2 days ago
ጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ
*ሊዮ 14ኛ በቀጣይ ጉብኝት የሚያደርጉባቸውን ሦስት ሀገራት ታውቀዋል።
#ethiopia | የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በኅዳር ወር በደቡብ አሜሪካ አገራት ጉብኝት ያደርጋሉ።
ፖፕ ሊዮ 14ኛ በኡሩጉዋይ፣ አርጀንቲና እና ፔሩ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን አስታውቋል።
ሊዮ 14ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑ በኋላ ወደ ደቡብ አሜሪካ ሀገራት የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጉዟቸው ይሆናል።
በዚህም ከኅዳር 6 እስከ 17 ባሉት 12 ቀናት ውስጥ በአጠቃላይ 10 ከተሞችን የሚሸፍን ጉብኝት ይሆናል ተብሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቀድሞ ስማቸው ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት በፔሩ አገር ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በምስዮናዊነት እና በጳጳስነት ያገለገሉ ሲሆን የዚያች አገር ሙሉ ዜግነትም እንዳላቸው ተገልጿል።
ፖፕ ሊዮ ረጅሙን የጉዞ ጊዜ በፔሩ የሚያሳልፉ ሲሆን ሊማ ቺክላዮና ኩስኮ ከተሞችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የትውልድ አገራቸው አርጀንቲናን በ12 ዓመታት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪነታቸው ወቅት መጎብኘት አልቻሉም ነበር።
አሁን የሊዮ 14ኛ የአርጀንቲና ጉብኝት በአገሪቱ ዜጎች በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #popeleo #vatican #peru #argentina #uruguay

7 days ago
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጉ ዘንድ ግብዣ እና የጸሎት ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ባሳለፍነው ሰኔ ወር በቅድስት መንበር ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጋር ባደረጉት የካርዲናሎች ጉባኤ ለቅዱስነታቸው የግብዣ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕነታቸው በየአመቱ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሚደረገው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉዞ የአፍሪካ ቀንድ ዋና ማዕከል ወደሆነችው ኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ እንደቀረበላቸው በመግለጽ ምዕመናን ለዚህ ምኞት መሳካት እንዲጸልዩ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ የዘመናት የታሪክ ባለቤት የሆነች፣ የአማኞች ሀገር፣ የአፍሪካ ማዕከል እና በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2027 ለሚዘጋጀው 32ኛው የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) በአዘጋጅነት የተመረጠች ሀገር በመሆኗ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በቀጣይ ዓመት ለሚኖራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን ማካተት እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል።
ከሐምሌ 11-19 ቀን 2018 ዓ.ም. በኬንያ ናይሮቢ በተካሔደው 21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤም ይህ ጥሪ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሌዎ 14ኛ መቅረቡ ተገልጿል።
ይህም ታላቅ እና የዘመናት የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ምኞት ምላሽ ይገኝ ዘንድ መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል #ethiopia #getutemesgen #getunews #catholic #popeleo

27 days ago
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የ50ኛ ዓመት የክህነት ወርቅ ኢዩቤልዩ ክብረ በዓላቸውን አከበሩ
#ethiopia | የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ እና የብፁዕ አቡነ ጸጋዬ 50ኛ ዓመት የክህነት አገልግሎት በዛሬው እለት ተከብሯል።
የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ እና የብፁዕ አቡነ ጸጋዬ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዪ የክህነት አገልግሎት በልደተ ማርያም ካቶሊክ ካቴድራል በመስዋዕተ ቅዳሴ ተከበረ።
ብፁዓን ጳጳሳቱም የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ክብር በማስቀደም ከ50 ዓመታት በላይ የሆነ የአገልግሎት ምስክር ሆነዋል ብለዋል።
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ የመልካም ምኞት መልዕክት በቅድስት መንበር ተወካይ ብፁዕ ሊቀጳጳስ ብሪያን አማካይነት የቀረበ ሲሆን ቅዱስነታቸው ብፁዓን ጳጳሳቱ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለነበራቸው አስተዋፅዖ እና የአገልግሎት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።
ለብዙዎች አብነት እና የአገልግሎት ጽናት ተምሳሌት የሆኑት ብፁዓን ጳጳሳቱ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እድገት ውስጥ ከፍተኛ አሻራ እንዳላቸው ተገልጿል።
በተለይም በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ያበረከቱት አስተዋፅዖ የላቀ ነው።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በጠቅላይ ጽ/ቤት ፕሬዝደንት ሆነው ከ26 አመት በላይ ያገለገሉ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ጸጋዬ ደግሞ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አሁናዊ መዋቅሩን በማደራጅት ለ 9 ዓመት በጠቅላይ ጸኃፊነት አገልግለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ethiopiacatholicchurch #cardinalbirhanyesussurafel

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሐምሌ 7/1940 ዓ.ም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጨለንቆ አቅራቢያ በምትገኝ ፈንዲዴ በተባለች መንደር ተወለዱ።
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ መንደራቸው ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በሐረር በሚገኘው የላዛሪስት አባቶች የዘርዐ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት መንፈሳዊ ጥሪያቸውን ጀመሩ።
ከዚያም በአዲስ አበባ በሚገኘው የካፑቺን ፍራንቸስካውያን የፍልስፍናና ቲዎሎጂ ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ወደ እንግሊዝ ሀገር በማምራት በለንደን ዩኒቨርሲቲ በሶሺዎሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
እ.አ.አ ሰኔ 1976 ምስጢረ ክህነትን የተቀበሉ ሲሆን
የማኅበረ ልዑካን አባቶች ላዛሪስት ገዳም ያፈራቸው ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ጥር 17/1990 ዓ.ም ጵጵስናን ፤ የካቲት 7/2007 ዓ.ም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አማካኝነት የካርዲናልነት ማዕረግን ያገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ታሪክ ከብፁዕ ጳውሎስ አድዋ ቀጥሎ ካርዲናል የሆኑ ሁለተኛው ጳጳስ ናቸው።
ብፁዕ ካርዲናል በኢትዮጵያ በሰላም ሚኒስቴር ስር ተቋቁሞ የነበረው የብሔራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን ውስጥ በሊቀመንበርነት አገልግለዋል።
ብፁዕነታቸው ለቅድስት መንበር ባቀረቡት የጡረታ ጥያቄ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጥያቄያቸውን መቀበላቸውን በቅድስት መንበር ልዪ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጀሮቲ አማካይነት ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።
ለብፁዕ አባታችን እንኳን ለ50ኛ ዓመት የክህነት በዓልዎ በሰላም አደረስዎት።

2 months ago
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ከሐዋርያዊ ኃላፊነታቸው በጡረታ አስረከቡ
#fastmereja | የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል በጡረታ ምክንያት ከኃላፊነታቸው ተሰናብተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ፣ ካርዲናሉ ቀደም ብለው ያቀረቡትን የጡረታ ጥያቄ በዛሬው ዕለት ተቀብለዋል።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀኖናዊ አሰራርን ተከትሎ የቀረበው ይህ ጥያቄ በቅድስት መንበር በኩል ተቀባይነት አግኝቷል። ውሳኔው በቅድስት መንበር ልዩ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ በኩል ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ የካርዲናሉ የረጅም ዘመን አገልግሎት በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ነው።
በብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ቦታ ላይ፣ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ረዳት ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ ተተኪ ሊቀጳጳስ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

3 months ago
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሰብዓዊ ክብር እና ሕይወት በተመለከተ የተላለፈ ሐዋርያዊ ጥሪ
“ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና”. (ማቴ 5:7)
ለፖለቲካ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ሚዲያዎች እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች
እኛ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት በመላው አለም ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወቅታዊ ሁኔታች እንዳሳሰበን ለመግለጽ እንፈልጋለን። በአገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች አገራቸውን ለቀው የሚወጡት ለአገራቸው ፍቅር በማጣት ሳይሆን፣ የተሻለ የሥራ ዕድል እና የኑሮ ሁኔታ በመፈለግ ነው። ተነሳሽነታቸው እጅግ ሊከበር የሚገባው እና መስዋዕትነት የሚጠይቅ ነው፤ ይህም ህይወታቸውን ለማሻሻል፣ ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እና በመጨረሻም ለአገራቸው እድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው። ነገር ግን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ስደተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን ሰብዓዊ ክብር ከማግኘት ይልቅ በመዋቅራዊ ብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በገለልተኝነት እና በከባድ ተጋላጭነት ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ። ሁኔታቸው ምንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፣ ቅዱስ የሆነው ሰብአዊ ክብራቸው ግን በድንበር፣ በሕጋዊ ሁኔታ ወይም በኢኮኖሚ ስርዓት ችላ ሊባል ወይም ሊጠፋ አይችልም።
የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፤ “በኢኮኖሚ የበለጸጉ መንግስታት፣ ሰዎች በትውልድ አገራቸው ጸጥታንና ለመተዳድሪያ የሚሆን ገቢ በማጣታቸው ወደ አገራቸው ሲገቡ ተቀብለው የተቻላቸውን እርዳታ መስጠት አለባቸው” (CCC 2241)። ይህ ትምህርት ስደተኞች እንደ ውጭ ወይም እንደሸክም መታየት እንደሌለባቸው ይልቁንም እንደ ወንድምና እህት ሰብዓዊ ክብራቸው ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባ ያስተምረናል።
ይሁን እንጂ፣ ብዙ ስደተኞች በስደት ጉዟቸው ወቅት ከባድ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል፤ በእጅጉም ይሰቃያሉ። እኛም ከዚህ በታች የተገለጹትን ቁልፍ የስደት መዳረሻዎች እና ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚያጋጥሟቸውን ተያያዥ ችግሮች ተመልክተናል።
1) አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች፡-
• ሳውዲ አረቢያ፡- በሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሚኖሩ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አሉ። የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በሰማነው መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ በተፈረደው የሞት ፍርድ ያለንን ስጋት፣ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት ለዜጎቻችን ሁሉ ርህራሄ እና ምሕረት እንዲያደርጉ ክቡር የሆነውን የሰው ሕይወት እንዲጠብቁ እንጠይቃለን።
• የመን፡- በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ የመን ለመግባት ወይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመጓዝ በቀይ ባህር፣ በጅቡቲ ወይም በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል ያልፋሉ። የመን ብዙውን ጊዜ ወደ ሌሎች የባህረ ሰላጤ አገሮች እንደ መጓጓዣ መንገድ ትጠቀማለች፤ ሆኖም ግን፣ ብዙ ስደተኞች በመንገድ ላይ ከፍተኛ ሥቃይ ይደርስባቸዋል፣ ዓመፅ፣ በደል እና ኢ-ሰብአዊ ተግባራት ይደርስባቸዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በጉዞው አደገኛ ባህሪ እና በሚገጥሟቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ።
• ሊባኖስ፡- በሊባኖስ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአገሪቱ ውስጥ ባለው ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። በዚህም ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ትውልድ አገራቸው በሰላም ለመመለስና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ይፈልጋሉ።
• የባህረ ሰላጤ አገሮች፡- በእነዚህ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሌሪካ በእስራኤል እና በኢራን መሃከል በተፈጠረው ጦርነት እና ግጭት ምክንያት በጭንቅ ውስጥ ይገኛሉ።
2) የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሌላ መዳረሻ ናት። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ለሕይወታቸውና ለንብረታቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ወደአስቡበት ሳይደርሱ በጉዞ ላይ እያሉ እስራት ይገጥማቸዋል፣ ሌሎቹ ደግሞ ወደ መድረሻቸው የሚደርሱ ሰዎች በፍርሃትና ውስጥ በምኖር ላይ ናቸው። በሚደርሱን ዘገባዎች መሰረት በደቡብ አፍሪካውያን የውጭ ዜጎች ጥላቻ የተነሳ በዓመፅ፣ እና በግድያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ክቡር ሕይወታቸው እየጠፋ ነው።
3) የሱዳን - ሊቢያ - የአውሮፓ መንገድ፡ ይህ መንገድ ለረጅም ጊዜ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች በብዛት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን፣ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ስደተኞች ከፍተኛ ስቃይ እና ህልፈተ ህይወት አስከትሏል። ብዙዎች አስቸጋሪ እና አደገኛ የሆነውን የበረሃ መንገድ በኢሰብአዊ ሁኔታዎች ሲያቋርጡ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት ይህንን ጉዞ የበለጠ አደገኛ አድርጎታል። ሊቢያ የሚደርሱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እስር፣ ዝርፊያ፣ የጉልበት ብዝበዛ እና ከባድ በደል ይደርስባቸዋል። አንዳንዶቹ በክርስትና እምነታቸው ምክንያት ስደት ደርሶባቸዋል እና ህይወታቸውን አጥተዋል። በአደገኛ ጀልባዎች የሜዲትራኒያንን ባህር ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ሲሰምጡ፤ ብዙዎቹ በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸውን ያጣሉ፣ ጥቂቶች ብቻ ወደ ላምፔዱዛ ዳርቻ መድረስ ችለዋል። ላምፔዱዛ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በአንድ ወቅት በባህር ላይ ለሞቱት ሰዎች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለስደተኞች ያላትን አንድነት፣ ርህራሄ እና ለስደተኞች ድምጽ የመሆን ተልዕኮ ለማስቀጠል ደሴቲቱን በቅርቡ እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።
ይህ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስቃይ ከቁጥርም በላይ ውድ እና የተከበረ ህይወት ያላቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በእንባ፣ በመስዋዕትነት እና በተስፋ የሸኟቸው ልጆች ናቸው። ብዙ ጊዜ ግን እነዚህ ስደተኞች በብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በደል፣ በመገለል እና ለጥቃት በመጋለጥ አላስፈላጊ ስርዓቶች ውስጥ ይወድቃሉ። ብዙዎች ለማሰብ አዳጋች በሆኑ ሁኔታዎችን ውስጥ በህይወት ለመቆየት ይታገላሉ።
በክርስቲያያዊ የበጎ አድራጎት እና በዓለም አቀፍ የወንድማማችነት መንፈስ፣ ለሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ማናቸውም የታቀዱ ግድያዎች እንዲቆሙ እና በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ምሕረትን እንዲያደርጉ ልመና እናቀርባለን። ምህረት ፍትህን አያዳክምም። ምህረት ፍትህን ከፍ በማድረግ ተስፋ ለቆረጡ ተስፋን ይሰጣል።
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን የሚያባብሱትን ጥልቅ ምክንያቶች ከመሰረቱ ለማስወገድ ይተባበር ዘንድ ዕድል የሚሰጥ ሊሆን ይገባል። ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ የከባቢ አየር ሁኔታ መቃወስ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በዓለም ዙሪያ አደገኛ የፍልሰት መንገዶችን እንዲከተሉ እንደሚያስገድዳቸው አስተውለናል። እነዚህን ዋና ዋና ምክንያቶች ችላ የሚል ዓለም የፍልሰት ቀውስን መፍታት አይችልም። በእርግጥም፣ የሰብዓዊነታችን እና የሥልጣኔ መለኪያ በዙሪያችን ያሉ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በምናሳሳየው እንክብካቤ ላይ የተመሠረተ ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት፣ ውይይት፣ ምሕረትና ጥበብ ተስፋ መቁረጥንና ሞትን እንዲያሸንፉ አጥብቀን መጸለያችንን እንቀጥላለን። እነዚህን ተጋላጭ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ሁሉንም ውሳኔ ሰጪዎች ለሁሉ ቻይ በሆነው የእግዚአብሔርን አምላክ ምህረት እና እገዛ ያገኙ ዘንድ እንጸልያለን።
የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ
አዲስ አበባ
10/09/2018

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ያስገነባው 1B+G+10 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።
በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ዘመነ ሢመት የተጀመረው በ480 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሁለገብ ሕንፃ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ዘመነ ሢመት ተጠናቆ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተባርኮ ተመረቀ።
EOTC

Sponsored by
Surafel

ዘገባው የEOTC ነው

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የደቡብ ጎንደር ዴራ ወረዳ አድያመ ዮርዳኖስ የወንቅሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም መስራች እና አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም፣ በአሜሪካ ሳክራሜንቶ፣ ካሊፎርኒያ ታላቅ ገዳም መመስረታቸው ተሰማ። በአሁኑ ወቅት በዳላስ የገዳመ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አስተዳዳሪ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት አባ ዮሐንስ፣ ይህ አዲሱ የካሊፎርኒያ ገዳም ምረቃ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በሰሜን አሜሪካ ይበልጥ ለማስፋት የወሰዱት ትልቅ ሐዋርያዊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ አገልግሎት መስፋፋት ድንገተኛ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በተሰጠ ይፋዊ ቡራኬ እና የሥራ ኃላፊነት ላይ የተመሰረተ ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በጻፉት እና ዘ-ሐበሻ እጅ የገባው ይፋዊ ደብዳቤ (ቁጥር ል/ጵ/452/420/2012)፣ አባ ዮሐንስ የወንቅሸት ገዳሙን ከመመስረት እና ከማቋቋም ደረጃ ጀምሮ ለማኅበረ ካህናት እና ለምዕመናን እያበረከቱ ያለውን የላቀ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት አድንቀዋል።
በደብዳቤው ላይ በግልጽ እንደሰፈረው፣ አባ ዮሐንስ ያላቸውን ሐዋርያዊ ተልእኮ ይበልጥ አጠናክረው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር እየተዘዋወሩ ማስተማር ይችሉ ዘንድ ከገዳሙ ጽ/ቤት የቀረበውን ጥያቄ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተቀብለውታል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓትን ሳይለቁ፣ በመላው ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን አገልግሎት እንዲሰጡ ዓለም አቀፍ የስብከተ ወንጌል ፈቃድ እንደሰጧቸው ይፋዊ ሰነዱ ያስረዳል።
አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ሃይማኖትን ከምግባር፣ ዕውቀትን ከትሕትና፣ እንዲሁም ምስጢርን ከታሪክ ጋር በማዋሃድ እንዲያስተምሩ በቅዱስ ፓትርያርኩ አደራ የተሰጣቸው ሲሆን፤ አሁን በሳክራሜንቶ፣ ካሊፎርኒያ የመሰረቱት አዲስ ገዳም (9249 Folsom Blvd, Sacramento, CA 95826) በውጭው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የቤተ ክርስቲያኒቱ እምነት ተከታዮች ትልቅ መንፈሳዊ መጠለያ፣ የስነ-ልቦና ማዕከል እና የበረከት ምንጭ እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ ክንውን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሐዋርያዊ ተልእኮ በቆራጥ አባቶች አማካኝነት ድንበር ተሻግሮ ፍሬ እያፈራ ለመሆኑ ማሳያ ሆኗል ተብሏል።

4 months ago
ኢራን በጣሊያን እንድትተካ የቀረበው አነጋጋሪ ጥያቄ
#fastmereja I የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ኢራን በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ተሰርዞ በጣሊያን እንድትተካ ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) ጥያቄ አቀረቡ።
ይህ ያልተጠበቀ ጥያቄ የቀረበው ልዩ መልዕክተኛው ፓኦሎ ዛምፖሊ ለፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ባስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል። ጥያቄው በዋናነት በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና በጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ቅራኔ ለመፍታት የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና በሜሎኒ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ ትራምፕ በኢራን ጦርነት ዙሪያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን በሰነዘሩት ትችት ሳቢያ መሆኑ ተነግሯል።
ልዩ መልዕክተኛው ዛምፖሊ ጣሊያን አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያሸነፈች ታሪካዊ ሀገር በመሆኗ፣ በውድድሩ የመሳተፍ "ብቃት" አላት ሲሉ ተከራክረዋል። ጣሊያን ለማጣሪያው በቦስኒያ ሄርዞጎቪና ተሸንፋ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ከዓለም ዋንጫ ውጪ መሆኗ ይታወሳል።
ኢራን በበኩሏ ለውድድሩ ዝግጁ መሆኗንና እንደምትሳተፍ በይፋ አስታውቃለች። ከዚህ ቀደም ጨዋታዎቿ ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ እንዲዛወሩ ለፊፋ ጥያቄ አቅርባ እንደነበር አይዘነጋም።
እስካሁን ፊፋም ሆነ የኋይት ሀውስ በጉዳዩ ላይ የሰጡት ይፋዊ ምላሽ የለም። ይሁን እንጂ የፊፋ ህግ አንድ ሀገር ራሷን ካገለለች ሌላ ሀገር የመተካት ሙሉ ስልጣን ለማህበሩ ይሰጣል።

የታሪካዊው የቁልቢ ገብርኤል ሕንጻ እድሳት በይፋ ተጀመረ!
#fastmereja :በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታዋቂና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምዕመናን የመጽናኛና የቃል ኪዳን ስፍራ የሆነው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ፣ በ134 ሚሊዮን ብር ወጪ መጠነ ሰፊ የእድሳት ሥራ እየተከናወነለት እንደሚገኝ በዛሬዉ እለት የገዳሙ አስተዳደር አስታወቀ።
የመሠረት ድንጋዩ በ1884 ዓ.ም የተጣለውና በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1954 ዓ.ም በዘመናዊ መልክ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው ይኸው ታሪካዊ ሕንጻ፣ ላለፉት 64 ዓመታት መሠረታዊ የእድሳት ሥራ ሳይደረግለት ቆይቷል። በዚህም ምክንያት በተፈጥሯዊ ዕርጅና እና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በሕንጻው መዋቅር፣ በጣሪያውና በውስጥ ገፅታው ላይ ከፍተኛ ብልሽት ደርሶበታል።
በዛሬው ዕለት በተሰጠው መግለጫ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ እንዲሁም ሌሎች ብፁዓን በተገኙበት የጋዜጣዊ መግለጫዉ የተሰጠ ሲሆን የገዳሙ አስተዳደር እንደገለጸው፣ በተለይ የጣሪያው ማፍሰስ በጥንታዊ ሥዕለ አድህኖዎችና ንዋየ ቅዱሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ፣ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ መሠረት በማድረግ እድሳቱ በይፋ መጀመሩን አስታዉቋል።
የእድሳት ሥራው በታዋቂው 'አዶር ኮንስትራክሽን" (Ador Construction) እና በ"ፋሲል ጊዮርጊስ ኮንሰልቲንግ" (Fasil Giorgis Consulting) እየተመራ የሚገኝ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ 40 በመቶ ደርሷል። ሥራው በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅም በቀንና በሌሊት በሁለት ፈረቃ (Two Shifts) እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የእድሳቱ ዋና ግብ ግንባታውን እስከ መጪው ሐምሌ 2018 ዓ.ም የቅዱስ ገብርኤል በዓል ድረስ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በበዓሉ ወቅት የሚኖረውን ከፍተኛ የምዕመናን ፍሰት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የቤተ መቅደሱ የውስጥ ክፍል ቅድሚያ ተሰጥቶት ተጠናቆ ለበዓሉ አገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆንና ቀሪው የውጭ አካል ግንባታ ከሐምሌ በኋላ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ቤተክርስቲያኗ ለዚህ ታላቅ የታሪክና የበረከት ሥራ ምዕመናን በዕውቀት፣ በገንዘብና በማቴሪያል እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀረበች ሲሆን ከዋናው ሕንጻ እድሳት በተጨማሪ የቤተልሔም ግንባታ፣ የክርስትና ቤት እድሳት፣ የእንግዶች ማረፊያና የግቢው ማስዋብ ሥራዎችም በበረከት ተሳታፊ መሆን ለሚፈልጉ ክፍት መሆናቸውን አስታውቃለች፡፡
ምዕመናን ድጋፋቸውን በነዚህ የባንክ አካውንቶች ማበርከት እንደሚችሉ ተገልጿል፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000759706165
አሐዱ ባንክ - 0093543510901
አባይ ባንክ - 18411129 58315015
አቢሲኒያ ባንክ -255602373
አዋሽ ባንክ - 6454
ዳሽን ባንክ - 517116 3880011
አማራ ባንክ - 9900050109805
ሕብረት ባንክ - 1090713234152990
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
+251 910 05 23 30
+251 911 24 38 71
+251 911 81 15 04
+251 913 82 45 47 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።

የቁልቢ ገብርኤል ገዳም በ134 ሚሊዮን ብር የህንጻ ዕድሳት ሥራ ተጀመረ
#ethiopia | በታሪካዊነቱና በታላቅነቱ የሚታወቀው የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ህንፃ ቤተክርስቲያን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ከማገልገሉ ጋር ተያይዞ በደረሰበት ከፍተኛ እርጅና ምክንያት አጠቃላይ እድሳት ስራ መጀመሩን ተገለጸ።
በዛሬው ዕለት በተሰጠው መግለጫ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ እንዲሁም ሌሎች ብፁዓን አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የገዳሙን ወቅታዊ ሁኔታና የታቀደውን የእድሳት ሥራ የሚመለከት ዝርዝር መረጃ ቀርቧል።
የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ታሪካዊ መሠረት ከአሥረኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ያለው ዘመናዊው ህንጻ በ1954 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የተገነባ በመሆኑ ለረጅም ዘመናት ለተፈጥሮ አደጋና ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋልጦ ቆይቷል።
በተለይም በህንጻው መዋቅር ላይ የሚታየው ስንጥቅ፣ የጣራው መዝለቅና የዝናብ ውሃ ወደ ውስጥ መግባት ጥንታዊ የሆኑ ሥዕለ አድኅኖዎችንና ንዋያተ ቅድሳትን ለከፍተኛ ጉዳት እየዳረጋቸው በመሆኑ አስቸኳይ ርብርብ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህንን ችግር ለመፍታትም መንፈሳዊና ታሪካዊ ግዴታን ለመወጣት የገቢ ማሰባሰቢያና የእድሳት ሥራው በይፋ መጀመሩ ተበስሯል።
ለዚህ ታላቅ የእድሳት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ይውል ዘንድ በጨረታ አሸናፊ ከሆነው አደር ኮንስትራክሽን ጋር ውል የተፈረመ ሲሆን፣ የፋሲል ጊዮርጊስ አማካሪ ድርጅት ደግሞ የህንጻውን ታሪካዊ ይዘት ሳይለቅ የሙያ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
የህንጻ እድሳት ሥራው አጠቃላይ 134,000,000 (መቶ ሰላሳ አራት ሚሊዮን) ብር የሚጠይቅ ሲሆን፣ ሥራው እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም ድረስ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ታቅዷል።
ሆኖም ግን በመጪው የሐምሌ ወር የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ምዕመናን በበዓሉ ወቅት እንዲገለገሉበት ቅድሚያ የሚሰጣቸው የውስጥ ክፍሎች ዝግጅት እንዲጠናቀቅ በሁለት ፈረቃ ስራው በርብርብ እየተሰራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ አመራሮችም ይህንን መንፈሳዊ ጥሪ በማስተላለፍ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ምዕመናን፣ በረከቱን ለመካፈልና ይህንን ታሪካዊ ገዳም ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ብጹአን አባቶች ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የእድሳት ሥራው የገዳሙን ጥንታዊ ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲከናወንና የታቀደው የገቢ ማሰባሰቢያ ግብ እንዲመታ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ በማሳሰብ፣ አጠቃላይ ሂደቱ በከፍተኛ ጥንቃቄና እየተሰራ ይገኛል።
የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የህንፃ እድሳት የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች
👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000759706165
👉 አሐዱ ባንክ - 0093543510901
👉 አባይ ባንክ - 18411129 58315015
👉 አቢሲኒያ ባንክ -255602373
👉 አዋሽ ባንክ - 6454
👉 ዳሽን ባንክ - 517116 3880011
👉 አማራ ባንክ - 9900050109805
👉 ሕብረት ባንክ - 1090713234152990
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአሥር ቀናት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በአልጄሪያ ጀመሩ
#ethiopia | የቫቲካኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአራት የአፍሪካ አገራት የሚያደርጉትንና አሥር ቀናት የሚፈጀውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት በአልጄሪያ ጀምረዋል።
ቅዱስነታቸው በአልጄሪያ መዲና ሲደርሱ በፕሬዝዳንት አብደልማጅድ ተቡኔ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በመጀመሪያው ቀን ውሏቸውም አልጄሪያ ለነፃነቷና ለሉዓላዊነቷ ባደረገችው ተጋድሎ ለወደቁ ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት በመገኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ እውነተኛ ሰላም የፍትህና የክብር መገለጫ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ሊረጋገጥ የሚችለው በይቅርታ ብቻ እንደሆነ አሳስበዋል።
ቅዱስነታቸው በአልጄሪያ፣ በካሜሩን፣ በአንጎላና በኢኳቶሪያል ጊኒ የሚገኙ 11 ከተማዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቫቲካን ከፍተኛ ባለሥልጣን ካርዲናል ማይክል ቼርኒ እንደገለጹት፣ ጉብኝቱ ከ20 በመቶ በላይ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በሚኖሩባት አፍሪካ ላይ የዓለምን ትኩረት ለማሳረፍ ያለመ ነው።
በጉዟቸው ወቅት ሰላም፣ ስደት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የወጣቶችና የቤተሰብ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚመክሩ ታውቋል።
ይህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት በአህጉሪቱ ካሉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከመለማመድ ባለፈ፣ አፍሪካ አሁን ላይ ለምትገኝባቸው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የቫቲካንን አጋርነት ለማሳየት ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #channeltv #vatican #popeleoxiv #africatour #algeria #cameroon #angola #equatorialguinea #peace #catholicchurch #ርዕሰሊቃነጳጳሳት #አፍሪካ #ሰላም #ቫቲካን

ሊዮ 14ኛው የትራምፕን "አንድ ስልጣኔ ዛሬ ምሽት ይጠፋል" የሚል ማስጠንቀቂያ አጥብቀው ኮነኑ
#fastmereja I ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ የሰነዘሩትን “አንድ ሙሉ ስልጣኔ ዛሬ ምሽት ይጠፋል” የሚል ማስጠንቀቂያ "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ ኮነኑ። ጳጳሱ በኢራን ህዝብ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት የዓለም አቀፍ ህግጋትን የሚጥስ መሆኑን ገልጸዋል።

5 months ago
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው፦ "ጦርነት የቪዲዮ ጌም አይደለም"
የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳሱ መገናኛ ብዙኃን ጦርነትን እንደ ቪዲዮ ጌም በማቅረብ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ እንዳይሆኑ አስጠነቀቁ።
ቅዱስነታቸው ትናንት መጋቢት 9,2018 ዓ. ም ለጣሊያን የቴሌቪዥን ባለሙያዎች በሰጡት መግለጫ፣ ጋዜጠኞች በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎችን ስቃይና እውነተኛውን የጦርነት ገጽታ ለዓለም እንዲያሳዩ አሳስበዋል።
ይህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትችት በተለይ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ የሚካሄደውን ጥቃት ለማስተዋወቅ ከቪዲዮ ጌምና ከአክሽን ፊልሞች የተቀነጩ ምስሎችን መጠቀሙን ተከትሎ የመጣ ነው።
የቺካጎው ካርዲናል ብሌጅ ሱፒች በበኩላቸው፣ የኋይት ሀውስ ድርጊት "አስጸያፊ" መሆኑን ገልጸው፣ የሰው ልጆች ሕይወት የሚጠፋበት ጦርነት እንደ መዝናኛ መቅረቡን ኮንነዋል።
በአሁኑ ወቅት የአሜሪካና የእስራኤል ሚሳኤሎች በኢራን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት ከ1,000 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይነገራል።
ይህ በኢራን ላይ የተከፈተው ጦርነት በአሜሪካ የውስጥ ፖለቲካና በሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ክፍፍል እየፈጠረ ይገኛል።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ 13ኛው በዓለ ሢመት ዛሬ በድምቀት ይከበራል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ ወደ መንበረ ፓትርያርክነቱ የመጡበት 13ኛው ዓመት የሢመት በዓል ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
በአዲስ አበባ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚከናወነው በዚህ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ፦
* ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
* የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣
* ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣
* ዲፕሎማቶችና በርካታ ምዕመናን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል
በዕለቱ የቅዱስነታቸውን የ13 ዓመታት ጉዞና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊና መንፈሳዊ አገልግሎቶች ላይ ያከናወኗቸው ተግባራት የሚዘከሩ ሲሆን፣ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችም ይከናወናሉ።
ቅዱስነታቸው በ2005 ዓ.ም ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አቡነ_ማትያስ #በዓለ_ሢመት #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን #መንበረ_ጸባዖት #eotc #abunemathias #ethiopia

ፖፕ ሊዮ ወደ አፍሪካ
#ethiopia | የአለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው እ.ኤ.አ. ከኤፕሪል 13 እስከ 23 ቀን 2026 ባሉት ቀናት በአራት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን ዛሬ አስታውቃለች።
ይህ ጉብኝት ቅዱስነታቸው በ2026 የሚያደርጉት የመጀመሪያው ትልቅ የባሕር ማዶ ጉዞ ሲሆን፣ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ወደምትገኝበት አህጉር የሚያደርጉት መሆኑ ልዩ ትርጉም ተሰጥቶታል።
ጳጳሱ በዚህ ጉዟቸው አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ካሜሩንን ይጎበኛሉ።
በቆይታቸውም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንደሚታደም የሚጠበቅ ሲሆን፣ የዓለም መሪዎች ለአፍሪካ ልማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮችን ውይይት የሚያጠናክሩ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉ ተመልክቷል።
እ.ኤ.አ. በግንቦት ወር የሟቹን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን በመተካት የተመረጡት ሊዮ 14ኛው፣ እስካሁን ያደረጉት ብቸኛ የውጭ ሀገር ጉብኝት ባለፈው ኅዳር እና ታኅሣሥ ወራት ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የተደረገውን ብቻ ነው።
የቫቲካን ባለሥልጣናት እና የአፍሪካ ቤተክርስቲያን መሪዎች እንደሚሉት፣ ይህ ጉብኝት ቤተክርስቲያኒቱ ለአፍሪካ አህጉር የሰጠችውን ከፍተኛ ቅድሚያ የሚያሳይ ነው።
በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ካሉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መካከል 20 በመቶ ያህሉ በአፍሪካ እንደሚኖሩ የቫቲካን ስታቲስቲክስ ያሳያል።
አልጄሪያ ከአሁን ቀደም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ጉብኝት አስተናግዳ የማታውቅ ሲሆን፣ ሊዮ 14ኛው ሀገሪቱን የሚጎበኙ የመጀመሪያው ጳጳስ ይሆናሉ።
ጳጳሱ የኦገስቲኒያን የሃይማኖት ሥርዓት አባል በመሆናቸው፣ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩት የታዋቂው ቅዱስ አውግስጢኖስ የትውልድ ስፍራ የሆነችውን አልጄሪያን ለመጎብኘት ልዩ ፍላጎት አላቸው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከአፍሪካ ጉዟቸው በፊት መጋቢት 28 ቀን ወደ ሞናኮ የአንድ ቀን ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን፣ ከሰኔ 6 እስከ 12 ቀን ደግሞ ስፔንን ይጎበኛሉ።
በስፔን ቆይታቸው ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት እንደ ዋና መሸጋገሪያ የሚጠቀሙባቸውን የካናሪ ደሴቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለመጨረሻ ጊዜ የአፍሪካ ጉብኝት የተደረገው በ2023 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን እና ደቡብ ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት ነበር።
አንጎላ እና ካሜሩን በ2009 በጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛው፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ1982 በዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተጎብኝተዋል።

6 months ago
በዙሪያችን የሞላውን ረብሻ፣ የውሸት ዜና፣ ሀሜት እና ምድራዊ ፍርድ ትተን በይቅርታ መንፈስ የዘለዓለማዊ ሕይወትን መንገድ እንጓዝ፦ ቤተክርስቲያኗ
#ethiopia | ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን
የ2018 ዓ.ም የዐቢይ ጾም መግቢያን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት
“አንተ ግን ስትጾም ራስህን ተቀባ፣ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር ላለው አባትህ እንጂ በሰዎች ዘንድ ጾመኛ ሆነህ እንዳትታይ፤ በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።” (ማቴዎስ 6: 17-18)
የተወደዳችሁ ካቶሊካውያን ምእመናን
በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የምትገኙ ሁሉ
እንዲሁም በጎ ፈቃድ ላላችሁ ሰዎች በሙሉ
የእግዚአብሔር አምላክ ጸጋ በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡-
በቅድሚያ እንኳን ለ2018 ዓ.ም. የዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
የጾም ወቅት ከተለመደው አለማዊ ውሏችን ገለል በማለት የመለወጥን ጉዞ ለማጠናከር ወይም ለመጀመር ቤተክርስቲያናችን የምትሰጠን የጸጋ ወቅት ነው።
በዚህ ቅዱስ ወቅት ራሳችንን በመግዛት፣ በሥነ-ምግባር በመጠንከር፣ ህሊናችንን በማዳመጥና በመመርመር ክርስቲያናዊ መታደስን ልንለማመድ ይገባል።
የዐቢይ ጾም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ህማማት፣ ሞትና ትንሳኤውን በጥልቅ ማሰብ እና በመንፈሳዊ ተጋድሎ ራሳችንን ለማዘጋጀት የተሰጠን የጸጋ ጊዜ ነው።
በፈተና በተሞላው ዘመናችን ክርስትናችንን በጸሎት፣ በጾም እና በምጽዋት ለማጠናከር የምንተጋበት ቅዱስ ወቅት ነው።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጸለይን በቃል ብቻ ሳይሆን በሕይወቱ አስተምሮናል።
“አባታችን ሆይ” በማለት ያስተማረን ጸሎት እንዲሁም በጸሎት የኖረው ሕይወቱ የእውነተኛ ጸሎት መሠረታዊ ባህሪያትን ያሳያል።
በዚህ ዓይነት፣ ከይዘቱ በተጨማሪ፣ ለማንኛውም እውነተኛ ጸሎት አስፈላጊ የሆኑትን ባህሪያት ያስተምረናል።
እነዚህም ባህሪያት የእግዚአብሔርን መንግስት የሚሻውና ጠላቶችን ይቅር የሚል የልብ ንጽሕና፣ ከስሜታችንና ከግንዛቤአችን ባሻገር ርቆ የሚሄድ ግልጽና የልጅነት እምነት እንዲሁም ደቀመዝሙሩን ከፈተና የሚጠብቀው ንቃት ናቸው።
(የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁጥር 2608)
በዚህ በዐብይ ጾም ወቅት የምናቀርበው ጸሎት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የበለጠ የሚያቀራርበን፤ ወደ እግዚአብሔር አብ የሚወስደን እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእምነት እና በተግባር የተሞላ ሊሆን ይገባል።
በጸሎታችንም ከራሳችን አልፈን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለተጨነቁ ነፍሶች፣ በሀዘን በስቃይ እና በጦርነት ላሉ ወገኖቻችን፣ ለሀገራችን እና ለመላው ዓለም እንድንጸልይ አደራ እላለሁ።
የጾም ወቅት በሥጋዊ ሕይወታችን ከምግብ ከመቆጠብ ባሻገር ራሳችንን፤ ፈጣሪያችንን እና ሌሎች ወገኖቻችንን ለማድመጥ እድል የሚሰጠን ወቅት ነው።
በማዳመጥ ውስጥ ሰላም አለ፤ በማዳመጥ ውስጥ እረፍት አለ፤ በማዳመጥ ውስጥ መግባባት አለ፤ በማዳመጥ ውስጥ ፍቅር ያብባል፣ በፍቅር ውስጥ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አለ።
የቤተክርስቲያናችን 266ኛው የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ “ሁላችንም ወንድማማቾችና እህትማማቾች ነን” በተሰኘው የሐዋርያዊ ማነቃቂያ መልዕክታቸው ውይይት ከልብ በማዳመጥ እና የሰውን ልጅ ሰብዓዊ ክብር ከመጠበቅ እንደሚጀምር ይገልጻሉ።
ህሊናውን የሚያዳምጥ አስተዋይ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ይችላልና ሁላችንም ቆም ብለን በግብረገባዊ ንቃተ ህሊና ፈጣሪያችንን እናዳምጥ።
በወቅታዊ ሀገራችን ሁኔታ ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን፣ መሪዎቻችን በጥበብ እንዲመሩ፣ ከተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ እንዲሰውረን፣ የታሰሩ ምህረትን እንዲያገኙ፣ እና በእነዚህ ጊዜያት በመጾምና በመጸለይ በእምነታችን እንጽና።
በክርስቶስ የተወደዳችሁ መላው ካቶሊካውያን እና የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣
በዚህ የዐቢይ ጾም ዘመን ቤተክርስቲያናችን የምታበረታታውን እውነተኛ ጾም እንድንጾም አደራ እላለሁ።
ይህም ጎረቤቶቻችንን በንግግር ባለማሳዘን፣ ከሀሜት በመቆጠብ፣ ክርስቲያናዊ የፍቅር ሥራዎችን በመሥራት፣ የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር በመጠበቅ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በማዳመጥ እና በእርሱ መኖር፣ በንስሃ፣ በመስዋዕተ ቅዳሴ በማስቀደስ በእውነተኛ መንፈሳዊ ንቃት እንጹም።
የእመቤታችንና የመላእክት አማላጅነት፣ የሰማዕታትንና የቅዱሳን ጸሎት አይለየን !
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ
ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9 ቀን 2018
ዓ/ም

የፖፕ ሊዮ ጥሪ
#ethiopia | ፖፕ ሊዮ "ጸረ ሴማዊነት እና መድልዎ የሌለባት ዓለምን እመኛለሁ" ብለዋል።
ዓለም አቀፍ የሆሎኮስት (Holocaust) መታሰቢያ ቀንን አስመልክተው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ዓለም ከጥላቻና ከዘር መድልዎ እንድትጸዳ ጥሪ አቅርበዋል።
ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት "በዚህ ዓመታዊ መታሰቢያ ሁሉን ቻይ አምላክን ጸረ ሴማዊነት (antisemitism) የሌለባት ዓለምን እንዲሰጠን እለምነዋለሁ" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ፖፕ ሊዮ የዓለም መሪዎች የዘር ማጥፋት (Genocide) አሰቃቂ ድርጊት በየትኛውም ሕዝብ ላይ ዳግም እንዳይከሰት ምንጊዜም ንቁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
ጳጳሱ ከጸረ ሴማዊነት ባለፈ በማንኛውም የሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም መድልዎ፣ ጭቆና እና ስደት እንዲቆም ጸልየዋል።
በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና በአይሁድ ዕምነት ተከታዮች መካከል የነበረው የዘመናት ቅራኔ ላለፉት አስርተ ዓመታት እየተሻሻለ መምጣቱን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
ይህም እ.ኤ.አ. በ1965 የወጣውንና ግንኙነታቸውን የቀየረውን 'Nostra aetate' የተሰኘውን ታሪካዊ ሰነድ ተከትሎ የመጣ ነው።
"ቤተክርስቲያን ጸረ ሴማዊነትን በጭራሽ አትታገስም፤ በወንጌል መሰረትም ትታገለዋለች" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቋማቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸረ ሴማዊነትና የጥላቻ ንግግሮች እየጨመሩ መምጣታቸው ለቫቲካን ትልቅ ስጋት ሆኗል።
ፖፕ ሊዮ ባለፈው ግንቦት ወር የ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተከታዮች ያሏት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ከሆኑ ጀምሮ፣ ይህንን የጥላቻ ድርጊት ደጋግመው ሲያወግዙ መቆየታቸው ይታወሳል።
#popeleoxiv #vatican #holocaustremembrance #antisemitism #worldnews #ርዕሰ_ሊቃነ_ጳጳሳት #ቫቲካን #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

7 months ago
ትራምፕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን ለ "ሰላም ምክር ቤት" ጋበዙ
ዶናልድ ትራምፕ፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑትን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቅርቡ በሚያቋቁሙት ዓለም አቀፍ የሰላም ምክር ቤት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።
የቫቲካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፡-
"ቅዱስ አባታችን ግብዣው ደርሷቸዋል፤ እያሰብንበትም ነው" ብለዋል።
ቫቲካን ውሳኔ ለመስጠት ጊዜ እንደሚያስፈልጋትና ጉዳዩን በጥልቀት እየመረመረችው መሆኑን ገልጸዋል።
ካርዲናል ፓሮሊን አክለውም ቫቲካን በገንዘብ ረገድ ድጋፍ የማድረግ አቅም እንደሌላትና የምክር ቤቱ አወቃቀር ከዓለም አቀፍ ሕግጋት ጋር ያለውን መጣጣም እንደምትከታተል አስረድተዋል።
ስለ ሰላም ምክር ቤቱ ፦ በመጀመሪያ በጋዛ ያለውን ግጭት ለመፍታት ታስቦ የተጀመረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በዓለም ዙሪያ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ሰፊ ተልዕኮ እንዲኖረው ታቅዷል።
ተሳታፊዎች፦ ትራምፕ ከ60 በላይ የዓለም መሪዎችን የጋበዙ ሲሆን፣ እስከ አሁን ሩሲያ፣ እስራኤል፣ ግብፅ፣ ካዛኪስታን፣ ሞሮኮ እና አርጀንቲና ግብዣውን ተቀብለዋል።
ተቃውሞዎች፦ እንደ እንግሊዝ፣ ስዊድን እና ኖርዌይ ያሉ የአውሮፓ ሀገራት ምክር ቤቱ የተባበሩት መንግስታትን (UN) ሚና ሊተካ ይችላል በሚል ስጋት ግብዣውን ውድቅ አድርገዋል።
ቋሚ አባል ለመሆን ሀገራት 1 ቢሊዮን ዶላር እንዲያዋጡ ጥሪ መቅረቡም ተነግሯል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ (ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የተመረጡትና የመጀመሪያው አሜሪካዊ ጳጳስ) በጋዛ ስላለው ሰብአዊ ሁኔታ ቀደም ሲል ስጋታቸውን ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል።

🇻🇦 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፦ "ጦርነት እንደ ፋሽን ተመልሷል"
#ethiopia | የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው የጥቃት እና የግጭት ዝንባሌ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በከፍተኛ ሀዘን ገለጹ። ጳጳሱ በቫቲካን ለሚገኙ የዓለም ዲፕሎማቶች ባደረጉት ንግግር፣ ዓለማችን ሰላምን እንደ ተፈላጊ ስጦታ ማየቷን ትታ ወደ ጥፋት እያመራች መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
⚠️ የጳጳሱ ዋና ዋና የጭንቀት ነጥቦች
* የጦርነት ስሜት መስፋፋት፦ "ጦርነት እንደ ፋሽን ተመልሷል" ያሉት ሊዮ 14ኛ፣ የሰው ልጅ ግጭትን እንደ አማራጭ መውሰዱ የዓለምን ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥል ገልጸዋል።
* የጉልበት ዲፕሎማሲ መንገስ፦ በሀገራት መካከል የሚደረጉ የጋራ ውይይቶችና ዲፕሎማሲያዊ ስምምነቶች መዳከማቸውን ጠቁመው፣ በምትኩ በኃያላን ሀገራት የሚመራ "የጉልበት ዲፕሎማሲ" እየነገሰ መሆኑን ተችተዋል።
* የድንበር መጣስ፦ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ተከብሮ የቆየው "የሌላን ሀገር ሉዓላዊነትና ድንበር ያለመድፈር" መርህ አሁን ላይ እየተጣሰ መሆኑን በጽኑ ወቅሰዋል።
🇺🇸 ልዩ ክስተት፦ የእንግሊዝኛ ንግግር እና አዲሱ ጳጳስ
ይህ ንግግር በታሪክ ልዩ የሚያደርገው ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ፦
* ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካ የተመረጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው።
* በተለምዶ በቫቲካን እንደሚደረገው በጣሊያንኛ ወይም በፈረንሳይኛ ፈንታ፣ ንግግራቸውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማቅረባቸው ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀጥተኛ መልዕክት ለማስተላለፍ ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመጨረሻም የዓለም መሪዎች ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እንዲመለሱና የሰው ልጅን ሰላም እንዲያስቀድሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ቫቲካን #ርዕሰሊቃነጳጳሳት #ሊዮ14ኛ #ሰላም #ዲፕሎማሲ #ዓለምአቀፍዜና #ጦርነት #vatican #popeleoxiv #peace

"ጦርነት እንደ ፋሽን ተመልሷል" — ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በዓለም ላይ እየታየ ባለው የግጭትና የጥቃት ዝንባሌ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ስጋት ገለጹ።
ጳጳሱ በቫቲካን ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ባደረጉት ንግግር የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል፡-
ስለ ጦርነት መስፋፋት፦ "ጦርነት እንደ ፋሽን ተመልሷል፤ የጦርነት ስሜትም በዓለም ላይ እየተስፋፋ ነው" ብለዋል።
የዲፕሎማሲ መዳከም፦ በሀገራት መካከል የሚደረግ የጋራ ውይይት (Multilateralism) እየተዳከመ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።
የጉልበት ዲፕሎማሲ፦ በውይይትና በስምምነት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ እየቀረ፣ በግለሰብ ሀገራት ወይም በሀይለኛ ጥመኞች የሚመራ "የጉልበት ዲፕሎማሲ" እየተተካ መሆኑን አስረድተዋል።
የድንበር መጣስ፦ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የጸደቀውና "የሌላን ሀገር ድንበር በኃይል መጣስን የሚከለክለው" መርህ መጣሱንም ወቅሰዋል።
ልዩ ሁኔታ፦
ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካ የተመረጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፣ በተለመደው የጣሊያንኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ፈንታ ንግግራቸውን በእንግሊዝኛ ማድረጋቸው ልዩ አድርጎታል።
ጳጳሱ በንግግራቸው ወቅት ሰላም እንደ ተፈላጊ ስጦታ መታየቱ ቀርቷል ሲሉ በሀዘን ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የዩክሬን ጦርነት እንዲያበቃ ዳግመኛ ጥሪ አቀረቡ
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመጀመሪያ የገና በዓል ንግግራቸው ዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነቱን ለማቆም ቀጥተኛ ንግግር እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።
ሊቀ ጳጳሱ በቫቲካን ከተማ ለተሰበሰቡ ምእመናን ባደረጉት ንግግር በዓለም ዙሪያ ያሉ ግጭቶች ሁሉ እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ በተለይም ስለ ዩክሬን ሲናገሩ "የጦር መሣሪያ ጩኸት ይቁም" ብለዋል።
የሚመለከታቸው አካላት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ቁርጠኛ፣ ቅን እንዲሁም ቀጥተኛ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ጦርነቱን ለማስቆም በአሜሪካ የሚመራው የሁለቱ ሀገራት ድርድር በቀጠለበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።
አሜሪካ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስምምነት እውን እንዲሆን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረገች ቢሆንም፤ እስካሁን በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ቀጥተኛ ውይይት አለመካሄዱ ተመልክቷል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የድንበር ግጭቶች የተከሰቱባቸው በሌሎች የዓለም ክፍሎች ያሉ ብጥብጥ እና ግጭቶችን አውግዘው ሰላም እንዲሰፍን ተማፅነዋል።
በተለይም የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የጥንት ወዳጅነት እንዲታደስ፣ እርቅ እና ሰላም እንዲሰፍን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መጠየቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።
@ጋዜጣ_ፕላስ

8 months ago
የሊቃዉንት መፍለቂያ ደብረ ገነት ኤልያስ
📍 እንኳን አደረሳችሁ
#ethiopia | የደብረ ኤልያስ ቤተክርስትያን በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በደብረ ኤልያስ ከተማ ይገኛል፡፡
ቤተ ክርስትያኑ የተመሰረተዉ በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን በአጼ ዘርዓያዕቆብ ዘመነመንግስት በ1466 ዓ/ም በደጅ አዝማች ድልአሰማ አማካኝነት ተመስርቷል፡፡
ይህ ቤተ ክርስትያን በ1912 ልዑል ራስ ሃይሉ ተክለሃይማኖት በጭቃ ጡብ ያሰሩት ላይ ቤት፣መሃል ቤት እና ምድር ቤት የሚባሉ 3 ክፍሎች ያሉት
እቃ ቤት አለዉ፡፡
በደብረ ገነት ኤልያስ ቤተክርስትያን ለደብሩ አስተዳዳሪዎች የሚሰጥ የማዕረግ ስያሜ "ድምሐነ-ገነት"የሚል ሲሆን ትርጓሜዉም "የገነት መሃል ወይንም ራስ "ማለት ነዉ፡፡ይህ ስያሜ የራሱ የሆነ ትርጓሜ ሲኖሩ በሌሎች አብያተ ክርስትያናት እንደማይሰጥ አባቶች ይገልጻሉ፡፡
በዚህ ቤተክርስትያን የሚገኙ ድሮ ሰዉ የነበሩ ናቸዉ ተብለዉ በአፈታሪክ የሚታመኑ ሁለት ድንጋዮች አሉ፡፡ ድንጋዮችም ሰዉ በነበሩበት ሰዓት ባልና ሚስት ሙሽሮች ሆነዉ ወደ ባልየዉ ሀገር ጉዞ ሲደረግ ሴቷ ሙሽራ ባስከተለችዉ ጥፋት የደረሰባቸዉ ቅጣት ለአሁኑ ድንጋይነታቸዉ እንዳበቃቸዉ ይነገራል፡፡
ድንጋዮቹ በመጠንና ቅርጽ ፈጽሞ የተለያዩ ናቸዉ፡፡ህብረተሰቡ በተለይም በበዓል ሰዓት ሴቷን ሙሽራ ለማንሳት የተለያዩ ሙከራዎችን ያደርጋሉ፡፡ ድንጋዋን በማንሳትም ህብረተሰቡ የተለያዩ አንድምታዎችን ይሰጣሉ፡፡
የደብረ ገነት ኤልያስ ቤተክርስትያን ከጥንት እስከ ዛሬ የዜማ ፣ቅኔ ፣አቋቋም ፣መጽሐፍና የቅዳሴ መርጌታዎች መፍለቂያ ማዕከል ነዉ፡፡ከዚህ ቦታ የእዉቀት መነሻቸን አድርገዉ በዓለምና ሀገር አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ምሁራንን ይኸዉ ቤተ ክርስትያን አፍርቷል፡፡
ከእነዚህም ጥቂቶቹ፡-
✒️ ታላቁ ደራሲና የቤተ ክህነት ሊቅ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ፣
✒️ ሁለተኛዉ ኢትዮጵያዊ ተወላጅ ጳጳስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣
✒️ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፣
✒️ ክቡር ደራሲ መላኩ በጎሰዉ
✒️ ታላቁና እዉቁ የረጅም ልብ ወለድ ድርሰት አባት ክቡር ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ፣
✒️ ዶክተር ኢሳያስ አለሜነህ ከብዙ በትቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡አሁንም ይህ የሊቃዉንት መፍለቂያ ቦታ ስራ በርካታ የአብነት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
በየአመቱ ታህሳስ 1 ቀን የነብየ ቅዱስ ኤልያስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በርካታ ሊቃውንት እና ህዝበ ክርስቲያን በተገኘበት በተለየ ሁኔታ ከዋዜማው ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊ ሰነስርዓቶች ይከበራል።
ዘንድሮም በዓሉ በልዮ ልዮ ሀይማኖታዊ ስነስርዓቶች ተክብሮ በሠላም ተጠናቋል።
📷 የደብረ ኤልያስ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንስ

59ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ 59ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን በእምድብር ሀገረስብከት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምረዋል።
ጉባኤው የ12 ሀገረስብከት ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በብፁዕ ሊቀጳጳስ ብሪያን የቅድስት መንበር ተወካይ በተገኙበት ተጀምሯል። በጉባኤው ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲግራት ሀገረስብከት ጳጳስ በወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት አለመገኘታቸው ተገልጿል።
ጉባኤው በአጀንዳው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በርካታ ጉዳዮችን እንደሚዳስስ የተገለጠ ሲሆን በተለይም የሲኖዶስን የመጨረሻ ሰነድ በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስችሉ አቅጣዎችን እንደሚያስቀምጥ የጉባኤው የህዝብ ግንኙነት ተወካይ ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ገልጸዋል።
ጉባኤው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዮ 14ኛ መልዕክት በማዳመጥ የተጀመረ ሲሆን ይህም ጉባኤው ከቅድስት መንበር ጋር ያለውን ህብረት የሚያመላክት ነው።
ጉባኤው በቀጣይ ቀናት እስከ ታህሳስ 2 ቀን የሚቆይ ሲሆን መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

10 months ago
ከንቲባ ከድር ጁሀር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተሸለሙ
📌በ፵፬ ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ለድሬዳዋ አሰተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የእውቅና ሽልማት አበረከተች።
#ethiopia | ሽልማቱን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለከንቲባው ተወካይ ለአቶ ገበየሁ ጥላሁን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አስረክበዋል።
ከንቲባ ከድር ጁሀር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ኢትዮጵያ ለምታከናውነው ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለ አድሎ በፍትሐዊነት መንግሥታዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ሽልማት የተበረከተላቸው።

11 months ago
የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው
የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች መከበር ጀምሯል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ክብረ በዓሉም በጸሎት አስጀምረዋል።
በበዓሉ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምእመናን እና ቱሪስቶች ተገኝተዋል።
Fbc

የመስቀል ደመራ በዓል
#ethiopia | የ2018 የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጨምሮ በርካታ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የኢፌድሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ክብርት ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አበቤ ጨምሮ ሌሎች በርካታ እንግዶች በተገኙበት መከበር ጀምሯል።

12 months ago
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ የዕረፍት መታሰቢያ ሥርዓተ ጸሎት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ
#ethiopia | የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ነሐሴ 10 ቀን በጸሎት ይታሰባል ።
በዘንድሮም የቅዱስነታቸው የዕረፍት መታሰቢያ የጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ጽባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት፣ ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሐዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጆችና የመምሪያና የድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ፣ሊቀ ትጉሀን ታጋይ ታደለ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ልጆቻቸዉ በተገኙበት ተከናውኗል ።
ቅዱስነታቸው በክህነት ዘመናቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዓለምአቀፍ ተሰሚነት እንዲኖራት በማድረግ እና አስተዳደሯ እንዲቀና በማድረግ ረገድ ጉልሕ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል ።
እንዲሁም በመርሐ ግብሩ ላይ አባታዊ መልዕክት ያስተላልፉት ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የነበራቸው ጠንካራ የአገልግሎት ዘመን ልንከተለው ይገባናል ሲሉ የገለጡ ሲሆን ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያንን በቀናነት አገልግለው አልፈዋል ለዚህም ቤተክርስቲያን ሁሌም ተዘክራችዋልች ሲሉ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ያሬዳዊ ዜማ እና ቅኔ ቀርቧል።

1 year ago
ልጅ በወለደች ቁጥር አንድ ታዋቂ ሰው እንደሚሞት የሚነገርላት ሴት
የትሪሻ ፓይታስ አስገራሚ ታሪክ በኢንተርኔት እየተሰራጨ ነው።
ትሪሻ ተራ ብሎገር እና ዘፋኝ ነች፣ ነገር ግን ልዩነት አለባት፡ በየጊዜው ልጅ በወለደች ቁጥር አንድ ታዋቂ ሰው ይሞታል።
የክስተቶች ታሪክ እነሆ፡-
ቀኑም ሆነ አመቱ በፈረንጆች ነው
👉 መስከረም 14፣ 2022፡ ትሪሻ ማሊቡ ባርቢ የተባለች ሴት ልጅ ትወልዳለች። በዚያው ቀን ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ ሞታለች።
👉ሰኔ 20፣ 2024፡ ትሪሻ ወንድ ልጅ ትወልዳለች። በዚያው ቀን ተዋናይ ዶናልድ ሰዘርላንድ ሞቷል።
👉ሚያዝያ 21፣ 2025፡ ትሪሻ ማርገዟን ታስታውቃለች። በዚህ ቀን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ይሞታሉ።
👉 ሐምሌ 22፣ 2025፡ ትሪሻ ሌላ ወንድ ልጅ ትወልዳለች። በዚያው ቀን ኦዚ ኦስቦርን ሞቷል።
ሴትየዋ ቀድሞውንም "በአለማት መካከል ያለች መተላለፊያ" የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷታል።

Comments