Logo
Getu Temesgen
የፖፕ ሊዮ ጥሪ
#ethiopia | ፖፕ ሊዮ "ጸረ ሴማዊነት እና መድልዎ የሌለባት ዓለምን እመኛለሁ" ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የሆሎኮስት (Holocaust) መታሰቢያ ቀንን አስመልክተው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ዓለም ከጥላቻና ከዘር መድልዎ እንድትጸዳ ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት "በዚህ ዓመታዊ መታሰቢያ ሁሉን ቻይ አምላክን ጸረ ሴማዊነት (antisemitism) የሌለባት ዓለምን እንዲሰጠን እለምነዋለሁ" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ፖፕ ሊዮ የዓለም መሪዎች የዘር ማጥፋት (Genocide) አሰቃቂ ድርጊት በየትኛውም ሕዝብ ላይ ዳግም እንዳይከሰት ምንጊዜም ንቁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ጳጳሱ ከጸረ ሴማዊነት ባለፈ በማንኛውም የሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም መድልዎ፣ ጭቆና እና ስደት እንዲቆም ጸልየዋል።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና በአይሁድ ዕምነት ተከታዮች መካከል የነበረው የዘመናት ቅራኔ ላለፉት አስርተ ዓመታት እየተሻሻለ መምጣቱን ሪፖርቱ ጠቁሟል።

ይህም እ.ኤ.አ. በ1965 የወጣውንና ግንኙነታቸውን የቀየረውን 'Nostra aetate' የተሰኘውን ታሪካዊ ሰነድ ተከትሎ የመጣ ነው።

"ቤተክርስቲያን ጸረ ሴማዊነትን በጭራሽ አትታገስም፤ በወንጌል መሰረትም ትታገለዋለች" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቋማቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸረ ሴማዊነትና የጥላቻ ንግግሮች እየጨመሩ መምጣታቸው ለቫቲካን ትልቅ ስጋት ሆኗል።

ፖፕ ሊዮ ባለፈው ግንቦት ወር የ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተከታዮች ያሏት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ከሆኑ ጀምሮ፣ ይህንን የጥላቻ ድርጊት ደጋግመው ሲያወግዙ መቆየታቸው ይታወሳል።
#popeleoxiv #vatican #holocaustremembrance #antisemitism #worldnews #ርዕሰ_ሊቃነ_ጳጳሳት #ቫቲካን #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.