Logo
FIDEL POST NEWS
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው፦ "ጦርነት የቪዲዮ ጌም አይደለም"

የካቶሊክ ​ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳሱ መገናኛ ብዙኃን ጦርነትን እንደ ቪዲዮ ጌም በማቅረብ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ እንዳይሆኑ አስጠነቀቁ።

ቅዱስነታቸው ትናንት መጋቢት 9,2018 ዓ. ም ለጣሊያን የቴሌቪዥን ባለሙያዎች በሰጡት መግለጫ፣ ጋዜጠኞች በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎችን ስቃይና እውነተኛውን የጦርነት ገጽታ ለዓለም እንዲያሳዩ አሳስበዋል።

​ይህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትችት በተለይ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ የሚካሄደውን ጥቃት ለማስተዋወቅ ከቪዲዮ ጌምና ከአክሽን ፊልሞች የተቀነጩ ምስሎችን መጠቀሙን ተከትሎ የመጣ ነው።

የቺካጎው ካርዲናል ብሌጅ ሱፒች በበኩላቸው፣ የኋይት ሀውስ ድርጊት "አስጸያፊ" መሆኑን ገልጸው፣ የሰው ልጆች ሕይወት የሚጠፋበት ጦርነት እንደ መዝናኛ መቅረቡን ኮንነዋል።

​በአሁኑ ወቅት የአሜሪካና የእስራኤል ሚሳኤሎች በኢራን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት ከ1,000 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይነገራል።

ይህ በኢራን ላይ የተከፈተው ጦርነት በአሜሪካ የውስጥ ፖለቲካና በሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ክፍፍል እየፈጠረ ይገኛል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.