27 days ago
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የ50ኛ ዓመት የክህነት ወርቅ ኢዩቤልዩ ክብረ በዓላቸውን አከበሩ
#ethiopia | የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ እና የብፁዕ አቡነ ጸጋዬ 50ኛ ዓመት የክህነት አገልግሎት በዛሬው እለት ተከብሯል።
የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ እና የብፁዕ አቡነ ጸጋዬ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዪ የክህነት አገልግሎት በልደተ ማርያም ካቶሊክ ካቴድራል በመስዋዕተ ቅዳሴ ተከበረ።
ብፁዓን ጳጳሳቱም የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ክብር በማስቀደም ከ50 ዓመታት በላይ የሆነ የአገልግሎት ምስክር ሆነዋል ብለዋል።
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ የመልካም ምኞት መልዕክት በቅድስት መንበር ተወካይ ብፁዕ ሊቀጳጳስ ብሪያን አማካይነት የቀረበ ሲሆን ቅዱስነታቸው ብፁዓን ጳጳሳቱ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለነበራቸው አስተዋፅዖ እና የአገልግሎት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።
ለብዙዎች አብነት እና የአገልግሎት ጽናት ተምሳሌት የሆኑት ብፁዓን ጳጳሳቱ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እድገት ውስጥ ከፍተኛ አሻራ እንዳላቸው ተገልጿል።
በተለይም በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ያበረከቱት አስተዋፅዖ የላቀ ነው።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በጠቅላይ ጽ/ቤት ፕሬዝደንት ሆነው ከ26 አመት በላይ ያገለገሉ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ጸጋዬ ደግሞ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አሁናዊ መዋቅሩን በማደራጅት ለ 9 ዓመት በጠቅላይ ጸኃፊነት አገልግለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ethiopiacatholicchurch #cardinalbirhanyesussurafel

Comments