Logo
Getu Temesgen
ከንቲባ ከድር ጁሀር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተሸለሙ

📌በ፵፬ ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ለድሬዳዋ አሰተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የእውቅና ሽልማት አበረከተች።
#ethiopia | ሽልማቱን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለከንቲባው ተወካይ ለአቶ ገበየሁ ጥላሁን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አስረክበዋል።

ከንቲባ ከድር ጁሀር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ኢትዮጵያ ለምታከናውነው ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለ አድሎ በፍትሐዊነት መንግሥታዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ሽልማት የተበረከተላቸው።

EOTC

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.