14 hours ago
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በዋና መ/ቤታችን እንዲህ በድምቀት ተከብሯል!!
መልካም የሰንደቅ ዓላማ ቀን!
#nationalflagday #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopiat

18 hours ago
19ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን!" በሚል መሪ ቃል በዋና መ/ቤት፣ በዞንና ሪጅን ጽ/ቤቶቻችን በድምቀት አክብረናል!
መልካም የሰንደቅ ዓላማ ቀን!
#nationalflagday #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

23 hours ago
1 day ago
ሰንደቅ ዓላማ፦ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት እና ለገዢ ትርክት
***************
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከትውልድ ትውልድ የተሸጋገረ፣ በአባቶች የደም ቀለም የተጻፈ፣ የጀግኖች አባቶች የደማቸው ፍሳሽ እና የመሥዋዕትነት ውጤት የድል ዓርማ በመሆኑ ከሀገር ሕልውና ጋር ተያይዞ የሚታይ ነው።
የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ሲከበር፣ ዜጎች በሰንደቁ ፊት ቆመው ቃለ መሐላ በመፈጸም ለሀገራቸው ያላቸውን የማይነጥፍ ፍቅር እና ክብር የሚያረጋግጡበት ታላቅ አውድ ይፈጥራል።
በአዋጅ ቁጥር 654/2001 ዓ.ም መሠረት የሰንደቁ ቀለማት ሕጋዊ ትርጉም አግኝተዋል፤ አረንጓዴ የሥራ፣ የልምላሜ እና የዕድገት፣ ቢጫ የተስፋ፣ የፍትሕ እና የእኩልነት፣ ቀይ ደግሞ ለነፃነት እና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመሥዋዕትነት እና የጀግንነት ምልክት ናቸው።
ሰንደቁን ከሚወክሉት መገለጫዎች አንዱ የሆነው ብሔራዊ ዓርማ፣ የሕዝቦች አጠቃላይ ፍልስፍና እና የርዕዮተ ዓለም አቅጣጫን በግልጽ ይጠቁማል። በሰንደቁ መሐል ላይ የሚያርፈው ዓርማ ቀጥታ እና እኩል የሆኑ መስመሮች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እንዲሁም የሃይማኖቶች እኩልነትን የሚያሳዩ ሲሆን፣ ከመስመሮቹ የተዋቀረው ኮከብ በመፈቃቀድ የመሠረቱትን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ይወክላል። ቢጫው ጨረር ደግሞ ለሁሉም አቅጣጫ የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ታሪክ ከቅኝ ገዥዎች ነፃ ከወጣችበት ሐቅ ጋር የተቆራኘ ነው። የዓድዋ ድል በሰንደቃችን ሥር ተሰባስበን ለክብራችን መዋደቃችን ዐቢይ አብነት በመሆኑ፣ የድል አድራጊነት ከፍታ እና የጋራ ገዢ ትርክት ግንባታ መሠረት ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ የረዥም ዘመናት የነፃነት ተምሳሌት በመሆን ለአፍሪካ እና ለዓለም ሕዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ እና የድል ብርሃን ፈንጣቂ ሆኖ አገልግሏል። በቅኝ ግዛት የተጨቆኑ አፍሪካውያን ሀገራት ነፃ ሲወጡ የሰንደቃችንን ቀለማት መሠረት በማድረግ የራሳቸውን ዓርማዎች መምረጣቸው፣ ሰንደቁ የአህጉር፣ የዘር እና የነፃነት የጋራ ቋንቋ መሆኑን በውል ያሳያል።
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ ያላት ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ላይ ሉዓላዊነቷ በዘላቂነት ሊረጋገጥ የሚችለው ሀገርን ከልመና እና ጥገኝነት ነፃ በማውጣት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ስናረጋግጥ ነው።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የተበሰሩ ስኬቶች ሀገራችን ብሔራዊ ጥቅሟን እንድታስከብር እና የውኃ ሀብት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እንድታረጋግጥ የሚያስችሉ ናቸው።
ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጽንተን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በከፍታ እናውለበልባለን በሚል መንፈስ፣ ዜጎች በየተሰማሩበት ዘርፍ ሁሉ ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ለሰንደቁ ልዕልና እና ለሀገር ከፍታ ዘብ መቆም ይጠበቅባቸዋል።
በሰለሞን ገዳ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #nationalflagday #medemer #medemergovernment

Comments