9 hours ago
ጆርዲ በዛብህ የፌስቡክ ተጠቃሚን አስመልክታ የሰጠችው አስተያየት አነጋጋሪ ሆነ
#fastmereja I የሴቶች መብት ተሟጋቿ ጆርዲ በዛብህ ከፌስቡክ ማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ራሷን ካገለለች ሁለት ዓመታት እንደሞላትና ወደ መድረኩ የመመለስ ፍላጎት እንደሌላት አስታወቀች።
ተሟጋቿ ይህን የተናገረችው የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀምንና የፌስቡክ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ባህሪ አስመልክታ በሰጠችው ግልጽና ጠንከር ያለ አስተያየት ነው።
ጆርዲ በዛብህ በሰጠችው አስተያየት "ፌስቡኬን ከዘጋውት ሁለት አመት አልፎኛል፣ የፌስቡክ ነገር በቅቶኛል፣ የመጨረሻ ፋ* ራ ህዝብ ነው ፌስቡክ ላይ ያለው፣ አ ህያ ነው የተሰበሰበበት።" ስትል ሃሳቧን ገልጻለች።

15 hours ago
አሳዛኝ የሐዘን ዜና | የሊዮኔል ሜሲ አባት ሆርሄ ሜሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::
የዓለማችን ታላቁ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ አባት እና ዋና ወኪል የሆኑት ሆርሄ ሜሲ (Jorge Messi) በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይፋ ሆኗል።
የልጁን ስኬታማ የእግር ኳስ ህይወት እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በቅርበት ሲመሩ የቆዩት አባት ሆርሄ ሜሲ፣ በትውልድ ከተማቸው ሮዛሪዮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው አርብ ነሐሴ 01 (August 7) ምሽት 4:00 ገደማ ሕይወታቸው ማለፉን የሜሲ ቤተሰቦች እና የአርጀንቲና መገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል።
እንደ ዴይሊ ሜይል (Daily Mail) እና ዘ ሰን (The Sun Football) ዘገባዎች ከሆነ፣ ይህ መረጃ በቤተሰቦቹ በኩል ይፋ የተደረገ እና ተረጋገጠ ነው።
ሆርሄ ሜሲ ላለፉት በርካታ ወራት ከልብ እና ከነርቭ ህመም ጋር ተያይዞ በጽኑ ሲታመሙ የቆዩ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው የህክምና ሁኔታቸውን ከሚዲያ እይታ ውጪ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።
በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ወቅት ሜሲ በሜዳ ላይ ያሳየው የተለየ የሐዘን ስሜት እና እንባ፣ ከአባቱ የጤና ሁኔታ ጋር የተያያዘ እንደነበር ይታወቃል።
ሆርሄ ሜሲ ለአልቢሴሌስቴው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ የአባትነት ሚናቸውን ከመወጣት ባለፈ፣ ገና በወጣትነቱ ከሮዛሪዮ እስከ ባርሴሎና እና ባሻገር ላስመዘገባቸው ድንቅ ስኬቶች እና ግዙፍ የቢዝነስ ግዛቶች ዋና መሃንዲስ በመሆን የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።
ይህ ወቅት ለሜሲ ቤተሰቦች እና ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብ እጅግ ከባድ አጋጣሚ በመሆኑ፣ ለሊዮኔል ሜሲ፣ ለእናቱ ሴሊያ ኩቺቲኒ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ ፈጣሪ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እንመኛለን።
ነፍስ ይማር!
Via Daily Mail , The Sun Football
Seledadotio

18 hours ago
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ባለፈው ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት አቶ አበበ አካሉ እና አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ ላይ ፍርድ ቤት የ12 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ፣ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ችሎቱ ለዛሬ ቀጥሮ ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከማስተላለፉ አስቀድሞ፤ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ማመልከቻው ያካተተውን እና ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋር ያደረጓቸውን ቃለ ምልልሶች ሊንኮች በትላንትናው ዕለት እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።
የፌደራል ፖሊስ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ማመልከቻ ላይ ተጠርጣሪዎቹ “የብሔር እና የሃይማኖት ግጭትን ለመፍጠር በማሰብ በውጭ ሀገር በሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ነበር” የሚል ውንጀላ አቅርቦ ነበር።
ከመገናኛ ብዙሃኑ መካከል በፖሊስ ማመልከቻ ላይ በስም የተጠቀሱት አንከር ሚዲያ፣ ኢትዮ ፎረም እና ኢትዮ 360 መገናኛ ብዙሃን ናቸው።
ከመገናኛ ብዙሃን ጋር የተደረጉ ቃለ ምልልሶችን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት፤ ፖሊስ ሊንኮቹን ለችሎቱ ማቅረቡን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋር አድርገዋቸዋል የተባሉትን ቃለ ምልልሶች ያደመጠው ፍርድ ቤቱ፤ ንግግሮቹ በሽብር ወንጀል ለመጠርጠር “መነሻ ይሆናሉ” ማለቱን አቶ ሰለሞን አስረድተዋል።

22 hours ago
u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) u12a8u12a6u1262u12a4u1295 u130bu122d u12ebu12f0u1228u1309u1275 u1246u12edu1273 u12adu134du120d 2 - u12dbu122c u121du123du1275 2u136130 u1260u1201u1209u121d u12e8u134bu1293 u121au12f2u12eb u12aeu122du1356u122cu123du1295 u12a0u121bu122bu132eu127d u12edu1320u1265u1241u1295","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[],"color_ranges":[]},"id":"UzpfSTEwMDA2OTY3MjY0MTY1OTpWSzoxMDM2MjgxMDM1Njk4MzM2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦቢኤን ጋር ያደረጉት ቆይታ ክፍል 2 - ዛሬ ምሽት 2፡30 በሁሉም የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አማራጮች ይጠብቁን
22 hours ago
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን
***************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦቢኤን ጋር ያደረጉት ቆይታ ክፍል 2
በሁሉም የኢቢሲ እና የዶትስትሪም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች
ዛሬ ምሽት 2፡30 ይጠብቁን
#pmoethiopia
1 day ago
አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ
በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እንዲከታተሉ አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ እና በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ብይን ተሰጠ።
አቃቢ ህግ በከፍተኛ የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾች እና ጠበቃቸው፣ የተከሰሱበት የክስ መዝገቡ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ እና በችሎት ውሳኔ ያልተሰጠበት ሆኖ እያለ በሚዲያ ላይ በመቅረብ ከክሱ አውድ ውጪ የሆነ ማብራሪያ በመስጠታቸው የፍትሕ ሂደቱን ተጽዕኖ ውስጥ ለመክተት እና ምስክሮችን ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ሞክረዋል በሚል የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ከማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የሚል አቤቱታ አቅርቦ ነበር።
በተጨማሪም ዘገባው የተጫነበት ሚዲያ ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ቪዲዮውን እንዲያወርድ ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 457 ስር በቀጥታ እንዲቀጡ እንዲወሰን የሚሉ አቤቱታዎችንም አቃቢ ህግ አካቷል።

በሁለቱ የኢሕአፓ ፖለቲከኞች እና በተቃዋሚዎች ጠበቃው አበራ ንጉሥ ላይ 12 የምርመራ ቀናት ተፈቀደ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት "በሽብር ወንጀል" የተጠረጠሩት ፖለቲከኞቹ አበበ አካሉ እና ይሳቅ ወልዳይ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉሥ ላይ የ12 የምርመራ ቀናት መፍቀዱን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዛሬ አርብ ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ የተሰየመው ችሎት የመርማሪ ፖሊስን ጥያቄ የተቀበለው፣ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ለተነሳው ጥርጣሬ በማስረጃነት የቀረቡት ቃለ መጠይቆች ላይ "የሽብር መነሻ ሐሳብ በማግኘታቸው" እንደሆነ ጠበቃው ገልጸዋል።
ሁለቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ፖለቲከኞች እና ለተቃዋሚዎች ጥብቅና በመቆም የሚታወቁት አበራ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰኞ ሐምሌ 27 ነበር። በፌደራል ፖሊስ አባላት በተያዙ ሁለተኛው ቀን ረቡዕ ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።
መርማሪ ፖሊስ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ "በመንግሥት የፀጥታ ተቋማት እና በመንግሥትት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የሽብር ጥቃት" ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለፍርድ ቤት ገልጿል።
ድርጊቱን ሊፈጽሙ የነበሩት "ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ድብቅ ግንኙነት በማድረግ" እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ፤ "ጽምዶ [ተ]ብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር በቀናጀት" ምልመላ እና ስለላ ሲያከናውኑ እንደነበር በመጥቀስም ወንጅሏል።
በዚህ ጉዳይ ላይ "ሥራውን አጠናቅቆ መዝገቡን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለመላክ" እንዲችልም 14 የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ፣ በሦስቱ ግለሰቦች ላይ የቀረበውን ውንጀላ ለማስረዳት በቀረቡት በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የተደረጉ ቃለ መጠይቆች 'የሽብር ይዘት አላቸው ወይስ የላቸውም' የሚለውን ለመወሰን ለዛሬ አርብ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት በመርማሪ ፖሊስ ቀረቡትን "የሐሰት ፕሮፓጋንዳ" ቪድዮ ሊንኮች መመልከቱን እንደገለጸ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ዳኞች በቀረቡላቸው የቪዲዮ ሊንኮች ላይ "የሽብር ይዘት" የሚያገኙ ከሆነ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ሊፈቀድ እንደሚችል፤ ካልሆነ ደግሞ በዋስትና ሊወጡ ይችሉ እንደነበር ጠበቃው አስረድተዋል።
እንደ ጠበቃው ገለጻ፣ ቪዲዮዎቹን የተመለከቱን ዳኞች ለፖሊስ ጥርጣሪ "መነሻ የሚሆኑ ይዘቶችን አግኝተናል" ብለዋል።
ዳኞች "በሰማነው ድምፅ ላይ ድርጊቱ የሽብር ሊመስል የሚችል የመነሻ ሀሳብ አግኝተናል። በተወሰነ መልኩ የመነሻ ሀሳብ ስላገኘን ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል" እንዳሉ ጠበቃው አስረድተዋል።
በዚህም መሠረት መርማሪ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ ተጠርጣሪዎቹ "ፍርድ ቤት ከቀረቡበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ የ12 ቀን የምርመራ ጊዜ" መፍቀዳቸውን ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ በቀጣዩ በሚኖረው ቀጠሮ ላይ "ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ" እንዲቀርብ ትዕዛዝ መሰጠቱንም ጠበቃ ሰለሞን ተናግረዋል።
BBC Amharic

የኢትዮጵያ የትምባሆ ቁጥጥር ዳሽቦርድ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | የትምባሆ ምርቶችን ጎጂነት ለመግታትና በዘርፉ የሚከናወኑ የሕግ ማስከበር ሥራዎችን በመረጃ ላይ የተመሠረቱ ለማድረግ ያለመው የትምባሆ ቁጥጥር ዳታ ኢኒሼቲቭ ዳሽቦርድ ይፋ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ፣ የጤና፣ ልማት እና ፀረ-ወባ ማኅበር እንዲሁም የመቋሚያ የማኅበረሰብ ልማት ድርጅት በጋራ በመሆን ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፣ የትምባሆ አጠቃቀምንና የኢንዱስትሪዎችን ተፅዕኖ ለመግታት መረጃን በአንድ ማዕከል ማሰባሰብ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተመልክቷል።
ይህ አዲስ የተበገገው ዳሽቦርድ በተለይም መረጃዎችን በሀገራችን የሥራ ቋንቋ በአማርኛ አካቶ ማዘጋጀቱ መረጃው ለፖሊሲ አውጪዎች ብቻ ሳይሆን ለሚዲያዎች፣ ለተመራማሪዎችና ለሰፊው ሕብረተሰብ ያለ ምንም የቋንቋ መሰናክል በቀላሉ እንዲደርስ ያስችላል።
በውስጡም የትምባሆ ተጠቃሚነት ስርጭትን፣ የሕገ-ወጥ ንግድ ሁኔታዎችን እንዲሁም ታክስ በጤና እና በሀገር ገቢ ላይ የሚያመጣውን አወንታዊ ተፅዕኖ የሚያሳዩ አገራዊ የምርምር ውጤቶችን ያካተተ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ዜጎች ከትምባሆ ሱስ የሚላቀቁበትንና ከምልሰተ-ሱስ የሚጠበቁበትን መንገድ የሚያመቻቹ መረጃዎች በውስጡ ተካተውበታል።
የትምባሆ ኢንዱስትሪዎችን የተቀናጀ እንቅስቃሴ በወቅቱ ለመቆጣጠር መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የማዘመን፣ ዳሽቦርዱን እስከ ታችኛው የመዋቅር ደረጃ ድረስ የማድረስና አቅም የመገንባት ሥራዎች በቀጣይ ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
ባለድርሻ አካላትም ይህንን ዝግጁ መረጃ በመጠቀም ሕግ የማስከበር፣ የግንዛቤ ማስጨበጥ እና ተጨማሪ የምርምር ሥራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።
#tobaccocontrol #publichealthethiopia #efda #tdi #tobaccodatainitiative #healthdevantimalaria

Sponsored by
Surafel
2 days ago
ተወዳጇ አርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ በነፃ ለSUSU HUMAN HAIR አምባሳደር ሆነች!!!
በህይወቴ ብዙ ፈተናዎችን እና ተስፋ የሚያስቆርጡ ውጣ ውረዶችን አሳልፌያለሁ። ነገር ግን ከልጅነቴ ጀምሮ ያሰብኩትን ነገር ከማሳካት የሚያስቆመኝ ምንም አይነት ችግር ሆነ ፈተና አልነበረም።
በስደት ሀገር እንደማንኛውም ስደተኛ ሰው ቤት ተቀጥሬ እሰራ ነበር። ከዛ በመውጣት የራሴን ስራ ለመስራት ሞከርኩ። በትንሽዬ የሴቶች የውበት ሳሎን በመጀመር፣ በሊባኖስ ዋና ከተማ ታዋቂ የሂውማን ሄር (Human Hair) አስመጪ እስከመሆን ደረስኩ። ህይወቴ እየተለወጠ፣ እያደግኩ እና እየተሳካልኝ ሲመጣ በማህበራዊ ሚዲያ (በቲክቶክ) ብቅ አልኩ በሀቢባ ቤት LIVE በመግባት እውቅናንም ማግኘት ጀመርኩ ሀቢባ ታዋቂ ለመሆኔ ምክንያት ሆነችኝ። ያኔም ነው ቬሮኒካ አዳነ ያወቀችኝ እንደምወዳት እና አድናቂዋ እንደሆንኩኝ በሷ ሙዚቃ በምሰራቸው ቪድዎች አየች ኮሜንት ለመጀርያ ጊዜ ስትፅፍልኝ የነበረውን ስሜት አልረሳውም። በቬሮኒካም ምክንያት በደንብ ታዋቂ መሆን ጀመርኩ፤
በዚያም ብዙ ወዳጆችን በማፍራት ስሜ በሀገሬ በኢትዮጵያም መታወቅ ጀመረ፤ ተደራሽነቴ እየሰፋ ሄዶ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ያሉ ደንበኞችን ማፈራት ቻልኩ። የመጀመሪያ ልጄንም በዚህ ስራ ላይ እያለሁ ወለድኩ፤ ይህም ይበልጥ ጠንካራ አደረገኝ።
ነገር ግን፣ ምንም በማላውቀው ምክንያት
ሁለት ወር እስራት ገጠመኝ ከዛ በኋላ ከእስር ቤት ወጥቼ ወደ ሀገሬ ገባው በህይወቴ ትልቁን ፈተና የተፈተንኩት ያኔ ነበር ለአስር ዓመታት የለፋሁበትን ህይወት፣ ስራዬን እና ከልጄ ጋር የነበረኝን አንድነት እንደ ቀልድ አጣሁት።
እውነት ለመናገር ያኔ ተስፋዬ ተሟጦ አልቆ ነበር። ነገር ግን ፈጣሪ ሁሌም አለ፤ አይተወኝም። ጠንካራ ሴት ነኝና በህይወቴ እንደ ሀቢባ እና ቬሮኒካ አዳነ ያሉ ጠንካራ ሴቶችን ላከልኝ። ልወድቅ ስል ደገፉኝ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉ ውድ የኢትዮጵያ ህዝቦችና የሚወዱኝ ሰዎች ትልቅ ድጋፍ ሆኑኝ።
ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በኋላ፣ የምወዳት እና የማደንቃት አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ በህይወቴ የማልረሳውን ትልቅ ውለታ ውላልኛለች፤ *«የሁለት ዓመት በነፃ ያለ ምንም ክፍያ የ’ሱሱ ሂውማን ሄር’ (Susu Human Hair) አምባሳደር ነኝ»* ብላ ሰርፕራይዝ አደረገችኝ። ይህ የህይወቴ ትልቁ ሰርፕራይዝ ነበር! ልጄም ወደ ሀገሩ ተመለሰ። በሀቢባ፣ በወዳጆቿ እና በአድናቂዎቼ አማካኝነትም የገንዘብ ድጋፍ ተደረገልኝ።
አሁን የህይወቴ ትልቁ ምዕራፍ ላይ እገኛለሁ። የሂውማን ሄር መሸጫዬን እና የውበት ሳሎኔን እዚሁ ሀገሬ ላይ ልከፍት ነው። ቬሮኒካ አዳነ የ2 ዓመት አምባሳደሬ ሆና በነፃ ትሰራለች፤ ከቻይና ሂውማን ሄር ኩባንያ ጋርም አብሬ እየሰራሁ እገኛለሁ።
አሁን ማንም ሊያስቆመኝ አይችልም! ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላም ከፍ እንድል ምክንያት ሆነውኛል
ከፈተናዎች ማዶ የተገነባ ስኬት:- የሱመያ ዋሪስ የህይወት ጉዞ
እኔ SUSU HUMAN HAIR ነኝ።

በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ።
የተላለፈው መግለጫ ከዩቲዩብ እንዲወርድ እና ይቅርታ እንዲጠየቅ ፍርድ ቤቱ አዟል።
ዐቃቤ ሕግ አርቲስቶቹ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ በመስጠታቸው የዋስትና መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉና ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።
ዛሬ ነሀሴ 01 2018 ዓ/ም ጠዋት በነበረው ችሎት ተጠርጣሪ አርቲስቶቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ለዐቃቤ ሕግ አቤቱታ በጽሑፍ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ለምን መግለጫ እንደሰጡም ለችሎቱ የቃል ማብራሪያ አቅርበዋል።
አርቲስቶቹ በማብራሪያቸው ድርጊቱን የፈጸሙት በማኅበራዊ ሚዲያ ከሚደርስባቸው ስም ማጥፋትና መልካም ስም ከማጉደፍ ራሳቸውን ለመከላከል አስበው እንደሆነ አስረድተዋል።
ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለከሰዓት 9:00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፤ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠትና ማብራሪያ ማቅረብ ጥፋት መሆኑን አመልክቷል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ለሚጠፋ ስም መልስ ለመስጠት እንኳን ቢሆን ድርጊቱን ፈጽሟል የሚሉትን አካል በሕግ መጠየቅ ሲገባ መግለጫ መስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ ጠቁሟል።
ሆኖም «በጥቃቅን ጥፋቶች የዋስትና መብትን ማገድ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም» ሲል ዐቃቤ ሕግ የተከሳሾች የዋስትና መብት ተነስቶ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።
በተጨማሪም አርቲስቶቹና ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት ድርጊቱን ሆን ብለው የፈጸሙት በመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 457 መሠረት እንዲቀጡ፣ ወይም በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ እንዲመሠረትባቸው ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም።
በዚህም መሠረት መግለጫ የሰጡት አርቲስቶች ሌላ ጊዜ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጽሙ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በሌላ በኩል «እግረኛው» በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ እንዲተላለፍ ያደረገው አቶ ተክለሃይማኖት አዳነ ቪዲዮውን ከዩቲዩብ (YouTube) ላይ እንዲያወርድና ይቅርታ እንዲጠይቅ ፍርድ ቤቱ አዟል።
የመደበኛው የሕግ ሂደት ቀጠሮ ለጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም የተቀጠረ መሆኑ ታውቋል።
ገዛ ጌታሁን

በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች ላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት ቀጠሮ ተሰጠ።
በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ መጠነ ሰፊ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ታዋቂ አርቲስቶች፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
ነገር ግን ተከሳሾቹ "እግረኛው" በተሰኘ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ቀርበው መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ ዐቃቤ ሕግ ባለ 5 ገጽ የክስ አቤቱታ አቅርቦ ስለነበር ጉዳዩ ከሰዓት በኋላ በሌላ ችሎት እንዲታይ ተደርጎ ፣ ለዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ጠዋት በነበረው ችሎት ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነን ጨምሮ አርቲስቶቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ዐቃቤ ሕግ ላቀረበው አቤቱታ በጽሑፍ ምላሽ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ለምን መግለጫ እንደሰጡ የቃል ማብራሪያ አቅርበዋል።
ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ፦ "እኛ የኪነ ጥበብ ሰዎች ነን፤ ነገር ግን በመልካም ስማችን ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ስለተከፈተብንና ስማችን በመጥፋቱ ሥራችን ስለተበላሸ ነው ምላሽ ለመስጠት የተገደድነው" ብለዋል።
"ለምሳሌ በዚህ ምክንያት አምስት የሥራ ውሎች ተቋርጠውብኛል፤ እኔና ጓደኛዬ የምንሰራው የቴሌቪዥን ፕሮግራምም እንዲቋረጥ ተደርጓል" ሲል አርቲስት ይገረም ደጀኔ ለችሎቱ አብራርቷል።
በነበረው መግለጫ የፍርድ ቤቱን የሕግ ሂደት እንዳያስተጓጉሉ ጥንቃቄ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።
አርቲስቶቹን በማኅበራዊ ሚዲያ አናግሮ መግለጫቸውን ያስተላለፈው ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በበኩሉ፦ "እኔ ይህን ፕሮግራም ሳቀርብ የመጀመሪያዬ አይደለም፤ አርቲስቶቹ በሕግ ከመያዛቸው አስቀድሞ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን በፊንቴክ ዙሪያ ተገልጋዮች ስለሚያነሱት ቅሬታ ጠይቄ ሰርቻለሁ፤ ከዚያ በኋላም አርቲስቶቹን ጥፋተኛ አድርገው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚዘግቡትን መረጃዎች መነሻ በማድረግ የጠየቅኋቸው ሰዎች አሉ። አሁን እነሱን ያናገርኩት ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የፍትሕ ሂደቱን እንደማይጎዳ የሕግ ባለሙያ አማክሬ ነው" ሲል ለችሎቱ አስረድቷል።
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የተሰጠው መግለጫ ከፍርድ ቤት ውጭ ውሳኔ መስጠት እንደሆነና በሕግ ሂደት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት በሕግ ወንጀል መሆኑ መደነገጉን አብራርቷል።
ቀጥሎም "ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ የአርቲስቶችን ጠበቃ ስለ መዝገቡ ጠይቆ ጠበቃው 'በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ አልሰጥም' ሲሉ 'ፈሪ ነህ ማለት ነው?' በማለት ተናግሯል፤ ይህም የተሳሳተ አካሄድ ነው።
ማንም ቢሆን መግለጫ መስጠት በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ አያውቅም ተብሎ አይገመትም፤ “የመጣው ይምጣ” በሚል ስሜት የተሰጠ መግለጫ እንደሆነ ስለምናምን፣ ፍርድ ቤቱ በአቤቱታው ላይ የተጠቀሱትን መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥልን" ሲል ጠይቋል።
ዐቃቤ ሕግ ከትላንት በፊቱ ችሎት በጽሑፍ ባቀረበው አቤቱታ፦
• የተከሳሾች የዋስትና መብት ተነስቶ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ፣
• የወንጀል ድርጊቱን ሆን ብለው የፈጸሙት በመሆኑ፣ ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖትን ጨምሮ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸሙ ተጠይቀው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 457 መሠረት እንዲቀጡ፣
• ፍርድ ቤቱ ቀጥታ የማይቀጣቸው ከሆነ፣ ዐቃቤ ሕግ በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ እንዲመሠረትባቸው እንዲያደርግ፣
• በተላለፈው ቪዲዮ ላይ ይቅርታ ተጠይቆ ከማኅበራዊ ሚዲያ እንዲወርድ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት፣ የሚሉ ነጥቦች ይገኙበታል።
ግራ ቀኙን ያደመጠው ችሎቱ የቀረቡትን አቤቱታዎች መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ ለ«ሱሱ ሂውማን ሄር» የሁለት ዓመት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነች!
#fastmereja :-በስደት ሀገር ከነበረ ከባድ የህይወት ውጣ ውረድ እና የእስራት ፈተና በመውጣት በጠንካራ ማንነቷ የራሷን ስኬት መገንባት የቻለችው ስራ ፈጣሪ ሱመያ ዋሪስ፣ በሀገሯ አዲስ የንግድ ምዕራፍ መጀመሯን በዛሬዉ እለት አስታወቀች።
በስደት ሀገር በሰው ቤት ተቀጣሪነት በመጀመር፣ በኋላም በሊባኖስ ዋና ከተማ በትንሽ የሴቶች ውበት ሳሎን ተነስታ ታዋቂ የሂውማን ሄር (Human Hair) አስመጪ መሆን የቻለችው ሱመያ፤ የማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) አጠቃቀሟ እና ከአርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ የተደረገላት ድጋፍ ለስኬቷ ትልቅ መንገድ መክፈቱን ገልጻለች።
በጉዞዋ ላይ ባጋጠማት ድንገተኛ የእስራት ፈተና ላለፉት 10 ዓመታት የደከመችበትን ሀብትና ንብረት ብታጣይም፣ ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ ከተመለሰች በኋላ በፈጣሪ እርዳታ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባሉ ኢትዮጵያውያን፣ በወዳጇ ሀቢባ እንዲሁም በአርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ ያልተቋረጠ ደጋፊነት መልሳ መቆም እንደቻለች ገልፃለች።
ድምጻዊ እና አርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ ለሱመያ ዋሪስ ባደረገችላት ትልቅ ሰርፕራይዝ፣ ለ«ሱሱ ሂውማን ሄር» (Susu Human Hair) ለሁለት ዓመታት ያህል ያለ ምንም ክፍያ በነፃ የብራንድ አምባሳደር ሆና ለመስራት ተስማምታለች።
በተጨማሪም ሱመያ ዋሪስ በሀገሯ ኢትዮጵያ ግዙፍ የሂውማን ሄር መሸጫ እና ዘመናዊ የውበት ሳሎን ለመክፈት ዝግጅቷን ያጠናቀቀች ሲሆን፣ ጥራት ያላቸውን የፀጉር ምርቶች በቀጥታ ከቻይና ግዙፍ የሂውማን ሄርኩባንያዎች ጋር በመስራት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ደንበኞች ለማቅረብ ስምምነት ላይ መድረሷ ተገልጿል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ በድጋሚ ለመክፈት ዝግጅቷን ማጠናቀቋን እንዲሁም ከቻይና ሂውማን ሄር ኩባንያ ጋር አብራ መስራት መጀመሯን አክላ አስታውቃለች።
ወደፊትም ተደራሽነቷን በማስፋት በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ቅርንጫፎችን የመክፈት እቅድ እንዳላትም ነዉ የገለፀችዉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት 118.91 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት አስመዝግቦት የነበረውን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን አብዛኞቹን ዋና ዋና ግቦች በላቀ ደረጃ ማሳካት መቻሉን እና በተለይም በአዳዲስ ደንበኞች ትስስር ረገድ በተቋሙ ታሪክም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ውጤት ማስመዝገቡን ይፋ አድርገዋል።
በበጀት ዓመቱ 800 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ 664 ሺህ 505 አባወራዎችን በማገናኘት የ83.1 በመቶ ስኬት ተመዝግቧል።
ይህም አፈጻጸም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ32.5 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ ተቋሙን በዓይነቱ ከአፍሪካ መሰል የኃይል አቅርቦት ኩባንያዎች የመሪነት ደረጃ ላይ አሰልፎታል።
በተጨማሪም የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሙን በማጠናከር ከዋናው ግሪድ እና ከኦፍ-ግሪድ የፀሐይ ኃይል አማራጮች 205 አዳዲስ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም በአገሪቱ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ተደራሽ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን ቁጥር ወደ 7 ሺህ 908 አድርሶታል።
በፋይናንስና በገቢ አሰባሰብ ረገድም ተቋሙ አስደናቂ ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን፣ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዳዲስ ደንበኞች መስተንግዶና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 115.86 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 118.91 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የ103 በመቶ አፈጻጸም አሳይቷል።
ይህ የገቢ መጠን ከቀደመው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ88.4 በመቶ ከፍተኛ እድገት ያሳየ ነው። ለዚህ አፈጻጸም መሻሻል የዲጂታል ክፍያ አማራጮች መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ክፍያ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር 95.3 በመቶ ደርሷል።
በተጨማሪም ተቋሙ ከስርቆትና ከኃይል ብክነት የመከላከል ሥራዎችን በማጠናከር ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ለተቋሙ ገቢ ማድረግ ችሏል።
ተቋሙ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማሻሻያ፣ የትራንስፎርመር ጥገናና የአቅም ማሳደግ ሥራዎችን ያከናወነ ቢሆንም፣ አሁንም የመሰረተ ልማት እርጅና፣ የግብዓትና የነዳጅ እጥረት እንዲሁም የመሰረተ ልማቶች ስርቆትና ውድመት ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተገልጿል።
ሆኖም ተቋሙ የተደቀኑበትን ተግዳሮቶች በመቋቋም የቴክኖሎጂ ትግበራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬት የሚጠበቅበትን የላቀ ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
ጌትነት ተመስገን
#ethiopianelectricutility #eeu #ethiopia #energysector #ethiopianeconomy #digitalethiopia2030 #ruralelectrification #offgridenergy #performancereport #africaenergy

"ዋንጫውን የሸጥኩት ቁምሳጥኔ ጠቦኝ ነው" - ቤንጃሚን ሜንዲ
#ethiopia | የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ቤንጃሚን ሜንዲ በ2018 እ.ኤ.አ ያሸነፈውን የዓለም ዋንጫ ምስለኔ (replica) በጨረታ መሸጡ መነጋገሪያ ሆኗል።
ሜንዲ ይህን ክብር ያለው የዋንጫ ቅጂ በጨረታ ያቀረበው ሲሆን፣ በጨረታውም በግምት 54,000 ዩሮ ገደማ መሸጡ ተገልጿል።
የተጫዋቹ እርምጃ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችት ያስከተለ ሲሆን በርካቶች ይህንን መሰል ታሪካዊና ክብር ያለው ዋንጫ መሸጥ አልነበረበትም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
ሆኖም ለተሰነዘሩበት ትችቶች በቀልድ የታጀበ ምላሽ የሰጠው ሜንዲ፣ "ለመሆኑ ዋንጫው የእኔ ነው ወይስ የእናንተ? ዋንጫው የእኔ በመሆኑ በፈለግኩት መንገድ የማድረግ መብት አለኝ፤ ደግሞም በቁምሳጥኔ ውስጥ አላስፈላጊ ቦታ አጥቦብኝ ነበር" ሲል ለተነሳው ውዝግብ ግድ የለሽነቱን አሳይቷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አንፃራዊ መረጋጋት መፈጠሩ ተዘገበ፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው በኢትዮጵያ መከላከያ ሀይልና በትግራይ ሀይሎች መካከል ግጭት ተፈጥሮበት የነበረው በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር አካባቢ ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት ተፈጥሮበታል፡፡ አካባቢው ነዋሪዎችን በምንጭነት የጠቀሰው ዘገባው ቅዳሜ እለት በኢትዮጵያ ሸረሪና አካባቢ የተጀመረው ይህ ግጭት ለጊዜው መቆሙን ያስታወቀ ሲሆን በግጭቱ ወቅት ከባድ መሳሪያዎችና ድሮኖች ጥቅም ላይ ውለው እንደነበር አስረድቷል፡፡ ግጭቱን በተመለከተ ህወሀት የፌዴራል መንግስቱ ወታደራዊ ውጥረቱን እያባባሰ ነው የሚል ክስ ማቅረቡን የጠቀሰው ዘገባው ይሁንና የአዲስ አበባው መንግስት በዚህ ላይ እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አለማውጣቱን አስታውቋል፡፡
የአካባቢው ምንጮች ለሱዳን ትሪቢዩን እንደገለጹት፣ በሱዳን ቁጥጥር ስር ባለችው አል-ፋሻጋ አቅራቢያ በምትገኘው የኢትዮጵያዋ ሸረሪና አካባቢ ቅዳሜ ዕለት ከተቀሰቀሰው ውጊያ በኋላ በድንበር ሰርጡ ላይ ይካሄድ የነበረው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለጊዜው ቆሟል። በግጭቱ ከባድ የጦር መሳሪያዎች እና ድሮኖች ጥቅም ላይ ውለው እንደነበርም ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት ውጥረቱ ከኤርትራዋ ኦምሃጀር፣ በኢትዮጵያዋ ሁመራ አድርጎ በሱዳን እስከሚገኙት ሀምዳይት እና አላቅዲ ድረስ ያለውን የሶስትዮሽ ድንበር ያካልላል።
ሕወሓት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትን ወታደራዊ ውጥረቱን በማባባስ የከሰሰ ሲሆን፣ አዲስ አበባ በበኩሏ በቅርቡ በተከሰቱት ክስተቶች ዙሪያ እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አላወጣችም። ይሁን እንጂ አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በሰጡት ቃል፣ ግጭቱን የጀመረው ሕወሓት መሆኑን በመግለጽ፣ ቡድኑ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል ብለዋል።
ባለሥልጣኑ አክለውም ሕወሓት ከፋኖ ታጣቂዎች፣ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና ከውጭ ኃይሎች ጋር "የሶስትዮሽ ጥምረት" በመፍጠር ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ እቅድ እንዳለው ጠቁመዋል። ይህንም ኢትዮጵያን ወደ ሰፋ ያለ ቀጠናዊ ግጭት ለማስገባት ያለመ የእጅ አዙር ጦርነት ሲሉ ገልጸውታል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዜና አውታሮች ማክሰኞ ዕለት እንደዘገቡት፣ በሱዳን ከሚገኘው ሰቲት ወንዝ የ15 የሕወሓት ታጣቂዎች አስከሬን የተገኘ ሲሆን፣ በምስራቅ ሱዳኗ ዋድ አል-ሂሊዮ ከተማ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል በግጭቱ የቆሰሉ ስድስት ሰዎችን አስተናግዷል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ቴሌቪዥን የኤርትራ ጦር ጀነራሎች እና የሕወሓት ባለሥልጣናት በትግራይ ያደረጉትን ስብሰባ የሚያሳይ ምስል ያስተላለፈ ሲሆን፣ በመድረኩም የኤርትራ፣ የትግራይ እና የሕወሓት ባንዲራዎች ታይተዋል። ይህ ስብሰባ "በኤርትራ እና በትግራይ መካከል ያለ ወታደራዊ ቅንጅት" ተብሎ የተገለጸ ሲሆን፣ ጊዜውም ከኦገስት 1 ጀምሮ በኢትዮጵያ ጦር እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል አዲስ ውጊያ መጀመሩ ከተዘገበበት ወቅት ጋር ተገጣጥሟል። በስብሰባው ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከኤርትራ መንግሥትም ሆነ ከሕወሓት በኩል እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ አስተያየት የለም።
እነዚህ አዳዲስ ክስተቶች የተፈጠሩት፣ እ.ኤ.አ. በግንቦት 2025 በኤርትራ እና በትግራይ ድንበር አካባቢ ማህበረሰቦች መካከል ውይይትን ለማበረታታት ያለመው "ጽምዶ" የተሰኘው ተነሳሽነት አከራካሪ በሆነበት ወቅት ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ይህ ተነሳሽነት በፌዴራል መንግሥቱ ኪሳራ የአስመራን እና የሕወሓትን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ሲል መተቸቱ ይታወሳል። ታዛቢዎች በበኩላቸው አዲስ ጦርነት ማገርሸቱ የ2022ቱን የሰላም ስምምነት ሊያፈርስ እና ሰፊውን የአፍሪካ ቀንድ ሊያተራምስ እንደሚችል እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።

የትግራይ ሚዲያዎች ከምድር በታች ወደተቆፈረ ስቱዲዮ ተሸጋግረዋል‼️
"ጥምረቱና ትብብሩ ወደ ከፍተኛ የትግል ደረጃ ተሸጋግሯል" ሲሉ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር የሆኑት ገብረ ገብረፃድቃን(ዓዴት) በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል።
ህወሓት የፌደራል መንግስቱን በጦርነት ለመጣል ወደ ራያ እና አፋር ድንበር መካናይዝድ ጦሩን ጨምሮ እያስጠጋ የሚገኝ ሲሆን መንግስትም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።
የትግራይ ሚዲያዎች ከመሬት በታች ወደተቆፈረ ስቱዲዮ ውስጥ መግባታቸውን የመቀሌ ምንጮች ገልጸዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጃኬን አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በድርጅቱ፣ በሰራተኞቹ እና በንብረቶቹ ላይ የተፈጸሙ ተከታታይ እና ከባድ ጥቃቶችን አስመልክቶ ለአጋሮቹ፣ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ፣ ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ለመላው ህዝብ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው መሰረት ቅዳሜ ኦገስት 1 ቀን 2026 የ'አዲስ ስታንዳርድ' ዋና አዘጋጅ የሆነው ዮናስ ከድር በጸጥታ ኃይሎች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ ለ24 ሰዓታት ያህል አካላዊ ጥቃት እና የተራዘመ ምርመራ ተፈጽሞበታል። ዋና አዘጋጁ ከተለቀቀ በኋላ በደረሰበት ጥቃት ዙሪያ ዝርዝር የጽሁፍ ሪፖርት ለድርጅቱ የህግ ክፍል ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም ማስረጃ ለቀጣይ የህግ ሂደት አካል ሆኖ መያዙን አሳታሚው ገልጿል።
በማግስቱ እሁድ ኦገስት 2 ቀን 2026 ደግሞ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የጸጥታ እና የደህንነት ኃይሎች ያለምንም ህጋዊ ሂደት ወደ አዲስ ስታንዳርድ ቢሮ በመግባት በልዩ ሁኔታ ከተገነባው የፕሮዳክሽን ስቱዲዮ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የመልቲሚዲያ እቃዎች ወስደዋል። ከጥቃቱ በኋላ የድርጅቱ የሰው ሀብት አስተዳደር እና የህንፃው አስተዳደር ባደረጉት ማጣራት፣ በርካታ ፕሮፌሽናል 4K የቪዲዮ ካሜራዎች፣ ትሪፖዶች፣ የድምፅ መቅረጫ መሳሪያዎች እና ሌሎች ለስራው እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የብሮድካስት ግብዓቶች መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በስቱዲዮው የብርሃን ስርዓቶች እና በተያያዥ መሳሪያዎች ላይ ሆን ተብሎ የተፈጸመ የውድመት ድርጊት መስተዋሉን አሳታሚው ጠቁሟል። የጠፉት እና የወደሙት ንብረቶች ሙሉ ዝርዝር እና ግምት ለህግ ሂደት እንዲያገለግል ተሰንዶ ተቀምጧል።
በድርጅቱ ላይ ያለው ጫና ይበልጥ ተባብሶ ሰኞ ኦገስት 3 ቀን 2026፣ ጃኬን አሳታሚ ላለፉት 16 ዓመታት ሲሰራበት የነበረው ህንፃ አስተዳደር በፖሊስ በተደረገበት ጫና ምክንያት ኩባንያው በሶስት ቀናት ውስጥ ቢሮውን ለቆ እንዲወጣ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዲሰጥ ተገዷል። ሆኖም የጃኬን የህግ ክፍል ይህ የማስወጣት እርምጃ ህጋዊ የውል መሰረት የሌለው እና አስገዳጅ የሆነውን የኪራይ ውል የሚጥስ መሆኑን በመግለጽ ማስጠንቀቂያውን ለመቃወም ህጋዊ እርምጃ መጀመሩን አስታውቋል።
እነዚህ ተከታታይ ክስተቶች የተፈጸሙት ጃኬን አሳታሚ የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን የ'አዲስ ስታንዳርድ'ን የኦንላይን ሚዲያ ምዝገባ ፈቃድ ለመሰረዝ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ላይ የህግ ክትትል እያደረገ ባለበት ወቅት ነው። ይህ የድርጊቶች ቅደም ተከተል ነጻ የሚዲያ ተቋማት ከማስፈራራት እና ከህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው ለመስራት ያላቸውን አቅም፣ እንዲሁም የህግ የበላይነት መኖር ላይ ጥልቅ ስጋት የሚፈጥር ነው ሲል ድርጅቱ ገልጿል።
ጃኬን አሳታሚ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የድርጅቱ የህግ ክፍል በሚያደርገው ማጣራት ላይ ሙሉ ትብብር እንዲያደርጉ፣ የተወሰደው እርምጃ ህጋዊ መሰረት እንዲገለጽ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪ አቅርቧል። እንዲሁም የሀገሪቱ የፍትህ ተቋማት የህግ ሂደትን እንዲያከብሩ እና በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠውን የሀሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የፕሬስ ነጻነት እና የህግ የበላይነት መብቶችን እንዲያስጠብቁ አሳስቧል።
ጃኬን አሳታሚ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ይህ ሁሉ ያልተጠበቀ ፈታኝ ሁኔታ ቢኖርም፣ ለነጻ፣ ሙያዊ እና የህዝብን ጥቅም ለሚያስቀድም የጋዜጠኝነት ስራ ያላቸውን ቁርጠኝነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ድርጅቱም የሰራተኞቹን ደህንነት ለመጠበቅ እና መብቱን ለማስከበር ሁሉንም ህጋዊ አማራጮች እንደሚጠቀም አስታውቋል።

3 days ago
u12a8u1218u1295u130du1225u1275 u12aeu1219u1292u12acu123du1295 u12a0u1308u120du130du120eu1275 u12e8u1270u1230u1320 u1218u130du1208u132b #u134bu1293u121au12f2u12ebu12aeu122du1356u122cu123du1295 #fanamediacorporation ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanamediacorporation
Sponsored by
Surafel
3 days ago
"በመሃል" የተሰኘው መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል
ዕዝራ እጅጉ
#ethiopia | በጋዜጠኛና ደራሲ እመቤት አብዲሳ ጅግሳ የተዘጋጀው «በመሃል» የተሰኘ የፈጠራ መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ፣ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ኧርባን ሴንተር (የከተማ ማዕከል) ይመረቃል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደራሲዋ እንግዶች፣ ወዳጆችና የሥነ ጽሑፍ አፍቃሪዎች እንደሚገኙ ሲጠበቅ፣ የመጽሐፍ ዳሰሳና ሌሎች ልዩ ልዩ የሥነ ጽሑፍ መሰናዶዎችም እንደሚካሄዱ ተገልጿል።
እመቤት አብዲሳ ጅግሳ ከተማሪነት ዘመኗ ጀምሮ ለቃላትና ለሐሳብ ያላትን ፍቅር በማዳበር ወደ ጽሑፍ ዓለም የገባች ጋዜጠኛ ናት። በጋዜጠኝነት፣ በቴሌቪዥን ሚዲያና በኮሙኒኬሽን ዘርፍ ያካበተችውን ልምድ በመጠቀም በርካታ ማኅበራዊና ባህላዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ሥራዎችን ለአንባቢዎችና ለተመልካቾች አቅርባለች።
«በመሃል» በ195 ገጾች የተዘጋጀ ሲሆን፣ 14 አጫጭር ታሪኮችንና 43 ግጥሞችን ያካተተ ነው። መጽሐፉ በ450 ብር እንደሚሸጥም ተገልጿል።
በቅርቡ በ«ንባብ ለሕይወት» ኤግዚቢሽን ላይ ለአንባቢዎች የቀረበው መጽሐፉ፣ የደራሲዋን የጽሑፍ ብቃትና የፈጠራ ክህሎት በሚያሳይ ጥራት የተዘጋጀ ሥራ መሆኑን ያነበቡት ሰዎች ገልጸዋል።

ለሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የባህልና ጥበባት አምባሳደር ሞዴል ሩት ይርጋለም ሸኝት ተደረገላት።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለምትወክለው ሞዴል ሩት ይርጋለም የእንኳን ደስ አለሽና የሽኝት መርሃ ግብር አደረገ።
ክብርት ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ለሞዴሏ መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ በድል እንድትመለስ ተመኝተዋል።
ክብርት ሸዊት በንግግራቸው ሞዴሏ የባህል አምባሳደር ሆና ከተሾመች በኋላ የሀገሪቱን ብዝሃ ባህላዊ ዕሴቶች በቅርበት ለመረዳት በተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት ማድረጓን አንስተዋል።
በዚሁ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ በመገኘት የህዝቡን ባህል፣ በአማራ ክልል ጎንደር በመሄድ የክልሉን ባህላዊ እሴቶች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ባሌ በመገኘት የገዳ ስርዓትንና ድቅ ተፈጥሮአዊ ሀብቶችን በበቂ ሁኔታ ጎብኝታለች ብለዋል።
ይህ በክልሎች ያደረገችው ቆይታ የሀገሪቱን ባህልና ጥበብ ጠልቃ እንድታውቅ የረዳት ሲሆን፣ ከ130 በላይ የዓለም ሀገራት ሞዴሎች በሚሳተፉበት መድረክ ኢትዮጵያን በብቃት ለማስተዋወቅና ገጽታዋን ከፍ ለማድረግ እንደሚያግዛት ገልፀዋል።
የገጠማትን ማንኛውንም ፈተና ተቋቁማ የሀገሯን ባህልና ጥበብ በዓለም አቀፍ አደባባይ ለማሳየት ቆርጣ የተነሳች ጠንካራ ወጣት በመሆኗ ትልቅ አድናቆትና ምስጋና እንደሚገባትም ክብርት ሸዊት ሻንካ አክለዋል።
ክብርት ሸዊት ለመላው ኢትዮጵያውያን ባስተላለፈው መልዕክት በመጪው ውድድር ላይ በሚፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ (Link) አማካኝነት ሁሉም ድጋፉን እንዲሰጥና ለሞዴሏ ስኬት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ሞዴል ሩት ይርጋለም በበኩሏ ለተደረገላት የሸኝትና መልካም ምኞት መርሀ ግብር ምስጋና አቅርባለች።
ሞዴሏ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለማስጠራት ቆርጣ እንደተነሳች በመግለፅ የገጠማት ችግር ወደሗላ እንደማይመልሳት አንስታለች።
ከዓለም አቀፉ ውድድር በሗላም በሀገሯ ያሉ ባህላዊና ጥበባዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ እደምሰራ ገልፃለች።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደር የባህልና ስፖርት ሴክተር አመራሮች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች፣ የሙያ ማህበራት አመራሮችና የሞዴሏ ቤተሰቦች ተገኝተው ለሞዴሏ የሀገር አደራ ተሰጥቷል።
Via የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

የከተማ አስተዳደሩ በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች እንዲበረታቱ ፣ የግብር ጫና እንዳይደርስባቸውና ትርፋማነታቸውን በማጎልበት ወደ ቀጣይ ደረጃ እንዲሸጋገሩ በቁርጠኛነት እየሰራ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በደረጃ ግብር ከፋዮች አከፋፈል ፣በሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች አፈታት ዙሪያ ለሚዲያ ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ።
ቢሮው ባለፉት 2 አመታት ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት ማከናወኑን በጋዜጣዊ መግለጫው የተገለፀ ሲሆን የሪፎርም ተግባራቱ መሰረታዊ ዓላማዎችም ፍትሐዊ የግብር አሰባሰብ ስርዐት መዘርጋት ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን መቅረፍ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች ጋር በተያያዘም አብዛኞቹ ግብር ከፋዮች በተቋሙ በተዘረጋ የኦንላይን የክፍያ ስርዓት መወጣታቸውና የተቀሩትም እየከፈሉ ናቸው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በከተማዋ በተለያዩ ንግዶች ፣ በኪራይና በራይድ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ ግብር ከፋዮች የሚገኙ መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን ከእነዚህ ግብር ከፋዮች በአጠቃላይ 9.2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተመላክቷል፡፡
ይህ ዓመታዊ የደረጃ ‹‹ለ›. ግብር ከፋዮች ገቢ በመንግስትና በግል ድርጅት ውስጥ ከሚገኙ ተቀጣሪ ደሞዝተኞች ዓመታዊ ደሞዝ ገቢ ግብር ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ እንደሆነ ተገልጿል
ይህም በዋነኛነት ዐላማው የከተማ አስተዳደሩ በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እንዲበረታቱ፣ የግብር ጫና እንዳይደርስባቸውና ትርፋማነታቸውን በማጎልበት ወደ ቀጣይ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ካለው አቋምና ቁርጠኛነት የመነጨ መሆኑም ተብራርቷል፡፡
በመሆኑም እስከ ሀምሌ 25 ድረስ ዓመታዊ ግብራችሁን እንድትከፍሉ መልዕክት በስልካችሁ የተላከላችሁ ግብር ከፋዮች በሙሉ እስከ ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም ድረስ የግብር ግዴታችሁን በኦንላይን በመክፈል ከቅጣትና ወለድ እራሳችሁን እንዲጠብቁ ጥሪ ተላልፏል፡፡
ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ቴክስት ያልደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እንዲሁም ከሀምሌ 25 በኃላ ቴክሰት( መልዕክት ) የተላከላችሁ ግብር ከፋዮች ወደ ቅጣት የማይገቡ በመሆኑ እስከ ነሀሴ 20/2018 ዓ.ም ዓመታዊ ግብራችውን መክፈል እንደሚችሉ በመግለፅ ቴክስት ያልተላከላቸው ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠባበቁ ቢሮው ይገልፃል ፡፡
በተያያዘም ቴክስት (መልዕክት ) ከተላከለት በኃላ ‹‹ግብር በዛብኝ›› የሚል ቅሬታ ላለው ማንኛውም ግብር ከፋይ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ቅሬታ ያለው ግብር ከፋይ በወረዳ ደረጃ ቅሬታ አቅርቦ መረጃው ለክፍለ ከተማ ከተላከ በኃላ በክፍለ ከተማ በተደራጀ የቀን ገቢ ገማች አማካኝነት ድጋሚ የቀን ገቢ ግምት በማካሄድ ቅሬታዎች የሚፈቱበት አሰራር መዘርጋቱ ተገልፆል፡፡
ከቅድመ ታክስ ክፍያ ጋር በተያያዘ ለደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በቴክስት የተላከ ዓመታዊ የግብር መጠንም ግብር ከፋዮች በቅድመ ታክስ የከፈሉትን የገንዘብ መጠን ተቀናሽ በማድረግ የተላከ እንደሆነም በጋዜጣዊ መግለጫው ተመላክቷል፡፡ በ2019 በጀት አመት እንደ ከተማ 502.27 ቢሊየን ፣ በገቢዎች ቢሮ 380 ቢሊየን ብር ገቢን በፍትሐዊነት ለመሠብሰብ መታቀዱም ተገልፆል፡፡
አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

ሊደነቅ የሚገባው ድንቅ ተግባር
ብዙ ጊዜ በየሚዲያው የምንሰማው የችግርና የቅሬታ ዜና ቢሆንም፣ ዛሬ የምናካፍላችሁ የደስታና የተስፋ ዜና ነው።
በአዲስ አበባ የካ አባዶ ደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን የተመለከትነው ግንባታ እጅግ አስደናቂ የሚባል ነው።
ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር የመሠረት ሥራ ብቻ የነበረው ይህ ግዙፍ ቤተ ክርስቲያን፣ በአንድ ዓመት ውስጥ የግንባታው ሥራ እስከ ጣሪያና ጉልላት ደርሶ መታየቱ በርካቶችን አስደንቋል።
በዚህ ዘመን ብዙ አሳዛኝ ክስተቶች በሚሰሙበት ጊዜ፣ በትጋት የሚሠራ የግንባታ ኮሚቴ፣ ሰበካ ጉባኤ እና በልግስና የሚያግዙ ምዕመናን መኖራቸው የሚያበረታታ ተግባር ነው።
የቤተ ክርስቲያኑን ግንባታ ለማጠናቀቅ አሁን የሚፈለገው ድጋፍ የፊኒሺንግ ሥራዎችን፣ በሮችና መስኮቶችን፣ አንድ መንበር (ከአራቱ መንበሮች ሦስቱ በአካባቢው ምዕመናን ተይዘዋል)፣ ምንጣፍ፣ ቅዱሳት ሥዕላት፣ የኤሌክትሪክ ሥራዎች፣ ብሎኬት፣ ጂፕሰም፣ ቀለም ሥራዎችና ንዋየ ቅድሳትን ያካትታል።
ለዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ሥርጭት መርሐ ግብር በፊታችን ነሐሴ 1፣ 2 እና 5 ቀን ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ይካሄዳል።
ድጋፍ ለማድረግ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000635044482
ስልክ፦
0911426464
በቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ላይ በመሳተፍ የታሪክ ሠሪ ትውልድ አካል እንሁን።
አድራሻ፦
የካ አባዶ መሰቀለኛው ጋር ሲደርሱ ቁልቁል ወደ ግራ በሚወስደው መንገድ መጨረሻ።
3 days ago
የቲቪ ፕሮግራም አቅራቢዋ እና የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዋ ዳናዊት መክብብ ቀርቦባት በነበረው ክስ በነፃ ተሰናበተች።
ዳናዊት ከ ኤቢኤል ኮንሰልታንሲ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ቤተልሔም ታደሰ፣ ገሊላ በለጠ እና ቤል ተስፋዬ ከተባሉ ሌሎች ተከሳሾች ጋር የፍትሐብሔር ክስ የተመሰረተባት ከወራት በፊት እንደነበረ ይታወቃል።
ቁጥራቸው 13 የሆኑ ከሳሾች «እነ ዳናዊት ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን በማለት ከእያንዳንዳችን 437,000 ብር ከተቀበሉ በኋላ ሳይልኩን ቀርተዋል» በሚል ክስ ለፍርድ ቤት አቅርበውባቸው ነበር።
«የተወሰደብንን ገንዘብ እንዲመለስልን በተለያዩ ጊዜያት የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ብንሰጣቸውም እና ጉዳዩን በጋራ መግባባት ለመፍታት ጥረት ብናደርግም ተከሳሾች ብሩን ለመመለስም ሆነ ለማስመለስ እንቢተኛ ሆነዋል» ሲሉ ባስገቡት የክስ ዝርዝር ላይ አብራርተዋል።
አያይዘውም «እኛ ከሳሾች ወደዚህ ጉዳይ በሙሉ መተማመን የገባነው አምስተኛ ተከሳሽ የሆነችው ዳናዊት መክብብ ለድርጅቱ የሰራችውን ማስታወቂያ በማመን ነው» ሲሉ በክሳቸው ላይ ጠቅሰዋል።
ለወራት ክሱን ሲመለከት የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 4ኛ የፍትሐብሔር ችሎት ትናንት ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት አራቱን ተከሳሾች ጥፋተኛ በመሆናቸው በአንድነት እና በነጠላ ገንዘቡን ሊከፍሉ ይገባል ሲል ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፣ አምስተኛ ተከሳሽ ዳናዊት መክብብ «ሥራን የሠራችው የንግድ ፈቃድ አይታ ነው፤ ስለዚህ ልትጠየቅ አይገባም» ከክሱ በነፃ ተሰናብታለች ሲል እንደወሰነ ሰምተናል።
ዘገባው የኢትዮጲካሊንክ ነው::

ዳናዊት መክብብ በፍትሐብሔር ክስ በነፃ ተሰናበተች
#fastmereja I የታዋቂዋ የቲቪ ፕሮግራም አቅራቢና የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዳናዊት መክብብ ቀርቦባት የነበረው የፍትሐብሔር ክስ ውድቅ ተደርጎ በነፃ የተሰናበተች ሲሆን፣ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች አራት ተከሳሾች ግን ጥፋተኛ ተብለው ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አራተኛ ፍትሐብሔር ችሎት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ፣ አምስተኛ ተከሳሽ ሆና የቀረበችው ዳናዊት መክብብ የንግድ ፈቃድ አይታ የማስታወቂያ ሥራ የሰራች በመሆኗ በጉዳዩ ላይ ልትጠየቅ አይገባም በሚል ከክሱ በነፃ አሰናብቷታል።
ጉዳዩ የተጀመረው 13 ከሳሾች «ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን» በሚል ከእያንዳንዳቸው 437 ሺህ ብር የተቀበላቸው የኤቢኤል ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የቤተልሔም ታደሰ፣ ገሊላ በለጠ፣ አቤል ተስፋዬ እና የዳናዊት መክብብ ክስ በመስረታቸው ነው። ከሳሾቹ የተወሰደብን ገንዘብ እንዲመለስልን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ተከሳሾቹ ሊመልሱልን አልቻሉም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አብራርተው ነበር።
እንደ ኢትዮጲካሊንክ ዘገባ ለወራት ክሱን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ፣ አራቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በነጠላና በአንድነት የተወሰደውን ገንዘብ ለከሳሾቹ እንዲከፍሉ ሲወሰን፣ ዳናዊት መክብብ ግን በነፃ ተሰናብታለች።

የኢትዮጵያ ትንሳኤ !
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብስራት አድማስ እና የዓለም ዓይኖች ማረፊያ እየሆነች ትገኛለች።
እሷ የታሪክ እምብርት፣ የሰው ዘር መገኛ እና የነፃነት ማኅተም ናት። ዛሬ ደግሞ በልጆቿ ጽናት እና በማይበገረው ህዝባዊ ወኔያቸው አዲስ የትንሳኤ ምዕራፍ እየተቀኘች ትገኛለች።
ይህ የትንሳኤ ብርሃን ለራሷ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ጥቁር ህዝብ እና ለአፍሪካ አህጉር አዲስ የብስራት አድማስ እየቀደደ ነው።
የዚህች ታላቅ ሀገር ትንሳኤ ከባዶ የተነሳ ሳይሆን፣ ከጥንታዊው የክብር ሥርዓቷ እና ካልተደፈረው ማንነቷ የተቀዳ ነው። አፍሪካ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር በነበረችበት የጨለማ ዘመን፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ብቸኛ ፋኖስ ሆና እንዳበራች ሁሉ፣ ዛሬም ያ የወርቃማ ታሪክ በዘመናዊው ትውልድ ልብ ውስጥ እንደገና እየተቀጣጠለ ይገኛል።
በመሆኑም ይህች የአናብስት ምድር የገጠሟትን ዘመናዊ ፈተናዎች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎች እና ማህበራዊ ውጣ ውረዶች በራሷ ልጆች ጥረት እና ጥንካሬ እያሸነፈች ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ህዝብ ታታሪነቱ፣ ለነጻነት ቀናኢነቱ፣ የማይበገረው ፅናቱ እና ለሀገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር አዲሱን የትንሳኤ መንገድ እያቀናው ነው።
በዚህ ጽናት ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ትንሳኤ የመላው አፍሪካም ትንሳኤ ነው። አፍሪካ ለዘመናት የድህነት፣ የጦርነት እና የተስፋ መቁረጥ ምድር ተደርጋ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስትሳል ብትኖርም፤ ኢትዮጵያ ይህንን የተሳሳተ ትረካ በተግባር እየቀየረችው ትገኛለች።
ከኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እስከ ቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶቿ፣ በአረንጓዴ ዐሻራዋ እና በኢኮኖሚ መነቃቃቷ አህጉራዊ ተምሳሌትነቷን በማደስ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም ማደግ፣ መበልጸግ እና የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ የሚያሳይ ትልቅ የብስራት አድማስ ሆኖ፣ አህጉሪቱ ወደ አዲስ የነፃነት እና የብልጽግና ምዕራፍ እንድትሻገር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው።
በዚህም የምክንያት ዛሬ የዓለም ዓይኖች ወደ እሷ እየተመለከቱ ነው። በዓለም ከሚታወቁት ግዙፍ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው የአሜሪካው ሲኤንኤን የሰሞኑ ዘገባው ይህን ያመለክታል። ይህ ዘገባ የአድናቆት እና የግርምት እይታ ነው።
በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በአቪየሽን እንዲሁም አጠቃላይ በልማት እያስመዘገበቸው ያለውን ዕምርታ በጥልቀት የዳሰሰው ሚዲያው የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ ያሳዬ ነበር፡፡ በዚህም ሀገራችን የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን እና ቱሪስቶች ቀልብ ስባለች።
ሰፊው የገበያ እምቅ አቅሟ እና ስትራቴጂካዊ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ የዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል እያደረጋት ሲሆን ፤ ከተፈጥሮ ውበቷ እስከ ጥንታዊ ስልጣኔዎቿ፣ ከላሊበላ እስከ አክሱም ዘመናትን የተሸገሩ ቅርሶቿ ደግሞ ዓለምን ማስደመማቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሩቅ ህልም ሳይሆን የዕለት ተዕለት እውነታ እየሆነ የመጣ ተጨባጭ ክስተት ነው። በራሷ ውስጣዊ ዕምቅ አቅም፣ በህዝቦቿ ላብ እና ጥረት የምታስመዘግበው ስኬት የዓለምን መድረክ እየማረከ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ትናንት የነፃነት ምልክት እንደነበረች ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ የብልጽግና እና የብስራት አድማስ ሆና በዓለም ፊት በኩራት ቆማለች ።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

የCPJ የ2026 ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አሸናፊዎች ተገለጹ
#ethiopia | የጋዜጠኞችን ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ለ36ኛ ጊዜ የሚያዘጋጀውን ዓመታዊ International Press Freedom Awards (IPFA) የ2026 ተሸላሚ ጋዜጠኞችን ይፋ አድርጓል።
የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ኅዳር 19 ቀን 2026 በኒውዮርክ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን፣ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች በድፍረታቸውና በሙያዊ ተግባራቸው ይሸለማሉ።
በዚህ ዓመት ከተሸለሙት መካከል ከሊባኖስ፣ ከኤርትራ፣ ከሀንጋሪ፣ ከኮሎምቢያ እና ከሚያንማር የመጡ ጋዜጠኞች ይገኛሉ።
ክርስቲና አሲ – ሊባኖስ
የAFP ፎቶ ጋዜጠኛ ክርስቲና አሲ በጥቅምት 2023 በእስራኤል–ሊባኖስ ድንበር ዘገባ ስትሰራ በደረሰባት ጥቃት ቀኝ እግሯን አጥታለች፤ የሮይተርስ ጋዜጠኛ ኢሳም አብዳላህም በዚያው ጥቃት ተገድሏል።
CPJ እንደሚለው፣ በዚህ ጉዳይ እስካሁን ተጠያቂ የሆነ አካል የለም። አሲ ከዚያ በኋላ ለጋዜጠኞች ደኅንነትና ለፍትሕ ድምፅ ሆና እየሠራች ነው።
"ኤርትራ 16"
CPJ በዚህ ዓመት ለ25 ዓመታት ያለ ፍርድ ታስረው የቆዩትን "ኤርትራ 16" የተባሉ 16 ጋዜጠኞች በጋራ ሸልሟል።
እነዚህ ጋዜጠኞች በ2001 የግል ሚዲያዎች ከተዘጉ በኋላ ታስረው ሲሆን፣ እስካሁን ክስ አልቀረበባቸውም፣ ፍርድ ቤትም አልቀረቡም። የጤናቸውና የሕይወታቸው ሁኔታ እንኳን በግልፅ አይታወቅም።
ሳቦልች ፓንዪ – ሀንጋሪ
የምርመራ ጋዜጠኛው ሳቦልች ፓንዪ የሩሲያ ተፅዕኖ፣ ሙስናና የፖለቲካ ሥልጣን ላይ በሠራቸው ዘገባዎች የሚታወቅ ሲሆን፣ በ2026 የሀንጋሪ ምርጫ ዋዜማ ከባድ ጫናና የስለላ ክስ ተጋፍጦበታል።
ኤስቴፋኒ ሮድሪጌዝ – ኮሎምቢያ
በአሜሪካ የስፓኒሽ ቋንቋ ሚዲያ Nashville Noticias ዘጋቢ የሆነችው ኤስቴፋኒ ሮድሪጌዝ በ2026 በICE ተይዛ ታስራ ነበር።
CPJ ጉዳዩ በስደተኞች ጉዳይ ላይ በምታደርገው ዘገባ ምክንያት በጋዜጠኞች ላይ የሚደረግ ጫናን የሚያሳይ ነው ብሏል።
ሳይ ዛው ታይክ – ሚያንማር
የMyanmar Now ፎቶ ጋዜጠኛ ሳይ ዛው ታይክ በ2023 የCyclone Mocha ጉዳትን ሲዘግብ ተይዞ 20 ዓመት ከባድ እስራት ተፈርዶበታል።
CPJ እንደሚለው ሚያንማር በዓለም ላይ ጋዜጠኞችን በእስር ከሚያቆዩ አገራት መካከል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የGwen Ifill የፕሬስ ነፃነት ሽልማት
የ2026 Gwen Ifill Press Freedom Award የኤል ሳልቫዶር ጋዜጠኛና El Faro መስራች ካርሎስ ዳዳ ተሸላሚ ሆኗል።
ዳዳ ለዓመታት በሙስና፣ በወንጀለኛ ቡድኖች፣ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና በመንግሥት አሰራር ላይ የምርመራ ዘገባዎችን በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከመንግሥታዊ ጫና የተነሳ በስደት እየኖረ ነው።
CPJ እንደገለጸው፣ የ2026 ተሸላሚዎች የተመረጡት ከፍተኛ አደጋና ጫና ውስጥ ሆነው ለሕዝብ እውነታን ለማድረስ ባሳዩት ድፍረትና ቁርጠኝነት መሠረት ነው።

የታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ ኡስማን ሥርዓተ ቀብር በአዳማ ተፈጸመ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የእስልምና ትምህርት እና የተውሒድ ጥሪ አስተምህሮ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ ኡስማን የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዳማ ከተማ የሙስሊሞች መካነ መቃብር ተፈጸመ።
ለረጅም ዓመታት የእስልምናን ዕውቀት በማስተማርና በርካታ ዓሊሞችን በማፍራት ለአገሪቱ የእስልምና ትምህርት ዕድገት ትልቅ ሚና የተጫወቱት የሸይኽ አህመድ ኡስማን ህልፈት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘንን ፈጥሯል።
እንደ ሃሩን ሚዲያ ዘገባ በአዳማ ከተማ በተፈጸመው በዚህ ሥርዓተ ቀብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ በርካታ ዓሊሞች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምዕመናን በመገኘት የመጨረሻ ሽኝት አድርገውላቸዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ጨምሮ ከፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሶስት ግለሰቦች ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ አሴረዋል በሚል ወንጀል ከሷቸዋል። ፖሊስ በነዚህ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።
ክሱ የቀረበው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ደረጃ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባቀረበው የቅድመ ምርመራ ጥያቄ ላይ ነው። ይህ የሆነው ኢህአፓ የሶስቱን ግለሰቦች መታሰር ካረጋገጠ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። የታሰሩት ግለሰቦች የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ይስሃቅ ወልዳይ፣ ከፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች በህግ ሲወክሉ የነበሩት ጠበቃ አበራ ንጉስ አየነው፣ እና መምህር እንዲሁም የኢህአፓ አባል የሆነው አበበ አካሉ ክብረት ናቸው።
የኢህአፓ ዋና ፀሀፊ ሚስጥረ-ስላሴ ታምራት እስሩ መጀመሩን አረጋግጠው፣ ጠበቃ አበራ ንጉስ እና ይስሃቅ ወልዳይ መጀመሪያ በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ አበበ አካሉ ደግሞ በማግስቱ መታሰሩን ገልፀዋል። ፓርቲው ባወጣው አጭር መግለጫ፣ ግለሰቦቹ በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን በነፃነት በመግለፃቸው ብቻ መታሰራቸውን አውግዞ፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ወንጀል ስላልሆነ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።
በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊስ የክስ መዝገብ እንደሚያትተው፣ ግለሰቦቹ የታሰሩት በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሳይሆን በኃይል ስልጣን ለመያዝ በተቀናጀ ሴራ ውስጥ በመሳተፋቸው ነው። የፖሊስ የምርመራ ቢሮ እንዳለው፣ ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፖለቲካ ፓርቲ እንደ ሽፋን በመጠቀም ከፓርቲው ህገ-ደንብ እና አላማ ውጪ መንግስትን በኃይል ለመገልበጥ ተንቀሳቅሰዋል። ፖሊስ አክሎም ግለሰቦቹ "የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች" ከተባሉት ህወሓት፣ ፅምዶ ከተባለ ቡድን እና ሌሎች ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በቅንጅት ሲሰሩ እንደነበር ወንጅሏል። በአዲስ አበባ አባላትን በመመልመል፣ የፀጥታ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመከታተል እና መረጃዎችን ለታጠቁ ኃይሎች በማስተላለፍ ተሳትፈዋል ተብለዋል።
ፖሊስ በክሱ ላይ እንዳሰፈረው ተጠርጣሪዎቹ የፖለቲካ፣ የወታደራዊ ስልጠና፣ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የድርጊት መርሃ-ግብር አስፈፃሚ ክንፎችን በማዋቀር ህገ-ወጥ አደረጃጀት ፈጥረዋል። አንከር ሚዲያ፣ ኢትዮ-ፎረም እና ኢትዮ 360 ሚዲያን ጨምሮ በውጭ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር ህዝቡን በመንግስት ላይ ለማነሳሳት የሀሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ እንደነበርም ተጠቅሷል።
ከዚህም ባሻገር ከከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ጋር በሚስጥር በመገናኘት በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግስት የፀጥታ ተቋማት እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ሲያደርጉ በፀጥታ ኃይሎች ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። ጉዳዩ እጅግ ውስብስብ እና ሀገራዊ አንድነትን የሚያፈርስ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ፣ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢለቀቁ ምስክሮችን ሊያባብሉ ወይም ሊያስፈራሩ ይችላሉ በሚል ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

Comments