Logo
SeledaPost
#እንድታውቁት

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ በጀመረው የሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤቱ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ-7ኛ ክፍል ለማስተማር ማቀዱን አስታውቋል።

ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ልጆች ዕድል እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን ባለው ክፍት ቦታ መሠረት ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ውጭ ላሉ ተማሪዎችም በውድድር ተደራሽ ይሆናል ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ትምህርቱን ለመስጠት ያቀደው 5 ኪሎ (በቀድሞው ድህረ ምረቃ/ፋርማሲ ትምህርት ቤት ግቢ) ሲሆን ምዝገባውም ማክሰኞ ሐምሌ 14 - ሐምሌ 21 /2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጿል።

ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል ?

- የመመዝገቢያ ክፍያ 1,000 ብር፤
- የተመዝጋቢ ልጆች የልደት ካርድ እንዲሁም ከቀድሞ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁበት ሰርተፊኬት፤
- 2 የወላጅ እና 4 የልጅ ፎቶግራፍ እንዲሁም ወላጆች ከሚሰሩበት የሥራ ክፍል የሰው ሀብት ቢሮ የተመዝጋቢው ወላጅ ወይም ህጋዊ አሳዳጊ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ፤
- የመመዝገቢያ ክላሰር እና የክፍያ ደረሰኝ

ዩኒቨረሲቲው በማኅበራዊ ሚዲያው ባወጣው መረጃ ወርኃዊ የተማሪዎች ክፍያን አላሳወቀም።

Seledadotio
Seledadotio
20 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.