Logo
YenetaTube
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የዩክሬን ጦርነት እንዲያበቃ ዳግመኛ ጥሪ አቀረቡ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመጀመሪያ የገና በዓል ንግግራቸው ዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነቱን ለማቆም ቀጥተኛ ንግግር እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

ሊቀ ጳጳሱ በቫቲካን ከተማ ለተሰበሰቡ ምእመናን ባደረጉት ንግግር በዓለም ዙሪያ ያሉ ግጭቶች ሁሉ እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ በተለይም ስለ ዩክሬን ሲናገሩ "የጦር መሣሪያ ጩኸት ይቁም" ብለዋል።

የሚመለከታቸው አካላት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ቁርጠኛ፣ ቅን እንዲሁም ቀጥተኛ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ጦርነቱን ለማስቆም በአሜሪካ የሚመራው የሁለቱ ሀገራት ድርድር በቀጠለበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስምምነት እውን እንዲሆን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረገች ቢሆንም፤ እስካሁን በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ቀጥተኛ ውይይት አለመካሄዱ ተመልክቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የድንበር ግጭቶች የተከሰቱባቸው በሌሎች የዓለም ክፍሎች ያሉ ብጥብጥ እና ግጭቶችን አውግዘው ሰላም እንዲሰፍን ተማፅነዋል።

በተለይም የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የጥንት ወዳጅነት እንዲታደስ፣ እርቅ እና ሰላም እንዲሰፍን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መጠየቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

@ጋዜጣ_ፕላስ

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.