14 hours ago
የኢትዮጵያ የትምባሆ ቁጥጥር ዳሽቦርድ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | የትምባሆ ምርቶችን ጎጂነት ለመግታትና በዘርፉ የሚከናወኑ የሕግ ማስከበር ሥራዎችን በመረጃ ላይ የተመሠረቱ ለማድረግ ያለመው የትምባሆ ቁጥጥር ዳታ ኢኒሼቲቭ ዳሽቦርድ ይፋ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ፣ የጤና፣ ልማት እና ፀረ-ወባ ማኅበር እንዲሁም የመቋሚያ የማኅበረሰብ ልማት ድርጅት በጋራ በመሆን ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፣ የትምባሆ አጠቃቀምንና የኢንዱስትሪዎችን ተፅዕኖ ለመግታት መረጃን በአንድ ማዕከል ማሰባሰብ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተመልክቷል።
ይህ አዲስ የተበገገው ዳሽቦርድ በተለይም መረጃዎችን በሀገራችን የሥራ ቋንቋ በአማርኛ አካቶ ማዘጋጀቱ መረጃው ለፖሊሲ አውጪዎች ብቻ ሳይሆን ለሚዲያዎች፣ ለተመራማሪዎችና ለሰፊው ሕብረተሰብ ያለ ምንም የቋንቋ መሰናክል በቀላሉ እንዲደርስ ያስችላል።
በውስጡም የትምባሆ ተጠቃሚነት ስርጭትን፣ የሕገ-ወጥ ንግድ ሁኔታዎችን እንዲሁም ታክስ በጤና እና በሀገር ገቢ ላይ የሚያመጣውን አወንታዊ ተፅዕኖ የሚያሳዩ አገራዊ የምርምር ውጤቶችን ያካተተ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ዜጎች ከትምባሆ ሱስ የሚላቀቁበትንና ከምልሰተ-ሱስ የሚጠበቁበትን መንገድ የሚያመቻቹ መረጃዎች በውስጡ ተካተውበታል።
የትምባሆ ኢንዱስትሪዎችን የተቀናጀ እንቅስቃሴ በወቅቱ ለመቆጣጠር መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የማዘመን፣ ዳሽቦርዱን እስከ ታችኛው የመዋቅር ደረጃ ድረስ የማድረስና አቅም የመገንባት ሥራዎች በቀጣይ ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
ባለድርሻ አካላትም ይህንን ዝግጁ መረጃ በመጠቀም ሕግ የማስከበር፣ የግንዛቤ ማስጨበጥ እና ተጨማሪ የምርምር ሥራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።
#tobaccocontrol #publichealthethiopia #efda #tdi #tobaccodatainitiative #healthdevantimalaria

22 days ago
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 100ኛ ዓመቱን አከበረ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) "የአንድ ክፍለ ዘመን ጥረት ለተሻለ የሕብረተሰብ ጤና" በሚል መሪ ቃል ታሪካዊ የ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ዛሬ በከፍተኛ ድምቀት አክብሯል።
ይህ መቶ ዓመታትን የተሻገረው ክብረ በዓል ተቋሙ ላለፉት አሥርት ዓመታት የሀገሪቱን የጤና ደህንነት ለመጠበቅ ያደረገውን ዘርፈ ብዙ ጉዞ የዘከረ ሲሆን፣ በቀጣይም የጤና ሥርዓቱን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር አዲስ ቃል ኪዳን የተገባበት መድረክ ሆኗል።
በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ታዬ አፅቀስላሴ ጠንካራ የሕብረተሰብ ጤና ተቋማት የሀገር ደህንነትና ልማት መሠረቶች መሆናቸውን በመግለጽ፣ መንግሥት ተቋሙን ይበልጥ ለማጠናከር ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ተቋሙ ከጊዜው ጋር እንዲራመድ የዲጂታል ቴክኖሎጂንና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀምን ማሳደግ እንደሚገባው አሳስበዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ ተቋሙ ላለፉት 100 ዓመታት በበሽታ ቅኝት፣ በላቦራቶሪ አገልግሎትና በምርምር ዘርፍ ያበረከተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያወሱ ሲሆን፣ አዳዲስ ወረርሽኞችንና የአየር ንብረት ለውጥ ያመጣቸውን የጤና ተግዳሮቶች ለመመከት ጠንካራ ተቋማዊ ትብብር እንደሚያስፈልግ በአፅንኦት ገልጸዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በኢትዮጵያ ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካስሎ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በአፍሪካ እጅግ ጠንካራ ከሆኑ የልህቀት ማዕከላት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተቋሙን የዓለም ጤና ድርጅት የትብብር ማዕከል ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።
የአፍሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጄን ካሴያም በበኩላቸው የወደፊቱ የሕብረተሰብ ጤና ያለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የማይታሰብ መሆኑን ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ እያደረገች ያለችው ጥረት ለጤናው ዘርፍ ስኬት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ ተቋሙ ያለፉትን ስኬቶች መሠረት በማድረግ በቀጣዩ መቶ ዓመታት የሀገሪቱን የሳይንስና የጤና ሉዓላዊነት በተሟላ ሁኔታ ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ቃል ገብተዋል።
በበዓሉ ማጠቃለያ ላይም ላለፉት ዓመታት ተቋሙን በምርምርና በአመራርነት ያገለገሉ ባለውለታዎች ከፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ እጅ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#healthsovereignty #publichealthethiopia
#aiinhealthcare #ethiopia
#ephi #ministryofhealthethiopia

Comments