በሰማይ ላይ ለሚያንዣብቡ አሞራዎች የማይበተን የኢትዮጵያ አንድነት
*********************
(የዕለቱ መልዕክት)
የኢትዮጵያ ታሪክ የትግል፣ የጽናት እና የጥልቅ ኅብረት ደማቅ ሸራ ነው።
ይህች ሀገር በታሪኳ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፋለች፤ ሆኖም የገዛ ልጆቿ በውስጣዊ አለመግባባት ክፍተት በፈጠሩ ቁጥር፣ ታሪካዊ ጠላቶቿ አጋጣሚውን ሲጠብቁና ሲያደቡ መኖራቸው የዘመናት ሐቅ ነው።
ይህ እውነት ዛሬም መልኩን ቀይሮ፣ በዘመናዊ የጂኦፖለቲካ ትርክት ተጠቅልሎ በደጃፋችን ቆሟል።
ሀገራዊ የልማት ውጥኖችን ስንጀምር፣ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ስንገነባና ከተሞቻችንን ስናዘምን ድምጻቸው የማይሰማ፣ አንዳች አስተዋጽኦ የማያደርጉ የውጭ ኃይሎች፣ በውስጣዊ ልዩነቶች ስንፋጠጥ ግን ከየት መጡ ሳይባሉ የጣልቃ ገብነት እጃቸውን ሲዘረጉ፣ የጥፋት መሣሪያና የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ ሲያቀብሉ ማየት የተለመደ ሆኗል።
እንደ ሀገር ትልቁ ፈተናችንና ድክመታችን የሚመነጨው ከራሳችን የውስጥ ክፍተት ነው። ከጉንደት እስከ ጉራ፣ ከዓድዋ እስከ ማይጨው፣ ከካራማራ እስከ ባድመ ያለውን ታሪካችንን ስንፈትሽ፤ ጠላቶቻችን ሁልጊዜም የሚንቀሳቀሱት የእኛን መነታረክ ተከትለው ነው።
ታላቋን ሀገር የጂኦግራፊ እስረኛ ያደረጋት፣ የባለቤትነት መብቷን የነጠቃትና ቀይ ባሕርን የመሰለ ስትራቴጂያዊ ሀብት ያሳጣን ይኸው የውስጥ መከፋፈል ያመጣው የታሪክ ስህተት ነው።
ዛሬም ቢሆን የትኛውም የውስጥ ጉዳይ ቢያከራክረን መፍትሔው በእኛው መካከል በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር መፈታት አለበት።
ለውጭ ኃይሎች መጠቀሚያ የሚሆን ቀዳዳ መክፈት፣ በታሪክ ፊት እንክርዳድ ሆኖ ከመታየትና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት የተለየ ትርጉም የለውም።
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት፣ የሀገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ ትርታና የሉዓላዊነት አቋም በጥልቅ የሚያንጸባርቅ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጠንባሮ አባቶች የከብትና የአሞራ ብሂል በሚገርም አገላለጽ መስለውታል።
"በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ለሚያንዣብቡ አሞራዎች ያለኝ መልዕክት ከብቱን መርጠን የምንገዛ እኛ ነን፤ የቅርጫውን ባለቤት የምንወስን እኛ ነን፤ የተረፈንን፣ የማንፈልገውን ካልሆነ በቀር የትኛውም አሞራ በጉልበት ከየትኛውም ቅርጫ መደብ ላይ አንዲት ኪሎ ስጋ መውሰድ እንደማይችል ላረጋግጥላቸው እፈልጋለሁ" በማለት የማያወላዳ አቋማቸውን አስረግጠው ተናግረዋል።
ይህ ጥልቅ መልዕክት ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን ሙሉ መብት እንዳላት እና ማንም በጉልበት ሊነጥቃት የሚችለው ሀብትም ሆነ ጥቅም እንደሌለ የተላለፈ ግልጽ መልዕክት ነው።
በመሆኑም በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የሚያንዣብቡ ዘመናዊ "አሞራዎች" ሊገነዘቡት የሚገባ አንድ ሐቅ አለ። ኢትዮጵያ በቀላሉ የምትበጠስ፣ በውጭ ፕሮፓጋንዳ ጫጫታ የምትዘናጋና ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፋ የምትሰጥ ደካማ ሀገር አይደለችም።
ለዘመናት በማይበጠስ ጠንካራ ገመድ የተሰናሰለች፣ የጸናች ሀገር ናት። የውጭ ኃይሎች የሀገራችንን እውነተኛ የጥንካሬ ታሪክ ወደ ኋላ መለስ ብለው በማንበብ፣ ከጣልቃ ገብነት ምኞታቸው ታቅበው ለጋራ ጥቅም በጋራ ለመሥራት ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው።
እኛም ኢትዮጵያውያን፣ የውስጥ ልዩነቶቻችንን በሠለጠነ የውይይት መንገድ እየፈታን፣ ሀገራችንን ከሚያንዣብቡ ታሪካዊ ጠላቶች በኅብረት ልንጠብቃት ግድ ይለናል። ያደፈጠው አሞራ ስሌት የሚከሽፈው፣ የእኛ ውስጣዊ አንድነት ሲጸና ብቻ ነውና።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

22 days ago