ፖፕ ሊዮ ወደ አፍሪካ
#ethiopia | የአለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው እ.ኤ.አ. ከኤፕሪል 13 እስከ 23 ቀን 2026 ባሉት ቀናት በአራት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን ዛሬ አስታውቃለች።
ይህ ጉብኝት ቅዱስነታቸው በ2026 የሚያደርጉት የመጀመሪያው ትልቅ የባሕር ማዶ ጉዞ ሲሆን፣ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ወደምትገኝበት አህጉር የሚያደርጉት መሆኑ ልዩ ትርጉም ተሰጥቶታል።
ጳጳሱ በዚህ ጉዟቸው አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ካሜሩንን ይጎበኛሉ።
በቆይታቸውም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንደሚታደም የሚጠበቅ ሲሆን፣ የዓለም መሪዎች ለአፍሪካ ልማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮችን ውይይት የሚያጠናክሩ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉ ተመልክቷል።
እ.ኤ.አ. በግንቦት ወር የሟቹን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን በመተካት የተመረጡት ሊዮ 14ኛው፣ እስካሁን ያደረጉት ብቸኛ የውጭ ሀገር ጉብኝት ባለፈው ኅዳር እና ታኅሣሥ ወራት ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የተደረገውን ብቻ ነው።
የቫቲካን ባለሥልጣናት እና የአፍሪካ ቤተክርስቲያን መሪዎች እንደሚሉት፣ ይህ ጉብኝት ቤተክርስቲያኒቱ ለአፍሪካ አህጉር የሰጠችውን ከፍተኛ ቅድሚያ የሚያሳይ ነው።
በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ካሉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መካከል 20 በመቶ ያህሉ በአፍሪካ እንደሚኖሩ የቫቲካን ስታቲስቲክስ ያሳያል።
አልጄሪያ ከአሁን ቀደም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ጉብኝት አስተናግዳ የማታውቅ ሲሆን፣ ሊዮ 14ኛው ሀገሪቱን የሚጎበኙ የመጀመሪያው ጳጳስ ይሆናሉ።
ጳጳሱ የኦገስቲኒያን የሃይማኖት ሥርዓት አባል በመሆናቸው፣ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩት የታዋቂው ቅዱስ አውግስጢኖስ የትውልድ ስፍራ የሆነችውን አልጄሪያን ለመጎብኘት ልዩ ፍላጎት አላቸው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከአፍሪካ ጉዟቸው በፊት መጋቢት 28 ቀን ወደ ሞናኮ የአንድ ቀን ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን፣ ከሰኔ 6 እስከ 12 ቀን ደግሞ ስፔንን ይጎበኛሉ።
በስፔን ቆይታቸው ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት እንደ ዋና መሸጋገሪያ የሚጠቀሙባቸውን የካናሪ ደሴቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለመጨረሻ ጊዜ የአፍሪካ ጉብኝት የተደረገው በ2023 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን እና ደቡብ ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት ነበር።
አንጎላ እና ካሜሩን በ2009 በጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛው፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ1982 በዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተጎብኝተዋል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ

5 months ago