19 days ago
ሀሳብ አልባ ፖለቲካ የፈጠረውን ታሪካዊ አዙሪት የሰበረው የመደመር ጉዞ
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ“የመደመር መንግሥት” መጽሐፋቸው “የሐሳብ አልባ ፖለቲካ ግብ ከሕግ በላይ ሆኖ ሀብት እና ሥልጣን መቀራመት ነው” ሲሉ ያሰፈሩት የዘመናዊ ታሪካችንን ፖለቲካዊ ስብራት በጥልቀት የፈተሸ እውነት ነው።
በመደመር ብያኔ መሠረት ሐሳብ አልባ ፖለቲካ ማለት የፖለቲካ ሥልጣንን ከሕዝብ አገልግሎት እና ከተቋማዊ አሠራር በመነጠል፣ ለግል ጥቅም ማክበሪያነት የማዋል ፍጹም አፍራሽ አካሄድ ነው።
የፖለቲካ ተዋንያን የሐሳብ ልዕልናን ሲያጡ ሥልጣን የሕግ ማስከበሪያ መሣሪያ መሆኑ ቀርቶ ከሕግ በላይ ይሆናል።
ይህ ሁኔታ ደግሞ በዘመናዊው የፖለቲካ ታሪካችን ተቋማት ገለልተኛ ሆነው እንዳያድጉ በማድረግ የሕዝብን ሀገራዊ ተስፋ ሲያጨልም ቆይቷል። ይህ አካሄድ በዘመናት ጉዟችን ያስከፈለን ዋጋ እጅግ ከባድ ነው።
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የነበሩ የሥልጣን ሽግግሮች አዲስ የመጣው ሁሉ የቀደመውን በጎ ነገር አፍርሶ ከዜሮ በመጀመር አክሳሪ አዙሪት የተተበተቡ ነበሩ።
ከዘውዳዊው ሥርዓት እስከ ደርግ፣ ከዚያም እስከ ኢሕአዴግ የነበረው ጉዞ አንዱን ጥሎ ሌላው የሚነሳበት በመሆኑ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሳይገነቡ ቀርተዋል።
በዚህም ምክንያት ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ከእኛ ኋላ የነበሩ ሀገራት ጭምር በጠንካራ ተቋማዊ መሠረት ተስፈንጥረው የዓለም የኢኮኖሚ ቁንጮ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ግን በእንደገና ጅምሮች እና በአለመረጋጋት ውስጥ እንድትባዝን ተደርጋለች።
ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ግን የመደመር መንግሥት ይህን አክሳሪ አዙሪት ለመስበር በጽናት የታጀቡ ተጨባጭ እርምጃዎችን ወስዷል።
መደመር የነበረውን አፍርሶ እንደገና የመጀመርን አጥፊ ልማድ በመግታት፣ የትናንት አዎንታዊ ወረቶችን ጠብቆ ማስፋት እና የተሠሩ ስህተቶችን ማረም የሚያስችል ሀገር በቀል ፍልስፍናን በተግባር እያሳየ ነው።
ሥልጣን ለሕግ እና ለሥርዓት የበላይነት እንዲገዛ ለማድረግ በፍትሕ፣ በጸጥታ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች ተቋማዊ ማሻሻያዎች ተተግብረዋል።
የጽንፍ ፖለቲካን ለመታገልም እንደ ሽምግልና ያሉ ሀገር በቀል ጥበቦችን ከዘመናዊ አስተዳደር ጋር በማጣመር አካታች የመግባባት ዴሞክራሲን መሠረት የሚያስይዝ ባህል እየተገነባ ይገኛል።
አሁን በተጀመረው የመደመር አካሄድ መፃኢው የኢትዮጵያ ተስፋ እጅግ ብሩህ ነው። አሁን ላይ የምናያቸው ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ስኬት፣ የተጀመሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና የዲፕሎማሲ ድሎች የዚህ የሐሳብ ልዕልና ውጤቶች ናቸው።
ሐሳብ አልባነትን በሐሳብ ልዕልና፣ መከፋፈልን በመደመር፣ እንዲሁም አፍርሶ መገንባትን በይዞ ማደግ በመተካት የተጀመረው ይህ ጉዞ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ መሠረት በጠንካራ ተቋማት ላይ አቁሞ ለአፍሪካም አርአያ ወደምትሆንበት ማማ የሚያሸጋግር ዘላቂ አቅጣጫ ነው።
በለሚ ታደሰ
#medemer #ethiopia #medemermengist #pmabiyahmed #ebc #nationalrenewal #ethiopianpolitics

Comments