የቻይንኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊሰጥ ነው
#fastmereja I በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን ለመጀመር የሚያስችል የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈርሟል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኦሮሚያ እና ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮዎች ጋር በጋራ ለመሥራት የተፈራረመው ይህ ስምምነት፣ የቋንቋ ትምህርቱን ጥራት ባለው መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው። ስምምነቱ በዋናነት መምህራንን በማሰልጠን፣ የማስተማር ብቃታቸውን በማሳደግ እና የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (Professional Certificate) በመስጠት ላይ ያተኩራል።
በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ የሁለቱ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ለሥልጠናው ብቁ የሆኑ መምህራንን የመመልመል፣ የሥራ አስተባባሪዎችን የመመደብ እና አስፈላጊውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ የማመቻቸት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ የሥልጠናውን አካዳሚያዊ ጥራት የመቆጣጠርና የመምራት ኃላፊነት ይኖረዋል።
ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የባህል እና የትምህርት ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል።
መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም.

6 months ago