Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "የሰኔ 15ቱ ክስተት መነሻ አድርጌ የምወስደው ቤዚክሊ ሁለት፣ ከሁለት ጉዳዮች የሆነ ይመስለኛል። አንደኛው ስሁት ግምገማ ነው፤ አንድ ነገር ለማሳካት የምትሰራው ግምገማ በበቂ ዳታ ላይ፣ በበቂ ኢንፎርሜሽን ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ፣ ጉጉት ይቀድምና መሻት ይፈጥርና ወደዚያ ለማድረስ የሚገባህን መንገድ በትክክል ዲዛይን ሳታደርግ ጥፋት ታመጣለህና ስሁት ግምገማ አንዱ ችግር ይመስለኛል። ይሄ እዛ ላይ ያበቃ ሳይሆን ከዛ በኋላም በተደጋጋሚ የምናየው ችግር ነው።

"ሁለተኛው ችግር በሁለት እግር ማነከስ ነው። ለውጥ ተቀብለህ፣ ሀላፊነት ተቀብለህ፣ የህዝብ አደራ ተቀብለህ በሌላ መንገድ ደግሞ ያልተቀደሰ ጋብቻ ከመደበኛ ሀይሎች ጋር አድርገህ እዚሁም እዚያም ለመሆን የሚፈለግ ሁኔታ በአንዳንድ ሰዎች ይታይ ነበረ፤ ያም የፈጠረው ይመስለኛል። ግምገማውም ችግር አለ፣ እንደገና ደግሞ በሁለት እግር ማነከሱም አለ፣ እዚህ ተቀምጦ እዚያ፣ እዚያ ሆኖ ደግሞ እዚህ የመሻቱ ፍላጎት የተቀላቀሉ ነገሮች አሉ። በአንድ መንግስት ወይም በአንድ ፓርቲ እቅድ የሚመራ ስብስብ ሳይሆን፣ እቅዱን ከተለያየ ሶርስ የሚወስድ ሀይል ያለበት፣ ግን በጋራ የሚነጋገር የሚሰበሰብ የሚወያይ፣ በዛ ሂደት ደግሞ ጥፋት ሊያመጣ የሚችል ክስተት ሆኗል።

"እንግዲህ ቅድም ላነሳልህ እንደሞከርኩት የኢትዮጵያ ህዝቦች የመዋሀድ ታሪክ ቢኖራቸውም፣ አብሮ የመዝመት ታሪክ ቢኖራቸውም፣ በዘመናት መካከል ስልጣን ሲመጣ በሀይል፣ አልጋ ሳይጸና የመገዳደል ፍላጎት የባህላችን አንዱ አካል ነው። ልጅ ኢያሱ ዘመን መለስ ብለህ ወደ ታሪክ ብታገላብጥ ይሄን ነገር በቀላሉ ማየት ትችላለህ። በዘመነ መሳፍንት የምንለውን፣ በኋላ 1966 ላይ ያጋጠመውን ብንወስድ የዚሁ ተቀጽላ ነው፣ በደርግ ዘመን 1981 ያየነው መሰል ባህሪ ነው፣ በኢህአዴግ ዘመን መጠኑ ዝቅ ያለ ቢሆንም በ2001 አካባቢ መጠነኛ ፍላጎቶች ተንጸባርቀዋል። በእኛም ጊዜ በሰኔ 2010 16 ላይ ከለውጡ ሁለት ወር ሶስት ወር በኋላ መሰል ሙከራዎች በመስቀል አደባባይ ተካሂደዋል። እዚህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁልጊዜም በሀይል ፍላጎትን ማሳካት፣ በሀይል ስልጣን ለመያዝ መሞከር፣ ሰው በመግደል ስልጣን ለመውረስ መሞከር ነበረ ማለት ነው።

"የሰኔ 15ቱም ከነዚህ ከላይ ከዘረዘርኳቸው ክስተቶች ለየት የሚያደርገው በክልል ደረጃ፣ በከተማ ደረጃ ዝቅ ብሎ ለመፈጸም የተሞከረ ሙከራ ነው። በክልል ደረጃ እንደዚህ ያለውን ጉዳይ ፈጽመህ ምን ታሳካለህ የሚለው ጉዳይ ቅድም ያልኩት የስሁት ግምገማ ውጤት አካል ይመስለኛል። እንዴት ታስታውሰዋለህ እንዴት ይታወሳል አልከው፣ የታሪካችን የጠባሳችን አካል አድርጌ ነው ማስታውሰው።"

- ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አህመድ

6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.