የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1988 ዓ.ም. ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ ተገናኙ!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1988 ዓ.ም. ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተገናኝተው ትዝታቸውን ያደሱበት ልዩ መድረክ ተካሄደ።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ ምሩቃኑን “ወደ ቀድሞ ቤታችሁና ዩኒቨርሲቲያችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ!” በማለት ተቀብለዋቸዋል።
የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪና የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ኃይሉ ወልደገብርኤል በበኩላቸው፣ ምሩቃኑ እርስ በርሳቸው በመወያየትና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በመነጋገር ዝግጅቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን ማድረግ እንደቻሉ አብራርተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ፣ ምሩቃኑን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ከተቀበሉ በኋላ፣ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት ራስ ገዝ ተቋም በመሆኑ፣ የቀድሞ ተማሪዎች በማንኛውም ጊዜ ወደ ግቢያቸው ተመልሰው የተማሩባቸውን ክፍሎችና የዩኒቨርሲቲውን ዕድገቶች እንዲጓበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም፣ የቀድሞ ተማሪዎች ወደ ተማሩበት ተቋም ተመልሰው ትዝታቸውን ማደሳቸውና ዩኒቨርሲቲውን መደገፋቸው ለቀጣዩ ትውልድ ታላቅ አርአያ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ምሩቃኑ በዝግጅቱ ላይ የቀድሞ ትዝታዎቻቸውን በማንሳት አስደሳችና ልዩ ቆይታ አድርገዋል። ትዝታዎቻቸውን ከመጋራት ባሻገርም፣ ያስተማራቸውን ዩኒቨርሲቲ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።
Via: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

27 days ago