Logo
Getu Temesgen
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ ተገናኙ
#ethiopia | ​የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1988 ዓ.ም. ምሩቃን ከ30 ዓመታት በኋላ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተገናኝተው የቀድሞ ትዝታዎቻቸውን በደስታና በፍቅር ያደሱበት ልዩ መድረክ ተካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የቀድሞ ተማሪዎቻቸውን የተቀበሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ምሩቃኑ ወደ ተማሩበትና ያደጉበት የቀድሞ ቤታቸው በመመለሳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ኃይሉ ወልደገብርኤል በበኩላቸው ይህ ስብሰባ እውን ሊሆን የቻለው ምሩቃኑ እርስ በርሳቸው ባደረጉት ውይይትና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በነበራቸው ንቁ ግንኙነት መሆኑን አብራርተዋል።

​በዕለቱ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ የቀድሞ ተማሪዎች በማንኛውም ጊዜ ወደ ግቢያቸው እየመጡ የተማሩባቸውን ክፍሎችና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲውን እድገት እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።

አክለውም፣ የቀድሞ ተማሪዎች ወደ ተማሩበት ተቋም ተመልሰው ትዝታቸውን ማደሳቸውና ለዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ለማድረግ መነሳታቸው ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ አርአያ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ምሩቃኑ በነበራቸው አስደሳችና ልዩ ቆይታ የነበሩትን ገጠመኞች ከመጋራት ባሻገር፣ ዕውቀትና ጥበብ ያገገኙበትን ዩኒቨርሲቲ በየዘርፉ ለመደገፍ ቃል በመግባት መርሃ ግብራቸውን አጠናቀዋል።

(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ )

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.