Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያውያኑ የአፍሪካን የበላይነት በመጨበጥ ወደ ዓለም አቀፍ ፍጻሜ ተሸጋገሩ
#ethiopia | ​የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የችሎት ክርክር ውድድር የአፍሪካ ቀጣናዊ ዙር አሸናፊ በመሆን ወደ ዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን እንዳረጋገጡ ከሊንክ አፕ ሰምተናል።

ተማሪዎቹ በዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና አርቢትሬሽን ዙሪያ በሚያተኩረው በዚህ ፈታኝ ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉ ቢሆንም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ 14 ቡድኖችን በመረታት ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት አንደኛ ደረጃን በመያዝ ድል አስመዝግበዋል።

ይህ በቀጣናው ያገኙት ታላቅ ስኬት ወደ ዓለም አቀፉ የፍጻሜ ውድድር የሚያሸጋግራቸው ሲሆን በዓለም አቀፍ መድረክም አህጉራችን አፍሪካን በላቀ ደረጃ ወክለው የሚቀርቡ ይሆናል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.