23 days ago
ለ85 አማተር ከያንያን ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የጽህፈተ ተውኔትና የትወና ስልጠና ተጠናቀቀ
#ethiopia | በአማራ ክልል ባህል ኪነ ጥበባትና ዝክረ ታሪክ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአገው ጥናት ኢንስቲቲዩት ትብብር የተዘጋጀው የኪነ ጥበብ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።
ከ85 በላይ ሰልጣኞች የተሳተፉበት ይህ መርሃ ግብር ላለፉት አስር ቀናት በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ የመሰረታዊ ትወና እና የድራማ ድርሰት አፃፃፍ ትምህርት ሲሰጥ ቆይቷል።
የስልጠናው ማጠቃለያ ስነ ስርዓት በተለያዩ ጥበባዊ ስራዎች ደምቆ የቀረበ ሲሆን በተለይም በአርቲስት ንብረት ያለው ተፅፎ የተዘጋጀው አያና የፈንዞ ጌታ የተሰኘ ትውፊታዊ ቴአትር በሰልጣኞቹ አማካኝነት ለእይታ በቅቷል።
ከዚህም በተጨማሪ መዝሙሮች፣ መነባንቦችና ድራማዊ ህብረ ዝማሬዎች የቀረቡ ሲሆን ስልጠናው በከፍተኛ ድምቀትና በምረቃ ስነ ስርዓት ፍፃሜውን አግኝቷል።
#culture #arts #theatre #training #injibara #amhara #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
🎭 የአንጋፋው አርቲስት ግዮን ዓለምሰገድ የክብር ምሽት! 🌟
#ethiopia | ከ"ፍቅር መጨረሻ" እስከ "ገዳይ"፤ ከመድረክ ቴአትር እስከ ቴሌቪዥን መስኮት... በገጸ-ባህሪያት ውስጥ ሕይወት እየዘራ ጥበብን ያከበረው ጉምቱው ባለሙያ አርቲስት ግዮን ዓለምሰገድ ሊመሰገን ነው!
ብዙዎች "የሞተ ገጸ-ባህሪ ቢሰጡትም ከሞት ቀስቅሶ አላዘር ያደርገዋል" የሚሉለት ይህ ድንቅ ተዋናይ፣ ለሀገራችን ጥበብ ላበረከተው ድንቅ አስተዋጽኦ የሚገባውን ክብርና ምስጋና ይቸረው ዘንድ የጥበብ ወዳጆቹና ጓዶቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በዕለቱ ምን ይጠበቃል?
🎬 ዘጋቢ ፊልም፦
ከታላቁ ጌትነት እንየው እስከ ሱራፌል ተካ ምስክርነት የተሰጠበትና የአርቲስቱን የሕይወትና የጥበብ ጉዞ የሚዘክር ድንቅ ፊልም ይቀርባል።
🏆 የክብር ሽልማት፦
ለአርቲስቱ የሥራ አሻራ እውቅና የሚሰጥ የክብር ሽልማት ይበረከታል።
🎁 የስጦታ መርሐ-ግብር፦
ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ያላችሁ ወዳጆቹ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ስጦታችሁን በማበርከት ምስጋናችሁን መግለጽ ትችላላችሁ።
የዝግጅቱ ዝርዝር፦
📅 እሁድ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 ዩኒሰን ሆቴል (Unison Hotel)
🕒 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ
ለበለጠ መረጃና ስጦታ ለማበርከት የኮሚቴ አባላትን ያነጋግሩ፦
📞 ስንታየሁ ገብሩ፡ 0910206765
📞 አበባው ደረበ (ኒቆ)፡ 0913504087
📞 ደሳለኝ ድረስ (መረዋ)፡ 0912491788
📞 ቻሌ ማረው (ቻቻ)፡ 0918766188
ኑ!
የአስከበሩንን እናክብር፤ የሰሩልንን እናመስግን።
#gyionalemseged #ethiopianart #theatre #cinema #recognition #ethiopia #artisthonor #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

5 months ago
ዮናስ አብርሀም : በሬዲዮ ድራማ
ዕዝራ እጅጉ ( ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | ዮናስ አብርሃምን ሳውቀው በትክክል 28 ዓመት ከ7 ወር ይሆነዋል። ያስተዋወቀችኝም የሀይስኩል ጓደኛዬ እርቀሠላም በለጠ ናት። ያኔ 12ኛ ጨርሼ ፋና ስመላለስ ዮኒ ስመጥር ጋዜጠኛ ነበር። ከ11 ዓመት በኃላ በ2000 ሐምሌ ስቀጠር ደግሞ የመዝናኛ ክፍል ዐለቃዬ ሆኖ ተከሰተ። 2014 ላይ ደግሞ የዮኒን ታሪክ ከ180 ጋዜጠኞች ጋር የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ( መዝገበ አእምሮ ),ላይ ሰነድኩት።
ዮናስ ከወርቅ ፀባዩ ጋር ለሁላችንም የሚመች ምርጥ ሰው መሆኑን በሙሉ አንደበት እመሰክራለሁ ። የሥራ ትጋቱና ለሙያው ያለው መሰጠትም የተለየ ነው። አንድ ቀን በአደባባይ ስናመሰግነው ዝርዝሩን አወራለሁ። አሁን ግን ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላቅና።
ዛሬ ታህሳስ 24 2018 ዮናስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ተማሪዎች በሬድዮ ድራማ አሠራር ዙሪያ ልምዱን አካፍሎ ነበር።
ተወዳጁ የሬድዮ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና አዘጋጁ ዮናስ አብርሃም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር እና ፊልም ጥበባት ት/ቤት በመገኘት በማታው መርኃ - ግብር (Extension) ለሚማሩ የ4ኛ ዓመት የቴአትር ተማሪዎች በተግባር የታገዘ የልምድ ልውውጥ ስልጠና እና ልምዱን በማካፈሉ ብዙዎች ርካታና ደስታቸውን ገልፀዋል።
የሬድዮ ድራማ ከቴአትር እና ፊልም ትወና [Acting for different media (theatre, film, TV, voiceover, digital) ] የሚለይበትን ይህንኑ ስልጠናም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እንዲሁም በእለቱ ለተገኙ ታዳሚያን በባሕል ማዕከል አዳራሽ በመገኘት ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ ሰጥቷል፡፡
የቴአትር እና የፊልም ጥበባት ትምህርት ቤቱም ስልጠናውን ለሰጠላቸው ለተወዳጁ የሬዲዮ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዮናስ አብርሃም ያለውን አክብሮት እና ምስጋና ገልጿል። ለወደፊትም ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ከሌሎች እውቅ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ምሁራን ጋር በመተባበር ባለሙያዎቹ ልምዳቸውን ለተማሪዎቻችን የሚያካፍሉበት ሁኔታ እንደሚቀጥል የትምህርት ክፍሉ ያምናል።
ዮናስ ምርጥ ጊዜ እንደነበረው ነግሮኛል። ተማሪዎቹም ሁሉም ተደስተዋል። በድጋሚ እንዲመጣም ጠይቀዋል።
▸ ስለ ሬድዮ ድራማ ስክሪፕት አፃፃፍ/Voice Theatre/
▸ ስለ ሬድዮ ተዋናይነት ልዩ ባህሪ /Sound Acters/
▸ ስለ ሬድዮ ድራማ ዓይነቶች፣
▸ ከሌላው ዘርፍ ጋር ያላቸው ልዩነት እና አንድነት፣
▸ የሬድዮ ድራማ ዓላማ፣ ግብ፣ ሥነምግባር... ላይ ዕውቀቱን አካፍሏል።
▸ የ31 አመት የመፃፍና የማዘጋጀት ሠፊ የሥራ ልምዱን ተሞክሮ ማጋራቱ ይበል ያሰኛል።
የዮናስ አብርሃም ሥራዎች በቁጥር ሲገለፁ:-
● ፅሑፍ/script
▸ በየቀኑ - በአማካይ 20 ገፅ ይፅፋል፣
▸ በወር - 600 ገፅ፣
▸ በአመት - 7,200 ገፅ፣
▸ በ31 አመት - 223,200 ገፅ አየር ላይ አውሏል።
▸ ድራማ - 1/4ኛውን ይይዛል፤ 56 ሺ ገፅ ፅፏል፤
▸ ሬድዮ ፋና ላይ ብቻ ከ42 በላይ ድራማዎች፣ "ትንንሽ ፀሐዮች" (እማማ ጨቤ) እና "የጨረቃ ውል" ድራማን ሳይጨምር። እነሱ ብቻቸውን 5 አመት ተኩል እና 2 አመት ተኩል ተላልፈዋል።
▸ ዋዜማ፣ የበዓል ቀን ጠዋትና ማታ የተላለፉ ባለ 3 ክፍሎችን የበዓል ልዩ ድራማዎች አልቆጠረም።
➙ ከ124 በዓላት በላይ ፅፏል = 372 ክፍሎች ይሆናሉ።
➙ ሃምሣ ስድስት ሺህ ገፅ ወደ ባለ 250 ገፅ መፅሐፍ ቢመነዘር = 223 መፅሐፍ ይሆናል።
● ቅንብር/production
▸ ቢያንስ በሣምንት 2 = በ52 ሣምንት 104፣
▸ በ1612 ሣምንት (31አመት) = 3,224 ቅንብር።
● ግጥም
▸ በወር በአማካይ ከ 7 > በላይ = በአመት በአማካይ 50 =1600 አካባቢ የግጥም ሥራዎች።
● ጭውውት
▸ የሺና ስለሺን ጨምሮ = በአማካይ 1,200 ዓይነት ጭውውቶች ፅፏል።
● ማሥታወቂያ
▸ ድሮ ለሬድዮ ፋና ከፃፈው ጀምሮ አሁንም በገቢ ምንጭነት ለኤጀንቶች የያዘጋጃቸው ስክሪፕቶች በጠቅላላ ከ6ሺ በላይ ይሆናሉ።
● በድምፅ
▸ አየር ላይ የዋለበት ጊዜ ቢቆጠር... ከግማሽ በላይ ዕድሜውን ሬድዮ ውስጥ የኖረ ነው። ዮናስን እጅግ የማደንቀው በምክንያት ነው።

6 months ago
የሥነ ፅሑፍ ምሽት በሎስ አንጀለስ ሊደረግ ነው
ከዕዝራ እጅጉ( ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | በገጣሚ ይበልጣል ታደሰ በአሜሪካ የሚዘጋጀው 4ኛው የሥነ-ፅሑፍ ምሽት በሎስ አንጀለስ ከተማ December 21 አመሻሽ 5:00pm ሊደረግ መሆኑን አዘጋጆች ለተወዳጅ ሚድያ ገልፀዋል።
በ ይኸው መርሀ- ግብር በHermosa beach Theatre የሚደረግ ሲሆን በዕለቱ የክብር እንግዶች የቀይ ምንጣፍ ሥነ ሥርአት ይከናወናል።
ከዚህ ቀደም በሥነ ፅሑፍ ምሽቱ ላይ ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም፣ አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ፣ ዶክተር ወዳጄነህ መሀረነ፣ አርቲስት ማሪቱ ለገሰ፣ ዶክተር አሁንገና፣ አርቲስት ቤቲ ጂ እንዲሁም በርካታ የሀገራችን ወጣት ገጣሚያን ሥራዎቻቸውን ማቅረባቸው አይዘነጋም።
በ4ኛው የሥነ ፅሑፍ ምሽት በዕለቱ ገጣሚ ሜሮን ጌትነት፥ ገጣሚ ኑረዲን ኢሳ፥ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፥ ቀሲስ ዶክተር መላኩ በመገኘት ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
እንዲሁም በገጣሚ ይበልጣል ታደሰ ተፅፈው የተዘጋጁ “ ፍርድ " እና “ ታገቢኛለሽ" የተሰኙ ግጥምን ከመድረክ ስራ ጋር ያዋሃደ ኤክስፐርመንታል ቴአትር ለታዳሚያን ይቀርባል።
ከዚህ ቀደም የተደረጉትን የሥነ ፅሑፍ ምሽቶች በእግር ሚድያ ቲዩብ ማግኘት እንደሚቻልም አዘጋጆች ከሎስ አንጀለስ ለተወዳጅ ሚድያ ተናግረዋል።
የመርሀ ግብሩ አዘጋጅ የኪነ ጥበብ ሰው ይበልጣል ታደሰ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቴአትር ጥበባት የተመረቀና ኪነ ጥበብን ለማሳደግ ፅኑ ምኞት ያለው እንደሆነ ይታወቃል።

9 months ago
የሜሮን ጌትነት "ሌላ ዕውነት የለኝም" ታተመ
(ከዕዝራ እጅጉ)
ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘውና 134 ገፆች ያሉት "ሌላ ዕውነት የለኝም" የተሰኘው የሜሮን ጌትነት መፅሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።
ሜሮን በተለያየ ጊዜ የጻፈቻቸውን ግጥሞች በአንድ ላይ አድርጋ ለሕትመት ያበቃች ሲሆን ግጥሞቹም በግላዊ ገጠመኝና ዕይታ ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ።
ለ 10 ዓመታት መኖሪያዋን ባህር ማዶ አድርጋ የነበረችው የኪነ- ጥበብ ሰው ሜሮን ጌትነት ለጥቂት ዓመታት ከጥበቡ ዓለም ራቅ ብላ መቆየቷ ይታወቃል።
ለሥነ- ግጥም ልዩ አክብሮት አለኝ የምትለው ሜሮን በአዲሱ መፅሐፏ የሚሰማትን ገልጻለች።
"ሌላ እውነት የለኝም በተለያየ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ሆኜ የፃፍኳቸው ግጥሞች ስብስብ ነው። ግላዊ ስሜቶች፣ እውነቶችና በህይወት መስመር ላይ ያስተዋልኳቸው ማህበራዊ ሁነቶች ከጫሩብኝ ሀሳቦች ተነስቼ የከተብኳቸው ናቸው ትወዷቸዋላችሁ።"ስትል ሜሮን ሀሣቧን ለተወዳጅ ሚድያ ትገልጻለች።
ሜሮን ጌትነት፣ የህይወት ታሪኳ በአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ መዝገበ አእምሮ ላይ የተሰነደ ሲሆን ከግጥም ባሻገርም ቴአትር ፍቅር አላት።
ሜሮን ጌትነት በምሥራቅ ሀረርጌ አሰበ ተፈሪ /ጭሮ/ ከተማ ሰኔ 10 ቀን 1975 ዓ.ም የተወለደች ሲሆን በወላጆችዋ የሥራ ዝውውር ምክንያት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በተለያዩ የሃገሪቷ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘዋውራ የተማረች ሲሆን ይህም 1ኛ ክፍልን ወለጋ ሻምቡ አንደኛ ደረጃ፤ 2ኛ እና 3ኛ ክፍልን በአዲስ አበባ ህብረት በልጅነት፤ 4ኛ ክፍል በአራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ፤ 5 ኛ ክፍልን በጠመንጃ ያዥ፤ 6ኛ ክፍል በአሰበ ተፈሪ ቁጥር አንድ፣ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል በእውቀት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች።
ከዚያም በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በማርኬቲንግ ክፍል በዲፕሎማ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል በዲግሪ የተመረቀች ሲሆን የሁለተኛ ዲግሪዋንም በዚሁ ትምህርት ክፍል በቴአትር ለልማት /Theatre for Development/ ተከታትላለች።
ይህ በተለያዩ አካባቢዎች የማደግና የመማር አጋጣሚ ከሰዎች ጋር በቶሎ የመግባባትና ወዳጅነት የመፍጠር እንዲሁም ከአካባቢና ሁኔታዎች ጋር በፍጥነት መላመድ እንድትችል ያገዛት ሲሆን ለኪነጥበባዊ ምልከታዎቿና ለፈጠራ ዝንባሌዋ መሰረት ሆኗታል።
የኪነጥበበ ጉዞዋን የጀመረችው ሜሮን የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ በነበረችበት ወቅት በጋሽ አበራ ሞላ የወጣቶች ፕሮጀክት አማካኝነት የኢትዮጵያንና የጃፓንን ግንኙነት በሙዚቃ ለማጠናከር በተደረገ ውድድር ተመርጣ ወደ ጃፓን ተጉዛለች። በቆይታዋም ቶኪዮ በሚገኝ የሙዚቃ ት/ቤት የድምጽ ስልጠና በመውሰድ በጃፓንኛ ያቀነቀነች ሲሆን ከዝነኛ የጃፓን ድምጻዊ ጋር በመሆን ዝግጅቷን በተለያዩ ከተሞች ተዘርዋውራ ስታቀርብ ከመቆየቷም በተጨማሪ በጃፓንኛ ነጠላ ዜማ ሰርታለች። ቲቪ አሳሂ በተባለ የቴሌቭዥን ጣቢያም ለአራት ወራት ያህል የተላለፈ አጠቃላይ ጉዞዋን የተመለከተ ሳምንታዊ ፕሮግራም ሰርታለች። “ይህ አጋጣሚ መክሊቴን ፍለጋ ከቆፈርኩባቸው ቦታዎች አንዱና የልጅነት ጀብዱዬ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ሌላ ታላቅ አጋጣሚ ፈጥሮልኝ አልፏል” ትላለች።
ሜሮን ግጥሞቿን በበርካታ መድረኮች፣ መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከማቅረብ ባሻገር በ1999 ዓ.ም “ዙረት” የተሰኘ የግጥም መድበል አሳትማ ለንባብ አብቅታለች። በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ውክልናም የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ወጣት ጀግኖች ተሸላሚ በመሆን በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ከነበሩት ከክቡር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ እጅ የሜዳሊያ ሽልማት ተቀብላለች።
ሜሮን ከሁለት እስከ አምስት አመታት ያህል በመድረክ ላይ በቆዩ የሙሉ ሰአት ቴአትሮች ላይ በመሪ ተዋናይነት ሰርታለች። እነዚህም
ፍሬሽማን፣ ትሩፋልዲኖ፣ መስተፋቅር፣ ሰማያዊ ዓይን በሃገር ፍቅር ቴአትር፤ እልባት በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ፤
ቅጥልጥል ኮከቦች በብሄራዊ ቴአትር ናቸው። በአንድ ቀን ሁለት የተለያዩ ቴአትሮችን በሁለት ተለያዩ መድረኮች ላይ ለአመታት የተጫወተች ሲሆን በ2ኛው የተስፋ ኢንተርፕራይዝ ሃገር አቀፍ የቴአትር ፌስቲቫል የሴት ኮከብ ተዋናይት ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች። በአሜሪካም በሚኔሶታ ግዛት የፍሪንጅ ቴአትር ፌስቲቫል ላይ ተሳትፋ ኢትዮጲያዊት ገጸ ባህሪ ወክላ በመጫወት የሀገሯን ባህል አስተዋውቃለች።
“የቴሌቭዥን ድራማዎች ከተመልካች ጋር የበለጠ እንድተዋወቅ አድርገውኛል” የምትለው ሜሮን ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2006 ዓ.ም በተከታታይነት በኢትዮጲያ ቴሌቭዥን ሲተላለፉ በቆዩ ገመና አንድ፣ ገመና ሁለትና ዳና በተሰኙ ሳምንታዊ ድራማዎች ላይ ተወዳጅ ገጸ ባህሪያትን ወክላ በመጫወት ትታወቃለች።
አንድ ዕድል፣ ፊደል አዳኝ፣ ኤልዛቤል፣ የእግር ዕጣ፣ ዱካ፣ ይሉኝታ፣ቤተልሄም፣ ሄሎ ኢትዮጵያ፣ ዲፕሎማት፣ ጊዜ ግዙን፣ የተከፈለበት፣ ትራፊኳ እና ድፍረት የተወነችባቸው ፊልሞች ሲሆኑ የተከፈለበት በድርሰት፣ በዝግጅትና በፕሮዲውሰርነት ተሳትፋለች። በዚህም በኢትዮጲያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል የተመልካች ምርጫ ፊልም አሸናፊ እንዲሁም በቤተልሄም ምርጥ ረዳት ሴት ተዋናይት ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች። ከሃገር ወጪም በጀርመን የበርሊን ፊልም ፌስቲቫልና በአሜሪካ የሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተገኝታ በድፍረት ፊልም “የ2014 መታየት ያለባቸው የተመረጡ ተዋንያን” ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
በሬዲዮ ድራማ የዘመን ችግኞች እና ቀጭን ፍቅር በተሰኙ ተከታታይ ድራማዎች ላይ በትወና፤ ቃና ዜማ የተሰኘ ሳምንታዊ የመዝናኛ ፕሮግራም (ራዲዮ ፋና) በአዘጋጅና አቅራቢነት ለ2 ዓመታት ሠርታለች።

#ethiopia | ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘውና 134 ገፆች ያሉት "ሌላ ዕውነት የለኝም" የተሰኘው የሜሮን ጌትነት መፅሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ፍሬሽማን፣ ትሩፋልዲኖ፣ መስተፋቅር፣ ሰማያዊ ዓይን በሃገር ፍቅር ቴአትር፤
እልባት በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ፤

Sponsored by
Surafel
10 months ago
🇺🇸 መምህር፣ ደራሲና አዘጋጅ ኪሩቤል አሰፋው ዛሬ ወደ አሜሪካ አቅንቷል🙌
Kirubel Asfaw Mengesha (KAM): The Quiet Force Behind Ethiopian Cinema
In Ethiopia’s film industry, few names carry the quiet power of Kirubel Asfaw Mengesha, the founder of KAM Global Pictures. For more than two decades, Kirubel has focused on building a lasting film culture rather than chasing the spotlight.
Born in 1975 in Addis Ababa, Kirubel grew up surrounded by art. His father, Asfaw Mengesha, managed the Hollywood Films Department at the National Theatre (then Hailesillassie Theatre). At just five years old, Kirubel began attending film screenings with his father and fell in love with the magic of cinema, especially 1980s Hollywood films.
After finishing high school, his passion took him to Nairobi, Kenya, where he studied photography and cinematography. Returning to Ethiopia in 2000, he opened his first photo studio in Sidist Kilo with the support of his father.
Soon after, Kirubel partnered with Ethiopian athletics legend Haile Gebresillassie to establish KAM Institute, one of Ethiopia’s pioneering schools of photography and cinematography. Over the years, more than 3,000 young Ethiopians graduated from the institute, many of whom went on to shape the country’s modern film industry.
Determined to strengthen his craft, Kirubel later studied film production in Bangalore, India. Upon returning, he began producing feature films—13 to date—while giving opportunities to fresh talents such as Solomon Bogale, Samson Tadese (Baby), Mahider Assefa, and Girum Ermias. His two standout works, Amalayu (adapted from the French film Hors de Prix) and Wedegedelew (from Agatha Christie’s Ten Little Niggers), won both critical acclaim and commercial success.
Currently, his ambitious TV series “Ye Yakob Lejoch” is airing on FANA TV. The project is being hailed as a milestone for Ethiopian television, not least because six months of pre- and post-production were completed before its premiere—a rare standard in local TV production.
Through it all, Kirubel Asfaw Mengesha has remained a humble builder, letting his films and his graduates speak louder than his name.
📌 Quick Reference Biography
Born: 1975, Addis Ababa, Ethiopia
Education: Photography & Cinematography (Nairobi, Kenya); Film Production (Bangalore, India)
Career Milestones:
2000 – Opened first photo studio in Sidist Kilo
Early 2000s – Co-founded KAM Institute with Haile Gebresillassie; trained 3,000+ students nationwide
2000s–present – Produced 13 feature films introducing new talents
Notable works: Amalayu, Wedegedelew
2020s – Producer of TV series Ye Yakob Lejoch (FANA TV)
Legacy: Pioneer of Ethiopian film education and production, mentor to thousands, and one of the most influential figures in Ethiopia’s cinematic history.
👉

ተስፋዬ እሸቱ (ረዳት ፕሮፌሰር) ከሳንሆዜ፣ ካሊፎርንያ 🇺🇸
የአገሬ ሰው "ዝንጅብል ሻጭና ያልሞተ ሰው ይገናኛል" ይላል።
ከብዙ አመት በኋለ ገጣሚ ኑረዲን ኢሳን ሳንሆዜ፣ ካሊፎርንያ አገኘሁት። የልጅነት ትዝታዬን መለሰልኝ።
በ1990ዎቹ በአማራ ክልል የኪነጥበብ አብዮት የተስፋፋበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። ከፈለጋችሁ አርቲስት አለማየሁ ገ/ህይዎትን ጠይቁት። ዳሩ ግን አልቀጠለም። እኔም አይገርመኝም፤ ሀገሬ ባለማስቀጠል አትታማምና።
ከወረዳ ወረዳ ዞን ከዞን ጋር የትያትር፣ የሙዚቃ፣ የግጥም ውድድር ይካሄድ ነበር። "መቅረዝ" የሚል የኪነጥበብ መድብል የዚህ ኪነጥበብ አብዮት አንዱ አካል ነበር። ደራሲ አንዷለም አባተ (ዶ/ር) እማኝ ሁነኝ።
የባህርዳሩ ኑረዲን ኢሳ
ታዲያ በጊዜው ታዋቂ ተዋናይ፣ ገጣሚና ጸሀፌ ተውኔት ነበር።
አማራ ክልል በአማተር ክበባት የታቀፈ ከያኒ በሙሉ ህልሙ ኑረዲን ኢሳን መሆን ነበር። የኔ ህልምም እንደ ኑረዲን መድረክ ላይ መምነሽነሽ ነበር።
በጊዜው እነኑረዲን ትያትር ይዘው ክልሉን ይዞሮ ነበር። ይዘውት ከዞሩት ትያትር መካከል "የመጨረሻው መንገደኛ"ን አስተውሰዋለሁ።
እነኑረዲን የአፍሪካ ትያትር አንዱ መገለጫ ከሆነው ተጓዥ ትያትር "traveling theatre" ጋር ትውውቅ ነበራቸው። አይገርምም!
እና "ኦክቶፐስ" የተሰኘ ትያትር ይዘው ሲዞሩ ከርመው፣ ተራችን ደርሶ ትያትሩን ከባህርዳር መርዓዊ ይዘውት መጡ። ኑረዲን መርዓዊ መጣ ተበላ። አገር ቀውጢ ሆነች። ኑረዲንን መድረክ ላይ ለማየት ጓጓን። ከፍሎ መግባት በጭራሽ አይታሰብም። እሱንና ትያትሩን ለማየት አዳራሽ አጸዳን። አዳራሹ ከመጸዳቱ ብዛት አዲስ ሆነ፤ አዳራሹም አዲስ ከመሆን፣ እኛም ከማጽዳት ውጭ አማራጭ አልነበረንም። የትያትሩ አዘጋጆች በዚህ አልተላቀቁንም። "ኦክቶፐስ" የሚለው የትያትራቸው ማስታወቂያ አቦጀዴ ጨርቅ ላይ በመጻፋ ቆሽሾ ስለነበር እንድናጸዳው አስገደዱን።
አሁንም ትያትራቸውን በነጻ ለመመልከት፣ ማስታወቂያው የተጻፈበትን አቦጀዴ ጨርቅ ልቡ እስኪ ጠፋ በረድ ወንዝ (መርዓዊ የሚገኝ ወንዝ ነው) ወስደን አጠብነው።
"ድሀ በጉልበቱ" እንደሚባለው በጉልበታችን በነጻ ወደ አዳራሽ ገባን። እንደተመኘነው ኑረዲን መድረኩ ላይ ሲምነሸነሽ አየነው። ትያትሩ እንዳለቀ፣ ከደብተራችን ላይ ቀደን በያዝነው ብጣሽ ወረቀት ላይ ኑረዲንን አስፈረምነው። ሰው ከቦት ስለነበር ማውራት አልቻልንም። በሰው ተከቦ ለመደነቅ ኑረዲንን መሆን ተመኘሁ!
በአመቱ ዘጠነኛ ክፍል ሆኘ እኔ የሜጫ ወረዳን ፣ ኑረዲን የባህርዳር ዙሪያን በመወከል የምዕራብ ጎጃም ዞን ባዘጋጀው የትያትር ውድድር ላይ ተሳተፍን። ውድድሩ እንዳለቀ በውድድሩ መዝጊያ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የመድረኩ አስተዋዋቂ"አሁን የዞኑን ኮከብ ተዋንያን እንሸልማለን" አለ። ሁላችንም ልባችን ቀጥ አለች። ከሦስተኛው ጀመረና ሁለተኛ የዞኑ ኮከብ ተዋናይ...."ተስፋዬ እሸቱ" አለ።
ከተቀመጥኩበት ተነስቸ መድረኩ ላይ እንዴት እንደደረስኩ አላስታውሰውም። ሰማንያ ብር ተሸለምኩ። አቤት ሰማንያ ብር.... ሰማንያ ሚሊዮን በሏት። መድረክ መሪው ቀጠለና"አንደኛ የወጣው..." ሲል አዳራሹ ውስጥ የተሰሰበው በሙሉ "ኑረዲን.... ኑረዲን... ኑረዲን" አለ። ሁላችንም እርግጠኞች ነበርን። "ኑረዲን ኢሳ" አለ አስተዋዋቂው። ኑረዲን አንደኛ ኮከብ ተዋናይ በመሆኑ መቶ ብር ለመሸለም የሄደበትን ዝንጡ አካሄዱን ዛሬም አረሳውም።
ኑረዲን ከመድረክ እንደወረደ ወደኔ መጣ። አይኔንን ማመን አልቻልኩም። እጁን እራሴ ላይ ጭኖ፣"ትያትሩ ላይ ያሳየኸውን ትወና አይቸዋለሁ። በጣም አሪፍ አድርገህ ነው የተጫወትኸው። ወደፊት ትልቅ ተዋናይ ትሆናለህ" ብሎኝ ሄደ። ከተሸለምኩት ሰማንያ ብር በላይ ያስደሰተኝ፣ ከሩቅ የምናውቀውና መሆን የምንፈልገው የኑረዲን ማበረታቻ ነበር። ፈነደቁ። አሁን ድረስ እራሴን እየነካካ ያለኝ ነገር አእምሮዬ ውስጥ አለ።
ውድድሩ አልቆ ሜጫ እንደተመለስን ማን ይቻለኝ። በተሸለምኩት ሰማንያ ብር ከላይ እስከታች ዘነጥኩ። አፈር አይንካኝ አልኩ። ጉራዬን ማን ይቋቋመው። "ስማ" እላለሁ፤ ያለ ልኬ የገዛሁትን ጅንስ ሱሪ አስሬ ወደላይ እየሳብኩ። "እኔ እኮ ኑረዲን ያደነቀኝ ተዋናይ ነኝ።" እላለሁ። እንደ ዳዊት እደግምላቸዋለሁ። ይሄንን አረፍተ ነገር በቀን ሀምሳ ጊዜ አላልኩትም ብላችሁ ነው። በመደጋገሙ የተነሳ እናቴን አሰለቸኋት። አንድ ቀን " እኔ እኮ.." ብዬ ሳልጨርሰው እናቴ፣" ይሄ ኑረዲን የተባለውን ሰውዬ እግዜር ይይለት" ያለችውን አረሳውም። ከዛ በኋላ ኑረዲንና እኔ ተገናኝተን አናውቅም።
የአገሬ ሰው "ዝንጅብል ሻጭና ያልሞተ ሰው ይገናኛል ይላል"። ከሀያ አመት በኋላ ኑረዲንን ሳኖዜ፣ ካሊፎርንያ አገኘሁት። ቤቱ ምሳ ጋበዘኝ። ስለብዙ ነገር አወራን። ጨዎታው አይጠገብም። ሩጫ የበዛበት አሜሪካ የሚኖር አይመስልም። ስቆ ያስቅሀል። ጽፎ ያስቀመጠው ትያትር እንዳለ ነገረኝ። አገሬ ስመለስ እንደማዘጋጀው ቃል ገባሁለት።
ኑረዲን ሁለት የግጥም መድብሎች አሉት። ኑረዲን የሀሳብ ጌታ ነው። በግጥም መድብሎቹ፣ ለድምጻዊያን በሰጣቸው የሙዚቃ ግጥሞቹ ጥልቅ ፍልስፍና ያነሳል። ካላመናችሁኝ "ኢሻራ" የተሰኘው መድብሉን አንብቡት። በተለይ አንዱ ግጥሙ ትንቢትም ይመስላል። እንዲህ ይጀምራል...
ኑረዲን ኢሳ የባህርዳሩ
- ግጥሞቹን አድንቂዎቹ በቃል ሲውረዱ አድምጫለሁ ....
የትንሽ ሰው መርህ!
_______________
አልሆን ያለህ ለታ ማደግና መግዘፍ፣
ከትላልቆቹ አንዱን መርጠህ ዝለፍ።
-
(ኑረዲን ኢሳ)
እኔ - [ "አንድ ትልቅ ሃገር፣ በትንሽ መንደር ላይ
ተጣጥፎ ተኝቶ...." ] ባነበብኩት ቁጥር ግርም ይለኛል።
ጹሁፌን በሚከተለው የኑረዲን ኢሳ ግጥም ልጨርሰው።
"መቃብሬ ላይ ሚጻፍ
ጥብቅ ማሳሳቢያ ሸክላን ለምትሰሩ
እዚህ መቃብር ላይ ዐፈር አትዝገኑ
ሲነድ ሲቃጠል ሲጨስ በመኖሩ
ሲቃጠል ለመኖር፣
ለጀበና መስሪያ አይሆንም አፈሩ።"
አይገርምም?!
ይመችህ ኑረዲን!!
መልካም ጊዜ!

11 months ago
✴️ ሲናፕስ ኢትዮጵያ ገባኤ (Synapse Ethiopia Summit)
#ethiopia | በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሴጅ ኢትዮጵያ ፤ ኬ ኤም ኤስ ኢ ቲ ኤች ኸልዝ ትሬዲንግ አ.ማ እና በኢትዮ-ማይንድ አካዳሚ አዘጋጅነት ኒዉሮ ሳይንስና የአዕምሮ ጤና በመለከተ በትናንትናው እለት ማለትም ሃምሌ 14፣ 2017 ዓ.ም በብሔራዊ ተያትር የሲናፕስ ኢትዮጵያ ጉባኤ ተከናወነ።
✴️በፕሮግራሙ ላይ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ያላቸውና በእንግሊዝ ሃገር የሚኖሩት አቶ ወንድሙ ነጋሽ ስለ ሲናፕስ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰተዉ ኒዉሮ ሳይንስና የአዕምሮ ጤና በሚል ሰፊ ገለፃም አድርገዋል።
✴️በተጨማሪም በጉባኤዉ ላይ በዘርፉ ላይ የካበተ ልምድ ያላቸዉ የስነ- አዕምሮ ሃኪሞች እንዲሁም የስነ-ልቦና ባለሙያዎች የፓናል ዉይይት አድርገዋል። ይህ ጉባኤም በአይነቱ ልዮና አስተማሪ ከመሆኑ አልፎ እንደ ሀገርና እንደማህበረሰብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለዉ የጉባኤዉ ተሳታፊዎች የገለፁ ሲሆን ቀጣይነት እንዲኖረዉም አሳስበዋል።
✴️የሲናፕስ ኢትዮጵያ ጉባኤ ቀጣይነት ያለዉና በየጊዜዉ የተለያዩ ርዕሶች እየተነሱበት የሚቀጥልና በተለያዩ አካባቢዎችም ተደራሽ ለማድረግ እየሰተራ መሆኑን የገለፁት አስተባባሪዎች ለዚህ በጎ አላማ የሚመለከታቸው የመንግስትና የግል አካላት ተባባሪና አጋር እንዲሆኑም ጠይቀዋል።
#ሲናፕስ ኢትዮጵያ ገባኤ❗️
✴️Synapse Ethiopia Summit✴️
✴️For the first time in Ethiopia, the Synapse Ethiopia Summit on neuroscience and mental health was held yesterday, July 14, 2017 E.C. (July 21, 2025 G.C.), at the National Theatre. The event was organized by Sage Ethiopia, KMS ETH Health Trading S.C., and Ethio-Mind Academy.
✴️During the program, Mr. Wendimu Negash, an experienced professional in the field residing in the UK, provided an explanation about Synapse Ethiopia and gave a comprehensive presentation on neuroscience and mental health.
Additionally, psychiatrists and psychologists with extensive experience in the field held a panel discussion at the summit. Participants described the summit as unique and educational, emphasizing its significant contribution to the country and community. They also urged for its continuation.
✴️The organizers stated that the Synapse Ethiopia Summit will be an ongoing event, addressing various topics over time and aiming to reach different areas. They called upon relevant government and private bodies to collaborate and partner in this noble cause.
#synapseethiopiasummit❗️
HakimEthio