Logo
EBC
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 18ኛው የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ ተጀመረ
*******************

ትልቅ የዕውቀት እና የባህል መድረክ የሆነው ​18ኛው የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በድምቀት ይካሄዳል።

ዩኒቨርስቲው 10 ዓመታትን በተሻገሩት ጊዜያት ለንባብና ለመፃህፍት ትልቅ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ዩኒቨርስቲው የአውደርዕዩን ቀጣይነት ማስጠበቅና ለውጡ የፈጠረውን እድል ተጠቅሞ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአውደ ርዕዩ ከ45 በላይ መጽሐፍት አከፋፋዮች፣ አሳታሚዎችና የመጽሐፍት መደብሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በሁሉም የዕውቀት ዘርፎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው መጽሐፍት ለጎብኚዎች እንደቀረቡም ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕረስ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዶ/ር ደርብ አዶ አውደ ርዕዩ ከዘመኑ ጋር እያደገ በስፋትም በተሳታፊዎች ቁጥርም መሻሻሉን ተናግረዋል።

ያነጋገርናቸው መፃህፍት ሻጮችም በአውደርዕዩ ከ20 እስከ 50 በመቶ ቅናሽ በሚሆን ዋጋ መፅሀፍቶችን እየሸጡ እንደሆነ ገልፀውልናል።

የአዳዲስ መጽሐፍት ምረቃ ሥነ ሥርዓቶች፣ ታዋቂና አንጋፋ ደራሲያን ተሞክሯቸውን ለወጣቱ ትውልድ የሚያካፍሉባቸው የውይይት መድረኮች እንዲሁም የሕፃናት የንባብ ማበረታቻ ልዩ ዝግጅቶችም ዓውደርዕዩ በሚቀጥልባቸው ቀናት የሚጠበቁ መርሃግብሮች ናቸው።

በዳዊት ጣሰው

Ethiopian Broadcasting Corporation #አዲስአበባዩኒቨርስቲ #መጽሐፍት #ኢትዮጵያ

7 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.