የአገሪቱን የመስኖ ሽፋን ወደ 2.6 ሚሊዮን ሄክታር ለማድረስ የተያዘው ግብ እመርታ እያሳየ መሆኑ ተገለጸ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
መግለጫ እነሆ ፥
#ethiopia | አገራዊ የመስኖ ልማት ጉዞ ተስፋ ሰጪ እመርታ የኢትዮጵያ በመስኖ የመልማት አቅሟን፤ ለመጠቀምና ተፈጥሮ የለገሰቻትን ውሃ፣ መሬት፣ ምቹ የአየር ሁኔታ እንደዚሁም አምራች የሰውሃይል በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሏ ለዘመናት የራሷን የምግብ አቅርቦት እንኳን መሸፈን ሳትችልና በችግር ወቅት ለዕርዳታ ወደ ውጪ ስታማትር መኖሯ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነው፡፡
ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜያት ያስተዳደሩ መንግስታት ምርታማነት ለማሳደግ ያስችለናል ያሏቸውን የተለያዩ ሙከራዎች በመከተል ጥረት ቢያደርጉም በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ አገራችን የራሷን የምግብ አቅርቦት መሸፈን ሳትችል፣ በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ በማውጣት ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የምግብ ምርቶችን ከውጭ ስታስገባ ኖራለች።
እንደ ሃገር ሰፋፊ የመስኖ ፕሮጀክቶች ከ1960ዎቹ ጀምሮ መተግበር ቢጀምሩም ቁጥራቸው እጅግ ጥቂትና ውጤታቸውም በዛው ልክ ውስን እንደነበር በመስኩ የተደረጉ የዳሰሳዎች ጥናቶች ያሳያሉ ፡፡ ለአብነትም ለስኳር ልማት የተገነቡ ፕሮጀክቶች እንደ ወንጂ፣ መተሃራ፣ ፊንጫ ፣ የአሚባራ፣ የአልዌሮ፣ የጎዴ፣ የተንዳሆ እና የከሰም መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠቃሾች ቢሆኑም በትግበራ ሂደት ግን ለአመታት ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ውጤታማ ሳይሆኑ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
ይህንን አዙሪት በመስበርና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ከተፈጥሮ ዝናብ ባሻገር የከርሰ-ምድርና የገጸ-ምድር ውኃን በአግባቡ በመጠቀም መስኖን ማስፋፋት ወሳኝ ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም ባለፉት የለውጥ አመታት የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ የተለመደና ፈተና የሆነ አዙሪት ለመላቀቅ የሚያስችሉ የተለያዩ እቅዶችን አዘጋጅቶ እና ዘርፉን ራሱን በቻለ ሚኒስቴር መስራቤት ደረጃ በማደራጀት አዲስ የፖሊሲ መር የልማት ጥረትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መስራት ጀምሯል፡፡
መንግስት የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ከወሰዳቸው ወሳኝ እርምጃዎች መካከል የመስኖ ልማት ዘርፍን ውጤታማ በሆነ መንገድ በማሻሻል ምርታማነትን ማሳደግ እንዲቻል ዘርፋ ለአጠቃላይ አገራዊ እድገት የሚኖረውን ሚናም በልዩ ትኩረት ለማሳደግ እንዲያስችለው መስኖ በጥናት በተለዩ ቦታዎች ላይ በልዩ ትኩረት እንዲያስፋፋ በማለም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርን በ2014 ዓ/ም እንዲቋቋም አድርጓል፡፡ በዚህም የአገር አቅም በፈቀደ ልክም መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ በጀት እንዲመደብለት እና በዘርፉ ተግባራዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችሉ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማትን ወደ ተቀናጀ የልማት አቅጣጫ በመምራት፤ ሀገራችን ያላትን ከፍተኛ የውሃና ሰፊ የመሬት ሀብት ማዕከል በማድረግ፤ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት እና በቆላማ አካባቢ የሚገኘውን እምቅ የልማት ፀጋዎችን በማጥናትና ለአርብቶአደሩና ከፊልአርብቶአደሩ ጥቅም እንዲዉል በማድርግ የሀገራችንን የምግብ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል መተግበር የጀመራቸውም ስራዎች አመርቂ ውጤቶች ማሳየት ጀምረዋል፡፡
መስሪያ ቤቱ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስጠናትና በመገንባት፤በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በክልሎች የሚገቡ አነስተኛ መስኖዎችን በመከታተልና ድጋፍ በመስጠት በሃገሪቱ ምርትና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያስቻሉ ተግባራትን መጀመሩም ከወዲሁ መታዘብ ይቻላል፡፡
በተለይ ደግሞ ባለፋት ሁለት የበጀት አመታት ማለትም በ2017 እና 2018 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈጻጸም ዙርያ የተከናወኑ ስራዎች በአጠቃላይ በዘርፋ የሚታዩ ጅምር ሙከራዎችን ወደ አዲስ ታሪክ ያሸጋገረ ምዕራፍ ላይ መድረሱን መታዘብ ይቻላል።
ዘርፋ ከተሰጠው ልዩ ትኩረትና በአገር አቀፍ ደረጃ የመስኖ ልማት ጥያቄዎች መበራከት ከጅምሩ በቂ ጥናቶችና የዲዛይን ስራዎች ጥልቅ የበጀት ዝግጅትና በከፍተኛ የህዝብና የመንግስት አመራር ማእቀፎች በቂ ውይይት ተደርጎባቸው እንዲሁም የአፈጻጸም ስጋቶችና በተለይም ከአጠቃላይ የበጀት ዝግጅቶች አንጻር በነበሩ ውስንነቶች ጉልህ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በፍጥነት በመመካከር መሰረታዊ የማጣጣም ስራዎች መከወን በመቻሉ በርካታ ስራዎችን በተከታታይ ወራት በስኬት ሐዲድ ለማስጓዝ ተችሏል።
በዚህም በነዚህ ሁለት አመታት ለበርካታ አመታት ግንባታቸው የተጓተቱ ፣ የዲዛይን ስራ ጉድለቶች የነበሩባቸው ተጠናቀውም ለረጅም ጊዜ ጥገና ያልተደረገላቸው እና ከፍተኛ ብልሽት አጋጥሟቸው የነበሩ ፕሮጀክቶችን ቁርጠኛ በሆነ የፕሮጀክት አመራር ክትትል እና ጥብቅ የኮንትራት አስተዳደር ስርዓትን መሰረት በማድረግ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
ለዚህ ስኬት ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንም መንግስት የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ያለውን ፅኑ ፍላጎትና እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ድጋፍ ከግንዛቤ በማስገባት ይህንንም በሚመጥን መልኩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በጥራት በፍጥነት እና የኮንትራት ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ የሰጠው በሳል አመራርም ተጠቃሽ ምክንያት ነው።
በዚህም ምክንያት ለአመታት የዘገዩና የማህበረሰባችን የአመታት የቅሬታ ምንጨ ሆነው የኖሩትን በአጠቃላይ 10 የሚሆኑ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በአጭር ግዜ ከውስብስብ ችግሮች በማላቀቅ በልዩ ትኩረት ቅድሚያ በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት በተፋጠነ ጊዜ እንዲጠናቀቁ ጥረት ተደርጓል።
እነዚህም የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የማልማት አቅማቸው እና ተጠቃሚ የሚያደርጉት እማና አባ ወራወዎች በቅደም ተከተላቸው መሰረት የሚከተሉት ናቸው ፡-
1.ጊዳቦ ሎት 2 - የማልማት አቅሙ- 13420 ሄ/ር 26840 እማ/አባወራዎች
2. ጎዴ -የማልማት አቅሙ -10,000 ሄ/ር 20000 እማ/አባወራዎች
3. ወልመል ሎት 1 እና 2 – 12040 ሄ/ር -24080 እማ/አባወራዎች
4. ጨልጨል ሎት 2- 4145 ሄ/ር 8290 እማ/አባወራዎች
5.የቄጦ መስኖ 5000 ሄ/ር 10,000 እማ/አባወራዎች
6. የታችኛው ርብ -3200 ሄ/ር 6400 እማ/አባወራዎች
7. የተንዳሆ - 60,000 ሄ/ርያለማል 120,000 እማ/አባወራዎች
8. የከሰም መስኖ -20 ሺኅ ሄ/ር 40,000 እማ/አባወራዎች
እንዲሁም አርጆ ዲዴሳ እና መገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች መሠረታዊ የግንባታ ሥራቸው አልቆ የማጠናቀቂያ ሥራቸው እየተፋጠነ ከመሆኑም በላይ በቅርቡ በክብር የሚመረቁ ይሆናል፡፡
መገጭ እና አርጆ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ የ10ሩ ፕሮጀክቶች ብቻ ድምር የማልማት አቅማቸው 224,805 ሄክታር ሲሆን 450,000 እማና አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚደርጉ ናቸው፡፡
በሌላ በኩል እንደ ጨልጨል (ሎት1) አጂማጫጫ፣ ካሊድ ዲጆ፣ ሎጊያ፣ ላይኛው ጉደር፣ አንገር ፣ ፈንታሌ፣ ወይቦ፣ ላይኛው ርብ፣ ሽንሌ፣ እና አደኣ በቾ የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዕቅዳቸው መሠረት የግንባታ ስራዎቻቸው እየተከናወ ባጠናቀቅናቸው የመስኖ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን በማልማት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጁ ስራዎች በመተግበር ላይ እንገኛለን፡፡
መንግስት ለመስኖ ልማቱ ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በተሰሩ ስራዎች ከለውጡ በፊት 490 ሺህ ሄክታር የነበረው የመስኖ ሽፋን ወደ 2.6 ሚሊዮን ሄክታር ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡ አሁን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችም ሲጠናቀቁ የአገራችን የመስኖ ሽፋን በከፍተኛ መጠን የሚጨምር ይሆናል፡፡ እነዚህ መሰረተ ልማቶችም የተጀመረውን የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት በማረጋገጥ ረገድ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
በ2017 እና በ2018 በጀት አመት ፕሮጀክቶች አጠናቅቀን ለስኬት ስንበቃ ፤ ግንባታዎች ባቀድነው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ስያደርጉ የቆዩትን፣ እንደዚሁም በቀጣይነትም ስራን ሊያስጓጉሉ የሚችሉትን ቁልፍ ማነቆዎች በጥናት በመለየት ውስብስብ ለሆኑና ለቆዩ ችግሮች ተገቢ እና ህጋዊ መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ሚናቸው ትልቅ ነው፡፡
በመሆኑም ይህ ፈጣን የፕሮጀክት አፈጻጸም እና ክትትል በቀላሉ የተገኘ እንዳልሆነ መገንዘብ ያሻል።
ለመሆኑ በእነዚህ የግንባታ 2 አመታት እንደማንኛውም የኮንስትራክሽን ዘርፍ የመስኖ ግንባታ ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የተሰጣቸው መፍትሔዎችስ ?
በግንባታ ሂደቱ ያጋጠሙንን ተጠባቂና ተጠባቂ ያልሁኑ ተግዳሮቶች ተወጥተን የግንባታ ስራችንን ስናከናውን በግንባታ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ያሳደሩ ዋና ዋና ተግዳሮቶችን የሚከተሉት ናቸው፦
* የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ከውኃ ጋር የተቆራኙና በካበተ የዘርፍ ጥናት የተደገፋ መሆን የሚገባቸው በመሆናቸው በዘርፉ ልምድ ያላቸው በቂ አገር በቀል የአማካሪና ተቋራጮች አቅም በበቂ አለመኖሩ ከጅምሩ የታዩ ተግዳሮቶች ነበሩ:: በተጨማሪም አብዛኞቹ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑት በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሲሆን ተቋማቱ በዘርፋ ለሚደረግ የመሰረተ ልማት ግንባታ የነበራቸው ልምድና አቅምም ውስን ከመሆኑም በላይ ከግሉ ዘርፍ የሚሳተፉት በጣት የሚቆጠሩ ተቋማትም ገና አጥጋቢ ቁመና ያልነበራቸው መሆኑ።
* የበጀት እጥረትና የገንዘብ አቅርቦት መዘግየት፦ ፕሮጀክቶቹ ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቁ ቢሆንም በየዓመቱ የሚመደበው በጀት አነስተኛ መሆኑና የተፈቀደው በጀትም በወቅቱ ጥሬ ገንዘብ ሆኖ ባለመለቀቁ ከክፍያዎች መስተጓጎል የተነሱ መጓተቶችና የዋጋ ንረት ፕሮጀክቶች በሚፈለገው ደረጃ ማከናወን አለመቻሉ፣
* ከፍተኛ የገበያ የዋጋ ንረት (Market Inflation)፦ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍና አገር ውስጥ ሁኔታዎች ምክንያት እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ነዳጅ እና የጉልበት ዋጋ ላይ በየግዜው ከፍተኛ ጭማሪ ማጋጠሙ። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክት በዘገዩ ቁጥር ወጪዎቻቸው በየግዜው እንዲጨምሩ ምክንያት ሆነዋል ::
* የስትራቴጂካዊ ግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት እጥረት፦ ሲሚንቶ፣ ብረትና ነዳጅ በገበያ ላይ በበቂ ሁኔታ በወቅቱ አለመገኘታቸው የግንባታውን ፍጥነት በእጅጉ ገድበውት ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቶች በእቅዳቸው ልክ እንዳይከወኑ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ::
* የግድብ እና መስኖ መሰረተ ልማቶች ዲዛይን ስራዎች ጉልህ ክፍተቶችና ያጋጠሙ የጂኦሎጂካል ውስብስብነት ችግሮች :: ምንም እንኳን ፕሮጀክቶች መነሻ የሚሆኑ ጥናትና ዲዛይን ተሠርቶባቸው ቢጀመሩም፣ በትግበራ ወቅት በሚያጋጥሙ የመሬት አቀማመጥና የጂኦሎጂካል ይዘቶች ምክንያት የዲዛይን ክለሳዎችን ማድረግ የግድ ማስፈለጉ የውል ማሻሻያዎችንና የጊዜ ማራዘሚያዎችን እንዲደረጉ የግድ የሚያስብሉ ሁኔታዎች አጋጥመዋል ::
በዚህም ምክንያት ለሚኖሩ ለውጦች ተጨማሪ የኮንትራት ወጪ እና ግዜ መጠየቃቸው የግድ ሆኗል።
የተወሰዱ ስልታዊና መዋቅራዊ የማስተካከያ እርምጃዎች የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ያጋጠሙትን የአሠራር ክፍተቶች፣ የኦዲት ግኝቶችና የባለድርሻ አካላትን አስተያየቶች እንደ ግብዓት በመውሰድ ሰፊ ተቋማዊ ለውጥ (Institutional Reform) አድርጓል።
በዚህም መሠረት የተወሰዱት ቁልፍ ተቋማዊ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
* ልዩ የፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በአዲስ መልክ በ2017ዓ/ም ተቋቁሟል ፦ከዋናው መሥሪያ ቤት እስከ ፕሮጀክት ሳይት የነበረውን የቁጥጥር እና ክትትል ለማጥበቅና የውል አስተዳደር እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓቱን (Contract Administration & Construction supervision) በዲጂታል ፕላትፎርም ጭምር ለማዘመን ዘርፈ-ብዙ ብቁ ባለሙያዎችን ያቀፈ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቁሟል።
* ጥብቅ የክትትልና ግምገማ (M&E) ሥርዓት መዘርጋት፦የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ወርሃዊ፣ ሩብ ዓመት፣ ግማሽ ዓመት እና ዓመታዊ የክትትልና የመስ ክምልከታ ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ ሆኗል።
* በኮንትራት ስምምነት መሰረት ለፕሮጀክቶች ክትትል የሚያስፈልገውን ሎጅስቲክስ እንዲሟላ ተደርጓል፥- በአዲስ መልክ ለተደራጀዉ ፕሮግራም ጽ/ቤት ከማዕከል እስከ ፕሮጀክት ሳይት ለተመደቡ የስራ መሪዎችና ሙያተኞች የሚያስፈልጉ የመስክን ነባራዊ ሁኔታ የሚቋቋሙ የመስክ ተሽከርካሪዎች እና የቢሮ ቁሳቁሶችን በኮንትራት ስምምነት ውስጥ በተቀመጠው መሰረት በማሟላት የክትትል አመራሮች እና ባለሙያዎች በተቀናጀ መልኩ ጉልበታችዉና እውቀታቸዉን ለፕሮጀክቶቹ ስኬት የሚያውሉበትን ሁኔታ በመፍጠር በጊዜና በጥራት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ውጤታማ ስራ እየተመዘገበ ይገኛል::
* የቁሳቁስ አቅርቦት ሰንሰለትን ማሳለጥ (Supply Chain Optimization)፦ የሲሚንቶ እና የነዳጅ እጥረትን ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ በቀጥታ ከአምራች ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች ጋር ስልታዊ ትስስር በመፍጠር የግንባታ ግብዓቶች ሳይቆራረጡ ፕሮጀክት ሳይት ላይ እንዲቀርቡ አድርጓል።
* ባለሦስት ወገን ስምምነት (Tri-party Agreement) መተግበር፦ በተቋራጭ፣ በአማካሪ መሐንዲስ፣ በባለቤት(ሚኒስቴሩ) እና በቁሳቁስ አቅራቢዎች መካከል የተቀናጀ የጋራ መግባቢያ ስምምነት በመፈረም ሥራዎች በተቀመጠላቸው ወሰን፣ በጀትና ጥራት ኮንትራት መሰረት አድርገው እንዲከናወኑ ተደርጓል።
* አዳዲስ መመሪያዎችና ስታንዳርዶች ማዘጋጀት፦ ወደፊት ለሚከናወኑ ማናቸውም ግንባታዎች መነሻ የሚሆኑ የፕሮጀክት አስተዳደርን የሚያዘምኑ አዳዲስ የአሠራር ደንቦችና መመሪያዎች ተዘጋጅተዋል።
* የዋጋ ማስተካከያ መፍቀድ፦ አገር በቀል ተቋራጮች ፕሮጀክቶች በወቅቱ መጠናቀቅ ባለመቻላቸው ያጋጠመውን የዋጋ ንረት በራሳቸ መቋቋም ባለመቻላቸው፣ በመንግስት የተቀመጡ አሠራሮችን በመከተል ቀደም ሲል የዋጋ ማስተካከያን ይከለክሉ የነበሩ ውሎችን ከ2013 ጀምሮ በተሰጠው የመንግስት ውሳኔ መሰረት ውሎችን በማሻሻል የዋጋ ማስተካከያ በሃገር ደረጃ እንዲደረግ ፈቅዷል።
* የበጀት እጥረትና የገንዘብ አቅርቦት መዘግየትን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት በመወያየት እና በመስራት አስፈላጊው በጀት እና ጥሬ ገንዘብ በወቅቱ ለመስኖ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲለቀቁ ማድረግ ተችሏል፡፡
የመስኖ ፕሮጀክቶች እንደ ማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክቶች መንግስት ባወጣው የግዥ መመሪያዎች፣ ደንቦች እና ውሎች የሚተዳደሩ ናቸው :: የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መ/ቤት ከሌሎች ተቋማት የተረከባቸውንም ሆነ በራሱ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች የሚያስተዳድረው የመንግስትን ህግና ስርአትን በማክበር በኮንትራት ውል ስምምነት መሰረት ብቻ ነው፡፡
በዚህም መሰረት በየግዜው ልዩ ፍቃድ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙም በህግ የመፍቀድ መብት ያለውን የመንግስት አካል ፍቃድ በማግኘት ብቻ የተፈፀሙ ስራዎችን መከወን ተችሏል ፡፡
ከመስኖ ፕሮጀክቶች ውስብስብ ባህሪ በመነሳት በተቻለ መጠን ባሉ ሀገራዊ አቅሞች እና ልምድና አቅም ባላቸው አማካሪ ድርጅቶች ዝርዝር ጥናትና ዲዛይን ሳይሰራ የመስኖ ፕሮጀክቶች አይጀመሩም፡፡ ሆኖም በትግበራ ወቅት የዲዛይን ክፍተቶች መኖራቸው ሲታወቅ በተቀመጠው የውል አስተዳደር ስምምነት መሰረት የፕሮጀክቶች የዲዛይን ችግር እንዲፈታ በማድረግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በዲዛይን
ማሻሻያው መሰረት እንዲቀጥሉ እና እንዲጠናቀቁ ይደረጋሉ፡፡
ምንም እንኳን የዲዛይን ክፍተቶች ችግር ደረጃ ቢለያይም ፕሮጀክቶች በተግባር የዲዛይን ክፍተቶች እንደሚያጋጥማቸው ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶች ውል አስተዳደር አንፃርም ተቋራጭ እና አማካሪ ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ብቻ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ውሎችን ያስተዳድራል በዚህም የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤትም ይህንኑ ሀቅ ያረጋግጣል። በመሆኑም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከውል ውጪ የሚፈፀሙ ምንንም አይነት ግዥዎችና ጭማሪዎችም የሉም።
አለማቀፍ ልምዶች እንደሚያሳዩት ማንኛውም ፕሮጀክት ተግባራዊ በሚደረግባት ወቅት በገቢያ ሁኔታ ለሚከሰቱ የዋጋ ጭማሪዎች ተገቢውን አሰራር እና ኮንትራት ስምምነትን በመከተል የሚፈቀዱ የዋጋ ማስተካከያዎችን በማድረግ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
በአገራችን ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ የግንባታ ግብአቶች በመጨመሩ፣የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ እና በአለማቀፍ ሁኔታዎች መለዋወጥ ምክንያት የግንባታ ሴክተሩ በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ ገብቶ ቆይተው የነበሩ ፕሮጀክቶች በመኖራቸውም እስካሁንም ከተመሳሳይ ችግሮች ሙሉ በሙሉ ለማገገም የሚያስችል ስራ መስራትም ቀጣይ የቤት ስራችን ይሆናል፡፡
በዚህም ምክንያት አገር በቀል ተቋራጭ ድርጅቶች የተከሰተውን የግንባታ ግብአቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በራሳቸው መቋቋም እንዳቃታቸው መንግስት በመገንዘቡ የተቀመጡ አሰራሮችን በመከተል የዋጋ ማስተካከያ እንዲደረግ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቀደም ሲል የዋጋ ማስተካከያ ይከለክሉ የነበሩ ውሎችን በማሻሻል የዋጋ መስተካከያ መፍቀድ እና ተግባራዊ ማድረግ ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የሚያስገኘውን ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት በተሰጠው ፍቃድ መሰረት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያ በዝናብ ጥገኝነት ላይ የተመሠረተውን የግብርና ክፍለ-ኢኮኖሚ ወደ መስኖ መርና አስተማማኝ ምርታማነት ለመቀየር የጀመረችውን ጉዞ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው አሁን የተጀመሩት ተቋማዊ ሪፎርሞች እና ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ወደ ውጤት የመቀየር ጅምሮች ቀጣይነት ሲኖራቸው ብቻ ነው። ይህንን ለማደናቀፍና ኮንትራትና ፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓትን በአግባቡ መረዳት ባቃታቸው ወይም ሆን ተብሎ ሂደቶችን ለማጠልሸት የሚሰሩ ስራዎች በፍፁም ተቀባይነት ሊኖራቸው አይችሉም ::
እንደሚታወቀው ሃገራችን በተለያዩ ሴክተሮች አስደናቂ የሆኑ ስኬቶችን እያስመዘገበች ትገኛለች፡፡ ከዚህ አንጻር እንደ ሃገር የምናስመዘግባቸው ስኬቶች ለህዝባችንን እና ለአጋሮቻችን የሚሰጠው ትርጉም ትልቅ የመሆኑን ያህል ይህ ጅምር እመርታ የማያስደስታቸው በከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት እና የአጋሮች ጥረት የተገኙ ውጤቶች የሚያቅራቸው ሀይላት መኖራቸው ግን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመስኖ ዘረፍ እየተገኘ ያለውን ስኬት ለመገንዘብና እውቅና ለመስጠት ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ይህንን ሁኔታ ወደ ጎን በመተው የተቋቋመለትን አላማ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉአላዊነት እና የህዝብ ጥቅም ታሳቢ በማድረግ በዘርፉ የሚገኙ አሰራሮችንና ህጎችን መሰረት በማድረግ በሃገሪቱ የጀመራቸውን በውጤት የታጀበ የመስኖ ፕሮጀክቶች የማጠናቀቅ ድሎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ለኢትዮጵያ የምግብ ሉኣላዊነት መረጋገጥ እንሰራለን!!
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚንስቴር
ሃምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

20 days ago