3 days ago
የአርሶ አደሩን ድካም የሚያቃልል አዲስ ማሽን በደብረ ታቦር ተፈጠረ
#ethiopia | የደብረ ታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተመራቂዎች በረከት ፀጋው እና ቤዛዊት ሲሳይ ሰብልን በአንድ ጊዜ የሚወቃና የሚያበጥር አዲስ የግብርና ማሽን በመፍጠር ትኩረት ስበዋል።
አዲሱ ማሽን አርሶ አደሮች እህል ለመውቃት ይጠቀሙበት የነበረውን ብዙ የሰው ኃይልና የእንስሳት ጉልበት የሚተካ ሲሆን፣ ሥራውን በሁለት ሰዎች ብቻ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ያስችላል። ይህም የምርት ሂደቱን በማፋጠን የሥራ ወጪን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
ወጣቶቹ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ይህን ፈጠራ ማበልጸጋቸው ለሌሎች ወጣቶች በፈጠራና በራስ አቅም ሥራ ፈጠራ ረገድ አርአያ ሆኗል።
የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደርም ለፈጠራው ቀጣይ እድገት የቦታ፣ የሼድ እና የብድር ድጋፍ በማድረግ ከፈጣሪዎቹ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል።
አሚኮ (AMICO)
#ethiopia #debretabor #innovation #agritech #tvet #ethiopianyouth #agriculture #ግብርና #ፈጠራ

3 months ago
የኢትዮጵያ ታዳጊዎች በዓለም አቀፉ የሮቦቲክስ ሻምፒዮና ታላቅ ድል ተቀዳጁ
#ethiopia | በአሜሪካ በሚቺጋን ሎውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የ2026 የሮቦፌስት ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሮቦቲክስ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ተወካይ ቡድን ደማቅ ስኬት አስመዝግቧል።
ቡድኑ እንደ ታይዋን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ቻይና ካሉ በቴክኖሎጂ የበለጸጉ 39 አገራት እና በዓለም ዙሪያ ከተወዳደሩ 738 ቡድኖች ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ የሚከተሉትን ከፍተኛ ውጤቶች አግኝቷል።
በሕክምና ሮቦቲክስ የሕዝብ ምርጫ ዘርፍ አንደኛ ደረጃ፣
በሕክምና ሮቦቲክስ ዋናው የውድድር ክፍል አምስተኛ ደረጃ፣
በፈጠራ ሥራዎች ማሳያ ዘርፍ ስድስተኛ ደረጃ፣
ይህ ስኬት ከመመዝገቡ ከአንድ ወር በፊት በግሪክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሚኖአን ሮቦቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሌላው የኢትዮጵያ የታዳጊዎች ቡድን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
እነዚህ ተከታታይ ውጤቶች የታዳጊዎቻችንን ዓለም አቀፍ ብቃት እና ትጋት ከማሳየታቸውም በላይ አገራችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ብሩህ ተስፋ የሚያረጋግጡ ናቸው።
#robofest2026 #robotics #ai #ethiopianyouth #technology #stem #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments