የቋንቋ አጥርን የሚሰብረው አዲሱ ስምምነት
የቻይንኛ ቋንቋ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊዘልቅ ነው
የኔታ ሚዲያ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በስፋትና በጥራት ለመስጠት የሚያስችል ታሪካዊ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮዎች ጋር ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የባህል እና የኢኮኖሚ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል የሚፈጥር ነው።
ስምምነቱ በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው ቋንቋውን የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት በማሳደግ ላይ ሲሆን ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ መምህራን የሙያ ማረጋገጫ (Professional Certificate) ይሰጣል።
ዩኒቨርሲቲው የትምህርቱን ጥራት የመቆጣጠር፣ ስልጠናዎችን የመስጠት እና የትምህርት ጥራቱ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርበታል።
የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮዎች ለስልጠናው ብቁ የሆኑ መምህራንን የመለየት አስተባባሪዎችን የመመደብ እና አስፈላጊውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ የማመቻቸት ስራዎችን ያከናውናሉ።
በአሁኑ ወቅት ቻይና በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የኢኮኖሚ ተጽዕኖ እየጎላ መምጣቱን ተከትሎ ቋንቋውን መማር ለተማሪዎች አዳዲስ የሥራ እና የትምህርት ዕድሎችን እንደሚከፍት ይጠበቃል።
ይህ ፕሮጀክት በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ክልሎችም ሊሰፋ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ተጠቁሟል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ አዳዲስ የውጭ ቋንቋዎችን በማካተት ረገድ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።

2 months ago