Logo
Getu Temesgen
"ዋንጫውን የሸጥኩት ቁምሳጥኔ ጠቦኝ ነው" - ቤንጃሚን ሜንዲ
#ethiopia | ​የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ቤንጃሚን ሜንዲ በ2018 እ.ኤ.አ ያሸነፈውን የዓለም ዋንጫ ምስለኔ (replica) በጨረታ መሸጡ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሜንዲ ይህን ክብር ያለው የዋንጫ ቅጂ በጨረታ ያቀረበው ሲሆን፣ በጨረታውም በግምት 54,000 ዩሮ ገደማ መሸጡ ተገልጿል።

​የተጫዋቹ እርምጃ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችት ያስከተለ ሲሆን በርካቶች ይህንን መሰል ታሪካዊና ክብር ያለው ዋንጫ መሸጥ አልነበረበትም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

ሆኖም ለተሰነዘሩበት ትችቶች በቀልድ የታጀበ ምላሽ የሰጠው ሜንዲ፣ "ለመሆኑ ዋንጫው የእኔ ነው ወይስ የእናንተ? ዋንጫው የእኔ በመሆኑ በፈለግኩት መንገድ የማድረግ መብት አለኝ፤ ደግሞም በቁምሳጥኔ ውስጥ አላስፈላጊ ቦታ አጥቦብኝ ነበር" ሲል ለተነሳው ውዝግብ ግድ የለሽነቱን አሳይቷል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.