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት የተሰበሰቡበትን ታሪካዊ ክስተት በኪነ-ጥበብ የሚያወሳው እና “የሚጨሰው ጠረጴዛ” (The Smoking Table) የተሰኘው ድንቅ የጥበብ ሥራ፣ በዛሬው ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለዕይታ ቀርቧል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው የአርት ፕሮፌሰር በሆኑት በፕሮፌሰር በቀለ መኮንን የተሠራው ይህ የጥበብ ሥራ፣ በኢትዮጵያ ለዕይታ ሲቀርብ የመጀመሪያው ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በጣሊያን ቀርቦ በበርካታ ዓለም አቀፍ ታዳሚዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።
በኤግዚቢሽኑ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዮሴፍ ቤኮ እና የሩሲያ፣ የቻይና እንዲሁም የሌሎች ወዳጅ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዮሴፍ ቤኮ፣ “የተሰበሰብነው ያለፈውን ታሪክ ብቻ ልናወራ ሳይሆን፣ ያንን መሠረት አድርገን ወደፊታችንን በጽናት ልናንጽ ነው” ሲሉ የዝግጅቱን ፋይዳ አስረድተዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ለዝግጅቱ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አጋር አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው፣ ለፕሮፌሰር በቀለ መኮንን የላቀ የጥበብ አስተዋፅኦ ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ፣ የአፍሪካን የመከፋፈል ታሪክ የሚወክለው ይህ ሥራ አፍሪካውያን በድል በደመቁበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ መቅረቡ ልዩ የታሪክ እና የሞራል ስሜት እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
ከኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን፣ ታሪካዊውን የመስከረም ዘጠኙን የክተት አዋጅ አስመልክቶ የመጀመሪያው የምክክር ጉባኤ ተካሂዷል።
ይህ የውይይት መድረክም በቀጣይ በየወሩ ተከታታይነት ባለው መልኩ እንደሚዘጋጅ አዘጋጆቹ ለኢቲቪ መዝናኛ አስታውቀዋል።
በሚሊዮን አደም
#ethiopia #ebc #scrambleforafrica #adwa

25 days ago
27 days ago
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ ተገናኙ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1988 ዓ.ም. ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተገናኝተው የቀድሞ ትዝታዎቻቸውን በደስታና በፍቅር ያደሱበት ልዩ መድረክ ተካሄደ።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የቀድሞ ተማሪዎቻቸውን የተቀበሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ምሩቃኑ ወደ ተማሩበትና ያደጉበት የቀድሞ ቤታቸው በመመለሳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ኃይሉ ወልደገብርኤል በበኩላቸው ይህ ስብሰባ እውን ሊሆን የቻለው ምሩቃኑ እርስ በርሳቸው ባደረጉት ውይይትና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በነበራቸው ንቁ ግንኙነት መሆኑን አብራርተዋል።
በዕለቱ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ የቀድሞ ተማሪዎች በማንኛውም ጊዜ ወደ ግቢያቸው እየመጡ የተማሩባቸውን ክፍሎችና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲውን እድገት እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
አክለውም፣ የቀድሞ ተማሪዎች ወደ ተማሩበት ተቋም ተመልሰው ትዝታቸውን ማደሳቸውና ለዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ለማድረግ መነሳታቸው ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ አርአያ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ምሩቃኑ በነበራቸው አስደሳችና ልዩ ቆይታ የነበሩትን ገጠመኞች ከመጋራት ባሻገር፣ ዕውቀትና ጥበብ ያገገኙበትን ዩኒቨርሲቲ በየዘርፉ ለመደገፍ ቃል በመግባት መርሃ ግብራቸውን አጠናቀዋል።
(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ )
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1988 ዓ.ም. ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ ተገናኙ!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1988 ዓ.ም. ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተገናኝተው ትዝታቸውን ያደሱበት ልዩ መድረክ ተካሄደ።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ ምሩቃኑን “ወደ ቀድሞ ቤታችሁና ዩኒቨርሲቲያችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ!” በማለት ተቀብለዋቸዋል።
የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪና የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ኃይሉ ወልደገብርኤል በበኩላቸው፣ ምሩቃኑ እርስ በርሳቸው በመወያየትና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በመነጋገር ዝግጅቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን ማድረግ እንደቻሉ አብራርተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ፣ ምሩቃኑን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ከተቀበሉ በኋላ፣ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት ራስ ገዝ ተቋም በመሆኑ፣ የቀድሞ ተማሪዎች በማንኛውም ጊዜ ወደ ግቢያቸው ተመልሰው የተማሩባቸውን ክፍሎችና የዩኒቨርሲቲውን ዕድገቶች እንዲጓበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም፣ የቀድሞ ተማሪዎች ወደ ተማሩበት ተቋም ተመልሰው ትዝታቸውን ማደሳቸውና ዩኒቨርሲቲውን መደገፋቸው ለቀጣዩ ትውልድ ታላቅ አርአያ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ምሩቃኑ በዝግጅቱ ላይ የቀድሞ ትዝታዎቻቸውን በማንሳት አስደሳችና ልዩ ቆይታ አድርገዋል። ትዝታዎቻቸውን ከመጋራት ባሻገርም፣ ያስተማራቸውን ዩኒቨርሲቲ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።
Via: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

1 month ago
አፍሪካ የ-Al ቴክኖሎጂ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን ፈጣሪ የምትሆንበትን መሠረት የጣለው አውደ ጥናት ተካሄደ!
#fastmereja :- "ለአፍሪካ ማህበረሰብ ተግዳሮቶች መፍትሔ የሚሰጡ መሠረታዊ ሞዴሎች" በሚል መሪ ቃል ለአራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የACT-Africa 2026 አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል በዛሬዉ እለት ተጠናቋል።
በአፍሪካ እና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ተመራማሪዎችን፣ የመረጃ ሳይንቲስቶችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን ያሰባሰበው ይህ መድረክ፤ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) ቴክኖሎጂዎችን ከአፍሪካ ልዩ ሁኔታዎች፣ ቋንቋዎች እና የልማት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዘርፎች ጋር ማጣጣም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት በማድረግ ነዉ የተካሄደዉ።
ዝግጅቱ በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የመረጃ እና አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ማህበረሰብ ተቋም (MIDAS) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እና በሽሚት ሳይንሶች የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዓላማውም አፍሪካውያን ባለሙያዎች የውጭ ሞዴሎችን በቃል ከመቀበል ይልቅ የራሳቸውን መፍትሄዎች እንዲገነቡ ማብቃት መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ እና ግንባታ አካባቢ ኮሌጅ ተመራማሪዎችና የACT-Africa 2026 ዋና አስተባባሪዎች ዶ/ር ዮናስ ምናሉ እማኙ እና ዶ/ር ደሳለኝ ወገሶ እንደገለጹት፤ መድረኩ በአህጉሪቱ ስነ-ምህዳር ውስጥ ለሚሰሩ ተመራማሪዎች የእውቀት ልውውጥና ጠንካራ አጋርነት ለመፍጠር ያለመ ስለመሆኑ ነዉ የገለፁት።
በአዘጋጅነት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከኡጋንዳ እና ኬንያ የመጡ ከፍተኛ ተመራማሪዎች የተሳተፉበት ይህ አውደ ጥናት፣ ተሳታፊዎች ከመሠረታዊ ንድፈ-ሐሳብ እስከ ተግባራዊ አተገባበር ያተኮሩ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ያስቻለ ሲሆን በተለይም በግብርና፣ ጤና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ መሠረተ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች ላይ ያተኮረ የሀካቶን ውድድር ተካሂዶ ተግባራዊ መፍትሄዎች ቀርበዋል።
ከስልጠናው ባሻገር ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩትን የጎበኙ ሲሆን፣ ዝግጅቱ ከመጪው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በዓል ጋር ተገጣጥሞ በመካሄዱ እንግዶች የሀገሪቱን ባህል እንዲለማመዱ እድል ፈጥሯል።
በአጠቃላይ አውደ ጥናቱ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የአርቲፊሻል ኢንተሊጂየንስ (AI) ሥርዓተ-ምህዳር ውስጥ የቴክኖሎጂ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን የራሷን ፈጠራ የምታመነጭበትን መሠረት በመጣል ተጠናቋል።

2 months ago
ኢትዮጵያውያኑ የአፍሪካን የበላይነት በመጨበጥ ወደ ዓለም አቀፍ ፍጻሜ ተሸጋገሩ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የችሎት ክርክር ውድድር የአፍሪካ ቀጣናዊ ዙር አሸናፊ በመሆን ወደ ዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን እንዳረጋገጡ ከሊንክ አፕ ሰምተናል።
ተማሪዎቹ በዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና አርቢትሬሽን ዙሪያ በሚያተኩረው በዚህ ፈታኝ ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉ ቢሆንም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ 14 ቡድኖችን በመረታት ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት አንደኛ ደረጃን በመያዝ ድል አስመዝግበዋል።
ይህ በቀጣናው ያገኙት ታላቅ ስኬት ወደ ዓለም አቀፉ የፍጻሜ ውድድር የሚያሸጋግራቸው ሲሆን በዓለም አቀፍ መድረክም አህጉራችን አፍሪካን በላቀ ደረጃ ወክለው የሚቀርቡ ይሆናል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የችሎት ክርክር ውድድር የአፍሪካ ቀጣናዊ ዙር አሸናፊ በመሆን ወደ ዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን እንዳረጋገጡ ከሊንክ አፕ ሰምተናል።
ተማሪዎቹ በዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና አርቢትሬሽን ዙሪያ በሚያተኩረው በዚህ ፈታኝ ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉ ቢሆንም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ 14 ቡድኖችን በመረታት ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት አንደኛ ደረጃን በመያዝ ድል አስመዝግበዋል።
ይህ በቀጣናው ያገኙት ታላቅ ስኬት ወደ ዓለም አቀፉ የፍጻሜ ውድድር የሚያሸጋግራቸው ሲሆን በዓለም አቀፍ መድረክም አህጉራችን አፍሪካን በላቀ ደረጃ ወክለው የሚቀርቡ ይሆናል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Sponsored by
Surafel
2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለመደብ መቅረታቸውን ኤስቢኤስ ራድዮ ከአውስትራሊያ ዘግበ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፤ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚካተቱ ተናግረዋል።
ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ደግሞ ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ እየተከናወነ ነው። በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ እና መሰል ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ማሳያ ይሆናል ተብሏል።

AAU ከ500 በላይ ሰራተኞቹን አሰናበተ‼️
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ-ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለ ምደባ ቀርተዋል።
ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፣ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል።
ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ነው።
በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጂማ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል።

አፈሳና ጦርነት የሰጉ የትግራይ ተማሪዎች አሁንም "ግቢ" ናቸው!
አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን በመስጋት ወደትግራይ ክልል መመለስ ያልቻሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ክረምቱን በግቢው ውስጥ ለማሳለፍ ፍቃድ ማግኘታቸውን ዋዜማ ሰምታለች፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች፣ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ስጋት ምክንያት ወደ ክልላቸው መመለስ ባለመቻላቸው፤ ክረምቱን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እንዲያሳልፉ ተፈቅዶላቸዋል።
ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ተማሪዎች እንደገለጹት፤ ጥያቄው መጀመሪያ ላይ በዩኒቨርሲቲው በኩል ተቀባይነት አጥቶ ለሳምንታት የቆየ ቢሆንም፤ ከጊዜያት በኋላ ግን በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ መፍትሔ ሊያገኝ ችሏል።

3 months ago
የዓለም የጸሐፍት ድርጅት (WOW) ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
ዕዝራ እጅጉ
#ethiopia | በኢትዮጵያውያን ደራሲያን እና በውጭ አገር የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች ተሳትፎ የሚካሄደው የዓለም የጸሐፍት ድርጅት (WOW) ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ይካሄዳል።
ጉባኤው "Africa in Shaping a Common Future" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣ በአፍሪካ ሥነ-ጽሑፍ፣ ባህላዊ እሴቶች እና የደራሲያን ዓለም አቀፍ ትብብር ዙሪያ የሚያተኩሩ ርዕሰ ጉዳዮች ይቀርባሉ።
በመድረኩ ላይ በአፍሪካ ሥነ-ጽሑፍ ላይ ጥናት ያካሄዱት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር አቢይ ዳንኤል የጥናት ወረቀት እንደሚያቀርቡ ሲገለጽ፣ ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱም ከዋና የጽሑፍ አቅራቢዎች መካከል ይገኛሉ።
የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ማርጋሪታ አል ለጉባኤው በተለይ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ሲሆን፣ የጉባኤው ሁሉም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸው ተገልጿል።
ጉባኤው በኢትዮጵያ መካሄዱ የኢትዮጵያ ደራሲያን ከዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ማኅበረሰብ ጋር ያላቸውን ትስስር በማጠናከር የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
በመጽሐፍ ዝግጅትና ሥነ-ጽሑፍ ሥራ ላይ የተሰማራው "ተወዳጅ ሚዲያ እና ኮምዩኒኬሽን" መሥራች ዕዝራ እጅጉን ጨምሮ የዝግጅት ኮሚቴው አባላትም በጉባኤው ይሳተፋሉ ተብሏል።
ስለ WOW
የዓለም የጸሐፍት ድርጅት (WOW) ዓለም አቀፍ ደራሲያንን ለማገናኘት፣ የሥነ-ጽሑፍ ሥራዎችን ለማበረታታት እና በባህሎች መካከል ውይይትን ለማጠናከር የተቋቋመ ዓለም አቀፍ ማኅበር ነው። ዋና መሥሪያ ቤቱ በሞስኮ የሚገኝ ሲሆን፣ በፕሬዝዳንት ማርጋሪታ አል ይመራል።
የድርጅቱ የምሥረታ ሀሳብ በ2019 በባኩ፣ አዘርባጃን የቀረበ ሲሆን፣ በ2023 በካይሮ፣ ግብፅ በስምምነት ሰነድ ተመስርቶ በዚያው ዓመት በይፋ ተመዝግቧል። የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ጉባኤውም በ2024 በዓቡጃ፣ ናይጄሪያ ተካሂዶ ነበር።
WOW በአሁኑ ጊዜ አባልነቱን በተለያዩ አገሮች እያስፋፋ ሲሆን፣ የፓናል ውይይቶችን፣ የልጆች የሥነ-ጽሑፍ መድረኮችን እና የጋራ የትርጉም ፕሮጀክቶችን በማካሄድ የዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ትብብርን ለማጠናከር እየሠራ ነው።

ጽናት
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ
1947-2017
#ethiopia | የዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን Asrat Atsedeweyn መጽሐፍ በጎንደር ከተማ እየተመረቀ ነው።
ይህ መጽሐፍ መታሰቢያነቱ ስጎንደር ዩኒቨርሲቲ ርስታቸወነ ስሰጡ 59 የጎንደር አርሶ አደሮች፧ እንዲሁም በተለያዩ ዘመናት በአመራርነት፤ በባለሙያነት፤ በሠራተኛነትና በአጋርነት አገልግለው ተቋሙን አሁን ላስበት ታላቅ ደረጃ ኣደረሱ ሞስንነ ባለውለታዎች በሙሉ ይሁን፡፡
***
ከመጽሐፉ ጀርባ (blurb)
ጎንደር የኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ዩኒቨርሲቲዎች በአንጋፋነት ተርታ የሚመደብ ነው:: በቅርቡም ሰባኛ ዓመቱንና የዩኒቨርሲቲው አስኳል የሆነውን ሆስፒታሉን መቶኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ መዘከሩ ይታወሳል። በዚህ የታሪክ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሆነው ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን እነሆ የዩኒቨርሲቲውን ታሪካዊ ጉዞ እርሱ ራሱ በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ካከናወናቸው ተግባራት ጋር አዛምዶ የሚዘግብ፣ በጠንካራ መረጃ ላይ የተዋቀረ መጽሐፍ አቅርቦልናል።
በዚህም የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ከግለ ታሪካቸው ጋር አሰናስለው ለንባብ ያበቁትን የቀደምት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንቶችን ፈለግ ተከትሏል ማለት ይቻላል። የተቋሙ ታሪካዊ ጉዞ በስኬት የታጀበውን ያህል አያሌ ፈተዎችና ተግዳሮቶችም የተጋረጡበት ነበር። የመጽሐፉ ትልቁ ፋይዳም እነዚህን ስኬቶችና ተግዳሮቶች ነቅሶ በማውጣት ሰፊ ግንዛቤ መስጠቱ ላይ ነው:: በተለይም በደራሲው አመራር የተከናወኑትን P70/100 ዝክረ በዓል ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶችና ክንዋኔዎች በዝርዝር ያትታል፤ ዘላቂ እርባናቸውንም ይጠቁማል። በመጨረሻም ከዩኒቨርሲቲ አመራር ተሞክሮው የቀሰማቸውን ትምህርቶች በተመሳሳይ ተቋም ግንባታ ላይ ላሉ ያካፍላል።
ባሕሩ ዘውዴ፣ የታሪክ ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
***
የስኬታማ ተቋማትና የአገር ግንባታ በትውልዶች ቅብብሎሽ፣ በቁርጠኝነትና በመሪዎች እቅድ ላይይመረኮዛል። ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን በዚህ መጽሐፋቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲን የ7ዐ ዓመታት ጉዞ፣ በየዘመናቱ የነበሩ መሪዎችንና ባለድርሻ አካላትን አበርክቶ፣ እንዲሁም የራሳቸውን የኃላፊነት ዘመን ፈተናና ስኬት በጥልቀት አቅርበዋል። በከፍተኛ ትምህርት አመራርነት በነበረኝ የረጅም ጊዜ ኃላፊነት ተቋሙንም ሆነ ደራሲውን በቅርብ እንደማወቄ መጠን፤ ይህ መጽሐፍ ከተጨባጩ ዓለም የተገኘ ጥልቅ እውቀት የሚሰጥ፣ ለመሰል ተቋማት መሪዎችና ተመራማሪዎች ታላቅ ማስተማሪያና ማጣቀሻ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።
ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚደንት
***
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈተናዎች ውስጥ ያለፈ ታላቅ ዓለም አቀፍ ተቋም ቢሆንም፣ የነበረው የታሪክ ምዝገባ ግን በቂ አልነበረም:: የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን “ጽናት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን የታሪክ ክፍተት ለመሙላት ሞክረዋል። መጽሐፉ፣ ተቋሙ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ለዛሬው ስኬት እንዲበቃ አሻራቸውን ያሳረፉ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮችን እውቅና ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ዶ/ር አሥራት ላለፉት ስምንት ዓመታት በኘሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ ያጋጠሟቸውን ከባድ ፈተናዎች እንዴት በብቃት እንደተወጧቸውና የዩኒቨርሲቲውን ስኬት እንዴት ማስቀጠል እንደቻሉ ያሳያል። ይህም ለተቋሙ ቀጣይ ጤናማ የአመራር ሽግግርና ለተተኪ አመራሮች ትልቅ ስንቅ የሚሆን ነው።
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ በኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር እና የቀድሞ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
እንኳን ደስ አለህ!

#እንድታውቁት
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ በጀመረው የሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤቱ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ-7ኛ ክፍል ለማስተማር ማቀዱን አስታውቋል።
ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ልጆች ዕድል እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን ባለው ክፍት ቦታ መሠረት ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ውጭ ላሉ ተማሪዎችም በውድድር ተደራሽ ይሆናል ብሏል።
ዩኒቨርሲቲው ትምህርቱን ለመስጠት ያቀደው 5 ኪሎ (በቀድሞው ድህረ ምረቃ/ፋርማሲ ትምህርት ቤት ግቢ) ሲሆን ምዝገባውም ማክሰኞ ሐምሌ 14 - ሐምሌ 21 /2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጿል።
ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል ?
- የመመዝገቢያ ክፍያ 1,000 ብር፤
- የተመዝጋቢ ልጆች የልደት ካርድ እንዲሁም ከቀድሞ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁበት ሰርተፊኬት፤
- 2 የወላጅ እና 4 የልጅ ፎቶግራፍ እንዲሁም ወላጆች ከሚሰሩበት የሥራ ክፍል የሰው ሀብት ቢሮ የተመዝጋቢው ወላጅ ወይም ህጋዊ አሳዳጊ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ፤
- የመመዝገቢያ ክላሰር እና የክፍያ ደረሰኝ
ዩኒቨረሲቲው በማኅበራዊ ሚዲያው ባወጣው መረጃ ወርኃዊ የተማሪዎች ክፍያን አላሳወቀም።

🎉 መልካም ልደት! 🎉
ለረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የትያትር ጥበብ፣ የከፍተኛ ትምህርት እና የባህል ልማት ዘርፍ ለዓመታት ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በአክብሮት እያሰብን፣ ዛሬ የልደት ቀንዎን በደስታ እናከብራለን።
እንደ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር መምህር እና የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፣ ለሥነ-ጥበብ እና ለትውልድ ግንባታ የሰጡት አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው።
መጪዎቹ ዓመታት በጤና፣ በሰላም፣ በደስታ እና በተጨማሪ ስኬቶች የተሞሉ ይሁኑልዎ። እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥዎ፤ ለሀገርዎና ለሙያዎ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦም ይበልጥ ይጎልብት።
"እያንዳንዱ ልደት አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ተስፋ እና አዲስ ዕድል ይዞ ይመጣል። ዕድሜዎ በጤና፣ በሰላምና በበረከት ይሞላ!" 🎂🎉
🎂 መልካም ልደት ለረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ! 🎉
#happybirthday #tesfayeeshetu #addisababauniversity #theatre #culture #getu

የቱሪዝም መዳረሻዎችን በዘመናዊ ስልት ለማስተዋወቅ የሚዲያ ፎረም ተመሰረተ
#ethiopia | የሀገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻዎች በዘመናዊ መንገድ ለዓለም ለማስተዋወቅና የመረጃ ልውውጡን በተቀናጀ ስልት ለመምራት የሚያስችል የቱሪዝም ኮሙኒኬሽን ስልጠና በአዳማ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፣ በዚሁ መድረክ ላይ የቱሪዝም ሚዲያ ፎረም በይፋ ተመስርቷል።
የፌደራልና የክልል የቱሪዝም ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞችንና ኃላፊዎችን ያሳተፈው ይህ መርሃ-ግብር፣ በዘርፉ የሚታየውን የተበታተነ የኮሙኒኬሽን ስራ በማስቀረት የተቀናጀ የቱሪዝም ዲፕሎማሲ ለመገንባት ያለመ ነው።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሴ ክብሩ፣ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከሀገሪቱ አምስት ዋና ዋና የኢኮኖሚ አመንጭ ዘርፎች ውስጥ አንዱ አድርጎ እየሰራበት መሆኑን ገልጸዋል።
በርካታ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማትና በነባሮቹ ላይ እሴት የመጨመር ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፣ እነዚህን ጸጋዎች በዘመናዊ ስልት ለአለም ማስተዋወቅና የሀገርን በጎ ገጽታ መገንባት የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሊወጡት የሚገባ ዋነኛ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለተሳታፊዎቹ ስልጠና የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት መምህር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የቱሪዝም ሚዲያ ስራ ከተለመደው የዜና አሰራር ወጥቶ ሳቢ፣ ታሪክን መሰረት ያደረገ እና ዲጂታል አማራጮችን የተጠቀመ ሊሆን እንደሚገባ አብራርተዋል።
አዲስ የተመሰረተው የሚዲያ ፎረም እስካሁን በዘርፉ በዘልማድ ከሚታየውና ለአንድ ወቅት ብቻ ከሚደረግ የመረጃ ልውውጥ ባለፈ፣ በክልሎችና በሚዲያ ተቋማት መካከል ወጥነት ያለውና ቀጣይነት ያለው የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት በመዘርጋት ለቱሪዝም እድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

4 months ago
ሠዓሊያንን ለዓለም የሚያስተዋውቅ የመረጃ ቋት እየተደራጀ ነው
#ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የሥነ-ጥበብ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ "Ethiopian Visual Arts Global Network" የተሰኘ የመረጃ ቋት በማደራጀት ላይ መሆኑን ገልጿል።
ይህ መድረክ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሰዓሊያንና የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች እርስ በርሳቸው እንዲገናኙ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ እና የፈጠራ ሥራዎቻቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲያስተዋውቁ የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህም የትምህርት ቤቱ ምሩቃን፣ በሌሎች ተቋማት የተማሩ እንዲሁም በልምድ የዳበሩ ሰዓሊያን በሙሉ በተዘጋጀው ዲጂታል ቅጽ በመመዝገብ የዚህ ዓለም አቀፍ መረብ አካል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ተሳታፊዎች ማንነታቸውን እና የሙያ ልምዳቸውን የሚገልጽ መረጃ በመሙላት የኢትዮጵያን ሥነ-ጥበብ በዓለም መድረክ ላይ በጋራ እንዲያደምቁ የአለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ጋብዟል።

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢ/ር አይሻ መሀመድ የበኩር ልጃቸውን ኸይሪያ አወል ዋግሪስን አስመረቁ
#ethiopia | ሚኒስትሯ በይፋዊ የ'ኤክስ' ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አጭር መልዕክት፣ እርሳቸው ቀደም ሲል ከተመረቁበት አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የበኩር ልጃቸው ተምራ በማጠናቀቋ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ ልጃቸው ኸይሪያ አወል ዋግሪስ ትምህርቷን የተከታተለችው በ'ሎጀስቲክስ እና ሰፕላይ ማኔጅመንት' የትምህርት ዘርፍ ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ ያስመረቀ ሲሆን፣ እንደ ዘሐበሻ ዘገባ የሚኒስትሯ የደስታ መግለጫም የዚሁ ትልቅ አገራዊ የምረቃ ስነ-ስርዓት አካል ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ethiopia | ሚኒስትሯ በይፋዊ የ'ኤክስ' ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አጭር መልዕክት፣ እርሳቸው ቀደም ሲል ከተመረቁበት አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የበኩር ልጃቸው ተምራ በማጠናቀቋ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ ልጃቸው ኸይሪያ አወል ዋግሪስ ትምህርቷን የተከታተለችው በ'ሎጀስቲክስ እና ሰፕላይ ማኔጅመንት' የትምህርት ዘርፍ ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ ያስመረቀ ሲሆን፣ እንደ ዘሐበሻ ዘገባ የሚኒስትሯ የደስታ መግለጫም የዚሁ ትልቅ አገራዊ የምረቃ ስነ-ስርዓት አካል ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
4 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሀመድ (ኢንጂነር) የበኩር ልጃቸውን ኸይሪያ አወል ዋግሪስን ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስመርቀዋል።
ሚኒስትሯ በይፋዊ የ'ኤክስ' ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አጭር መልዕክት፣ እርሳቸው ቀደም ሲል ከተመረቁበት አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የበኩር ልጃቸው ተምራ በማጠናቀቋ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ ልጃቸው ኸይሪያ አወል ዋግሪስ ትምህርቷን የተከታተለችው በ'ሎጀስቲክስ እና ሰፕላይ ማኔጅመንት' የትምህርት ዘርፍ ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ ያስመረቀ ሲሆን፣ የሚኒስትሯ የደስታ መግለጫም የዚሁ ትልቅ አገራዊ የምረቃ ስነ-ስርዓት አካል ነው።

u12e8u12a0u12f2u1235 u12a0u1260u1263 u12e9u1292u1268u122du1232u1272 u12e8u1270u121bu122au12ceu127d u121du1228u1243 u1225u1290 u1225u122du12d3u1275
#aau #addisbabauniversity #graduation ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት
#aau #addisbabauniversity #graduation
4 months ago
በኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ የሕይወት ተሞክሮ ላይ የሚያተኩር አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
#ethiopia | በአይናለም አዱኛ (ዶክተር) የተሰናዳውና በውጭ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕይወትና ተግዳሮቶች ላይ የሚያጠነጥነው "Walking Between Worlds: Letter to the Next Generation of the Ethiopian Diaspora" የተሰኘው መጽሐፍ በይፋ ተመርቋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በተከናወነው የገበያ ማቅረቢያ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣ ታዋቂ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና በርካታ የክብር እንግዶች ታድመዋል።
በዕለቱም በምሁራንና በተሳታፊዎች አማካኝነት ስለ ዲያስፖራው ማኅበረሰብ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ለአምስት አሥርት ዓመታት ገደማ (ከ38 ዓመታት በላይ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የኖሩት ደራሲዋ ዶክተር ዓይናለም አዱኛ፣ መጽሐፉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው ስለ አገራቸው በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸውና የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በስደት ዓለም ያሳለፉትን የረጅም ጊዜ የሕይወት ተሞክሮና ገጠመኝ መሠረት በማድረግ ያዘጋጁት ይህ መጽሐፍ ለሌሎች ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ዶክተር ዓይናለም ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን በጎ ተግባር ማከናወናቸውንና እንዲህ ዓይነቱ አበረታች ሥራ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ባለ 480 ገጽ ሆኖ ለንባብ መብቃቱ ታውቋል።
#diaspora #ethiopiandiaspora #booklaunch #aau #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው 18ኛው የመጻሕፍት ኤግዚቢሽን በይፋ መካሄድ ጀመረ
#ethiopia | ታላቅ የዕውቀት እና የባህል መድረክ የሆነው ባለታሪኩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጀመረው 18ኛው የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በድምቀት መካሄዱን ቀጥሏል።
በዝግጅቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ላለፉት አሥር ዓመታት ለንባብ ባህል ማደግና ለመጻሕፍት ስርጭት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሲሠራ መቆየቱን ጠቁመው፣ የዚህን ዓውደ ርዕይ ቀጣይነት በላቀ ሁኔታ ማስጠበቅና ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲው ፕረስ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዶክተር ደርብ አዶ በበኩላቸው ዝግጅቱ በየጊዜው በይዘቱም ሆነ በተሳታፊዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን በዝርዝር አብራርተዋል።
በዚህ ታላቅ የዕውቀት መድረክ ላይ ከ45 በላይ የሚሆኑ መጽሐፍት አከፋፋዮች፣ ዋና ዋና አሳታሚዎችና ታዋቂ የመጽሐፍት መደብሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ በሁሉም የዕውቀት ዘርፎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው መጻሕፍት ከ20 እስከ 50 በመቶ በሚደርስ ትልቅ ቅናሽ ለጎብኚዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
ከሽያጭና ከግዢ ስምምነቶች ባሻገርም የአዳዲስ መጻሕፍት ምረቃ ሥነ ሥርዓቶች፣ አንጋፋ ደራሲያንና ምሁራን ለወጣቱ ትውልድ ጠቃሚ ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉባቸው የውይይት መድረኮች እንዲሁም የሕፃናትን የንባብ ልማድ የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በዓውደ ርዕዩ ቀናት ውስጥ የሚጠበቁ ማራኪ መርሃግብሮች መሆናቸው ታውቋል።
#aaubookfair2018 #ethiopianliterature #readtolead #addisababauniversity #bookfair #ethiopia #ንባብለህይወት #የመጽሐፍትዓውደር #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 18ኛው የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ ተጀመረ
*******************
ትልቅ የዕውቀት እና የባህል መድረክ የሆነው 18ኛው የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በድምቀት ይካሄዳል።
ዩኒቨርስቲው 10 ዓመታትን በተሻገሩት ጊዜያት ለንባብና ለመፃህፍት ትልቅ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ዩኒቨርስቲው የአውደርዕዩን ቀጣይነት ማስጠበቅና ለውጡ የፈጠረውን እድል ተጠቅሞ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በአውደ ርዕዩ ከ45 በላይ መጽሐፍት አከፋፋዮች፣ አሳታሚዎችና የመጽሐፍት መደብሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በሁሉም የዕውቀት ዘርፎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው መጽሐፍት ለጎብኚዎች እንደቀረቡም ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕረስ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዶ/ር ደርብ አዶ አውደ ርዕዩ ከዘመኑ ጋር እያደገ በስፋትም በተሳታፊዎች ቁጥርም መሻሻሉን ተናግረዋል።
ያነጋገርናቸው መፃህፍት ሻጮችም በአውደርዕዩ ከ20 እስከ 50 በመቶ ቅናሽ በሚሆን ዋጋ መፅሀፍቶችን እየሸጡ እንደሆነ ገልፀውልናል።
የአዳዲስ መጽሐፍት ምረቃ ሥነ ሥርዓቶች፣ ታዋቂና አንጋፋ ደራሲያን ተሞክሯቸውን ለወጣቱ ትውልድ የሚያካፍሉባቸው የውይይት መድረኮች እንዲሁም የሕፃናት የንባብ ማበረታቻ ልዩ ዝግጅቶችም ዓውደርዕዩ በሚቀጥልባቸው ቀናት የሚጠበቁ መርሃግብሮች ናቸው።
በዳዊት ጣሰው
Ethiopian Broadcasting Corporation #አዲስአበባዩኒቨርስቲ #መጽሐፍት #ኢትዮጵያ

ዩኒቨርሲቲው ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዕውቀትን ለትውልድ የማሻገሩን ሥራ ያጠናክራል - ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትን ለትውልድ የማሻገሩን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)::
18ኛው ዓመታዊ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት ዓውደ ርዕይ ስድስት ኪሎ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በይፋ ተከፍቷል።
ዓውደ ርዕዩ ከሰኔ 1 ቀን እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን÷ ከ40 በላይ የመጻሕፍት አከፋፋዮች፣ አሳታሚዎችና የመጻሕፍት መደብሮች ተሳትፈዋል፡፡
በመጻሕፍት ዓውደ ርዕዩ በሁሉም የዕውቀት ዘርፎች ላይ የሚያተኩሩ በርካታ ነባርና አዳዲስ መጻሕፍት ለአንባቢያን በቅናሽ ዋጋ ቀርበዋል፡፡
አዳዲስ መጻሕፍት ይመረቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ላለፉት ከ50 ዓመታት በላይ በርካታ መጻሕፍትን ሲያሳትምና ተደራሽ ሲያደርግ ቆይቷል።
ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት በሚያደርገው ጉዞም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስን አቅም የማሳደግና የዘመኑን ገበያ በመጠቀም ተደራሽነቱን የሚያሰፉ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዕውቀትን ለትውልድ የማሻገርና ተቋሙ ከሌሎች መሰል ተቋማት ጋር ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እንደሚሠራም አረጋግጠዋል፡፡

6 months ago
ሰይፉ ፋንታሁን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፍቅር ስጦታ አበረከተ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ባዘጋጀው የ53ኛው ሳምንት መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የቀረበው ታዋቂው የሚዲያ ባለሙያ ሰይፉ ፋንታሁን ለተማሪዎች ያልተጠበቀ ስጦታ አበርክቷል።
ሰይፉ በዚህ መርሃ ግብር ላይ ለዘንድሮው የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች የሚሆኑ 25 ሙሉ የሱፍ ልብሶችን በስጦታ መልክ ሰጥቷል።
ታዋቂው የቪዲዮ እና የሬዲዮ ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል እንግዳ ሆኖ በቀረበበት ወቅት ለተመራቂ ተማሪዎች የላቀ ደግነቱን አሳይቷል።
ሰይፉ ለዘንድሮ ተመራቂዎች የ25 ሱፍ ልብሶችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ይህም ተማሪዎቹ በምረቃ ቀናቸው ደምቀው እንዲታዩ ለማስቻል የታለመ ነው።
ይህ ዓይነቱ የበጎ አድራጎት ተግባር ለሰይፉ ፋንታሁን የመጀመሪያው አይደለም። ባለፉት ዘጠኝ ተከታታይ ዓመታት በአማካኝ በየዓመቱ ለ40 ተማሪዎች የሱፍ ልብስ ሲያበረክት መቆየቱ ይታወሳል።
የሚዲያ ባለሙያው በየዓመቱ የሚያደርገው ይህ ድጋፍ በኢኮኖሚ አቅም ደካማ የሆኑ ተማሪዎች የምረቃ ቀናቸውን በደስታ እንዲያሳልፉ ትልቅ እገዛ እያደረገ ይገኛል።
#ሰይፉፋንታሁን #አዲስአበባዩኒቨርሲቲ #ደግነት #ምረቃ #በጎአድራጎት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

"ታዲያስ ሰይፋ" ምሽት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!
ሰይፉ ፋንታሁን የክብር እንግዳ ነው!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ለ53ኛ ጊዜ የሚያዘጋጀው ታላቅ የኪነ-ጥበብ ምሽት ረቡዕ ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
የዘንድሮው ምሽት ልዩ የሚያደርገው፣ ተወዳጁ የሚዲያ ሰውና የ"ታዲያስ አዲስ" ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን የክብር እንግዳችን ሆኖ በመካከላችን መገኘቱ ነው።
ሰይፉ ፋንታሁን ሙያዊ ልምዱንና የስኬት ጉዞውን ለታዳሚው ያካፍላል።
ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ በባህል ማዕከል አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ይቀርባሉ።
ዝግጅቱ ከቀኑ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ይጀምራል።
ሰይፉ ፋንታሁን በኢትዮጵያ ሚዲያ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያረፈ ሰው ነው። ከእሱ ልምድ መማርና በኪነ-ጥበብ ምሽት መታደም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለአዲስ አበባ ስነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ትልቅ ዕድል ነው።
ሼር በማድረግ እንተባበር፤ ኪነ-ጥበብን በጋራ እናክብር!
#getu #seyfufantahun #tadiyasseyfa #aau #culturecenter #artnight #literatureethiopia #poetrymusicmonologue #አዲስአበባዩኒቨርሲቲ #ባህልማዕከል #ሰይፉፋንታሁን #ኪነጥበብ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስፋፋትና ጥራቱን ለማረጋገጥ ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮዎች ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱ በዋናነት የመምህራንን የማስተማር ብቃት በማሳደግ የሙያ ማረጋገጫ (Professional Certificate) አሰጣጥ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ የክልል ትምህርት ቢሮዎች በበኩላቸው ለስልጠናው ብቁ የሆኑ መምህራንን የመለየት፣ አስተባባሪዎችን የመመደብ እና አስፈላጊውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ የማመቻቸት ኃላፊነት እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል።
seledadotio

የቻይንኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊሰጥ ነው
#fastmereja I በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን ለመጀመር የሚያስችል የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈርሟል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኦሮሚያ እና ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮዎች ጋር በጋራ ለመሥራት የተፈራረመው ይህ ስምምነት፣ የቋንቋ ትምህርቱን ጥራት ባለው መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው። ስምምነቱ በዋናነት መምህራንን በማሰልጠን፣ የማስተማር ብቃታቸውን በማሳደግ እና የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (Professional Certificate) በመስጠት ላይ ያተኩራል።
በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ የሁለቱ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ለሥልጠናው ብቁ የሆኑ መምህራንን የመመልመል፣ የሥራ አስተባባሪዎችን የመመደብ እና አስፈላጊውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ የማመቻቸት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ የሥልጠናውን አካዳሚያዊ ጥራት የመቆጣጠርና የመምራት ኃላፊነት ይኖረዋል።
ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የባህል እና የትምህርት ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል።
መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም.

የቋንቋ አጥርን የሚሰብረው አዲሱ ስምምነት
የቻይንኛ ቋንቋ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊዘልቅ ነው
የኔታ ሚዲያ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በስፋትና በጥራት ለመስጠት የሚያስችል ታሪካዊ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮዎች ጋር ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የባህል እና የኢኮኖሚ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል የሚፈጥር ነው።
ስምምነቱ በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው ቋንቋውን የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት በማሳደግ ላይ ሲሆን ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ መምህራን የሙያ ማረጋገጫ (Professional Certificate) ይሰጣል።
ዩኒቨርሲቲው የትምህርቱን ጥራት የመቆጣጠር፣ ስልጠናዎችን የመስጠት እና የትምህርት ጥራቱ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርበታል።
የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮዎች ለስልጠናው ብቁ የሆኑ መምህራንን የመለየት አስተባባሪዎችን የመመደብ እና አስፈላጊውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ የማመቻቸት ስራዎችን ያከናውናሉ።
በአሁኑ ወቅት ቻይና በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የኢኮኖሚ ተጽዕኖ እየጎላ መምጣቱን ተከትሎ ቋንቋውን መማር ለተማሪዎች አዳዲስ የሥራ እና የትምህርት ዕድሎችን እንደሚከፍት ይጠበቃል።
ይህ ፕሮጀክት በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ክልሎችም ሊሰፋ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ተጠቁሟል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ አዳዲስ የውጭ ቋንቋዎችን በማካተት ረገድ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።

Comments