"ጦርነት እንደ ፋሽን ተመልሷል" — ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በዓለም ላይ እየታየ ባለው የግጭትና የጥቃት ዝንባሌ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ስጋት ገለጹ።
ጳጳሱ በቫቲካን ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ባደረጉት ንግግር የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል፡-
ስለ ጦርነት መስፋፋት፦ "ጦርነት እንደ ፋሽን ተመልሷል፤ የጦርነት ስሜትም በዓለም ላይ እየተስፋፋ ነው" ብለዋል።
የዲፕሎማሲ መዳከም፦ በሀገራት መካከል የሚደረግ የጋራ ውይይት (Multilateralism) እየተዳከመ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።
የጉልበት ዲፕሎማሲ፦ በውይይትና በስምምነት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ እየቀረ፣ በግለሰብ ሀገራት ወይም በሀይለኛ ጥመኞች የሚመራ "የጉልበት ዲፕሎማሲ" እየተተካ መሆኑን አስረድተዋል።
የድንበር መጣስ፦ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የጸደቀውና "የሌላን ሀገር ድንበር በኃይል መጣስን የሚከለክለው" መርህ መጣሱንም ወቅሰዋል።
ልዩ ሁኔታ፦
ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካ የተመረጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፣ በተለመደው የጣሊያንኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ፈንታ ንግግራቸውን በእንግሊዝኛ ማድረጋቸው ልዩ አድርጎታል።
ጳጳሱ በንግግራቸው ወቅት ሰላም እንደ ተፈላጊ ስጦታ መታየቱ ቀርቷል ሲሉ በሀዘን ገልጸዋል።

5 months ago