አሳዛኝ የሐዘን ዜና | የሊዮኔል ሜሲ አባት ሆርሄ ሜሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::
የዓለማችን ታላቁ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ አባት እና ዋና ወኪል የሆኑት ሆርሄ ሜሲ (Jorge Messi) በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይፋ ሆኗል።
የልጁን ስኬታማ የእግር ኳስ ህይወት እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በቅርበት ሲመሩ የቆዩት አባት ሆርሄ ሜሲ፣ በትውልድ ከተማቸው ሮዛሪዮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው አርብ ነሐሴ 01 (August 7) ምሽት 4:00 ገደማ ሕይወታቸው ማለፉን የሜሲ ቤተሰቦች እና የአርጀንቲና መገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል።
እንደ ዴይሊ ሜይል (Daily Mail) እና ዘ ሰን (The Sun Football) ዘገባዎች ከሆነ፣ ይህ መረጃ በቤተሰቦቹ በኩል ይፋ የተደረገ እና ተረጋገጠ ነው።
ሆርሄ ሜሲ ላለፉት በርካታ ወራት ከልብ እና ከነርቭ ህመም ጋር ተያይዞ በጽኑ ሲታመሙ የቆዩ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው የህክምና ሁኔታቸውን ከሚዲያ እይታ ውጪ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።
በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ወቅት ሜሲ በሜዳ ላይ ያሳየው የተለየ የሐዘን ስሜት እና እንባ፣ ከአባቱ የጤና ሁኔታ ጋር የተያያዘ እንደነበር ይታወቃል።
ሆርሄ ሜሲ ለአልቢሴሌስቴው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ የአባትነት ሚናቸውን ከመወጣት ባለፈ፣ ገና በወጣትነቱ ከሮዛሪዮ እስከ ባርሴሎና እና ባሻገር ላስመዘገባቸው ድንቅ ስኬቶች እና ግዙፍ የቢዝነስ ግዛቶች ዋና መሃንዲስ በመሆን የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።
ይህ ወቅት ለሜሲ ቤተሰቦች እና ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብ እጅግ ከባድ አጋጣሚ በመሆኑ፣ ለሊዮኔል ሜሲ፣ ለእናቱ ሴሊያ ኩቺቲኒ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ ፈጣሪ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እንመኛለን።
ነፍስ ይማር!
Via Daily Mail , The Sun Football
Seledadotio

20 hours ago