9 days ago
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን AHEFT ሽልማትን ተቀበለ
#ethiopia | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን የተዘጋጀውን Africa Higher Education for Transformation (AHEFT) Prize በመጀመሪያው ዙር ከተሸለሙ አምስት የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ሆኖ ተቀብሏል።
ሽልማቱ በተቋማዊ ደረጃ ዘላቂ ለውጥ በማምጣት ላይ ያሉ የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሽልማቱን ያገኘው በምርምርና ፈጠራ ዘርፍ ባሳየው ተቋማዊ ለውጥና እድገት ነው።
ዩኒቨርሲቲው ሽልማቱን መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. በጋና አክራ በተካሄደው የመጀመሪያው Higher Education Transformation Convening ላይ ተቀብሏል። መድረኩ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮችን፣ የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮችን፣ የመንግሥት ተቋማትን፣ የፋይናንስና የግል ዘርፍ አጋሮችን፣ የልማት አጋሮችን እና ወጣቶችን አሰባስቧል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የቡርኪና ፋሶው International Institute of Water and Environmental Engineering፣ የጋናው Kwame Nkrumah University of Science and Technology፣ የዩጋንዳው Muni University እና University of Rwanda የ2026 የAHEFT Prize ተሸላሚዎች ሆነዋል።
እያንዳንዱ ተሸላሚ ተቋም ለወጣቶች የትምህርት ዕድሎችን ለማስፋትና ተቋማዊ ለውጥን ለማጠናከር ሥራዎቹን እንዲያስፋፋ 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ያገኛል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመድረኩ በተቀዳ የቪዲዮ መልዕክት የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ወጣቶችን ለወደፊቱ ዓለም ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊቱን ዓለም እንዲቀርጹ የማስቻል ኃላፊነት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።
የAHEFT ሽልማት በመማርና ማስተማር፣ በምርምርና ፈጠራ፣ ተማሪዎችን ወደ ሥራ ዓለም በማሸጋገር እና በጤና ውጤቶች ላይ ዘላቂ ተቋማዊ ለውጥ እያመጡ ያሉ የአፍሪካ ተቋማትን ለመደገፍ የተጀመረ ዓመታዊ ሽልማት ነው።
በ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተደገፈው መርሐ ግብሩ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ቢያንስ 150 የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እውቅና ለመስጠት ያለመ ነው።
በአክራው መድረክ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት፣ የምርምር፣ የፈጠራ እና የችግር ፈቺ ሐሳቦች ማዕከላት ሆነው ሊያበረክቱ ስለሚችሉት ሚና ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱም በተለይ በከፍተኛ ትምህርት፣ በኢንዱስትሪና በማኅበረሰብ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር፣ ወጣቶችን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፈጣሪና መሪ እንዲሆኑ ማስቻል እና ምርምርን ወደ ኢንዱስትሪና ማኅበረሰብ ማድረስ ላይ አተኩሯል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያዎቹ የAHEFT Prize ተሸላሚዎች አንዱ መሆኑ፣ በመማርና ማስተማር፣ በምርምርና ፈጠራ፣ በአጋርነት እና ለወጣቶች ዕድል በመፍጠር የሚያከናውናቸውን ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎች ለማጠናከር የሚያግዝ እውቅና ሆኗል።
#aau #education #africa #aheft #mastercardfoundation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 months ago
በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ያለመው "ኤድቴክ ሳምንት 2026" መካሄድ ጀምሯል
#ethiopia | በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል ያለመው ሁለተኛው የ"ኢትዮጵያ ኤድቴክ ሳምንት" በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ሪች ፎር ቼንጅ ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎችና ስራ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል።
"ቴክኖሎጂን ለሁሉ አሳታፊና ጾታን መሰረት ላደረገ ትምህርት ማዋል" በሚል መሪ ቃል በሳይንስ ሙዚየም መካሄድ የጀመረው ይህ መድረክ፤ በኢትዮጵያ የትምህርት ቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪዎች የደረሱበትን ደረጃ ለማሳየትና ከባለሀብቶች ጋር ለማገናኘት ያለመ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዲጂታል ሽግግር ለማሳካት የትምህርት ስርአቱን በቴክኖሎጂ መደገፍ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
ባለፉት ጥቂት አመታት በሀገሪቱ የነበሩ የጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ቁጥር ከ50 ወደ 300 ማደጉን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ይህም ከ30 ሺህ በላይ የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ የጀመረችው የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ትልቅ ውጤት እያመጣ ነው።
ቴክኖሎጂ ግብ ሳይሆን የዜጎችን ህይወት ማሻሻያ መሳሪያ ነው።
ስራ ፈጣሪዎች የሚያመጧቸው አዳዲስ ሀሳቦች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል"ብለዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአማካሪዎች ሰብሳቢና የክልል ተጠሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት በበኩላቸው፤ መንግስት የብሄራዊ ፈተናዎችን በዲጂታል መንገድ ለመስጠት የጀመረው ጥረት የዘርፉን ትኩረት ያሳያል ብለዋል።
ቴክኖሎጂው ተደራሽነቱ ከከተማ አልፎ ገጠር ለሚገኙ ተማሪዎችና ሴቶች እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራም አክለዋል።
የሪች ፎር ቼንጅ ግሎባል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሶፊያ ብሬትሆልትስ በበኩላቸው፤ ድርጅታቸው ባለፉት ሶስት አመታት 34 የኤድቴክ ስራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ ከ400 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አሁን ላይ ትኩረቱ አዳዲስ ፈጠራዎችን ከመሞከር ባለፈ በስፋት ወደ ትምህርት ስርአቱ እንዲገቡ (Scale-up) ማድረግ መሆኑን አመልክተዋል።
በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የፈጠራ ትምህርት ማእከል ዳይሬክተር ዋዲኮ ዋይታ፤ ቴክኖሎጂ መምህራንን የሚተካ ሳይሆን የሚያግዝ መሆን እንዳለበትና ወጣቶች ለነገው የስራ አለም ብቁ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።
ለሚቀጥሉት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ ስራ ፈጣሪዎች የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ለእይታ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ከፖሊሲ አውጪዎችና ከአጋር አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ታውቋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen
#getutemesgen #ethiopia #edtechweek2026 #educationtechnology #digitalethiopia #reachforchange #mastercardfoundation #innovation #getutemesgen #moe #mint

Comments