7 days ago
የሀገራዊ ሕልውናችን ዋስትና እና የዘላቂ ሰላማችን የጀርባ አጥንት፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት
*********************
የሕዝቦች አብሮነት፣ የልማት ሥራ እና ሀገራዊ ዕድገት ሊቀጥል የሚችለው አስተማማኝ ሰላም ሲኖር ብቻ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር እና የሕዝቦችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ቀዳሚው እና ጠንካራው የጀርባ አጥንት ሆኖ ይገኛል። ይህ ታሪካዊ ሠራዊት ዛሬ ላይ በመደመር መንግሥት ሁለንተናዊ የማድረግ አቅም ፍልስፍና እና ስትራቴጂ ተደግፎ በሁሉም መስክ አሸናፊነቱን እያረጋገጠ ይገኛል።
ሠራዊታችን በአሁኑ ወቅት ራሱን በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በማደራጀት ከፍተኛ እመርታ አስመዝግቧል። የመደመር መንግሥት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትን፣ ሀገርን በሁሉም ዘርፍ በብቃት የመገንባት ራዕዩ አካል በማድረግ፣ አቅሙን በዘመኑ ቴክኖሎጂ ገንብቶ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል።
በዚህም የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የምድር ኃይሉን ስልታዊ ዝግጁነት፣ የአየር ኃይሉን የላቀ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ፣ የባሕር ኃይሉን እና የሳይበር ደህንነት አቅሙን በማቀናጀት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ማንኛውንም ስጋት በአጭር ጊዜ የመቀልበስ ሙሉ ብቃት ገንብቷል።
የሠራዊታችን ጥንካሬ የሚለካው በዘመናዊ መሳሪያዎቹ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ የሠራዊቱ አባል በውስጡ ባለው ፅኑ የሀገር ፍቅር፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥነ-ምግባር እና ሕዝባዊ ወገንተኝነት ጭምር ነው። የመደመር መንግሥት በሠራዊቱ ውስጥ ማኅበራዊ ፍትሕን እና ብዝኃነትን ያከበረ አደረጃጀት ተግባራዊ በማድረጉ፣ ሠራዊቱ የኢትዮጵያ ሕዝቦች እውነተኛ ፍቅር እና አንድነት ማሳያ ሆኗል። ሠራዊቱ ከወታደራዊ ግዳጅ ጎን ለጎን በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ወቅት እንዲሁም በልማት ሥራ ከሕዝብ ጎን በመቆም የሚያደርገው ድጋፍ የዚሁ ሕዝባዊ ዓላማው ህያው ማረጋገጫ ነው።
በተጨማሪም በተለያዩ ማዕዘናት የሚከናወኑ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች፣ ዋና ዋና የንግድ መተላለፊያ መስመሮች እና የሕዝቦች የዕለት ተለት እንቅስቃሴዎች በሰላም እንዲቀጥሉ ከለላ በመስጠት ለሀገራዊ ብልፅግናችን የማይተካ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
በዚህም የመደመር ሁለንተናዊ የዕድገት ማዕቀፍ ከሰላም ጋር ተሳስሮ እንዲቀጥል በማድረግ ረገድ ሠራዊቱ የሰላም እና የኢኮኖሚ ልማት ዋስትናችን ሆኗል።
ከሀገር ወሰን ተሻግሮም በአፍሪካ ኅብረት እና በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ባሳየው ወታደራዊ ዲሲፕሊን እና ሥነ-ምግባር የኢትዮጵያን መልካም ስም በዓለም አቀፍ መድረክ በማስጠራት የሰላም አምባሳደርነቱን አስመስክሯል።
ለሀገሩ ክብር እና ለሕዝቡ ሰላም ሲል ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጠው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የትናንት ታሪካችን ወራሽ፣ የዛሬ ሰላማችን የጀርባ አጥንት እና የነገ ተስፋችን አስተማማኝ ዋስትና ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
#ethiopia #medemer #ethiopianarmy #endf #nationaldefense #peace #security #sovereignty #ebc

17 days ago
የፀና ሀገረ-መንግስትን በተቋማት ልዕልና መገንባት
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ሀገር ከትውልድ ወደ ትውልድ በክብር የምትሻገረው፣ በግለሰቦች ትከሻ ላይ ሳይሆን በማይናወጡ ጽኑ ተቋማት ስትገነባ ነው።
"የፀና ሀገረ-መንግስት" እንደየወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ ወዲያና ወዲህ የማይዋልል፣ በተቋማት ልዕልና ላይ ጽኑ መሰረት ያለው መንግስት ማለት ነው።
ይህ አይነቱ ታላቅ ግንባታ፣ ከነባር ኢትዮጵያዊ የባህል እሴቶቻችን ጋር ተሰናስሎ የሚዋቀር እንጂ በነፋስ ሽውታ በቀላሉ የሚናድ አይደለም።
ኢትዮጵያ የዘመናት የሀገረ-መንግስትነት ታሪክ ያላት ብትሆንም፣ በተዋረድ የመጣው የፖለቲካ ባህላችን ግን ከተቋማት ይልቅ ግለሰቦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የገዘፉበት ነበር።
አዲስ መንግስት ስልጣን በጨበጠ ቁጥር የነበረውን አፈራርሶ ከባዶ የመጀመር አባዜ፣ ሀገራችን የጸና ስርዓት እንዳትገነባ ፈተና ሆኖባት ቆይቷል።
በተለይም በደርግና በኢህአዴግ ዘመናት እንደ መከላከያ፣ ፖሊስና ደህንነት ያሉ ቁልፍ የሀገር ምሰሶዎች የገዥዎች ርዕዮተ-ዓለም መጠበቂያ በመሆን፤ ሀገርን ከመምሰል ይልቅ ፓርቲን እንዲመስሉ ተገደው ነበር።
ዛሬ ግን "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" የሚለውን ይህንን አፍራሽ ትርክት በመስበር፣ የለዉጥ መንግስት "ከማፍረስ ወደ መደመር" በሚል የላቀ እሳቤ የተቋማት ግንባታን የሀገረ-መንግስት ጉዟችን የጀርባ አጥንት አድርጎታል።
ይህን የታሪክ ስብራት በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "መደመር አፍርሶ የመጀመርን የፖለቲካ ባህል ለኢትዮጵያ እንደማይጠቅም ያምናል፤ ይህ አባዜም መቆም አለበት" ብለዋል።
የዚህ ጽኑ አቋም ፍሬም ዛሬ ላይ በግልጽ እየታየ ነው። የመከላከያ ሰራዊታችንን ጨምሮ ሌሎችም የጸጥታ ተቋማት ከጠባብ የፖለቲካ ተልዕኮ ተላቀው፣ የህዝብና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ብቻ በጽናት ወደሚያስጠብቁ ገለልተኛ የኢትዮጵያ ዋልታነት በመቀየር ላይ ይገኛሉ።
ሀገር በጽኑ መሰረት ላይ ልትቆም የምትችለው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ በኩራት የሚሸጋገሩና በብቃት የተካኑ ገለልተኛ ተቋማትን ማነጽ ስንችል መሆኑን የዘመናችን እውነታ በጉልህ እያስመሰከረ ነው።
ከተቋማት ጽናት ጎን ለጎን፣ የማይናወጥ ሀገረ-መንግስት ለመገንባት ህዝብን በጋራ ስነ-ልቦና የሚያስተሳስር አቃፊ ገዥ ትርክት መፍጠር ወሳኝ ነው።
ኢትዮጵያችን የበርካታ ማንነቶች፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች ውብ ዉህድ እንደመሆኗ፣ ይህንን ጸጋ ለልዩነት ማራገቢያነት ሳይሆን ለህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን ማጽኛነት ልንጠቀምበት ይገባል።
እውነተኛ ሀገራዊ ትርክት አንዱን ጥሎ ሌላውን የሚያነግስ ሳይሆን የጋራ ታሪካችንን፣ ጥልቅ ስነ-ልቦናዊ ትስስራችንን እና የማይነጣጠለውን የጋራ እጣ ፈንታችንን የሚያጎላ መሆን አለበት።
በአጠቃላይ፣ የተጀመረው የሀገረ-መንግስት ግንባታችን ከፍጻሜ የሚደርሰው የትላንት ስህተቶችን በማረም፣ ዛሬ የተገኙ ድሎችን በማጎልበትና ትላንትን ከነገ በሚያስተሳስር የጥበብ ድልድይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳሉት፣ ለዛሬና መጪው ትውልድ ጥቅም እና ፍላጎት የሚሰራ ሀሳብ እና ተቋም ማቆየት የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
የሀገረ-መንግስት ግንባታ ብዝሃነትን ባከበረ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የህዝቦችን እኩልነት በጽኑ የሚያረጋግጥ ነው።
ስለሆነም፣ የትላንት ቁስሎችን ሽረን የዛሬን አቅም አሟጠን በመጠቀም፤ ሀገራዊ መግባባትን ከተቋማት ልዕልና ጋር በማዋሃድ የማይናወጥና ለትውልድ የሚሻገር ሀገረ-መንግስት መገንባት የዘመናችን ትልቁ አጀንዳ ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

19 days ago
ሀሳብ አልባ ፖለቲካ የፈጠረውን ታሪካዊ አዙሪት የሰበረው የመደመር ጉዞ
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ“የመደመር መንግሥት” መጽሐፋቸው “የሐሳብ አልባ ፖለቲካ ግብ ከሕግ በላይ ሆኖ ሀብት እና ሥልጣን መቀራመት ነው” ሲሉ ያሰፈሩት የዘመናዊ ታሪካችንን ፖለቲካዊ ስብራት በጥልቀት የፈተሸ እውነት ነው።
በመደመር ብያኔ መሠረት ሐሳብ አልባ ፖለቲካ ማለት የፖለቲካ ሥልጣንን ከሕዝብ አገልግሎት እና ከተቋማዊ አሠራር በመነጠል፣ ለግል ጥቅም ማክበሪያነት የማዋል ፍጹም አፍራሽ አካሄድ ነው።
የፖለቲካ ተዋንያን የሐሳብ ልዕልናን ሲያጡ ሥልጣን የሕግ ማስከበሪያ መሣሪያ መሆኑ ቀርቶ ከሕግ በላይ ይሆናል።
ይህ ሁኔታ ደግሞ በዘመናዊው የፖለቲካ ታሪካችን ተቋማት ገለልተኛ ሆነው እንዳያድጉ በማድረግ የሕዝብን ሀገራዊ ተስፋ ሲያጨልም ቆይቷል። ይህ አካሄድ በዘመናት ጉዟችን ያስከፈለን ዋጋ እጅግ ከባድ ነው።
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የነበሩ የሥልጣን ሽግግሮች አዲስ የመጣው ሁሉ የቀደመውን በጎ ነገር አፍርሶ ከዜሮ በመጀመር አክሳሪ አዙሪት የተተበተቡ ነበሩ።
ከዘውዳዊው ሥርዓት እስከ ደርግ፣ ከዚያም እስከ ኢሕአዴግ የነበረው ጉዞ አንዱን ጥሎ ሌላው የሚነሳበት በመሆኑ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሳይገነቡ ቀርተዋል።
በዚህም ምክንያት ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ከእኛ ኋላ የነበሩ ሀገራት ጭምር በጠንካራ ተቋማዊ መሠረት ተስፈንጥረው የዓለም የኢኮኖሚ ቁንጮ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ግን በእንደገና ጅምሮች እና በአለመረጋጋት ውስጥ እንድትባዝን ተደርጋለች።
ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ግን የመደመር መንግሥት ይህን አክሳሪ አዙሪት ለመስበር በጽናት የታጀቡ ተጨባጭ እርምጃዎችን ወስዷል።
መደመር የነበረውን አፍርሶ እንደገና የመጀመርን አጥፊ ልማድ በመግታት፣ የትናንት አዎንታዊ ወረቶችን ጠብቆ ማስፋት እና የተሠሩ ስህተቶችን ማረም የሚያስችል ሀገር በቀል ፍልስፍናን በተግባር እያሳየ ነው።
ሥልጣን ለሕግ እና ለሥርዓት የበላይነት እንዲገዛ ለማድረግ በፍትሕ፣ በጸጥታ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች ተቋማዊ ማሻሻያዎች ተተግብረዋል።
የጽንፍ ፖለቲካን ለመታገልም እንደ ሽምግልና ያሉ ሀገር በቀል ጥበቦችን ከዘመናዊ አስተዳደር ጋር በማጣመር አካታች የመግባባት ዴሞክራሲን መሠረት የሚያስይዝ ባህል እየተገነባ ይገኛል።
አሁን በተጀመረው የመደመር አካሄድ መፃኢው የኢትዮጵያ ተስፋ እጅግ ብሩህ ነው። አሁን ላይ የምናያቸው ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ስኬት፣ የተጀመሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና የዲፕሎማሲ ድሎች የዚህ የሐሳብ ልዕልና ውጤቶች ናቸው።
ሐሳብ አልባነትን በሐሳብ ልዕልና፣ መከፋፈልን በመደመር፣ እንዲሁም አፍርሶ መገንባትን በይዞ ማደግ በመተካት የተጀመረው ይህ ጉዞ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ መሠረት በጠንካራ ተቋማት ላይ አቁሞ ለአፍሪካም አርአያ ወደምትሆንበት ማማ የሚያሸጋግር ዘላቂ አቅጣጫ ነው።
በለሚ ታደሰ
#medemer #ethiopia #medemermengist #pmabiyahmed #ebc #nationalrenewal #ethiopianpolitics

20 days ago
የመደመር አንቀጽ
የዓባይን ልጅ ለምን ውኃ ጠማው?
ሀገራችን ከዓለም ወደ ኋላ ለመቅረት ምክንያት እንዳይኖራት ተደርጋ የተፈጠረች እስኪመስል ድረስ ብዙ ጸጋን የተቸረች ምድር ናት።
ከመሬት እስከ መልከ ብዙ የአየር ሁኔታ ተንበሽብሻለች። ከተፋሰሶች እስከ ከርሰ ምድር ውኃ ተጥለቅልቃለች። ከወርቅ እስከ ታንታለም፣ ከጋዝ እስከ ፖታሽ ታድላለች።
ከስትራቴጂያዊ ጂኦፖለቲካዊ አቀማመጥ እስከ ከፍተኛ ተራሮች ተሞልታለች። ከታሪክ እስከ ቅርስ፣ ከኅብረ ብሔራዊነት እስከ ብዝኃ እምነት ተትረፍርፋለች።
ኢትዮጵያ ከስጦታዎች ይህ አጠራት የምትባል አይደለችም። እነዚህን የተፈጥሮ ችሮታዎች ተጠቅመን ማደግ እንዳንችል ብዙ ተግዳሮቶችን በታሪካችን አሳልፈናል።
በሆኑ ዘመናት ብቅ ያሉትን የፈጠራ ፍንጮችም፤ ፈጥነን ወደ ዘላቂ ልማት አልቀየርናቸውም። ያለንን ጸጋም አዳዲስ ሀብት ለመፍጠር አልተጠቀምንም።
እነዚህ ተግዳሮቶች አንዱ ለአንዱ መነሻ ምክንያት እየሆነ፤ ዛሬ ካለንበት የድህነት ደረጃ ላይ እንገኛለን። የመከራ አዙሪትና የሥልጣኔ ሾተላይ አለብን።
ሀብቶች ሳይባክኑ በሀገር ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እያንዳንዱን ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመቀየር መሠረተ ልማት ወሳኝ ነው።
በሀገራት የልማት ጉዞ መሠረተ ልማት መገንባት የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠውም ለዚህ ነው።
ይሁንና መሠረተ ልማቶችን መገንባት በቀላል ዐቅም የሚተገበር አይደለም። በአነስተኛ ሥራዎች ጀምሮ እያደጉ መሄድ የብዙ ሀገራት ተሞክሮ ነው።
ከትንሽ ተነሥቶ ሩቅ የሚያልም ጉዞ ማሳካት፤ ወደ ሚቀጥለው ግዙፍ መሠረተ ልማት ግንባታ ለመሸጋገር ወሳኝ ነው።
ማደግ ዳገት የሆነባቸው ሀገራት ተግዳሮት፤ ከእነዚህ አነስተኛ ጉዞዎች መኮላሸት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #medemer #እመርታ #መደመር #ኢትዮጵያ

ተናግሮ ማድረግ ፣ ቃል ገብቶ መፈጸም:- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ
***********************
የዘንድሮው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ተራ የቀን መቁጠሪያ ለውጥ ብቻ አይደለም። ሀገራችን አዲስ ገጽ ገልጣ አዲስ ታሪክ ጽፋለች፤ መርጣለች፣ መክራለች፣ አሸንፋለች፣ አንሰራርታለችም። ፈተናዎች ወደ ታላቅ ዕድል ተቀይረዋል።
በጸኑ እና ዝቅ ብለው በሠሩ ልጆቿ ጥረት የዘመናት የአዙሪት ጥላ ላይመለስ ተገፏል፤ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት ብቻ ለበርካታ አስርት ዓመታት ያላሳካናቸውን ድሎች ማሳካት ችለናል። ሩቅ የማለም፣ አቅዶ የመጀመር እና በፍጥነት የማጠናቀቅ አዲስ የሥራ ባህልም ገንብተናል። ይህ የሀገራችንና የመንግሥቷ ልዩ መገለጫ ሆኗል።
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር የሚጨበጥ ብርሃን ፈንጥቋል። ከአፈሙዝ የሥልጣን ውርስ ተላቆ «ሀገረ መንግሥት በሕዝብ ካርድ ብቻ ይጽና» የሚል ድምፅ ከአጽናፍ አጽናፍ አስተጋብቷል። ሕዝባችን ቀን በፀሐይ፣ ሌት በውርጭ፣ ከሕመሙ ታግሎ፣ አትምረጥ ካለው ጋር ገጥሞ፣ የሚፈልገውን ነግሮናል። ሀገር አጽንቷል፣ ዴሞክራሲን መርጧል።
በሀገራዊ የምክክር ማዕቀፍ የኅብረ-ብሔራዊቷ ሀገራችን ልጆች ተሰባስበው ስለ እናት ሀገራቸው በአንድ አዳራሽ መክረዋል፤ ዘክረዋል። ይበጃል ያሉትን በጎ ሐሳቦች በነፃነት አቅርበዋል። በአጭሩ በኢትዮጵያ ምድር በዘመኑ አርበኞች አዲስ ገድል ተፈጽሟል። ይህ እውነት የልጆቻችንን ተስፋ ያለመለመ፣ በዘመናት መካከል በኩራት የምንተርከው ወርቃማ ታሪካችን ነው።
አንቆምም! ገና ብዙ ሥራ አለብን፤ እንፈጥናለን፣ መሰናክሎቻችንን ሁሉ በብሕላት እየዘለልን ወደ ሀገራችን መሻቶችና ሕልሞች በጽናት እንዘልቃለን። ታላቅ ሀገር አለችን፤ እየተማከርን እንገነባታለን፣ እየገነባንም እንማክራለን። ሁሉንም አሸናፊ ያደረገው አዲሱ መንገዳችን ይኸው ነው። መመካከር ።መመካከር ። መመካከር።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሕግ የበላይነት በጥብቅ ዲሲፕሊን ከተመራበት መንገድ ጎን ለጎን፣ መንግሥታችን ያጠፉ ልጆቹን በምሕረት አቅፏል፤ በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን በይቅርታ ፈትቷል። ይህ ውሳኔ ብዙ ሀገራት የተመኙት፣ ኢትዮጵያ ግን ያሳካችው የበቀል አዙሪትን የሰበረ ታላቅ እርምጃ ነው።
ውሳኔው ለሀገራችን ዘላቂ ጥቅም ሲባል የተከፈለ ውድ ዋጋ መሆኑን የመደመር መንግሥት ይገነዘባል። ይቅርታ የጽኑ ሀገረ-መንግሥት ዋነኛ ምሰሶ ነው፤ ውሳኔው ከሀገራዊ ምክክሩ ጋር ተጣጥሞ ብሔራዊ መግባባትን ያጠናክራል። የተፈቱት ወገኖቻችን ዕውቀታቸውን እና አቅማቸውን ለሀገር ግንባታ እንደሚያውሉ እናምናለን፤ ይህም ለነገዋ ኢትዮጵያ የማይናወጥ መሠረት ይጥላል።
ከፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ መግባባት ጎን ለጎን፣ በአንድ ሀገር ፖለቲካዊ መረጋጋት እየተሻሻለ የሚመጣው በሀገር ደረጃ ጠንካራ የኢኮኖሚ ስኬቶች ሲመዘገቡ እና ሕዝባዊ አመኔታ ሲገነባ ነው። ኢትዮጵያ ይህን አድርጋዋለች።
ዛሬ ላይ በሀገራችን እየተመዘገበ ያለው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት በአፍሪካ ፈጣኑ እና መሠረቱ የሰፋ አስደናቂው እድገት ነው። ይህን እውነት ባንዳውም ባዳውም ሳይወድ በግዱ ይቀበለዋል።
የመደመር መንግሥት ጉርሷን የማትለምን እና ክብሯን የጠበቀች ሉዓላዊት ሀገር ለመፍጠር
በሁሉም መስክ ጥረት አድርጓል ።አበራታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከለጋሽ እጅ ስንዴ የመጠበቅ ታሪካችን አብቅቶ በበጋ ስንዴ ራስን ከመቻል ያለፈ አዲስ ታሪክ ጽፈናል።
በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የራሳችንን ክብረ ወሰን ደጋግመን አሻሽለናል፤ በአካባቢ ጥበቃም ለዓለም አቀፍ ትብብር አርአያ ሆነናል። ይህ ስኬት በሌላ ሀገር የተፈጸመ ቢሆን ምንኛ በተነገረ ነበር፤ ዳሩ ግን እኛ ድልን ደጋግመን ያጣጣምን የጀግኖች አባቶቻችን ልጆች ነን። ፈጽመነዋል።
ርዕያችን ሩቅ ነው ፣ መንገዳችን መደመር ነው፣ ስንደመር አትርፈናል ፤ ስንሰባሰብ ጠንክረናል። በሌሎች ሀገራት የጸብ መንስኤ፣ የሀገር ዕዳ የሆኑትን ማዕድናት እኛ የሀገር ምንዳ ፣ የሀገር ተስፋ አድርገናል፤ በታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶቻችን ቀጣናውን አስተሳስረናል፤ የከተሞቻችን ገጽታ በዘመናዊ የኮሪደር ልማት ተለውጧል። የኮንፈረንስ ቱሪዝም ተስፋፍቷል ፤ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ገንበተናል።
ነባር ቅርሶቻችንንም አቧራቸውን አራግፈን ወደ ነገ አሻግርናል።
ትውልድን አስበን የዲጂታል 2030 ስትራቴጂን ተግባራዊ እያደረግን ነው። የመንግሥት አሠራርንም ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ መሠረት ተጥሏል ። ከሁሉም በላይ ሀገራችንን ከሚሽኮረመም የውጭ ፖሊሲ አላቀን ለብሔራዊ ጥቅማችን በጽናት ቆመናል ፤ በአለም መድረክ የሚገባንን ጠይቀናል።
የምንገነባው ሀገረ-መንግሥት የመደመር እሳቤ ላይ የተመሠረተ ነው ፣ ትኩረቱም በጽኑ ተቋማት ግንባታ ላይ ነው። የፍትሕ፣ የፀጥታ እና የዴሞክራሲ ተቋሞቻችን ጠንካራ መሠረት ይዘዋል። ወገባችንን አጥብቀን ዝቅ ብለን በሠራነው ሥራ ቀና ብለን መሄድ ጀምረናል፣ ዛሬ ላይ ሀገር የሚሸከሙ፣ መጪውን ጊዜ የተለሙ እና ከሥርዓት መቀያየር የተሻገሩ ተቋማዊ አቅሞች ተፈጥረዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት፣ የለውጡ መንግሥት ልዩ የሚያርገውን መገለጫን አስተዋውቋል፤ ፕሮጀክቶችን ይጀምራል፣ አጠናቆም ይመርቃል። ይህ በሕዝባችን አንደበት ተደጋግሞ የሚነገር እውነትኛ ምስክርነት ነው። የተዘጉ ኢንዱስትሪዎች ተከፍተዋል፤ ለዘመናት የኪሳራ ምሳሌ የሆኑ ተቋማት ወደ ትርፋማነት ተሸጋግረዋል ፤ በኢንቨስትመንት ፣በኤክስፖርት እና በተኪ ምርት እመርታዊ ለውጥ አሳክተናል።
ከዚህም በላይ ታላቁን የህዳሴ ግድባችንን ባጠናቀቅንበት ማግስት በጉባ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ እና የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል የሚወስኑ አዳዲስ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለሕዝባችን አብሰረነዋል።
የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ የኒውክሌር ማዕከል ለመገንባት አዲስ ውል ታስሮ ሥራ ተጀምሯል ፤ በሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ ጸጋዎችን ገልጠናል። የተፈጥሮ ጋዝ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች ቀን ከሌት እየተሰራ ይገኛል ። በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግደው የቢሾፍቱ ኤርፖርት የአፍሪካ አቪዬሽን ዘውድ ደፍቶልን በሰማዩ ያነግሰናል።
በዓመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያድነው የማዳበሪያ ፋብሪካም የግብርና ምርታማነትን በማረጋገጥ ለገበሬዎቻችን እፎይታ ይሆናል ፤ ተስፋችን ብዙ ነው። የብዙዎችን ህይወት የሚቀይረው የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ልማት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ሥራው ተጀምሯል። እናሳካዋለን ! ተናግሮ ማድረግ ፣ ቃል ገብቶ መፈጸም በመደመር መንግሥት ለትውልድ የተጣሉ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው።

26 days ago
ታሪካችንን በራሳችን ብዕር፡ የኢትዮጵያ የድልና የተስፋ አዲስ ዓመት
(የዕለቱ መልዕክት)
*******************
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ተፈጥሮ ራሷን የምታድስበት፣ የደፈረሱ ወንዞች የሚጠሩበት፣ ምድሪቱ በአደይ አበባ የምታጌጥበትና የመስቀል ወፎች ብቅ የሚሉበት ልዩ ወቅት ነው።
ይህ የተፈጥሮ ዑደት ለሀገራችን የብሩህ ተስፋና የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።
አዲሱ ዓመት ከምንጊዜውም በተለየ ሁኔታ ፈተናችንን ከኋላ ትተን፣ ተስፋችንን ከፊት በማስቀደም ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና የምናዞርበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
እየተከናወኑ ያሉ ሰፋፊ የልማት ሥራዎች በተለይም የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ የተጀመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ሀገራዊ ራዕይን እውን የማድረግ ማሳያዎች ናቸው።
"የምንሠራው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገ እና ለቀጣዩ ትውልድ ነው በሚል መርህ፣ ለትውልድ የሚሻገር ዘላቂ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ብልጽግናዋንና ድሎቿን ለመጻፍ ስትነሳ መጻፊያ ብዕሯ ዜጎቿ ሲሆኑ፣ ቀለሙም ከእያንዳንዱ የላብና የትጋት ውጤት የሚቀዳ ነው።
ኢትዮጵያ ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር ታሪክ ከሚያነሣቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ የሚያስችል በቂ አቅምም ሆነ ጽኑ አቋም አላት፤ ለዘመናት ያቆየችው የነጻነት ታሪክም የዚሁ ማሳያ ነው።
አዲሱ ዓመት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ይበልጥ የሚጸናበትና ዴሞክራሲያዊ ዕሴቶቻችን ሥር ሰደው የሚጎለብቱበት እንዲሆን እያንዳንዳችን የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል።
በሀገር ፍቅር የታነጸ፣ አካባቢያዊ ማንነቱን ከሀገራዊ ማንነቱ ጋር አዋሕዶ የያዘ፣ ለፈጠራ የተጋለጠና ያልተሄደበትን መንገድ ለመጓዝ ድፍረት ያለው ትውልድ መፍጠር የዘመኑ ግዴታ ነው።
አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን ይዞ የሚመጣው፣ እኛ ራሳችንን ለለውጥ ባዘጋጀንበት ልክ ብቻ ነው።
በሀገር ጉዳይ ላይ ጣት ከመጠቆም ይልቅ፣ “ከእኔ ምን ይጠበቃል?” የሚለውን ጥያቄ በማስቀደም ለጋራ ራዕይ መትጋት ይኖርብናል።
የሚጎዱንን አሮጌ አስተሳሰቦች ወደ ጎን ትተን፣ ጠቃሚ በሆኑ አዳዲስ ዕሴቶች መተካት የመጻኢው ጉዟችን መሠረት ነው።
ጊዜው ለሁሉም ባዶ ሆኖ የቀረበ አዲስ የዘመን መጽሐፍ ገልጦልናል። የዚህ መጽሐፍ ዋና ጸሐፊዎች እኛው ራሳችን ነን። እኛ ዝም ብንል ሌሎች በፈለጉት መንገድ ሊጽፉት እንደሚችሉ መገንዘብ ያሻል።
ይሁንና የራሳችንን የዘመን አቆጣጠር የፈጠርን ሕዝቦች፣ የራሳችንን ዕጣ ፈንታ በገዛ እጃችን ከመጻፍ የሚያግደን ምንም ዓይነት ኃይል የለም።
እኛው አቅደን፣ እኛው ሠርተን፣ ችግሮቻችንን በውይይትና በምክክር ፈትተን የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን የመወሰን ባህል መለማመድ ጀምረናል፤ አቅሙም እንዳለን አሳይተናል።
ዘመኑ የኢትዮጵያውያንና የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ነው። ዜጎች ልዩነታቸውን ጠብቀው በጋራ ጉዳዮች ላይ በአንድነት ሲቆሙና እርስ በርስ ሲደጋገፉ፣ የሀገራችን የብልጽግና ብዕር የላቀ አሸናፊነትን፣ ታላቅነትንና አንጸባራቂ ድልን አድምቆ ይጽፋል።

27 days ago
አዲስ ዓመት፤ አዲስ ተስፋና የተግባር ዘመን
************
(የዕለቱ መልዕክት)
ዘመን ፈጣሪ ለሰው ልጆች የሰጠውና የራሳችንን ታሪክ እንድንጽፍበት የተቸረን ባዶ ማስታወሻ ነው። በዚህ ማስታወሻ ላይ የዕድገትን፣ የሥልጣኔንና የፈጠራን ብሩህ ገጾች መጻፍ እንደሚቻለው ሁሉ፤ የጥፋትን፣ የጦርነትንና የኋላቀርነትን ታሪክም ማሰፈር ይቻላል።
እኛ ኢትዮጵያውያን በረጅም ታሪካችን በዘመን መጽሐፋችን ላይ ዓለምን ያስደነቁ የሥነ-ሕንፃ፣ የንግድ፣ የጥበብና የነፃነት ታሪኮችን ጽፈናል።
በሌላ በኩል ደግሞ የእርስ በርስ ግጭት፣ የረሃብ፣ የመለያየትና የውድቀት መራራ ገጾችንም አኑረናል። ይሁን እንጂ ከትናንት ስሕተታችን ተምረን ዛሬን በብሩህ ተስፋ ለመቅረጽ የቆረጥንበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።
የተሰናበትነው 2018 ዓ.ም የዚህ አዲስ ንቅናቄ ማሳያ ሲሆን የተቀበልነው አዲሱ የ2019 ዓ.ም ደግሞ የጀመርናቸውን ዐበይት ሀገራዊ ራእዮች ይበልጥ አጽንተን የምናሰፋበት የብልጽግና ዘመን እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር) ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት መልዕክት ያለቸዉን እምነት ገልጸዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ከፍታ የሚያሸጋግሩ በርካታ ታላላቅ ተግባራት እውን ማድረግ ተችሏል። በአረንጓዴ አሻራን የተፈጥሮ ሚዛንን ከመጠበቅ ጀምሮ በቱሪዝም የገበታ ፕሮጀክቶች፣ በበጋ ስንዴና በሌማት ትሩፋት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው። በተጨማሪም 'ኢትዮጵያ ታምርት' በሚል ንቅናቄ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ እየተነቃቃ ይገኛል።
የሕዳሴው ግድብ ለፍጻሜ ማብቃቱ፣ የኮሪደር ልማቱ የከተሞቻችንን ውበትና ጤናማነት መቀየሩ እንዲሁም ሰፊው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል 2030 ስኬቶቻችን፤ አዲሱ ዓመት ይበልጥ ፍሬያማ እንደሚሆን የሚያበስሩ ማሳያዎች ናቸው።
ከሁሉ በላይ ግን ይህንን አዲስ ዓመት ልዩ የሚያደርገው የዘመናት የፖለቲካ ስብራታችንን ለመጠገን የሚያስችለውን ታሪካዊ ሀገራዊ ምክክር በስኬት ማጠናቀቃችን ነው።
ይህ የምክክር መድረክ "ኢትዮጵያውያን ሊግባቡ አይችሉም፤ ሐሳብ ለሐሳብ መሸማገል አይችሉም" የሚለውን ሟርት ያከሸፈ ነው። ከልሂቃን የሥልጣን ክፍፍልና "እኛ እናውቅልሃለን" ባይነት ወጥተን፤ ሕዝብ ራሱ ለችግሮቹ መፍትሔ የሚያመነጭበትን አዲስ የዴሞክራሲ ባህል ተፈጥሯል።
በምክክሩ የተደረሰባቸው ስምምነቶች የነገይቱን ኢትዮጵያ ጽኑ መሠረት የጣሉ ሲሆን የዚህ ሀገራዊ መግባባት የመጀመሪያ ፍሬም በአዲስ ዓመት ዋዜማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መደረጉ ነው።
ይህ እርምጃ መንግሥት ለሰላምና ለዕርቅ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ የጉልበትና የመሣሪያ ፖለቲካ አብቅቶ የብዕር፣ የሐሳብና የውይይት ዘመን መጀመሩን ያረጋግጣል። ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ላይ አሮጌው የጦርነትና የመጠላለፍ ታሪክ ዳግም ሊጻፍ አይገባም።
በመሆኑም አዲሱ የ2019 ዓ.ም የዴሞክራሲ ባህላችን የበለጠ የሚጎለብትበት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የጀመረችሁ ጥረት ፍሬ የሚያፈራበትና በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተሻለ ውጤት የምታስመዘግብበት የዕመርታ ዘመን ይሆናል። ይህ ታላቅ ራእይ እውን ሊሆን የሚችለው ግን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አምራቹ ዘርፍ፣ ሲቪል ሰርቪሱ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም መላው ሕዝብ በብሔራዊ ጥቅማችን ዙሪያ በአንድነት ሲቆሙ ብቻ ነው።
ልዩነቶቻችንን በውይይት እየፈታን፣ አንድነታችንን እያጸናን፣ አዲሱን ዓመት በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ሥልጣኔ የምንጽፍበት የሰላምና የብልጽግና ዘመን እናድርገው!

Sponsored by
Surafel
30 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ድሮ ድሮ ገበያ ሲቀዘቅዝ... ነጋዴው ሸቀጡን እያወደሰ አላፊ አግዳሚውን መለማመጥ ይጀምር ነበር። ዛሬ ግን በዲጂታሉ መንደር የትኩረት ገበያ ሲቀዘቅዝ፣ ነጋዴው ሸቀጡን ሳይሆን የደንበኛውን ዘር እና ጎሳ ማውደስ ይጀምራል።
ወዳጃችንን ታውቁታላችሁ። ቲክቶክ መንደር ገና ሲቀላቀል፣ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ የማያደርገው የሰርከስ ትርኢት አልነበረም። አንዴ ፊቱን ዱቄት ተለቅልቆ ብቅ ይላል፣ ሌላ ጊዜ አፉን እያሞጠሞጠ የህንድ ዘፈን ከንፈር ያላውሳል። ተመልካችም በሳቅ ጦዞ ላይክ እና ሼር ያንበሸብሸው ነበር። ነገር ግን የሰው ልጅ የትኩረት ዕድሜ አጭር ናትና፣ የወዳጃችን የፈጠራ ጓዳ ሲመተር፣ ቪው እንደ በጋ ምንጭ ድርቅ አለ። አልጎሪዝሙም ፊቱን አዞረበት።
በዚህ ጭንቅ ጊዜ ነው እንግዲህ ወዳጃችን አንድ ትልቅ የንግድ ሚስጥር ያገኘው። በአገራችን የፖለቲካ ገበያ የማይነጥፍ፣ ፈጠራ የማይጠይቅ እና ድካም የሌለበት አንድ ሸቀጥ አለ፤ እርሱም የብሔር ሽቀላ ነው። ጭንቅላትህ አዳዲስ ሀሳቦችን ማመንጨት ሲያቆም፣ ቀጥታ ወደ ታሪክ ማህደር ገብተህ የቅድመ አያቶችን አጥንት መቆፈር ትጀምራለህ።
ትናንት በቦብ ማርሌይ ቲሸርት እና በተቀዳደደ ሱሪ የዳንስ ቻሌንጅ ሲለማመድ የነበረው ወዳጃችን፣ ዛሬ ጠዋት ብቅ ሲል ጋቢ ለብሷል። ከጀርባው የጥንት ጦር መሣሪያ እና የጀግና ፎቶ ለጥፏል። ድምጹን አጎንኖ፣ ፊቱን አስቆጥቶ፣ “የብሔራችን መብት፣ ታሪካችን፣ ክብራችን!” እያለ እንደ አዲስ ኪዳን ነብይ ይለፍፋል። ትላንትና “እንዴት ናችሁ ጋይስ” ይል የነበረው አንደበት፣ ዛሬ “እኛ እና እነሱ” ወደሚል የጦርነት አዋጅ ተሸጋግሯል። የብሔሩ ጠበቃ ሆኖ ራሱን ሾመ።
የሚገርመው ነገር እርሱ ስለ ብሔሩ ታሪክ የሚያውቀው ከፌስቡክ መንደር በስህተት የተጻፉ አጫጭር የጥላቻ ጽሁፎችን ብቻ ነው። ለብሔሩ የሚጠቅም አንድ ችግኝ ተክሎ አያውቅም፣ አንድ የታመመ አረጋዊ ጠይቆ አያውቅም። ነገር ግን በቲክቶክ ላይቭ ገብቶ "ለብሔራችን ክብር ጊፍት ላኩ፣ አንበሳ ላኩ!" እያለ ይማጸናል። የአያቶቹን ደምና አጥንት በዲጂታል ጽጌረዳ ይመነዝረዋል።
እውነት ግን ብሔር እና ባህል በቲክቶክ ላይቭ በሚለገስ 'አንበሳ' እና 'የበረዶ ግግር' የሚታደግ ቢሆን ኖሮ፣ ኢትዮጵያችን የዓለም ኃያል በሆነች ነበር። እውነተኛ ማንነትን መውደድ ማለት ግን፣ ማሰብ፣ መስራት፣ መፍጠር እና ማሳደግ እንጂ፣ የራስህ ፈጠራ ሲያልቅብህ ማካካሻ የምታደርገው የኪሳራ ንግድ አይደለም። ለወዳጃችን ግን ይህ አይገባውም፤ ምክንያቱም ለእሱ ብሔር ማለት ትራፊክ ማምጫ ሞተር ብቻ ነውና።
ይህ ዓይነቱ አርበኛ የጥይት ድምጽ ሲሰማ ሎግ-አውት አድርጎ የሚጠፋ፣ ጦርነቱ ደግሞ በኮመንት መስጫ ሳጥን ብቻ የሚካሄድ ይመስለዋል። ፈጣሪ የፈጠራ ድርቅን ያርቅልን እንጂ፣ አእምሮ ሲከስር መሸሸጊያው ብዙ ነው።
ቶሎሳ ከአሶሳ

1 month ago
ይህ ኤርትራዊቷ ስኒት ሀብተአብ የለበሰችው ቀሚስ በትግርኛ፣ በአረብኛ እና በእንግሊዝኛ የተጻፉ ታሪኮችን በያዘ የጋዜጣ-ህትመት ጨርቅ የተሰራ ነው። ሚስ ወርልድ እንዳስታወቀው፣ በጨርቁ ላይ የታተመው ጽሑፍ ልዩ የሆነ ትዕይንታዊ ትረካን የሚፈጥር ሲሆን፣ ወደ ታች የሚንጠለጠለው የትከሻ ካባ ደግሞ ገና ወደፊት የሚጻፉ ታሪኮችን ይወክላል። ዲዛይኑ የኤርትራን ትውፊት፣ ባህላዊ ማንነት እና ራስን መግለጽ የሚያንጸባርቅ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ በሚስ ኤርትራ የመጀመሪያ የውበት ውድድር ድል ላይ ያተኮረ ታሪክ እና ፎቶግራፍ በውስጡ ተካቶበታል። ይህም ለወጣት ኤርትራውያን፤ ፋሽንን ጨምሮ ማንኛውም የጥበብ ዘርፍ የራሱ ዓላማ ሊኖረው፣ የመጣንበትን ታሪክ ሊያከብር፣ እንዲሁም የፈጠራ ስራችን፣ ህልማችን እና ታሪካችን ለዓለም እንዲደርስ ምቹ መድረክ ሊፈጥር እንደሚችል የሚያስታውስ መልእክት ነው። ይህንን ቀሚስ ዲዛይን ያደረገው አሊ መሐመድ ነው።
📷ሪካርዶ ሲቪየሮ

የ፴፻ ዓመታት ታሪክን ከፍልሰት እንታደግ!
“ዓይኖች ሁሉ ወደ ጣና ቂርቆስ ይሆናሉ!”
ለሦስት ሺህ ዓመታት ያህል የአባቶቻችንን እምነት፣ ታሪክና ቅርስ ጠብቆ ለትውልድ ያስተላለፈው ጥንታዊው ጣና ቂርቆስ ገዳም አሁን በገጠመው ችግር ምክንያት የሁላችንንም አስቸኳይ ድጋፍ ይሻል።
ይህን ታሪካዊ ቅርስና ቅዱስ ስፍራ ለመታደግ እንረባረብ!
በተዘጋጀው የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፍ፣ የበኩልዎን አሻራ ያኑሩ።
የቀጥታ ስርጭቱ በፈውስ መንፈሳዊ እና በሌሎች ሚዲያዎች ይተላለፋል።
ገዳሙን ለመርዳት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000016689843 (1527)
አሐዱ ባንክ
0085165811801 (1521)
አቢሲኒያ ባንክ
260616412 (1505)
ዳሸን ባንክ
5442102261011 (2115)
አባይ ባንክ
4491113090983013 (1521)
ታሪክ የሚኖረው በትውልድ እጅ ነው። ዛሬ የምናደርገው ድጋፍ የነገውን ቅርስ ይታደጋል!
ጣና ቂርቆስን እንታደግ!
ታሪካችንን እንጠብቅ!
ቅርሳችንን ለትውልድ እናስቀምጥ!
#ጣናቂርቆስ #ቅርሳችን #ታሪካችን #ኢትዮጵያ #የቅርስጥበቃ #ትውልድ

ኃያላኑን ከኢትዮጵያ ጎን ያሰለፉት የለውጥ ፍሬዎች
*************
ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም የጀመረችው የለውጥ ጉዞ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መዋቅሮቻችንን በስር ነቀል ሁኔታ ያሻገረ ታሪካዊ ክስተት ነው።
በለውጡ መባቻ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች መጋጨት ፈጥሮት የነበረው ውዥንብር፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች በጥርጣሬ ፊታቸውን እንዲያዞሩብን አድርጎ ነበር።
ይሁን እንጂ የተጋረጡትን ውስብስብ ፈተናዎች በጽናት በማለፍ እና ማዕከላዊ መስመሯን በመጠበቅ ሀገራችን ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበችው ሁለንተናዊ ዕድገት እነዚህን አጋሮች ወደ ትብብር መድረክ በድጋሚ መመለስ ችሏል።
በተለይም ከአሜሪካ እና ከሌሎች ምዕራባውያን አጋሮች ጋር የታደሰው ስትራቴጂያዊ ትብብር የዚሁ የጸና የዲፕሎማሲ እና የለውጥ ጉዞ አንዱ ማሳያ ነው።
ይህ የአጋርነት መታደስ በተጨባጭ በተተገበሩ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች የተገኘ ውጤት ነው።
ሐምሌ 2016 ዓ.ም የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉን ተከትሎ፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የነበራቸውን ስጋት አንስተው ወደ ሙሉ አጋርነት ተመልሰዋል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያጸደቀው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር እና የዓለም ባንክ የ10.7 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ የዚሁ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ፍሬዎች ናቸው።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ የብሪክስ (BRICS) አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተፈላጊነት፣ ሰፊ የገበያ ተደራሽነት እና ጂኦፖለቲካዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት በግልጽ ያረጋገጠ ታላቅ የዲፕሎማሲ ድል ነው።
ከዚህ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድል ባሻገር፣ ኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመኗን የሚያደምቁ እና ብሩህ ተስፋን ሰንቀው የተጠናቀቁ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በተግባር አሳይታለች።
ከእነዚህም ግንባር ቀደሙ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተደረገው የግብርና ትራንስፎርሜሽን ነው። በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አማካኝነት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የስንዴ ምርትን ከውጭ መግዛት ከማቆም አልፈን ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምረናል።
ለዚህም ታሪካዊ ስኬት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ጥር 2016 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁን የአግሪኮላ ሜዳሊያ አበርክቷል።
በሌላ በኩል በአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁ እና በከፍተኛ አቅም ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የብልጽግናችን አንዱ እና ዋነኛው ምሰሶ ሆኖ ቀጥሏል።
በከተማ ልማት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎችም አስደናቂ ለውጦች ተመዝግበዋል።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልል ከተሞች የተተገበረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የእግር መንገዶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን እና የዘመናዊ ከተማ መሠረተ ልማቶችን በጥበብ በማቀናጀት የከተማ መሬት አጠቃቀምን ሙሉ ለሙሉ አዘምኗል።
በተመሳሳይ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋናችንን ወደ 23.6 በመቶ ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ አበርክቶው ከፍተኛ ዕውቅና አስገኝቷል።
በዲጂታል ዘርፍ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ ጠንካራ መሠረት በመጣል ለ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ዕቅድ መድረኩን አመቻችቷል።
የበርካታ ሚሊዮን ዜጎችን የዕለት ተለት እንቅስቃሴ እያዘመነ የሚገኘው የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ እንዲሁም የቴሌብር፣ የ5ጂ አገልግሎት እና የኢ-ኮመርስ ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችንን በከፍተኛ ደረጃ እያፋጠኑት ይገኛሉ።
ከተወሳሰቡ ፖለቲካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ወጥተን በማዕከላዊው የመደመር መስመር ላይ በመቆም ታሪካችንን በድል አድራጊነት እየጻፍን እንገኛለን።
እውን የሆኑት እጅግ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጋር ዳግም የተገነባው ስትራቴጂያዊ አጋርነት ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የማትበገር እና በዘላቂ ብልጽግና ጎዳና ላይ የምትገኝ መሆኗን በተጨባጭ ያረጋግጣሉ።
በቀጣይም ይህ የጸና የለውጥ ጉዞ ለዜጎቻችን የላቀ የኑሮ ደረጃን የሚያረጋግጥ፣ እንዲሁም ለቀጣናው የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ትስስር ማዕከልነታችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ይሆናል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #economicreform #digitalethiopia #greenlegacy #gerd #brics #ebc

ከተዋስዖ መር እስከ ላቀ መግባባት፡ አዲሱ የሀገር ግንባታ መንገድ በኢትዮጵያ
*****************
ተዋስዖ መር ዴሞክራሲ በዘመናዊው የፖለቲካ ሳይንስ ዓለም ውስጥ በስፋት መታወቅ የጀመረው በ1980ዎቹ አካባቢ ቢሆንም፣ የፅንሰ ሐሳቡ ስረ መሠረት ግን ከጥንቷ ግሪክ የፖለቲካ ልምምድ የሚነሳ ነው።
በጥንቷ አቴንስ ዜጎች በአደባባይ ተሰብስበው ጉዳዮችን በምክንያት እና በውይይት ይወስኑ ከነበረው ልምምድ ይመነጫል። ነገር ግን ፅንሰ ሐሳቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነትን ያገኘው እና ጀርመናዊው ዩርገን ሀበርማስ እና አሜሪካዊው ጆን ሮልስ ባዳበሩት "የፐብሊክ ሪዝን ፅንሰ ሐሳቦች አማካኝነት በስፋት ታውቋል።
ተዋስዖ መር ዴሞክራሲ የድምፅ ብልጫን መሠረት በማድረግ ውሳኔ ከማሳለፍ ባለፈ፣ በጥልቅ የሐሳብ ልውውጥ፣ በመደማመጥ እና የጋራ መግባባትን በመፍጠር ላይ ሲቆም እውነተኛ የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትን ያረጋግጣል። በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ "ተዋስዖ መር ዴሞክራሲ" እና ከ"መደመር" እሳቤ ጋር በጥብቅ ተቆራኝቶ የሚነሳው ለዚሁ ነው።
ተዋስዖ መር ዴሞክራሲ፣ የሐሳብ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በማምጣት፣ ያልተደመጡ ድምፆችን በማካተት እና የልሂቃንን ተቃርኖ ከማስፋት ይልቅ ወደ የጋራ ማዕከል በማምጣት ላይ ያተኩራል። አሸናፊ እና ተሸናፊ ከሚፈጥረው የአንዱ አገኘ ሌላው ሲያጣ ዕሳቤ በመውጣት፣ በጋራ አሸናፊ ወደምንሆንበት አዎንታዊ የሰላም ግንባታ የሚያሸጋግር ቁልፍ መሣሪያ ነው።
የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ስንመለከት፣ ኢትዮጵያ እጅግ ሰፊ የባህል፣ የቋንቋ እና የማንነት ብዝኃነት ያላት ሀገር ናት። ይህን ብዝኃነት በአብላጫ (Majoritarian) የዴሞክራሲ ሥርዓት እና በውህደት (Integrationist) አቀራረብ ብቻ ለማስተዳደር መሞከር፣ ብዙ የሕብረተሰብ ፍላጎቶችን ከማፈኑም ባለፈ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ማህበረሰቦችን ፍላጎት በመደፍጠጥ፣ ላለፉት አስርት ዓመታት ፖለቲካዊ መገለልን፣ የልሂቃን ጽንፈኝነትን እና ማለቂያ የሌላቸውን ግጭቶችን ሲወልድ ቆይቷል።
የመደመር እሳቤ ይህንን የፖለቲካ ስብራት በጥልቀት በመገንዘብ፣ በብቸኝነት ጉድለት ውስጥ ከምትዳክር ሀገር በመውጣት፣ ችግሮቻችንን ከራሳችን ባህላዊ ዕሴቶቻችን በመነሳት እንድንፈታ አቅጣጫ ያስቀምጣል።
የኢትዮጵያውያን የቆየ የመተሳሰብ፣ የመቻቻል፣ የሽምግልና፣ የይቅርታ እና የእርቅ ባህሎች ለመግባባት ዴሞክራሲ ጠንካራ መደላድሎች እና ማኅበራዊ ካፒታሎች ናቸው። ተዋስዖ መር ዴሞክራሲ እነዚህን ዕሴቶች ተቋማዊ በማድረግ፣ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ እውነተኛ ባለቤት የሚሆኑበትን ሰፊ ምህዳር ይከፍታል።
አሁን ባለንበት ወቅት ይህ ተዋስዖ መር የዴሞክራሲ ግንባታ ከንድፈ ሐሳብ አልፎ ወደ ተግባር ሲቀየር በጉልህ እያየነው ነው። በተለይም በቅርቡ በታላቅ ስኬት የተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፣ የዚህ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ማሳያና የዘመኑ ትልቁ የፖለቲካ ትሩፋት ነው።
በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተለያየ የፖለቲካ አቋም፣ የተለያዩ ትርክቶች እና የተራራቁ ፍላጎቶች ያላቸው አካላት በአንድ መድረክ ተሰባስበው፣ በውይይትና በድርድር ሀገራዊ ስምምነት ላይ መድረስ መቻላቸው የተዋስዖ መር ዴሞክራሲ አንጸባራቂ ስኬት ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በስኬት መቋጨት፣ መግባባት የተደበቀ አቅማችንን አውጥቶ አንድነታችንን ያጠነከረበት እንዲሁም ዜጎች በጠብመንጃ ሳይሆን በሐሳብ ልዕልና እና በምክንያታዊነት የተወያዩበት ታሪካዊ ክስተት ነው።
በእንዲህ ዓይነት መድረኮች የሚካሄዱ ተዋስዖ መር ድርድሮች ለመፍትሔና ለአቋም ከመሮጥ በፊት፣ ግንኙነቶችን በማስተካከል እና ታፍነው የቆዩ ሐሳቦችን ወደ አደባባይ በማውጣት ጠንካራ ማኅበራዊ መሰረት ይጥላሉ።
በመጨረሻም፣ ተዋስዖ መር ዴሞክራሲ የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን፣ ቀጣይነት ያለው የፖለቲካ ባህል ነው። ከሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ስኬታማ መቋጨት በኋላ የሚኖረን የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉዞ፣ በተገኙት ዘላቂ ስምምነቶች ላይ ተመስርቶ ፍትሐዊ፣ አካታች እና ተጠያቂነት ያለው ተቋማዊ ሥርዓት መገንባትን አጥብቆ ይጠይቃል።
ኢትዮጵያ በውስጧ ያሉትን ልዩነቶችና ብዝኃነቶች እንደ ጸጋ በመቀበል፣ በመደመር ዕሳቤ የተቃኘ የመግባባት ዴሞክራሲን እውን ማድረግ የምትችለው የጀመረችውን የንግግር፣ የድርድርና የተዋስዖ ባህል ማጽናት ስትችል ነው።
የምክክሩ ስኬትና የዘመኑ ትሩፋት የሰጠን ብሩህ ተስፋ፣ ጠንካራና የሲቪክ ባህል የዳበረባትን ኢትዮጵያን በጋራ አቅም መገንባት እንደምንችል ነው። በመሆኑም፣ በምክንያታዊነት እና በመግባባት ላይ የቆመው ይህ ሥርዓት ኢትዮጵያን ከባለፉት የታሪክ ስብራቶች በማላቀቅ፣ ወደ ላቀ የሥልጣኔ፣ የትብብርና ብልጽግና ከፍታ የሚያሸጋግራት አስተማማኝ የጋራ ድልድያችን ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #nationbuilding #nationaldialogue #nationalconsensus

በጠላቶች ትብብር የማይገታው የኢትዮጵያ ጽናት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታሪኳ በርካታ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን፣ የታሪካዊ ጠላቶቿን ጥምረትና የተደራጁ ሴራዎችን በጽናት በማሸነፍ ነጻነቷን አስከብራ የኖረች ሀገር ናት።
ትናንት አባቶቻችን በዓድዋ ድል የተባበረውን የቅኝ ግዛት ኃይል በጽናትና በአንድነት እንዳሸነፉት ሁሉ፣ ዛሬም እኛ የዚህ ትውልድ ልጆች ያንን ድል በዘመናዊ መልክ እየደገምነው እንገኛለን።
በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲና የደኅንነት ጫናዎች ሲያርፉባትም፣ የሕዝቡ የጋራ ማንነትና አገራዊ ፍቅር ፈተናዎቹን ወደ ዕድል የመቀየር አቅም ሆኖ አገልግሏል።
ለዚህም ማሳያ ከሆነው ሁነት ውስጥ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ለመግባትና ሉዓላዊነታችንን ለመገዳደር የተነሱ ኃይሎችን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዙሪያ የሚገኘው ዳያስፖራ ማህበረሰብ በአንድ ድምፅ “ኖሞር” (No More) በማለት የውጭ ሴራዎችን አክሽፏል፤ የኢትዮጵያ ጽናት ጊዜያዊ ሳይሆን ጥንታዊና መዋቅራዊ መሠረት ያለው መሆኑንም አሳይቷል።
በቅርብ ጊዜያት የኢትዮጵያ ጽናት በከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊና የውስጥ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈበትና ጥንካሬዋ የተመሰከረበት ወቅት ነው። የውጭ ታሪካዊ ጠላቶችና የጥቅም ተጻራሪዎች የሀገሪቱን ጉዞ ለማደናቀፍ በተቀናጀና በተባበረ መልኩ የሰነዘሯቸው ተጽዕኖዎች በሕዝቡና በመንግሥት ጽናት መክነዋል።
እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች፣ የተለያዩ የውጭ ተፅዕኖዎችና የጠላቶች ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ቢኖርባቸውም፣ በሕዝቡ ጽናትና የገንዘብ ድጋፍ እውን መሆን ችለዋል። የ”አጎዋ”(AGOA) ዕድልን በመሰረዝና በመጫን ሀገራዊ ውሳኔዎችን ለመጠምዘዝ ቢሞከርም፣ ኢትዮጵያ እነዚህን ጫናዎች ተቋቁማ በራሷ አቅም መደበኛ ሥራዎቿንና ግዙፍ የኮሪደር ልማቶቿን ሳታቋርጥ አስቀጥላለች።
ኢትዮጵያ የምትገኝበት ቀጣና ለዓለም አቀፍ ንግድና ደኅንነት ወሳኝ በመሆኑ፣ የተለያዩ ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች በጋራም ሆነ በተናጠል ተፅዕኖ ለማሳደር ይሞክራሉ።
ነገር ግን የኢትዮጵያ የመንግሥት መዋቅር፣ ጠንካራ ማኅበራዊ እሴቶች እና ለነፃነት የሚሰጠው የላቀ ክብር ሀገሪቱ በማንኛውም ዓይነት የጠላቶች ትብብር እንዳትገታ ያደረጓት ዋና ምስሶዎች ናቸው።
ይህ የኢትዮጵያ የአይበገሬነት ታሪክ ለወደፊት ትውልድም ትልቅ ትምህርትና የጥንካሬ ምንጭ ሆኖ የሚቀጥል ነው።
ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት ሳታጥፍ፣ የሕዝቦቿን የህልውና ጥያቄ ለመመለስ የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በጽናትና በማይናወጥ አቋም እየገፋችበት ትገኛለች።
የቅርብ ጊዜ ታሪካችን የሚያሳየው የኢትዮጵያ ጠላቶች ስልታቸውን ቀይረው በዲጂታል ሚዲያ፣ በዲፕሎማሲና በኢኮኖሚ ማዕቀብ ተባብረው ቢመጡም፤ የሀገሪቱ የቆየ የመንግሥትነት መዋቅርና የሕዝቡ የነፃነት አርበኝነት ጽናት ዛሬም የማይበገር ጋሻ ሆኖ መቀጠሉን ነው።
በትዕግስት ግዛቸው

በቴክኖሎጂ እና በእውቀት የሚጻፍ አዲስ ታሪክ፡ የባሕር በር አጀንዳችን እና የዲጂታሉ ትውልድ አሸናፊነት
***********************
ለዘመናት ሀገራዊ ፈተናዎችን የመጋፈጥ እና የመሸጋገር ታሪካችንን ስንቃኝ፣ ትውልዶች ነፃነትን ለማስጠበቅ በጽናት ተዋግተዋል፤ አባቶቻችንም የተበታተነውን ለመገንባት ሌት ተቀን ጥረዋል።
በዚህ ዘመን ግን የሀገሩን ነገ በመቀየር ሂደት ውስጥ የተሰለፈው አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ የተቃኘ አዲስ የትግል ምዕራፍ ከፍቷል።
በአሁኑ ወቅት የሀገራት ድንበር በጦርነትና በኃያላን ጣልቃ ገብነት ሲታመስ፣ የዓለም ፍላጎትና ውድድር በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚ እና በፈጠራ በሚገነቡ አዳዲስ መስኮች ላይ ያተኮረ ሆኗል።
የዛሬው ወጣት በኮድ የሚገነባ፣ በፈጠራ የሚያስብ እና በቴክኖሎጂ መፍትሔ የሚፈልግ ሲሆን፣ የባሕር በር ጉዳይም ከምኞትና ከቁጭት ባለፈ በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በልማት፣ በዲፕሎማሲ፣ በእውቀት እና በቴክኖሎጂ በተገነባ አቅም የሚረጋገጥ መሆኑን በጥበብ ተረድቷል።
በየትኛውም መንገድ የውስጥም ሆነ የውጭ ጫናዎች ቢበዙብን፣ የቱንም ያህል ፈተናዎች ቢደቀኑብን ዓይናችን ከባሕር በር አጀንዳችን ፈጽሞ አይነቀልም፤ ይህ ትውልድም የታሪክ እና የጂኦግራፊ ስብራታችንን በጽናት ያሳካዋል።
አንድ መሐንዲስ የወደብ ቴክኖሎጂን ሲያጠና፣ አንድ ተመራማሪ የባሕር ኢኮኖሚን ሲመረምር ወይም አንድ የቴክኖሎጂ ባለሙያ የዘመናዊ ሎጂስቲክስ መፍትሔ ሲያመጣ እየተገነባ ያለው ከአንድ ሙያ በላይ የሆነ ሀገራዊ ህልውና ነው።
የዛሬው ትውልድ ቀድሞ ያልነበሩ የዲጂታል መሳሪያዎች በእጁ የሚገኙ በመሆናቸው፣ በአዲስ አበባ የሚገኝ ወጣት ከዓለም የቴክኖሎጂ ማዕከላት ጋር የመማር፣ የመወዳደር፣ ሀሳቡን ወደ ሶፍትዌር እና ፈጠራውን ወደ ንግድ የመቀየር ሙሉ አቅም አለው።
በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ በእውቀት የታጠቀ እና በራዕይ የተመራ ትውልድ ሀገሩን አይቻልም ወደሚባለው ህልም የማድረስ ችሎታ ያለው ሲሆን፣ በወጣቶች እጅ ያለው ስልክ የመዝናኛ ብቻ ሳይሆን የመማሪያ፣ የፈጠራ እና የዓለም ግንኙነት መስኮት ሆኗል።
ዛሬ የሚጻፈው ኮድ የነገን ኢኮኖሚ ይገነባል፤ ዛሬ የሚደረገው ምርምርም የሀገርን የዲፕሎማሲና የባሕር በር አቅም ያጠናክራል።
ምናልባትም የባሕር በርን የሚያስመልሰው ትውልድ በባሕር ዳርቻ ላይ ቆሞ የሚያልም ሳይሆን በዩኒቨርሲቲዎች እየተማረ፣ በላቦራቶሪዎች እየተመራመረ፣ በኮምፒዩተር ኮድ እየጻፈ እና አዳዲስ ሀሳቦችን ወደ እውነታ እየቀየረ ያለው ትውልድ ነው።
ይህ ትውልድ ታሪክን በቁጭት ብቻ የሚያስታውስ ሳይሆን ታሪክን በአዲስ መልክ የሚሰራ፣ የባሕር በር መብታችንን በእውቀት፣ በፈጠራ፣ በጠንካራ ሀገራዊ አቅም እና በሰለጠነ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በተግባር የሚያሳካ የጽናት ትውልድ ነው።
በልዩ እሸቱ
#ebc #redseaaccess #techforethiopia #ethiopianyouth #digitaltransformation #ethiopiarising

የሀገራዊ ስኬት፣ የቅርሶች ዘላቂነት እና የአህጉራዊ ተሞክሮ አዲስ ከፍታ
********************
መንግሥት የቱሪዝም ዘርፍን ከአምስቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ አድርጎ በትኩረት እየሰራበት በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ በዘርፉ እየተካሄዱ ያሉ መሠረታዊ ለውጦች የኢኮኖሚ ገቢን ከማሳደግ ባሻገር የሀገራችንን ዘመን ተሻጋሪ የታሪክና የባህል ቅርሶች ኅልውና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ታሪካዊ መደቦች ሆነዋል።
በአሁኑ ወቅት ዘርፉ ከባህላዊ የጉብኝት ዘይቤ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ፣ ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ የልማት ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል።
እንደ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ባሉ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የተገነቡት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜና ወጪ በመጨመር ሀገራዊ ገቢውን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደጉ ሲሆን፣ ዘመናዊ የቲኬት ማግኛ መንገዶች፣ የዲጂታል ማስታወቂያዎችና የሳይበር ደኅንነት ሥርዓቶች በመዘርጋታቸውም የአገልግሎት ጥራትና የገቢ አሰባሰቡን ቀልጣፋ አድርገውታል።
ይህ አገራዊ ስኬት የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ከመሆኑ ባሻገር፣ ከቱሪዝም ከሚገኘው ገቢ የተወሰነው የታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን ጥገና፣ ደኅንነትና እንክብካቤ በቀጥታ እንዲደግፍ የሚያደርግ አሠራር እንዲዘረጋ በማስቻል ትልቅ ምሳሌነትን ፈጥሯል።
የማኅበረሰብ አቀፍ ቱሪዝም መተግበሩ ደግሞ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከዘርፉ በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆንና ቅርሶቹን የራሱ አድርጎ እንዲጠብቃቸው በማድረግ የሕዝብ ባለቤትነትን አረጋግጧል።
በጥቂት የታወቁ መዳረሻዎች ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ወደ አዳዲስና አህጉራዊ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎች ማስፋፋቱ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብት በአዲስ ገጽታ ለዓለም ያስተዋወቀ ሁነኛ አጋጣሚ ሆኗል።
ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ እያረጋገጠች ያለችው ይህ አዲስ እመርታ የኢኮኖሚ ዕድገትን ከቅርስ እንክብካቤ ጋር አጣጥሞ ማስኬድ እንደሚቻል ለአፍሪካ አህጉር ትልቅ ተሞክሮና አርአያ የሚሆን ስኬት ነው።
የታሪካችን እና የባህላችን መገለጫ የሆኑ ቅርሶች ለወደፊቱ ትውልድ ሳይበላሹና ሳይደፈርሱ እንዲሸጋገሩ የተዘረጋው ይህ አስተማማኝ መደብ፣ ሀገራችን በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ የቱሪዝም መድረክ ላይ ያላትን መሪነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ይበልጥ የሚያጎለብተው ይሆናል።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #ethiopiantourism #visitethiopia #tourismdevelopment #africanheritage #sustainabletourism

ሰላም፥ እንደምን አደራችሁ?
የኢትዮጵያ የጋራ አንድነትና የሀገረ መንግሥት ህልውና መሠረት - ብሔራዊ ትርክት
ጠንካራ ሀገራት የተገነቡት በጸና ወታደራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ አቅም ብቻ ሳይሆን፤ ዜጎችን በሚያስተሳስርና በአንድ የጋራ ራዕይ በሚመራ ብሔራዊ ትርክት ጭምር ነው።
ብሔራዊ ትርክቶች የሚቀዱት ከሕዝቦች ባሕላዊ ታሪክ ነው፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የበርካታ ባሕል ባለቤት ሕዝቦች ሙዚየም ናት።
ብሔራዊ ትርክት ዜጎችን በጋራ ዓላማ የሚያነቃቃ፣ የሀገር ፍቅርን የሚያሰርፅና ህዝብን ለጋራ ራዕይ የሚያሰልፍ ታላቅ ኃይል አለው።
መጪው የጋራ ዕድላችን መመሥረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረም ይሆናል።
ጠቃሚና የጋራ ከነበሩ የአብርኾት ታሪኮች በመነሳት ብሔራዊ ትርክትን መፍጠር ይቻላል።
ከጋራ ትርክቶቹ ውስጥ በዓድዋ ድል ውስጥ ተደጋግሞ እንደሚነገረው አይበገሬነት፣ ጀግንነት፣ አልሸነፍ ባይነትና ድል አድራጊነት የኢትዮጵያውያን መለያዎች ተደርገው ይገለጻሉ።
ትርክቶቹ የሀገረ መንግሥት ግንባታውን ለማሳለጥ አስፈላጊ በመሆናቸው የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸውን ኃይሎች ወደ ብሔራዊ መግባባት ማምጣት ወሳኝ ተግባር ነው።
ኢትዮጵያውያን አንዳችም የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ጣጣ ሳይጫናቸው ባሕሎቻቸውን፣ አልባሶቻቸውን፣ ምግብና አመጋገባቸውን ተወራርሰዋል።

በመደመር እሳቤ ላይ የተመሰረተው የብሔራዊነት ትርክት ትውልዱን አንድ የሚያደርግና ብዝሃነትን ከሀገራዊ አንድነት ጋር አዋህዶ የሚይዝ አዲስ ዕይታ ነው።
ሁላችንንም ሊያግባባ የሚችልና ሀገርን የሚያፀና የጋራ ብሔራዊ ትርክት ለመገንባት የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድርሻ ወሳኝ ነው።
የጋራ መግባባት መፍጠርና ስምምነት ላይ መድረስ የሚያስችል አጀንዳ አለን፤ ከፋፋይ ትርክቶችን በመቃወምና አስተሳሳሪ የወል ትርክቶችን በማፅናት ለሀገር ብልፅግና መረባረብ ያስፈልጋል።
ሀገርና ሀገረ መንግስት በህዝቦች የጋራ ስምምነት፣ የጋራ ፍላጎት፣ የጋራ መረዳት ላይ የሚቆም ስለሆነ የጋራ የሆነ ትርክት፣ የጋራ የሆነ አረዳድ እና ንግግሮች እጅግ አስፈላጊ ናቸው፤ ለዚህም ማሳያ ሀገራዊ ምክክሩ ተጠቃሽ ነው።
ኢትዮጵያ የሁሉም ሀገር በመሆኗ ከሁሉም የተውጣጣ እንደ ሀገር የጋራ የሆነ ማንነት መገንባት ያስፈልጋል።
ታሪክን እንደ መከፋፈያ መሳሪያ እንጂ ማስተሳሰሪያና መማሪያ የመጠቀም ልማድ ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባት ጉዟችንን ፈትኖታል።
ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ወደ ተሟላና አሰባሳቢ ብሔራዊ ትርክት ማሸጋገር ዛሬ ላይ ሀገርን ከማፍረስ አደጋ ለመታደግ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደትና የብሔራዊ ትርክት ግንባታ ጥረቶች ለሀገሪቱ ሰላም፣ መረጋጋት እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ።

ሰላም፣ እንደምን አደራችሁ?
ይበልጥ የተጠናከረው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መዳረሻነት
ኢትዮጵያ ተፈጥሮ በወርቅ ብዕሯ ያሸበረቀቻት፣ ታሪክ በክብርና በግርማ ያነጻት፣ የአስራ ሶስት ወር ጸጋ ባለቤት፤ የሰው ዘር መገኛና የጥንታዊ ጥበባት ማህደር ናት።
የዚህች ታላቅ ሀገር የቱሪዝም ሀብት በቃላት ድርደራ የሚገለጽ ተራ ገጽታ ሳይሆን፤ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እሳታማ ምድር እስከ ምዕራብ አረንጓዴ ገበታ ድረስ እያንዳንዱን ተጓዥ በድንቅ አግራሞት የሚይዝ፣ የሚጨበጥና የሚዳሰስ እምቅ ኃይል ነው።
የአክሱም ድንቅ ሐውልቶች የቀደሙ አባቶቻችንን ምህንድስና እና የግዛት ግርማ ይመስክራሉ። ከአንድ ወጥ ዓለት የተፈለፈሉት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትም፣ ጥበብና እምነት ውህደት ፈጥረው ጽንፍ የረገጡበት ተአምራት ናቸው።
በምስራቅ፣ ተፈጥሮ ከሰው ልጅ ጥበብ ጋር የተቀላቀለችበት የሶፍ ዑመር ዋሻ የጥበብን ጥግ ያሳያል። ወደ አፋር ድንበር ስንሻገር ደግሞ፣ የዳሎል ቀለማትና የኤርታሌ የመሬት ውስጥ እሳት ድምቀት ሰውን ከምድር አውጥተው ሌላ የጠፈር አካል ላይ የረገጡ ያህል መንፈስን የሚያስደምም ተአምራዊ ስሜት ይፈጥራሉ።
በተጨማሪም ሀገራችን በዓለም ላይ በሌላ ቦታ የማይገኙ ሀገር በቀል የእጽዋት፣ የአዕዋፍና የእንስሳት ዝርያዎች ማዕከላዊ መኖሪያ በመሆን የተፈጥሮ ተመራማሪዎችንና ቱሪስቶችን ቀልብ ትስባለች።
ይህንን ዘመን ተሻጋሪ የታሪክና የተፈጥሮ ሀብት ከወትሮው የዝምታና የመዘናጋት ካባ በማውጣት፣ የመደመር መንግሥት ላለፉት ጥቂት ዓመታት የወሰደው የቆራጥነት ርምጃ የዘርፉን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል፤ ቱሪዝምንም የሀገራዊ ብልጽግና ዋና አምድ አድርጎታል።
ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ፡ እነዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ተፈጥሮ የሰጠችንን በረከት ወደ ዘመናዊ፣ ማራኪና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ወደጠበቁ የመዳረሻ ስፍራዎች ቀይረዋቸዋል።
የእንጦጦ ፓርክ፣ የወንጪ፣ የኮይሻ፣ የሃላላ ኬላ እና የጎርጎራ ፕሮጀክቶችም ተፈጥሮን ከማደንቅ ባሻገር፣ ተፈጥሮን በመንከባከብና ለትውልድ በሚመች ውበት አዘጋጅቶ ማቅረብ እንደሚቻል ማረጋገጫ ሆነዋል።
የላሊበላ እና የጎንደር ፋሲለደስ ጥገና፣ የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት እድሳት፣ እንዲሁም የብሔራዊ ቤተ መንግሥት፤ዘመናዊ ቅርስ ጥበቃ፣ ታሪክን ከዘመናዊ የእንግዳ ተቀባይነት አገልግሎት ጋር አስተሳስረዋል።
ዘርፉን ሙሉ በሙሉ ለማዘመንና መረጃዎችን ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ፣ አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በዲጂታል አማራጮች የታገዙ እንዲሆኑም ተደርጓል።
በጥቅሉ፣ ኢትዮጵያ የነበራትን እምቅ ሀብት ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ጥንካሬና ፍጹም ሀገራዊ ምስል በመቀየር ላይ ትገኛለች።
የቀደመ ታሪካችን ግርማ ከዘመናዊ የልማት ራዕይ ጋር ተዋህዶ ሀገራችንን በዓለም ቱሪዝም መድረክ ላይ በደማቅ ብርሃን እያበራት ይገኛል።

2 months ago
ወርቃማው ምዕራፍ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለዘመናት የተንከባለሉና ያልተፈቱ የፖለቲካ ስብራቶቿን በአዲስ ተስፋና በሰለጠነ መንገድ ለመጠገን ወደሚያስችላት ወርቃማው የፖለቲካ ምዕራፍ ተሸጋግራለች።
አዲሱ የመደመር ዕሳቤ፣ ችግሮችን በግጭትና በጠብመንጃ ከመፍታት ይልቅ፣ በውይይትና በምክክር የጋራ መግባባትን በመፍጠር ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የላቀ ትኩረት ሰጥቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወደ ሀገር መሪነት መንበር ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ያቀረቡት ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪ፣ ዛሬ ላይ ታሪካዊውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔን እውን በማድረግ ውስብስብ የፖለቲካ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል ደማቅ የተስፋ ብርሃን ፈንጥቋል።
ለብዙ ዘመናት መሳሪያ ሲያማዝዙ፣ ሲያገዳድሉ፣ ጫካ ሲያስገቡና በረሃ ሲያስወርዱ የነበሩ አጀንዳዎች ወደ አንድ አዳራሽ ገብተው የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት መሆናቸው እጅግ አስደናቂና ልብን በሀሴት የሚሞላ ነው።
በታሪካችን ተስኖን የነበረውን ቁጭ ብሎ የመመካከር ባህል ስንለማመድ፣ ተወያዮች ቢከራከሩ፣ በሐሳብ ቢለያዩና ቢሞግቱ ከቶ ሊያስገርመን አይገባም።
የሐሳብ ጦርነት እንጂ የጠብመንጃ ጦርነት ባለመሆኑ፣ ልዩነቶች እየተፋጩና እየተጋጩ ወደሚያዋጣው 'ወርቃማው መካከለኛ መንገድ' ያደርሱናል።
የትኛውም የበለጸገ ዓለም የተጓዘበት ይህ የሐሳብ ልዕልና መንገድ፣ ዋነኛ ማዕከሉና ቀዳሚ መመዘኛው የሀገር ሕልውና፣ ብሔራዊ ጥቅም፣ ሰላምና ደህንነት ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከታዩት እንደ ቱኒዚያ፣ የመን፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ የምክክር ሒደቶች አኳያ ሲመዘን፣ እጅግ የተለየና በአብነት የሚጠቀስ የላቀ ተሞክሮ ያለው ነው።
በሌሎች ሀገራት ሒደቱ በአብዛኛው ጥቂት አካላትን ያካተተ የልሂቃን የሥልጣን ክፍፍልና ድርድር ሲሆን ፥ የኛዋ ሀገር ምክክር ግን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ዜጎችን፣ ከ1 ሺህ 234 ወረዳዎች የተውጣጡ 1 ሺህ 600 የሕዝብ አጀንዳዎችን እንዲሁም አራት ሺህ ተወያዮችን በአንድ አዳራሽ ያሳተፈ የሀገር ህመም መፈወሻ ነው።
በዐዋጅ የተቋቋመውና ሙሉ ነፃነቱ የተጠበቀው ይህ ኮሚሽን፣ መንግሥትን ጨምሮ ከማንኛውም አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆኖ ሒደቱን በገለልተኛነትና በቁርጠኝነት እየመራው ይገኛል።
ይህ የሕዝብ ውክልና በተግባር የተረጋገጠበት እውነተኛ ሀገራዊ የምክክር ሂደት፣ የፖለቲካ ልሂቃን ብቻ ሳይሆን፤ ከከተሜው አልፎ አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩንና ብሔረሰቦችን በባለቤትነት ያሳተፈ ደማቅ ታሪካዊ መድረክ ነው።
የሀገራችን አዲሱ ትውልድ በጠረጴዛ ዙሪያ በልዩነት ውስጥ አንድነትን የመፍጠርና ምክክርን ባህል የማድረግ የዴሞክራሲ ልምምዱን እያጠናከረ ነው።
የዚህ ጉባኤ የውሳኔ ሐሳቦች ወደ ተጨባጭ ውጤት ሲቀየሩ የሀገራችንን የግጭት ታሪክ በዘላቂነት በመዝጋት ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያሸጋግሩ ጠንካራ የመሠረት ድንጋይ ይሆናሉ።
ይህ ታሪካዊ ክስተት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ልዩ ሥፍራ የሚሰጠውና ወርቃማው ምዕራፍ ተብሎ በኩራት የሚዘከር ነው።
በአሰፋ አሕመድ

የብሔራዊነት ትርክት
***********
በዓለማችን ላይ ያሉ ጠንካራ ሀገራት የተገነቡት በጸና ወታደራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ አቅም ብቻ ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በሚያስተሳስርና በአንድ የጋራ ራዕይ በሚመራ ብሔራዊ ትርክት ጭምር ነው።
ትርክት ማለት ዓለምን፣ ሀገርን፣ አካባቢን እና ህዝብን የምንመለከትበት አጠቃላይ መነፅር ነው። ትርክት ዜጎችን በጋራ ዓላማ የሚያነቃቃ፣ የሀገር ፍቅርን የሚያሰርፅ እና ህዝብን ለጋራ ራዕይ የሚያሰልፍ ታላቅ ሀይል አለው።
የታላላቅ ሀገራትን ተሞክሮ ስንመለከት፣ የትኛውም ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ያለ አሰባሳቢ ትርክት ሊገነባ እንደማይችል እንረዳለን። ሀገራት የራሳቸውን ታሪክ፣ ስነ-ልቦና እና እሴት መሰረት ያደረገ ትርክት ገንብተዋል፡
አሜሪካውያን፡ "የአሜሪካ ልዩ መሆን" (American Exceptionalism) በሚለው እሳቤ እና በዴሞክራሲያዊ እሴቶቻቸው ላይ የተመሰረተ ትርክት በመገንባት፣ ዜጎቻቸው በሀገራቸው ታላቅነት እንዲኮሩና ዓለም አቀፍ ተፅእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ አድርገዋል። ይህንን ትርክታቸውንም በተለያዩ መንገዶች (እንደ ሆሊውድ ፊልሞች) ለትውልድ ያስተላልፋሉ።
ጃፓናውያን፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት አስከፊ ውድመት በኋላ የሳሙራይ የጀግንነት ባህላቸውንና ለሀገር ክብር መስዋዕት የመሆን እሴትን፣ ከተፈጥሮ አክብሮትና ከዘመናዊ ስራ ወዳድነት ጋር በማዋሃድ፣ ሀገራቸውን ከአመድ ላይ አንስተው በዓለም የኢኮኖሚ ከፍታ ላይ አቆሙ።
ደቡብ አፍሪካውያን፡ ከአፓርታይድ አስከፊ የዘረኝነት እና የመከፋፈል ስርዓት ማግስት፣ "የቀስተ ደመና ሀገር" (Rainbow Nation) በሚል አቃፊ ትርክት፣ ልዩነታቸውን ወደ ውበት፣ አንድነት እና እርቅ ቀይረው ጠንካራ ሀገር መገንባት ቻሉ።
ሲንጋፖር፡ ከትንሽ እና ደሃ ደሴትነት ተነስታ፣ አለም አቀፍ የፋይናንስ ማዕከል ወደ መሆን ያደረገችውን ፈጣን የኢኮኖሚ ለውጥ ትርክት የሀገረ መንግሥቷ ማንነት መቅረጫ አድርጋ ተጠቅማበታለች።
ወደ ሀገራችን ታሪክ ስንመጣ፣ ላለፉት ዘመናት ሲያጋጩን የነበሩት የተዛቡ ትርክቶች ወደ ጽንፍ ያዘነበሉ እና መካከለኛውን መንገድ የሳቱ ነበሩ። በዚህም የተነሳ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የመገንባት ጉዟችን ተስተጓጉሎ፣ በማይደፈሩ የሀገር ቀይ መስመሮች ላይ እንኳ ጠንካራ የጋራ ስምምነት እንዳይኖረን አድርጓል። ተቋማትም ይህንን በማስተካከል ፋንታ፣ የዚሁ ሰለባ ሆነው ቆይተዋል።
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ይህንን ፈታኝ የአስተሳሰብ ጽንፍ ሰብሮ የሚወጣ፣ ህዝቦችን የሚያስታርቅ፣ አንድ የሚያደርግ እና ብዝሃነትን ከሀገራዊ አንድነት ጋር አዋህዶ የሚይዝ አዲስ ዕይታ ይፈልጋል። ይኸውም በመደመር እሳቤ ላይ የተመሰረተው የብሔራዊነት ትርክት ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደ ሰርገኛ ጤፍ የተሰባጠረ ማንነት ያለው መሆኑን አምኖ በመቀበል፣ ሆኖም ግን ሀገራዊ አንድነትን እና ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥትን ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚያስቀድም መንገድ ነው።
ከቁዘማ ወደ ተስፋ መሻገር፡ ያለፈውን እያመነዠጉ ከመወቃቀስ ይልቅ፣ የትናንት ጥፋቶችንም ሆነ ድንቅ ልማቶችን የጋራ ታሪካችን አካል መሆናቸውን ተቀብሎ ዛሬንና ነገን በጋራ ብሩህ ለማድረግ ይሰራል፤ አዲሱን ትውልድም ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋል።
እውነተኛ አካታችነት፡ ማንኛውንም ዜጋ በማንነቱ ሳያገል፣ ሁሉም በሀገሩ ግንባታ ላይ እኩል ድርሻና የባለቤትነት ስሜት እንዲኖረው በማድረግ ጥልቅ የወንድማማችነት እሴትን ያጎለብታል።
የሀገር ብሔራዊ ጥቅም፡ ከሀገር ህልውና፣ ሉዓላዊነት እና የጋራ ደህንነት የሚበልጥ አጀንዳ እንደሌለ በማስገንዘብ፣ ጠንካራ ብሔራዊ ስሜትን ይፈጥራል።
ይህ አሰባሳቢ እሳቤ ኢትዮጵያን ከተሰበረ እና ከተከፋፈለ የትናንት ታሪክ አውጥቶ፣ ወደማትናወጥ እና ፅኑ ሀገረ መንግሥትነት የሚቀይር ጉልበት አለው። ልዩነቶቻችንን በወንድማማችነት ማዕቀፍ ውስጥ በማስተናገድ ሀገራችንን ሁላችንም ወደምንመኛት ዘላቂ የብልፅግና ጎዳና የሚወስዳት ይኸው መንገድ ነው። ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ፈተና አሻግሮ ወደ ተፈጠረችበት ታላቅ የከፍታ ማማ የሚያወጣት፣ እንዲሁም የዜጎቿን ሰላምና ክብር በዘላቂነት የሚያረጋግጠው ጠንካራው የብሔራዊነት ትርክት ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ትርክት

ከአፈሙዝ ወደ ውይይት ጠረጴዛ፦ የፖለቲካ ባህላችንን እየቀየረ ያለው ሀገራዊ ምክክራችን
**************************
በኢትዮጵያ እውን እየሆነ ያለው ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት የሕዝብ ብሶቶች እና ጥያቄዎች እንዲሁም ለታሪክ ስብራቶች በሰለጠነ መንገድ እልባት ለመስጠት ያለመ አዲስ ልምምድ ነው።
በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አመለካከቶችን ይዞ ወደ ውይይት ጠረጴዛ በመምጣት በእኩልነት መምከር መቻል በራሱ ትልቅ ታሪካዊ ስኬት ነው።
እንዲህ ያለው አካታች ምክክር ከዚህ ቀደም ለተነሱ ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ሊነሱ ለሚችሉ የማኅበረሰብ ጥያቄዎች ዘላቂ እና አስተማማኝ ምላሽ የሚገኝበት ዋነኛ መንገድ ነው።
ምክንያቱም እውነተኛና ዘላቂ መፍትሔ የሚወለደው ሁሉን ወገኖች በማካተት ከሚደረግ የሰከነ ውይይት እንጂ ከታጣቂዎች አፈሙዝ ሊሆን አይችልም።
በሀገራዊ ምክክራችን ሂደት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተለያዩ አካላት የሚሰነዘሩ ከእውነታ የራቁ አሉባልታዎች እና አሉታዊ ሀሳቦች ወደ ዘላቂ ሰላም የጀመርነውን ጉዞ ሊያስተጓጉሉት አይችሉም።
እነዚህ አሉባልታዎች እና አሉታዊ ሀሳቦች የሕዝቡን ፍላጎት የማይወክሉ፣ ይልቁንም የሰላም ሂደቱን ለማስተጓጎል እና ጥርጣሬን ለመዝራት የሚደረጉ ከንቱ መፍጨርጨሮች ናቸው።
ከእልቂት እና ከውድመት በቀር ከጦርነት እና ከጽንፈኝነት ያተረፍነው አንዳች ጥቅም እንደሌለ ያለፈው ታሪካችን ሕያው ምስክር ነው።
በመሆኑም ከብጠመንጃ ይልቅ አሁን የጀመርነው የሰለጠነ የምክክር መንገድ ሁላችንንም አሸናፊ የሚያደርግ ብቸኛው አማራጭ ነው።
ሀገር የምትመራው እና የምትገነባው በሰከነ ውይይት እና በሕግ ጽኑ መሠረት ላይ እንጂ በኃይል እና በጠመንጃ አይደለም።
አሁን እያካሄድነው ያለው ሀገራዊ ምክክር የረጅም ሂደት ጅማሮ እንጂ መዳረሻው አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ምክክሩ ወደፊትም ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የፖለቲካ ኃይሎች እያሳተፈ፣ ድምጻቸው እንዲሰማ እያደረገ በተደራጀ እና በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላል።
ሀገራዊ ምክክሩ ሁሉም የመፍትሔው አካል የሚሆንበት በመሆኑ፣ ለነገዋ ሰላማዊት እና የበለጸገች ኢትዮጵያ ጠንካራ መሠረት እየጣለ ይገኛል።
ምክክሩ ለዛሬ ሰላማችን የምንጠቀምበት ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ትውልድ ጭምር በቅርስነት የሚተላለፍ የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ነው።
በሰከነ ሀገራዊ ምክክር ከግጭት አዙሪት በመውጣት ለቀጣዩ ትውልድ ሰላም እና አንድነቷ የተጠበቀ የበለጸገች ኢትዮጵያን ከሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ጋር እናስረክባለን።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #nationaldialogue #peacebuilding #ebc

ክብ ታሪኮች /በቡናዬ እስኪሰክን/
* ገጣሚ ታገል ሰይፉ የቤተ-ማሪያም ተሾመ ቡናዬ እስኪሰክን መፅሐፍ የህይወትና የታሪክ አዙሪቶችን የዳሰሰበት መንገድ
#ethiopia | ይህ እንደሃያሲ መፅሐፉ እንዴት እንደተፃፈ ለመፈተሽ የቀረበ ትንተና አይደለም፡፡ እኔ እንዴት እንዳነበብኩት ለመግለፅ እንጂ…
እንደ እኔ ንባብ ከሆነ የደራሲ ቤተ-ማሪያም ተሾመ “ቡናዬ እስኪሰክን” እንደኦሎምፒክ አርማ በብዙ ህብረ ቀለማዊ ክብ ቀለበቶች የተሞላ መፅሐፍ ነው፡፡
መፅሐፉ በአእምሮ ውስጥ እንደጅረት የሚፈስን ሃሳብ ተከትሎ የሚጓዝ ዓይነት ነው፡፡ በሰው አእምሮ ውስጥ እንደጅረት የሚፈሱት ሃሳቦችና ስሜቶች ከጅረቱ በተቃራኒ ከሚጓዙት ድርጊቶችና ንግግሮች ጋር ትይዩነት አላቸው፡፡ ብዙ ጊዜ እነዚህን የተቃረኑ ቁርኝቶች ጮክ ብለን አናወራቸውም፡፡ በአእምሯችን ሸለቆ ውስጥ ተቀብረው ይፈሳሉ እንጂ…
በዚህ መፅሐፍ ግን በፍሰታቸው ውስጥ የራሳቸውን ክብ እየፈጠሩ ያልፋሉ እንጂ ቀጥ ብለው አይጓዙም፡፡ በአጭሩ ይህ መፅሐፍ የብዙ ክብ ታሪኮች ስብስብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ክቦቹ ከህይወታችንና ከታሪካችን የተቀዱ ናቸው፡፡
ክብ በሆነ መንገድ ላይ ስንጓዝ የትም አንደርስም፡፡ ከማያቋርጠው ድግግሞሽ የተነሳ ዞረን ዞረን እዛው ነን፡፡ ደራሲው በቡናዬ እስኪሰክን መፅሐፉ ቀጥ ብሎ ወደ ሆነ ግብ የሚያመራ ታሪክ አያሳየንም፡፡ ከዋናው ገፀ ባህሪይ ስሜት እና ፍላጎት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ታሪኮች የራሳቸውን ክብ እየሰሩ ይጠናቀቃሉ፡፡
ለምሳሌ ሚስቱ ጠዋት ያሳየችውን የተሸመደደ ጠባይ ማታም ትደግመዋለች፡፡ በማለዳው የቡና ስኒ የተጀመረው ታሪክ ዞሮ ዞሮ እዚያው ሲኒ ላይ ያከትማል፡፡ በታሪኩ መጀመሪያ አካባቢ የአደጋ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሰውዬ መጨረሻ ላይ አደጋውን ያስተናግዳል፡፡ በአስመራው ባሬስታ ላይ የደረሰው ነገርም በለሚ ኩራው ባሬስታ ላይ ይደገማል፡፡ የጀብሎዎቹና የሊስትሮዎቹ ምሬትና አመፅም በሀገሪቱ ግዙፍ የታሪክ አዙሪት ተውጦ ይቀራል፡፡ የአታክልቲ መጨረሻም እንዲሁ፡፡
መፅሐፉ በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥም ዞሮ ዞሮ ያው የሆነውን የመበላላት አዙሪት ያነሳል፡፡ በኮሎኔል መንግስቱና በእነተፈሪ ባንቴ መካከል የተፈጠረውን… በህወአት አመራሮች የእርስ በእርስ ግጭት የተደገመውንና በቅንጅት መሪዎች የተሰለሰውን የመበላላት አዙሪት ይታዘባል፡፡
የዋናው ባለታሪክ አለም አቀፍ ግንዛቤዎች ጭምር ዞሮ ዞሮ እዛው በሆነ የታሪክ አዙሪት የተዋጡ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ማ ቤከርን ያነሳል፡፡ ቦኒየሞች የዘፈኑላት ማ ቤከር በዘመኗና በመንደሯ የበረታው ግፍና ወንጀል አስመርሯት ከአራት ልጆቿ ጋር አመፅ ማስነሳቷን ይነግረናል፡፡ ድል አድራጊው የማ ቤከርና የልጆቿ ስኬታማ አመፅ የሚጠናቀቀው ግን ያንኑ ግፍና ወንጀል በመድገም ነው፡፡
የስኒውን ምልኪ ጨምሮ በቡናዬ እስኪሰክን ደጋግመን የምናገኛቸው እንደ ውርርድ፣ እጣ ፋንታና የአርባ ቀን እድል ዓይነት ቃላት ራሳቸው የክብነት ባህሪይ አላቸው፡፡ ንግርት ሁሌም የሚነግርህ የፈለግከውን ያክል ብትፍጨረጨር ከተፃፈልህ እጣ ፋንታ እንደማታመልጥ ነው፡፡
የሰው ልጅ የሚሆነውን ነገር ለምን እንደሚሆን የሚረዳበት አእምሮ እና ተጨባጭ ምክንያት ሲያጣ የምልኪ ፣ የጥንቆላና የአርባ ቀን እድል ሰለባ ይሆናል፡፡ በማይቆጣጠረው የህይወት አዙሪት ውስጥም ይወድቃል፡፡
በዚህና በሌሎች ምክንያቶች የተፈጠረው የሃሳብና የታሪክ አዙሪት መፅሐፉን አሰልቺ አለማድረጉ ይልቁንም ጣእሙን እንዳሳመረ እስከመጨረሻው የመዝለቁ ነገር የፅሁፌ ዋና ጉዳይ ነው፡፡ ይህን የማነሳው አለምክንያት አይደለም፡፡
ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሁፍ ፈር ቀዳጅ የተባሉ አንዳንድ የስነ-ፅሑፍ ሙከራዎች አንባቢን የማታከት ባህሪይ ይታይባቸዋል፡፡ አንዱን ሲይዙት ብዙ ያመልጣቸዋል፡፡ በእኔ እምነት የተሟላ ፈር ቀዳጅ ስራ ነጠላ መልክም ትርጉምም የለውም፡፡ ቢያንስ አምሰት ተጨማሪ ሙላቶች አሉት፡፡ ስድስተኛውም እጅግ ይመረጣል እላለሁ፡፡
-የመጀመሪያው የቋንቋ ውበት ነው፡፡ ቋንቋው ካላማረህ ጀምረህ አትጨርሰውም፡፡ በዚህ መፅሐፍ ዋናው ባለታሪክ ህይወትን አሟጦ ሲኖር አይታይም፡፡ ኑሮን በቀጥታ የመጋፈጥ ድፍረት ይጎለዋል፡፡ በአብዛኛው የታሪኩ ክፍል ሲሸሽ እንጂ ሲያሳድድ አናየውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የተላኩለትን ሁለት አጓጊ ደብዳቤዎች እንኳ አንብቦ የመጨረስ ድፍረት የለውም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ዋና ገፀ-ባህሪይ ይዞ ማራኪ ታሪክ መፍጠር ይከብዳል፡፡ ያም ሆኖ የደራሲው ቋንቋ ቀላል እና ውብ ስለሆነ ሳይሰለቸን እንዲያውም ደስ እያለን እናነበዋለን፡፡
-ሁለተኛው የሃሳብ ጉልበት ነው፡፡ በሃሳብ ጥልቀት የዳበሩ መፅሐፎችን ስናሰላስላቸው እንከርማለን እንጂ አንብበን አንጨርሳቸውም፡፡ “እግሮችህ የአንተ ናቸው፡፡ ወዳሻው የሚራመድበት ግን ሌላ ነው” የምትለው የመፅሐፉ ደማቅ አረፍተ ነገር ተነባ የምታልቀው መቼ ነው?
-ሶስተኛው የትውልድና የዘመን ነፀብራቅነት ነው፡፡ አፈወርቅ ገብረ እየሱስ የባሪያ አሳዳሪውን ዘመን… ሃዲስ አለማየሁና ዳኛቸው ወርቁ የፊውዳሉን… በአሉና ብርሃኑ ዘሪሁን የአብዮቱን ዘመን ከነሙሉ ጠረኑና ለዛው እንደፃፉልን ሁሉ ቤተ-ማሪያምም የኮሪደር ዘመኗን አዲስ አበባ ፊልም በሚመስል ትእይንት ያሳየናል፡፡
-አራተኛው ከውስጥ የመነጨ ልዩነት ነው፡፡ ለየት ለማለት ብሎ ከእውነታውም ከችሎታውም ከማንነቱም ከስሜቱም የራቀ ደራሲ ህያው እስትንፋስ ያለው የጥበብ ስራ ሊያቀርብልን መቻሉን እጠራጠራለሁ፡፡ እንዲያውም በእኔ እምነት መለየት የሚባለው ነገር ፈልገህ የምታገኘው ሳይሆን ተለይተህ የምትገኝበት ወይም የምትፈጠርበት ዓለም ነው፡፡ ቤተ-ማሪያም ተሾመ በጠያይም መላእክትም ሆነ በዚህኛው መፅሐፉ ተለይቶ የተፈጠረ ወዛም ደራሲ እንጂ ለመለየት የተፍጨረጨረ ችኮ ብእረኛ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
-አምስተኛው ውስጡ የሰፋ ስስነት ነው፡፡ ራስህ ካልተቆነጠጥክ በቀር ህመም የማይሰማህ ከሆነ አንተ ዳያሪ ፀሃፊ እንጂ የተዋጣለት ደራሲ የመሆን እድልህ ጠባብ ነው፡፡ ለትልቅነት የታጨ ደራሲ በቤቱ ብቻ ሳይሆን በጎረቤቱ… በሰፈሩ ብቻ ሳይሆን በሀገሩ የመጣ ቁንጥጫ ያመዋል፡፡ ከዚያም አልፎ የሰው ልጅ ውጋት ይቀስፈዋል፡፡ ከእኛ ዘመን እና ሀገር የራቁ ታላላቅ ደራሲያን በሌላ ቋንቋ ፅፈው ስሜታቸውን የሚያጋቡብን ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ ቤተ-ማሪያም ተሾመ በሰፈሩም በሃገሩም የሚሆነው ነገር የሚሆነውን የሚያሳጣው ዓይነተ ደራሲ መሆኑን ከስራዎቹ መረዳት ችያለሁ፡፡
በዚህ ዓይነት ደረጃ ከመሰጡኝ የሀገራችን ደራሲያን ግን የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሁፍ ታሪክ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ያገኘሁት ከፍቅር እስከ መቃብር በኋላ ያነበብኩትን የዳኛቸው ወርቁን አደፍርስን ነው፡፡ በአጭር ልብ-ወለድ ዘርፍም ከስብሃት ገብረእግዚአብሔር በኋላ ያነበብኳቸው የአዳም ረታ አጫጭር ልብ -ወለዶች በእኔ እይታ የኢትዮጵያ ስነ-ፅሁፍ ፈር ቀዳጅ ስራዎች ናቸው፡፡ በተለይ አለንጋና ምስር ውስጥ ያሉት…
ከእነዚህ ሁለት ታላላቅ ደራሲያን ስራዎች በኋላ በተሟላ ሁናቴ ፈር ቀዳድ ሆኖ ያገኘሁት የቤተ-ማሪያም ተሾመን ቡናዬ እስኪሰክን ነው፡፡
ቤተ-ማሪያም በዚህ መፅሐፉ ከተጠቀማቸው ቃላት በላይ ብዙ ፅፏል፡፡ በበኩሌ አንድን ስራ ምርጥ ስነ-ፅሁፍ ከምልባቸው ምክንያቶች ስድስተኛው በትንሽዬ መፅሐፍ ውስጥ ብዙ ሺህ ገፆች ሲያስነብበኝ ነው፡፡
ለጆርጅ ኦርዊል አኒማል ፋርም… ለሚካኤል ቡልጋከቭ ሳባቺዬ ሴርሴ… ለሄሚንጉዌይ ሽማግሌውና ባህሩ… ለቼሆቭ ዋርድ ነበር ሲክስ… ለቶልስቶይ የኢቫን ኤሊይች እረፍት… ለአልበርት ካሙ ባይተዋር… ከፍተኛ አድናቆት ያለኝ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡
ቡናዬ እስኪሰክን ከላይ ከገለፅኳቸው መፅሐፎች ጋር የሚመጣጠን ልዩ እርካታ ፈጥሮብኛል፡፡ በእያንዳንዱ አዙሪት እያሽከረከረ እኛንም ዘመናችንንም ሀገራችንንም በጥልቀትና በድምቀት ያሳየ ስራ በመሆኑ…
በነገራችን መሀል በቤተ-ማሪያም ተሾመ ቡናዬ እስኪሰክን የክብ ታሪኮች ጅረት የመጨረሻ ገፅ ላይ ያሉት የመጨረሻዎቹ ሁለት መጠይቃዊ ቃላት ራሳቸው አዙሪቱ የፈጠረውን ተደጋጋሚ ክብ አሳስበውኛል፡፡
“… ተጀመረ? ወይስ ተፈፀመ? …” ይላሉ፡፡
ህይወትም ታሪክም ፖለቲካም ክብ ሲሆንብህ እንዲህ ትጠይቃለህ፡፡
ክቡ የት ጋ እንደሚጀምር አታውቅም፡፡ የት ጋ እንደሚጠናቀቅ ጭምር፡፡
#bunaeeskisekin #betemariamteshome #ethiopianliterature #amharicbooks #ethiopianwriters #bookreview #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

አረንጓዴ ዐሻራ፡- የኢትዮጵያውያን የሕብረትና የፅናት ህያው ሐውልት
**************************
ኢትዮጵያውያን በጋራ ስንቆም የሚያስቆመን ምድራዊ ኃይል እንደሌለ የቀደመው ታሪካችን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
በዓድዋ ጦርነት በአንድ ልብ ተሰልፈን ቅኝ ግዛትን ድል እንደነሳነው እና ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የሀገራዊ ቁርጠኝነት ምልክት አድርገን እንደገነባነው ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ በተፈጥሮ ጥበቃ ታሪክ አዲስ ሀገራዊ ገድል እየፈጸምን እንገኛለን።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው ታላቁ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፣ በሕብረትና በፅናት ከተጓዝን ሁለንተናዊ ለውጥን በተግባር ማምጣት እንደምንችል ያረጋገጠ ደማቅ የስኬት ማሳያ ሆኗል።
ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ እስከ 56 ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን በመትከል የሀገራችንን የደን ሽፋን ከ17.2 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደግ ተችሏል።
በቅርቡም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያውያን በድጋሚ ዓለምን ያስደመመ ታላቅ የአንድነት ድል አስመዝግበዋል።
ይህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከአርሶ አደር እስከ ከተሜው የተሳተፈበት ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ የተራቆቱ መሬቶችን ከማገገም ባሻገር፤ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያና ቡና ያሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በማካተት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ አቅምን ለመገንባት ትልቅ መሰረት ጥሏል።
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ጥበቃና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እያስመዘገበችው ያለው ይህ አስደናቂ ስኬት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈጥሮ እንክብካቤ ተምሳሌት እንድትሆን አድርጓታል።
ከዚህም የተነሳ ሀገራችን ቀጣዩን ታላቅ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) እንድታስተናግድ ታሪካዊ ኃላፊነት ተጥሎባታል።
የተተከሉትን ችግኞች በተከታታይ መንከባከብና ማሳደግ የነገ ሀገራዊ ፅናታችንን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ይህን ኃላፊነት በመወጣት ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገችና ያሸበረቀች ኢትዮጵያን በሕብረት ሊያወርስ ይገባል።
በብሌን ደምበሎ
#greenlegacy #ethiopia #climateaction #planthope #cop32 #ebc

80 ዓመት ኩራት፤ 80 ዓመት ትሕትና — የኢትዮጵያ አየር መንገድ!
(የኢትዮጵያ አየር መንገድን 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ የተጻፈ)
ተስፋዬ እሸቱ (ረዳት ፕሮፌሰር)
ሮም፣ ጣሊያን
#ethiopia | “የኢትዮጵያ አየር መንገድ” የሚለው ዓለም አቀፍ ዝና ያለው ስያሜ ለእኔ በደማቅ ወርቃማ ቀለም የተጻፈ የክብር ስሜ ነው። ለእኔ ብቻም ሳይሆን፣ ለአንተም፣ ለአንቺም፣ ለእሱም፣ ለእሷም፣ ለእነሱም… ለሁላችንም ዓለም አቀፍ ታላቅነትን ያጎናጸፈን የወል መለያ፣ የክብር ስማችን ነው።
ክብርና ኩራታችን የሆነው ይህ ታላቅ አየር መንገዳችን፣ በዓለም ሁሉ የእኛ የኢትዮጵያውያን ባለሙሉ ሥልጣን ልዩ ልዑክ፤ የምድርና የሰማይ ወኪል እንደራሴም ነው።
የአየር መንገዳችን ታሪክ የአንድ ተቋም ታሪክ ብቻ አይደለም። አንድ ሕዝብ ራሱን ለዓለም ያስተዋወቀበት፣ የገለጠበት ታሪክ ነው፤ ልክ እንደ አድዋ በዓለም ላይ ያልተሸነፍንበት ታሪካችን ነው።
ለዚህም ነው “የኢትዮጵያ አየር መንገድ” ስለተባለው የማንነታችን ልዩ ምልክት ዕድሜዬን ሙሉ ብጽፍ የማይሰለቸኝ።
አንዳንድ ተቋማት ትርፍ ብቻ ሊያጋብሱ ይችላሉ፤ እሰየው ነው። አንዳንዶች ደግሞ ከትርፍ በላይ የሀገርን ክብር በኩራት ይሸከማሉ፤ ይሄማ ሲሆን ይበልጥ መታደል ነው።
ታዲያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገርን ክብር የተሸከመ፣ ላለፉት ሰማንያ ዓመታት ሳይታክት፣ ሳይዛነፍ የኩራታችን ምንጭ የሆነ፣ በአልማዝ ያጌጠ ስማችን ነው።
ለ80 ዓመታት ተሳፋሪን ከነሻንጣው ብቻ አላጓጓዘም፤ የአፍሪካን ተስፋ፣ የኢትዮጵያን ስም፣ የጥራትን ልክ ተሸክሞ የበረረ ኩራታችን ነው።
ኩራት ከተደጋጋሚ ስኬት ይወለዳል።
አንድ ጊዜ ተወዳድሮ ማሸነፍ ክስተትም ዕድልም ሊሆን ይችላል፤ ለ80 ዓመታት ግን በዓለም የአቪዬሽን ገበያ ውስጥ ተወዳድሮ መቆየትና ለአንድ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለአንድ አህጉር የኩራት ምንጭ መሆን ክስተት አይደለም፤ ዕድልም ሊሆን አይችልም።
ያ ራዕይ ነው።
ያ ፕሮፌሽናሊዝም ነው።
ያ ተቋማዊ ባህል ነው።
ያ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ የሥራ ሥነ-ምግባር ነው።
ያ እንደ አድዋ ድል የማይበገር ጽናትን በዘመናዊ ውድድር ውስጥ በአዲስ መልክ የገለጠ የቆራጥነት መንፈስ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእኛ ኩራት የሆነው ከፍ ብሎ ስለበረረ ብቻ አይደለም፤ ለ80 ዓመታት ከፍ ብሎ መቆየት ስለቻለ ነው።
የኩራታችን መሠረቱም በተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ፣ በማይገመት የዓለም ኢኮኖሚ፣ በከባድ ዓለም አቀፍ ውድድር፣ በተለያዩ ችግሮችና ፈተናዎች መካከል ስሙን ጠብቆ መጓዝ በመቻሉ ነው።
ስለዚህ “80 ዓመት ኩራት” ስል በተቋሙ የተቆጠረውን 80 ዓመት ብቻ ማለቴ አይደለም።
80 ዓመት ያልተቋረጠ ብቃት፤
80 ዓመት ተጠብቆ የኖረ ስም፤
80 ዓመት ያልተሸነፈ ተወዳዳሪነት፤
80 ዓመት የተገነባ እምነት ማለቴ ነው።
ላለፉት ሰማንያ ዓመታት ተከብሮ አስከብሮናል።
ሌላው፣ ብዙ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲወራ ያገኛቸውን ሽልማቶች፣ የሚያስመዘግበውን ትርፍ፣ የሚገዛቸውን ዘመናዊ አውሮፕላኖችና የሚደርስባቸውን ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች እንቆጥራለን።
ነገር ግን በሰማንያ ዓመት ታሪኩ ውስጥ አንድ የተዘነጋ፣ ወይም በበቂ ሁኔታ ጎልቶ ያልወጣ ጌጥ ያለው ይመስለኛል።
በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳፋሪዎችን በአንድ ቃል የሚቀበልበትና የሚሸኝበት፤ የኢትዮጵያዊ ትሕትና ተግባራዊ መገለጫ፤ የእኛ የኢትዮጵያውያን የአክብሮትና የመስተንግዶ ባህል ማሳያ፦
“አንቱ!”
“አንቱ…” የሚለው ቃል በጣም አጭር፣ ሲሰሙትም ቀላል ይመስላል። ሆኖም የተሸከመው ሥልጣኔ ትልቅ ነው።
በአማርኛ “አንተ” እና “አንቱ” መካከል ያለው ልዩነት የሰዋስው ልዩነት ብቻ አይመስለኝም፤ የአመለካከት፣ የክብርና የማኅበራዊ ግንኙነት ልዩነትም አለው።
“አንቱ” ማለት፣ “እርስዎ ዋጋ አለዎት” እንደማለት ነው።
“አንቱ” ማለት፣ “የተከበሩ ነዎት” እንደማለትም ነው።
ታዲያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ኢትዮጵያዊ ከበሬታና ትሕትና በየቀኑ ለዓለም አስተዋውቋል፤ አስተምሯል።
አቤት ትሕትና በአየር መንገዱ ሠራተኞች ላይ ሲያምር!
ትሕትና መልክ ቢኖረው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ይመስል ነበር።
በዚህም በየቀኑ የሚሸጠው ቲኬት ብቻ አይደለም፤ ኢትዮጵያዊ የሆነውን፣ እንግዶችን በትሕትና ተቀብሎ በፍቅር የማስተናገድ ባህልንም ጭምር እንጂ!
80 ዓመታት ሙሉ ኢትዮጵያውያን ለሰው ልጅ ክብር የሰጡበትን ባህል በደመና ላይ ሳይቀር ይዞት ሲበር፣ ሲያኮራን ኖሯል።
አዎ! 80 ዓመት ኩራት፤ 80 ዓመት ትሕትና!
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጭ በሌላ በምንም መልኩ እንደዚህ ተገልጦ አላየሁም፤ አልተሰማኝምም!
ዘለዓለማዊ ክብርና ሞገስ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ!
መልካም 80ኛ ዓመት!

የኢዜማ መሪ - እዮብ መሳፍንት ስለምክክሩ!...
የእሁድ ማለዳ ከዕለት ተዕለት ጫና ትንሽ ፋታ ወስደን፣ የወቅቱን ከባድነትና የተሸከምነውን ኃላፊነት የምናስብበት ጊዜ ይሰጠናል።
በተለይም ፍትሐዊት፣ አንድነቷ የተጠበቀና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የሚናፍቁ ሚሊዮኖችን ተስፋና ምኞት ይዘን እንደ ኢዜማ በሀገራዊ ምክክሩ መድረክ ላይ እየተሳተፍን ባለንበት በዚህ ወቅት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል።
አንድ ነገር በግልጽ ላስቀምጥ፤ ኢዜማ ወደዚህ ምክክር የገባው በፖለቲካዊ ንግግር ብቻ ለመሳተፍ ወይም በአጭር ጊዜ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ለመደራደር አይደለም። የመጣነው መሠረታዊና ሥርዓታዊ ለውጥ እንዲመጣ ለመታገል ነው።
ኢዜማ እስከ ምክክሩ የመጨረሻ ቀን ድረስ፣ በማይበገር አቋም የሚከተሉትን ሶስት መሠረታዊ ምሠሦዎች ያራምዳል፦
1. የማንደራደርበት የዜግነት ፖለቲካ፣
ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሙሉ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓታችን ቀዳሚና የማይደፈር መሠረት መሆን አለበት። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለው መብት፣ ክብርና ዕድል በማንነቱ ወይም በሚኖርበት አካባቢ ሊወሰን፣ ሊገደብ ወይም ሊነፈግ ፈጽሞ አይገባም።
2. እውነተኛ ነፃና ገለልተኛ የመንግሥት ተቋማት፣
የፍትሕ አካላት፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የምርጫ ተቋማትና የፀጥታ ኃይሎች ከፖለቲካዊ ወገንተኝነትና ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆን አለባቸው። መንግሥታት ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ። ተቋማት ግን የሕገ መንግሥቱና የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ መሆን አለባቸው።
3. በዘመድ አዝማድና በፖለቲካዊ ወገንተኝነት ሳይሆን በብቃት ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ፣
ሙስናን እንዲሁም በመንግሥት ድጋፍ የተቋቋሙ ገበያን ጠቅልለው የያዙ አካላትንና የጥቅም ትስስርን ማፍረስ ይገባል። ወጣት ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች በግንኙነት ወይም በወገንተኝነት ሳይሆን፣ በብቃታቸው፣ በፈጠራ ችሎታቸውና በትጋታቸው ውጤታማ የሚሆኑበትን ሥርዓት መገንባት አለብን።
አንድ ሀገር በትናንት ግጭቶቿ ታስራ ወደፊት መፈተን አትችልም።
ለኢትዮጵያ ወጣቶች፤ በዚህ የምክክር ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጥነው የመከፋፈልንና የግጭትን አዙሪት ለመስበር፣ ለወደፊት ሕይወታችሁም የሚመጥን ጠንካራ ሀገራዊ ሥርዓት ለመገንባት ነው። ኢዜማ እነዚህ መርሆች የሪፐብሊካችን የዕለት ተዕለት እውነታ እስኪሆኑ ድረስ በጽናት ይቆማል፤ ያለማቋረጥም ይታገልላቸዋል።
የጋራ ዕጣ ፈንታችን ከተከፋፈለው ታሪካችን እጅግ የላቀ ነው። የዜጋ ክብር ፍጹምና የማይደፈር የሆነባትን ኢትዮጵያ በጋራ እንገንባ።
የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ሰላማዊና የማሰላሰል ጊዜ የሞላበት መልካም የእረፍት ጊዜ እንደነበር በመተማመን መጪው ሳምንት ብሩህ እንዲሆንልን እመኛለሁ።
#ኢዜማ

“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) "የሰኔ 15ቱ ክስተት መነሻ አድርጌ የምወስደው ቤዚክሊ ሁለት፣ ከሁለት ጉዳዮች የሆነ ይመስለኛል። አንደኛው ስሁት ግምገማ ነው፤ አንድ ነገር ለማሳካት የምትሰራው ግምገማ በበቂ ዳታ ላይ፣ በበቂ ኢንፎርሜሽን ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ፣ ጉጉት ይቀድምና መሻት ይፈጥርና ወደዚያ ለማድረስ የሚገባህን መንገድ በትክክል ዲዛይን ሳታደርግ ጥፋት ታመጣለህና ስሁት ግምገማ አንዱ ችግር ይመስለኛል። ይሄ እዛ ላይ ያበቃ ሳይሆን ከዛ በኋላም በተደጋጋሚ የምናየው ችግር ነው።
"ሁለተኛው ችግር በሁለት እግር ማነከስ ነው። ለውጥ ተቀብለህ፣ ሀላፊነት ተቀብለህ፣ የህዝብ አደራ ተቀብለህ በሌላ መንገድ ደግሞ ያልተቀደሰ ጋብቻ ከመደበኛ ሀይሎች ጋር አድርገህ እዚሁም እዚያም ለመሆን የሚፈለግ ሁኔታ በአንዳንድ ሰዎች ይታይ ነበረ፤ ያም የፈጠረው ይመስለኛል። ግምገማውም ችግር አለ፣ እንደገና ደግሞ በሁለት እግር ማነከሱም አለ፣ እዚህ ተቀምጦ እዚያ፣ እዚያ ሆኖ ደግሞ እዚህ የመሻቱ ፍላጎት የተቀላቀሉ ነገሮች አሉ። በአንድ መንግስት ወይም በአንድ ፓርቲ እቅድ የሚመራ ስብስብ ሳይሆን፣ እቅዱን ከተለያየ ሶርስ የሚወስድ ሀይል ያለበት፣ ግን በጋራ የሚነጋገር የሚሰበሰብ የሚወያይ፣ በዛ ሂደት ደግሞ ጥፋት ሊያመጣ የሚችል ክስተት ሆኗል።
"እንግዲህ ቅድም ላነሳልህ እንደሞከርኩት የኢትዮጵያ ህዝቦች የመዋሀድ ታሪክ ቢኖራቸውም፣ አብሮ የመዝመት ታሪክ ቢኖራቸውም፣ በዘመናት መካከል ስልጣን ሲመጣ በሀይል፣ አልጋ ሳይጸና የመገዳደል ፍላጎት የባህላችን አንዱ አካል ነው። ልጅ ኢያሱ ዘመን መለስ ብለህ ወደ ታሪክ ብታገላብጥ ይሄን ነገር በቀላሉ ማየት ትችላለህ። በዘመነ መሳፍንት የምንለውን፣ በኋላ 1966 ላይ ያጋጠመውን ብንወስድ የዚሁ ተቀጽላ ነው፣ በደርግ ዘመን 1981 ያየነው መሰል ባህሪ ነው፣ በኢህአዴግ ዘመን መጠኑ ዝቅ ያለ ቢሆንም በ2001 አካባቢ መጠነኛ ፍላጎቶች ተንጸባርቀዋል። በእኛም ጊዜ በሰኔ 2010 16 ላይ ከለውጡ ሁለት ወር ሶስት ወር በኋላ መሰል ሙከራዎች በመስቀል አደባባይ ተካሂደዋል። እዚህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁልጊዜም በሀይል ፍላጎትን ማሳካት፣ በሀይል ስልጣን ለመያዝ መሞከር፣ ሰው በመግደል ስልጣን ለመውረስ መሞከር ነበረ ማለት ነው።
"የሰኔ 15ቱም ከነዚህ ከላይ ከዘረዘርኳቸው ክስተቶች ለየት የሚያደርገው በክልል ደረጃ፣ በከተማ ደረጃ ዝቅ ብሎ ለመፈጸም የተሞከረ ሙከራ ነው። በክልል ደረጃ እንደዚህ ያለውን ጉዳይ ፈጽመህ ምን ታሳካለህ የሚለው ጉዳይ ቅድም ያልኩት የስሁት ግምገማ ውጤት አካል ይመስለኛል። እንዴት ታስታውሰዋለህ እንዴት ይታወሳል አልከው፣ የታሪካችን የጠባሳችን አካል አድርጌ ነው ማስታውሰው።"
- ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አህመድ

''አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡'' ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፳፰ ፤ ፭፡፲፭ ሰዓት
#ethiopia | ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ፣ አዋቂነታቸው እና ትህትናቸው ከገፃቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብስ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር ፡፡
በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሰየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም የጣሊያኖች የጦር ሹማምንት ናቸው፡፡ የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ እራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም “ካህናቱም ሆኑ የቤተ-ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣሊያንን መንግሥት ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን ዐመፁ? ለምን ብቻዋን አፈንጋጭ ሆኑ?” ሲል ጠየቃቸው፡፡
አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መለሱ፡፡ “አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሐላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ” አሉ፡፡
“ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ “አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተ-ክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ ለመሥራት እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ፡፡ ነፃነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን፡፡”
ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣልያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ ፡፡ በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ ፡፡ሐምሌ 22 ሰዓቱም 5፡15 ነበር ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር ፡፡ ታላቅ ፍርሃትም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር፡፡
(ከታሪክ ማህደር አጠር ተደርጎ የቀረበ)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago
በቅጠሉ ንጹህ አየርን የሚፅፍ፣ በሥሩ አፈርን የሚያፀና
ታሪክ ሁልጊዜ በብዕር ብቻ አይጻፍም፤ አንዳንዴ በእጅ የተቆፈረ ትንሽ ጉድጓድ፣ በውስጡ በተተከለ አንዲት ችግኝ እና በላዩ በተጨመረ አፈር ይጻፋል።
ዛፍ የሚተክል ሰው ለዛሬ ብቻ አይሠራም፤ ያላየውን ትውልድ እያሰበ ይተጋል። ከራሱ ዕድሜ የሚረዝም ተስፋን በምድር ውስጥ ያኖራል። ስለዚህ አንድ ችግኝ መትከል አንድ የወደፊት ምዕራፍ መጀመር ነው።
በዚህ ምክንያት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ ዘመቻ ብቻ አይደለም። አንድ ሕዝብ ከተፈጥሮው ጋር የሚያድሰው የታሪክ ውል ነው።
በዚህ ውል ላይ ፈራሚው መንግሥት ብቻ አይደለም። አርሶአደሩ፣ ተማሪው፣ መምህሩ፣ ሠራተኛው፣ ወጣቱ፣ እናት፣ አባት እና ሕፃን ጭምር ናቸው።
ምክንያቱም አካባቢን መጠበቅ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ አደራ ስለሆነ።
በዚህ ዓመት በ"ተስፋ እንትከል" መሪ ሐሳብ የወደፊት ታሪካችንን በራሳችን እጅ የምንቀርጽበት ነው። ምድር የምትለምልመው በዝናብ ብቻ አይደለም። በሰው ኃላፊነት፣ በሰው ራዕይ እና በሰው ፍቅርም ጭምር እንጂ።
ዛፍ ደግሞ ዝም ብሎ የሚቆም ፍጥረት ሳይሆን በዝምታው ብዙ ነገር ይናገራል። በቅጠሉ ንጹህ አየርን ይጽፋል፤ በሥሩ አፈርን ያጸናል፤ በጥላው ሕይወትን ያቅፋል፤ በፍሬው ተስፋን ያበቅላል። ስለዚህ አንድ ዛፍ መትከል የነገን ሕይወት መትከል ነው።
ዛሬ የዓለማችን ፈተና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የደን መመናመን፣ የመሬት መራቆትና የውኃ እጥረት ሆኗል። እነዚህን ችግሮች በንግግር ብቻ መፍታት አይቻልም፤ በተግባር የተደገፈ ኃላፊነት ይፈልጋሉ። የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴም የዚህ ኃላፊነት ሕያው መግለጫ ነው።
የዘንድሮው "ተስፋ እንትከል" መሪ ቃል በውስጡ ጥልቅ ፍልስፍና ይዟል።
ተስፋ አይዘራም፤ ይተከላል እንጂ። ምክንያቱም ሥር ማበጀት አለበት፣ በትዕግሥት ማደግ አለበት፣ ፍሬ ማፍራት አለበት። ልክ እንደ ዛፍ።
በዛፍ የሚጀምር ልማት በሀገር ዘላቂ እድገት ላይ ያለውን እምነት በተግባር ያሳያል።
የዘንድሮው ጉዞ በቁጥርም ሲገለጽ ትልቅ ራዕይን ያሳያል። በ2018 ዓ.ም 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል።
በዚህም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ቀደም ሲል የነበረውን 48 ቢሊየን ችግኞች የመትከል ግብ ወደ 56 ቢሊየን ከፍ አድርጎታል። እነዚህ ቁጥሮች የተቆጠሩ ችግኞችን ብቻ አይወክሉም። የሕዝብ ተሳትፎን፣ የሀገር ቁርጠኝነትን እና ለቀጣይ ትውልድ የሚገነባውን አረንጓዴ ተስፋ ይወክላሉ።
ዘንድሮ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የተከላ መርሃ ግብርም የዚህ ጉዞ ከፍተኛ ምዕራፍ ይሆናል። በመላ ኢትዮጵያ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአንድ ዓላማ ይሰባሰባሉ።
የመደመር መንግሥት አመራሮች፣ የልማት አጋሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተማሪዎች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች በጋራ ይሳተፋሉ።
ይህ ለሀገር አንድ የጋራ ዓላማ ሲኖር ልዩነቶች ከአንድነት ፊት እንደሚያንሱ የሚያሳይ ተጨባጭ ምሳሌ ነው። ምክንያቱም የዛሬው ችግኝ የነገው ደን ነው፤ የዛሬው አሻራ ደግሞ የኢትዮጵያ የወደፊት ታሪክ ነው።

የአገሪቱን የመስኖ ሽፋን ወደ 2.6 ሚሊዮን ሄክታር ለማድረስ የተያዘው ግብ እመርታ እያሳየ መሆኑ ተገለጸ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
መግለጫ እነሆ ፥
#ethiopia | አገራዊ የመስኖ ልማት ጉዞ ተስፋ ሰጪ እመርታ የኢትዮጵያ በመስኖ የመልማት አቅሟን፤ ለመጠቀምና ተፈጥሮ የለገሰቻትን ውሃ፣ መሬት፣ ምቹ የአየር ሁኔታ እንደዚሁም አምራች የሰውሃይል በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሏ ለዘመናት የራሷን የምግብ አቅርቦት እንኳን መሸፈን ሳትችልና በችግር ወቅት ለዕርዳታ ወደ ውጪ ስታማትር መኖሯ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነው፡፡
ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜያት ያስተዳደሩ መንግስታት ምርታማነት ለማሳደግ ያስችለናል ያሏቸውን የተለያዩ ሙከራዎች በመከተል ጥረት ቢያደርጉም በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ አገራችን የራሷን የምግብ አቅርቦት መሸፈን ሳትችል፣ በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ በማውጣት ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የምግብ ምርቶችን ከውጭ ስታስገባ ኖራለች።
እንደ ሃገር ሰፋፊ የመስኖ ፕሮጀክቶች ከ1960ዎቹ ጀምሮ መተግበር ቢጀምሩም ቁጥራቸው እጅግ ጥቂትና ውጤታቸውም በዛው ልክ ውስን እንደነበር በመስኩ የተደረጉ የዳሰሳዎች ጥናቶች ያሳያሉ ፡፡ ለአብነትም ለስኳር ልማት የተገነቡ ፕሮጀክቶች እንደ ወንጂ፣ መተሃራ፣ ፊንጫ ፣ የአሚባራ፣ የአልዌሮ፣ የጎዴ፣ የተንዳሆ እና የከሰም መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠቃሾች ቢሆኑም በትግበራ ሂደት ግን ለአመታት ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ውጤታማ ሳይሆኑ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
ይህንን አዙሪት በመስበርና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ከተፈጥሮ ዝናብ ባሻገር የከርሰ-ምድርና የገጸ-ምድር ውኃን በአግባቡ በመጠቀም መስኖን ማስፋፋት ወሳኝ ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም ባለፉት የለውጥ አመታት የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ የተለመደና ፈተና የሆነ አዙሪት ለመላቀቅ የሚያስችሉ የተለያዩ እቅዶችን አዘጋጅቶ እና ዘርፉን ራሱን በቻለ ሚኒስቴር መስራቤት ደረጃ በማደራጀት አዲስ የፖሊሲ መር የልማት ጥረትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መስራት ጀምሯል፡፡
መንግስት የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ከወሰዳቸው ወሳኝ እርምጃዎች መካከል የመስኖ ልማት ዘርፍን ውጤታማ በሆነ መንገድ በማሻሻል ምርታማነትን ማሳደግ እንዲቻል ዘርፋ ለአጠቃላይ አገራዊ እድገት የሚኖረውን ሚናም በልዩ ትኩረት ለማሳደግ እንዲያስችለው መስኖ በጥናት በተለዩ ቦታዎች ላይ በልዩ ትኩረት እንዲያስፋፋ በማለም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርን በ2014 ዓ/ም እንዲቋቋም አድርጓል፡፡ በዚህም የአገር አቅም በፈቀደ ልክም መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ በጀት እንዲመደብለት እና በዘርፉ ተግባራዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችሉ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማትን ወደ ተቀናጀ የልማት አቅጣጫ በመምራት፤ ሀገራችን ያላትን ከፍተኛ የውሃና ሰፊ የመሬት ሀብት ማዕከል በማድረግ፤ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት እና በቆላማ አካባቢ የሚገኘውን እምቅ የልማት ፀጋዎችን በማጥናትና ለአርብቶአደሩና ከፊልአርብቶአደሩ ጥቅም እንዲዉል በማድርግ የሀገራችንን የምግብ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል መተግበር የጀመራቸውም ስራዎች አመርቂ ውጤቶች ማሳየት ጀምረዋል፡፡
መስሪያ ቤቱ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስጠናትና በመገንባት፤በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በክልሎች የሚገቡ አነስተኛ መስኖዎችን በመከታተልና ድጋፍ በመስጠት በሃገሪቱ ምርትና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያስቻሉ ተግባራትን መጀመሩም ከወዲሁ መታዘብ ይቻላል፡፡
በተለይ ደግሞ ባለፋት ሁለት የበጀት አመታት ማለትም በ2017 እና 2018 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈጻጸም ዙርያ የተከናወኑ ስራዎች በአጠቃላይ በዘርፋ የሚታዩ ጅምር ሙከራዎችን ወደ አዲስ ታሪክ ያሸጋገረ ምዕራፍ ላይ መድረሱን መታዘብ ይቻላል።
ዘርፋ ከተሰጠው ልዩ ትኩረትና በአገር አቀፍ ደረጃ የመስኖ ልማት ጥያቄዎች መበራከት ከጅምሩ በቂ ጥናቶችና የዲዛይን ስራዎች ጥልቅ የበጀት ዝግጅትና በከፍተኛ የህዝብና የመንግስት አመራር ማእቀፎች በቂ ውይይት ተደርጎባቸው እንዲሁም የአፈጻጸም ስጋቶችና በተለይም ከአጠቃላይ የበጀት ዝግጅቶች አንጻር በነበሩ ውስንነቶች ጉልህ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በፍጥነት በመመካከር መሰረታዊ የማጣጣም ስራዎች መከወን በመቻሉ በርካታ ስራዎችን በተከታታይ ወራት በስኬት ሐዲድ ለማስጓዝ ተችሏል።
በዚህም በነዚህ ሁለት አመታት ለበርካታ አመታት ግንባታቸው የተጓተቱ ፣ የዲዛይን ስራ ጉድለቶች የነበሩባቸው ተጠናቀውም ለረጅም ጊዜ ጥገና ያልተደረገላቸው እና ከፍተኛ ብልሽት አጋጥሟቸው የነበሩ ፕሮጀክቶችን ቁርጠኛ በሆነ የፕሮጀክት አመራር ክትትል እና ጥብቅ የኮንትራት አስተዳደር ስርዓትን መሰረት በማድረግ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
ለዚህ ስኬት ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንም መንግስት የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ያለውን ፅኑ ፍላጎትና እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ድጋፍ ከግንዛቤ በማስገባት ይህንንም በሚመጥን መልኩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በጥራት በፍጥነት እና የኮንትራት ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ የሰጠው በሳል አመራርም ተጠቃሽ ምክንያት ነው።
በዚህም ምክንያት ለአመታት የዘገዩና የማህበረሰባችን የአመታት የቅሬታ ምንጨ ሆነው የኖሩትን በአጠቃላይ 10 የሚሆኑ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በአጭር ግዜ ከውስብስብ ችግሮች በማላቀቅ በልዩ ትኩረት ቅድሚያ በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት በተፋጠነ ጊዜ እንዲጠናቀቁ ጥረት ተደርጓል።
እነዚህም የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የማልማት አቅማቸው እና ተጠቃሚ የሚያደርጉት እማና አባ ወራወዎች በቅደም ተከተላቸው መሰረት የሚከተሉት ናቸው ፡-
1.ጊዳቦ ሎት 2 - የማልማት አቅሙ- 13420 ሄ/ር 26840 እማ/አባወራዎች
2. ጎዴ -የማልማት አቅሙ -10,000 ሄ/ር 20000 እማ/አባወራዎች
3. ወልመል ሎት 1 እና 2 – 12040 ሄ/ር -24080 እማ/አባወራዎች
4. ጨልጨል ሎት 2- 4145 ሄ/ር 8290 እማ/አባወራዎች
5.የቄጦ መስኖ 5000 ሄ/ር 10,000 እማ/አባወራዎች
6. የታችኛው ርብ -3200 ሄ/ር 6400 እማ/አባወራዎች
7. የተንዳሆ - 60,000 ሄ/ርያለማል 120,000 እማ/አባወራዎች
8. የከሰም መስኖ -20 ሺኅ ሄ/ር 40,000 እማ/አባወራዎች
እንዲሁም አርጆ ዲዴሳ እና መገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች መሠረታዊ የግንባታ ሥራቸው አልቆ የማጠናቀቂያ ሥራቸው እየተፋጠነ ከመሆኑም በላይ በቅርቡ በክብር የሚመረቁ ይሆናል፡፡
መገጭ እና አርጆ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ የ10ሩ ፕሮጀክቶች ብቻ ድምር የማልማት አቅማቸው 224,805 ሄክታር ሲሆን 450,000 እማና አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚደርጉ ናቸው፡፡
በሌላ በኩል እንደ ጨልጨል (ሎት1) አጂማጫጫ፣ ካሊድ ዲጆ፣ ሎጊያ፣ ላይኛው ጉደር፣ አንገር ፣ ፈንታሌ፣ ወይቦ፣ ላይኛው ርብ፣ ሽንሌ፣ እና አደኣ በቾ የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዕቅዳቸው መሠረት የግንባታ ስራዎቻቸው እየተከናወ ባጠናቀቅናቸው የመስኖ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን በማልማት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጁ ስራዎች በመተግበር ላይ እንገኛለን፡፡
መንግስት ለመስኖ ልማቱ ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በተሰሩ ስራዎች ከለውጡ በፊት 490 ሺህ ሄክታር የነበረው የመስኖ ሽፋን ወደ 2.6 ሚሊዮን ሄክታር ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡ አሁን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችም ሲጠናቀቁ የአገራችን የመስኖ ሽፋን በከፍተኛ መጠን የሚጨምር ይሆናል፡፡ እነዚህ መሰረተ ልማቶችም የተጀመረውን የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት በማረጋገጥ ረገድ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
በ2017 እና በ2018 በጀት አመት ፕሮጀክቶች አጠናቅቀን ለስኬት ስንበቃ ፤ ግንባታዎች ባቀድነው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ስያደርጉ የቆዩትን፣ እንደዚሁም በቀጣይነትም ስራን ሊያስጓጉሉ የሚችሉትን ቁልፍ ማነቆዎች በጥናት በመለየት ውስብስብ ለሆኑና ለቆዩ ችግሮች ተገቢ እና ህጋዊ መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ሚናቸው ትልቅ ነው፡፡
በመሆኑም ይህ ፈጣን የፕሮጀክት አፈጻጸም እና ክትትል በቀላሉ የተገኘ እንዳልሆነ መገንዘብ ያሻል።
ለመሆኑ በእነዚህ የግንባታ 2 አመታት እንደማንኛውም የኮንስትራክሽን ዘርፍ የመስኖ ግንባታ ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የተሰጣቸው መፍትሔዎችስ ?
በግንባታ ሂደቱ ያጋጠሙንን ተጠባቂና ተጠባቂ ያልሁኑ ተግዳሮቶች ተወጥተን የግንባታ ስራችንን ስናከናውን በግንባታ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ያሳደሩ ዋና ዋና ተግዳሮቶችን የሚከተሉት ናቸው፦
* የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ከውኃ ጋር የተቆራኙና በካበተ የዘርፍ ጥናት የተደገፋ መሆን የሚገባቸው በመሆናቸው በዘርፉ ልምድ ያላቸው በቂ አገር በቀል የአማካሪና ተቋራጮች አቅም በበቂ አለመኖሩ ከጅምሩ የታዩ ተግዳሮቶች ነበሩ:: በተጨማሪም አብዛኞቹ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑት በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሲሆን ተቋማቱ በዘርፋ ለሚደረግ የመሰረተ ልማት ግንባታ የነበራቸው ልምድና አቅምም ውስን ከመሆኑም በላይ ከግሉ ዘርፍ የሚሳተፉት በጣት የሚቆጠሩ ተቋማትም ገና አጥጋቢ ቁመና ያልነበራቸው መሆኑ።
* የበጀት እጥረትና የገንዘብ አቅርቦት መዘግየት፦ ፕሮጀክቶቹ ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቁ ቢሆንም በየዓመቱ የሚመደበው በጀት አነስተኛ መሆኑና የተፈቀደው በጀትም በወቅቱ ጥሬ ገንዘብ ሆኖ ባለመለቀቁ ከክፍያዎች መስተጓጎል የተነሱ መጓተቶችና የዋጋ ንረት ፕሮጀክቶች በሚፈለገው ደረጃ ማከናወን አለመቻሉ፣
* ከፍተኛ የገበያ የዋጋ ንረት (Market Inflation)፦ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍና አገር ውስጥ ሁኔታዎች ምክንያት እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ነዳጅ እና የጉልበት ዋጋ ላይ በየግዜው ከፍተኛ ጭማሪ ማጋጠሙ። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክት በዘገዩ ቁጥር ወጪዎቻቸው በየግዜው እንዲጨምሩ ምክንያት ሆነዋል ::
* የስትራቴጂካዊ ግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት እጥረት፦ ሲሚንቶ፣ ብረትና ነዳጅ በገበያ ላይ በበቂ ሁኔታ በወቅቱ አለመገኘታቸው የግንባታውን ፍጥነት በእጅጉ ገድበውት ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቶች በእቅዳቸው ልክ እንዳይከወኑ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ::
* የግድብ እና መስኖ መሰረተ ልማቶች ዲዛይን ስራዎች ጉልህ ክፍተቶችና ያጋጠሙ የጂኦሎጂካል ውስብስብነት ችግሮች :: ምንም እንኳን ፕሮጀክቶች መነሻ የሚሆኑ ጥናትና ዲዛይን ተሠርቶባቸው ቢጀመሩም፣ በትግበራ ወቅት በሚያጋጥሙ የመሬት አቀማመጥና የጂኦሎጂካል ይዘቶች ምክንያት የዲዛይን ክለሳዎችን ማድረግ የግድ ማስፈለጉ የውል ማሻሻያዎችንና የጊዜ ማራዘሚያዎችን እንዲደረጉ የግድ የሚያስብሉ ሁኔታዎች አጋጥመዋል ::
በዚህም ምክንያት ለሚኖሩ ለውጦች ተጨማሪ የኮንትራት ወጪ እና ግዜ መጠየቃቸው የግድ ሆኗል።
የተወሰዱ ስልታዊና መዋቅራዊ የማስተካከያ እርምጃዎች የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ያጋጠሙትን የአሠራር ክፍተቶች፣ የኦዲት ግኝቶችና የባለድርሻ አካላትን አስተያየቶች እንደ ግብዓት በመውሰድ ሰፊ ተቋማዊ ለውጥ (Institutional Reform) አድርጓል።
በዚህም መሠረት የተወሰዱት ቁልፍ ተቋማዊ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
* ልዩ የፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በአዲስ መልክ በ2017ዓ/ም ተቋቁሟል ፦ከዋናው መሥሪያ ቤት እስከ ፕሮጀክት ሳይት የነበረውን የቁጥጥር እና ክትትል ለማጥበቅና የውል አስተዳደር እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓቱን (Contract Administration & Construction supervision) በዲጂታል ፕላትፎርም ጭምር ለማዘመን ዘርፈ-ብዙ ብቁ ባለሙያዎችን ያቀፈ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቁሟል።
* ጥብቅ የክትትልና ግምገማ (M&E) ሥርዓት መዘርጋት፦የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ወርሃዊ፣ ሩብ ዓመት፣ ግማሽ ዓመት እና ዓመታዊ የክትትልና የመስ ክምልከታ ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ ሆኗል።
* በኮንትራት ስምምነት መሰረት ለፕሮጀክቶች ክትትል የሚያስፈልገውን ሎጅስቲክስ እንዲሟላ ተደርጓል፥- በአዲስ መልክ ለተደራጀዉ ፕሮግራም ጽ/ቤት ከማዕከል እስከ ፕሮጀክት ሳይት ለተመደቡ የስራ መሪዎችና ሙያተኞች የሚያስፈልጉ የመስክን ነባራዊ ሁኔታ የሚቋቋሙ የመስክ ተሽከርካሪዎች እና የቢሮ ቁሳቁሶችን በኮንትራት ስምምነት ውስጥ በተቀመጠው መሰረት በማሟላት የክትትል አመራሮች እና ባለሙያዎች በተቀናጀ መልኩ ጉልበታችዉና እውቀታቸዉን ለፕሮጀክቶቹ ስኬት የሚያውሉበትን ሁኔታ በመፍጠር በጊዜና በጥራት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ውጤታማ ስራ እየተመዘገበ ይገኛል::
* የቁሳቁስ አቅርቦት ሰንሰለትን ማሳለጥ (Supply Chain Optimization)፦ የሲሚንቶ እና የነዳጅ እጥረትን ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ በቀጥታ ከአምራች ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች ጋር ስልታዊ ትስስር በመፍጠር የግንባታ ግብዓቶች ሳይቆራረጡ ፕሮጀክት ሳይት ላይ እንዲቀርቡ አድርጓል።
* ባለሦስት ወገን ስምምነት (Tri-party Agreement) መተግበር፦ በተቋራጭ፣ በአማካሪ መሐንዲስ፣ በባለቤት(ሚኒስቴሩ) እና በቁሳቁስ አቅራቢዎች መካከል የተቀናጀ የጋራ መግባቢያ ስምምነት በመፈረም ሥራዎች በተቀመጠላቸው ወሰን፣ በጀትና ጥራት ኮንትራት መሰረት አድርገው እንዲከናወኑ ተደርጓል።
* አዳዲስ መመሪያዎችና ስታንዳርዶች ማዘጋጀት፦ ወደፊት ለሚከናወኑ ማናቸውም ግንባታዎች መነሻ የሚሆኑ የፕሮጀክት አስተዳደርን የሚያዘምኑ አዳዲስ የአሠራር ደንቦችና መመሪያዎች ተዘጋጅተዋል።
* የዋጋ ማስተካከያ መፍቀድ፦ አገር በቀል ተቋራጮች ፕሮጀክቶች በወቅቱ መጠናቀቅ ባለመቻላቸው ያጋጠመውን የዋጋ ንረት በራሳቸ መቋቋም ባለመቻላቸው፣ በመንግስት የተቀመጡ አሠራሮችን በመከተል ቀደም ሲል የዋጋ ማስተካከያን ይከለክሉ የነበሩ ውሎችን ከ2013 ጀምሮ በተሰጠው የመንግስት ውሳኔ መሰረት ውሎችን በማሻሻል የዋጋ ማስተካከያ በሃገር ደረጃ እንዲደረግ ፈቅዷል።
* የበጀት እጥረትና የገንዘብ አቅርቦት መዘግየትን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት በመወያየት እና በመስራት አስፈላጊው በጀት እና ጥሬ ገንዘብ በወቅቱ ለመስኖ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲለቀቁ ማድረግ ተችሏል፡፡
የመስኖ ፕሮጀክቶች እንደ ማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክቶች መንግስት ባወጣው የግዥ መመሪያዎች፣ ደንቦች እና ውሎች የሚተዳደሩ ናቸው :: የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መ/ቤት ከሌሎች ተቋማት የተረከባቸውንም ሆነ በራሱ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች የሚያስተዳድረው የመንግስትን ህግና ስርአትን በማክበር በኮንትራት ውል ስምምነት መሰረት ብቻ ነው፡፡
በዚህም መሰረት በየግዜው ልዩ ፍቃድ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙም በህግ የመፍቀድ መብት ያለውን የመንግስት አካል ፍቃድ በማግኘት ብቻ የተፈፀሙ ስራዎችን መከወን ተችሏል ፡፡
ከመስኖ ፕሮጀክቶች ውስብስብ ባህሪ በመነሳት በተቻለ መጠን ባሉ ሀገራዊ አቅሞች እና ልምድና አቅም ባላቸው አማካሪ ድርጅቶች ዝርዝር ጥናትና ዲዛይን ሳይሰራ የመስኖ ፕሮጀክቶች አይጀመሩም፡፡ ሆኖም በትግበራ ወቅት የዲዛይን ክፍተቶች መኖራቸው ሲታወቅ በተቀመጠው የውል አስተዳደር ስምምነት መሰረት የፕሮጀክቶች የዲዛይን ችግር እንዲፈታ በማድረግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በዲዛይን
ማሻሻያው መሰረት እንዲቀጥሉ እና እንዲጠናቀቁ ይደረጋሉ፡፡
ምንም እንኳን የዲዛይን ክፍተቶች ችግር ደረጃ ቢለያይም ፕሮጀክቶች በተግባር የዲዛይን ክፍተቶች እንደሚያጋጥማቸው ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶች ውል አስተዳደር አንፃርም ተቋራጭ እና አማካሪ ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ብቻ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ውሎችን ያስተዳድራል በዚህም የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤትም ይህንኑ ሀቅ ያረጋግጣል። በመሆኑም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከውል ውጪ የሚፈፀሙ ምንንም አይነት ግዥዎችና ጭማሪዎችም የሉም።
አለማቀፍ ልምዶች እንደሚያሳዩት ማንኛውም ፕሮጀክት ተግባራዊ በሚደረግባት ወቅት በገቢያ ሁኔታ ለሚከሰቱ የዋጋ ጭማሪዎች ተገቢውን አሰራር እና ኮንትራት ስምምነትን በመከተል የሚፈቀዱ የዋጋ ማስተካከያዎችን በማድረግ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
በአገራችን ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ የግንባታ ግብአቶች በመጨመሩ፣የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ እና በአለማቀፍ ሁኔታዎች መለዋወጥ ምክንያት የግንባታ ሴክተሩ በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ ገብቶ ቆይተው የነበሩ ፕሮጀክቶች በመኖራቸውም እስካሁንም ከተመሳሳይ ችግሮች ሙሉ በሙሉ ለማገገም የሚያስችል ስራ መስራትም ቀጣይ የቤት ስራችን ይሆናል፡፡
በዚህም ምክንያት አገር በቀል ተቋራጭ ድርጅቶች የተከሰተውን የግንባታ ግብአቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በራሳቸው መቋቋም እንዳቃታቸው መንግስት በመገንዘቡ የተቀመጡ አሰራሮችን በመከተል የዋጋ ማስተካከያ እንዲደረግ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቀደም ሲል የዋጋ ማስተካከያ ይከለክሉ የነበሩ ውሎችን በማሻሻል የዋጋ መስተካከያ መፍቀድ እና ተግባራዊ ማድረግ ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የሚያስገኘውን ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት በተሰጠው ፍቃድ መሰረት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያ በዝናብ ጥገኝነት ላይ የተመሠረተውን የግብርና ክፍለ-ኢኮኖሚ ወደ መስኖ መርና አስተማማኝ ምርታማነት ለመቀየር የጀመረችውን ጉዞ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው አሁን የተጀመሩት ተቋማዊ ሪፎርሞች እና ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ወደ ውጤት የመቀየር ጅምሮች ቀጣይነት ሲኖራቸው ብቻ ነው። ይህንን ለማደናቀፍና ኮንትራትና ፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓትን በአግባቡ መረዳት ባቃታቸው ወይም ሆን ተብሎ ሂደቶችን ለማጠልሸት የሚሰሩ ስራዎች በፍፁም ተቀባይነት ሊኖራቸው አይችሉም ::
እንደሚታወቀው ሃገራችን በተለያዩ ሴክተሮች አስደናቂ የሆኑ ስኬቶችን እያስመዘገበች ትገኛለች፡፡ ከዚህ አንጻር እንደ ሃገር የምናስመዘግባቸው ስኬቶች ለህዝባችንን እና ለአጋሮቻችን የሚሰጠው ትርጉም ትልቅ የመሆኑን ያህል ይህ ጅምር እመርታ የማያስደስታቸው በከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት እና የአጋሮች ጥረት የተገኙ ውጤቶች የሚያቅራቸው ሀይላት መኖራቸው ግን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመስኖ ዘረፍ እየተገኘ ያለውን ስኬት ለመገንዘብና እውቅና ለመስጠት ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ይህንን ሁኔታ ወደ ጎን በመተው የተቋቋመለትን አላማ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉአላዊነት እና የህዝብ ጥቅም ታሳቢ በማድረግ በዘርፉ የሚገኙ አሰራሮችንና ህጎችን መሰረት በማድረግ በሃገሪቱ የጀመራቸውን በውጤት የታጀበ የመስኖ ፕሮጀክቶች የማጠናቀቅ ድሎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ለኢትዮጵያ የምግብ ሉኣላዊነት መረጋገጥ እንሰራለን!!
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚንስቴር
ሃምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

በሰማይ ላይ ለሚያንዣብቡ አሞራዎች የማይበተን የኢትዮጵያ አንድነት
*********************
(የዕለቱ መልዕክት)
የኢትዮጵያ ታሪክ የትግል፣ የጽናት እና የጥልቅ ኅብረት ደማቅ ሸራ ነው።
ይህች ሀገር በታሪኳ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፋለች፤ ሆኖም የገዛ ልጆቿ በውስጣዊ አለመግባባት ክፍተት በፈጠሩ ቁጥር፣ ታሪካዊ ጠላቶቿ አጋጣሚውን ሲጠብቁና ሲያደቡ መኖራቸው የዘመናት ሐቅ ነው።
ይህ እውነት ዛሬም መልኩን ቀይሮ፣ በዘመናዊ የጂኦፖለቲካ ትርክት ተጠቅልሎ በደጃፋችን ቆሟል።
ሀገራዊ የልማት ውጥኖችን ስንጀምር፣ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ስንገነባና ከተሞቻችንን ስናዘምን ድምጻቸው የማይሰማ፣ አንዳች አስተዋጽኦ የማያደርጉ የውጭ ኃይሎች፣ በውስጣዊ ልዩነቶች ስንፋጠጥ ግን ከየት መጡ ሳይባሉ የጣልቃ ገብነት እጃቸውን ሲዘረጉ፣ የጥፋት መሣሪያና የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ ሲያቀብሉ ማየት የተለመደ ሆኗል።
እንደ ሀገር ትልቁ ፈተናችንና ድክመታችን የሚመነጨው ከራሳችን የውስጥ ክፍተት ነው። ከጉንደት እስከ ጉራ፣ ከዓድዋ እስከ ማይጨው፣ ከካራማራ እስከ ባድመ ያለውን ታሪካችንን ስንፈትሽ፤ ጠላቶቻችን ሁልጊዜም የሚንቀሳቀሱት የእኛን መነታረክ ተከትለው ነው።
ታላቋን ሀገር የጂኦግራፊ እስረኛ ያደረጋት፣ የባለቤትነት መብቷን የነጠቃትና ቀይ ባሕርን የመሰለ ስትራቴጂያዊ ሀብት ያሳጣን ይኸው የውስጥ መከፋፈል ያመጣው የታሪክ ስህተት ነው።
ዛሬም ቢሆን የትኛውም የውስጥ ጉዳይ ቢያከራክረን መፍትሔው በእኛው መካከል በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር መፈታት አለበት።
ለውጭ ኃይሎች መጠቀሚያ የሚሆን ቀዳዳ መክፈት፣ በታሪክ ፊት እንክርዳድ ሆኖ ከመታየትና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት የተለየ ትርጉም የለውም።
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት፣ የሀገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ ትርታና የሉዓላዊነት አቋም በጥልቅ የሚያንጸባርቅ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጠንባሮ አባቶች የከብትና የአሞራ ብሂል በሚገርም አገላለጽ መስለውታል።
"በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ለሚያንዣብቡ አሞራዎች ያለኝ መልዕክት ከብቱን መርጠን የምንገዛ እኛ ነን፤ የቅርጫውን ባለቤት የምንወስን እኛ ነን፤ የተረፈንን፣ የማንፈልገውን ካልሆነ በቀር የትኛውም አሞራ በጉልበት ከየትኛውም ቅርጫ መደብ ላይ አንዲት ኪሎ ስጋ መውሰድ እንደማይችል ላረጋግጥላቸው እፈልጋለሁ" በማለት የማያወላዳ አቋማቸውን አስረግጠው ተናግረዋል።
ይህ ጥልቅ መልዕክት ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን ሙሉ መብት እንዳላት እና ማንም በጉልበት ሊነጥቃት የሚችለው ሀብትም ሆነ ጥቅም እንደሌለ የተላለፈ ግልጽ መልዕክት ነው።
በመሆኑም በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የሚያንዣብቡ ዘመናዊ "አሞራዎች" ሊገነዘቡት የሚገባ አንድ ሐቅ አለ። ኢትዮጵያ በቀላሉ የምትበጠስ፣ በውጭ ፕሮፓጋንዳ ጫጫታ የምትዘናጋና ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፋ የምትሰጥ ደካማ ሀገር አይደለችም።
ለዘመናት በማይበጠስ ጠንካራ ገመድ የተሰናሰለች፣ የጸናች ሀገር ናት። የውጭ ኃይሎች የሀገራችንን እውነተኛ የጥንካሬ ታሪክ ወደ ኋላ መለስ ብለው በማንበብ፣ ከጣልቃ ገብነት ምኞታቸው ታቅበው ለጋራ ጥቅም በጋራ ለመሥራት ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው።
እኛም ኢትዮጵያውያን፣ የውስጥ ልዩነቶቻችንን በሠለጠነ የውይይት መንገድ እየፈታን፣ ሀገራችንን ከሚያንዣብቡ ታሪካዊ ጠላቶች በኅብረት ልንጠብቃት ግድ ይለናል። ያደፈጠው አሞራ ስሌት የሚከሽፈው፣ የእኛ ውስጣዊ አንድነት ሲጸና ብቻ ነውና።

Comments