25 days ago
በቀን ከ36 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ የሚያቃጥሉት ሁለቱ ሀገራት
#ethiopia | ከነዳጅ ጥገኝነት መላቀቅ ያልቻለችው ዓለማችን በቀን 16 ቢሊዮን ሊትር ነዳጅ ትጠቀማለች።
ይህ ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ ከዓለም አቀፍ የትራንስፖርት የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ እና የኤቪዬሽን ዘርፍ ማደግ ጋር ተያይዞ በየቀኑ እየጨመረ የመጣ ነው ተብሏል።
በዚህ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ፍጆታ ውስጥ ቀዳሚውን ድርሻ የሚወስዱት ሁለቱ የኢኮኖሚ ሃያላን ሀገራት አሜሪካ እና ቻይና ናቸው፡
ከሜሪካ በቀን ከ20 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ በመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፋለች።
ይህ መጠን ዓለም አቀፉ አጠቃላይ ፍጆታ ከ20 በመቶ በላይ የሚሸፍን ሲሆን በዋናነት ለትራንስፖርት እና ለኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።
ቻይና በቀን ወደ 16 ሚሊዮን በርሜል ገደማ ነዳጅ በመጠቀም ሁለተኛዋ ትልቋ ተጠቃሚ ሀገር ሆናለች።
የሀገሪቱ የፋብሪካዎች መስፋፋት እና የህዝብ እንቅስቃሴ የነዳጅ ፍላጎቷ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲያድግ አድርጎታል ተብሏል።
የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች እንደሚሉት ከሆነ ምንም እንኳን ዓለም ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ጥረት እያደረገች ቢሆንም ከነዳጅ ጥገኝነት መላቀቅ አልቻለችም።
የትራንስፖርት የመርከብ እና የአቪዬሽን ዘርፎች አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ በነዳጅ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ዕለታዊው የፍጆታ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ይገኛል ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #globalnews #oilmarket #globaleconomy #usaeconomy #chinaeconomy #renewableenergy #energysector

2 months ago
2 months ago
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት 118.91 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት አስመዝግቦት የነበረውን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን አብዛኞቹን ዋና ዋና ግቦች በላቀ ደረጃ ማሳካት መቻሉን እና በተለይም በአዳዲስ ደንበኞች ትስስር ረገድ በተቋሙ ታሪክም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ውጤት ማስመዝገቡን ይፋ አድርገዋል።
በበጀት ዓመቱ 800 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ 664 ሺህ 505 አባወራዎችን በማገናኘት የ83.1 በመቶ ስኬት ተመዝግቧል።
ይህም አፈጻጸም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ32.5 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ ተቋሙን በዓይነቱ ከአፍሪካ መሰል የኃይል አቅርቦት ኩባንያዎች የመሪነት ደረጃ ላይ አሰልፎታል።
በተጨማሪም የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሙን በማጠናከር ከዋናው ግሪድ እና ከኦፍ-ግሪድ የፀሐይ ኃይል አማራጮች 205 አዳዲስ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም በአገሪቱ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ተደራሽ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን ቁጥር ወደ 7 ሺህ 908 አድርሶታል።
በፋይናንስና በገቢ አሰባሰብ ረገድም ተቋሙ አስደናቂ ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን፣ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዳዲስ ደንበኞች መስተንግዶና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 115.86 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 118.91 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የ103 በመቶ አፈጻጸም አሳይቷል።
ይህ የገቢ መጠን ከቀደመው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ88.4 በመቶ ከፍተኛ እድገት ያሳየ ነው። ለዚህ አፈጻጸም መሻሻል የዲጂታል ክፍያ አማራጮች መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ክፍያ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር 95.3 በመቶ ደርሷል።
በተጨማሪም ተቋሙ ከስርቆትና ከኃይል ብክነት የመከላከል ሥራዎችን በማጠናከር ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ለተቋሙ ገቢ ማድረግ ችሏል።
ተቋሙ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማሻሻያ፣ የትራንስፎርመር ጥገናና የአቅም ማሳደግ ሥራዎችን ያከናወነ ቢሆንም፣ አሁንም የመሰረተ ልማት እርጅና፣ የግብዓትና የነዳጅ እጥረት እንዲሁም የመሰረተ ልማቶች ስርቆትና ውድመት ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተገልጿል።
ሆኖም ተቋሙ የተደቀኑበትን ተግዳሮቶች በመቋቋም የቴክኖሎጂ ትግበራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬት የሚጠበቅበትን የላቀ ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
ጌትነት ተመስገን
#ethiopianelectricutility #eeu #ethiopia #energysector #ethiopianeconomy #digitalethiopia2030 #ruralelectrification #offgridenergy #performancereport #africaenergy

የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የኃይል ዘርፍ ትብብር
******************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀገሪቱን የኢነርጂ ዘርፍ ወደ ላቀ የዲጂታል እና የዘመናዊነት ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ወሳኝ ውይይት ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ልዑካን ጋር አካሂዷል።
ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፣ በአሜሪካ መንግስት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል የተመራውን ልዑክ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
በምክክሩ ላይ የኤሌክትሪክ ስርጭት አውታር መረብን (Grid) ማዘመን፣ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን፣ ስማርት ቆጣሪዎችን ማስፋፋት፣ ንጹህ ኢነርጂን ማልማት እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን (EVs) ማበረታታት ዋነኛ አጀንዳዎች ነበሩ። ከዚህም በተጨማሪ ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል።
ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በውይይቱ ወቅት፣ ተቋማቸው ለደንበኞች ምቹ፣ ጠንካራ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈጠራንና ቴክኖሎጂን አቅፎ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የረጅም ዓመታት ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተጨባጭ የልማት ፕሮጀክቶች እንደሚሸጋገር ያላቸውን ጽኑ እምነት መግለጻቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል እና ልዑካን ቡድናቸው በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘመናዊነት እርምጃዎችን አድንቀው፣ የሀገሪቱን የኃይል ዘርፍ አስተማማኝነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋፋት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገትና የኢንዱስትሪ ሽግግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚደግፍ ተጠቁሟል።
#ethiopia #ethiopianelectricutility #energysector #cleanenergy #usethiopia

Sponsored by
Surafel
6 months ago
የኬንያ መንግስት በነዳጅ ምክንያት የስራ ሀላፊዎችን እያባረረ ነው
#ethiopia | በኬንያ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ላይ በተደረገ ጥልቅ ምርመራ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ከስልጣናቸው እንዲነሱና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተወሰነ። ይህ እርምጃ የተወሰደው በሀገሪቱ የነዳጅ ዘርፍ ላይ በተፈጸመ የኢኮኖሚ አሻጥር እና የሀሰት መረጃ ስርጭት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
ከሃላፊነታቸው በአስቸኳይ ከተነሱት ባለስልጣናት መካከል፦
* መሐመድ ሊባን – የነዳጅ ዘርፍ ዋና ጸሐፊ
* ጆ ሳንግ – የኬንያ ፓይፕላይን ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ
* ዳንኤል ኪፕቶ ባርጎሪያ – የኢነርጂና ነዳጅ ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ይገኙበታል።
የኬንያ ፕሬዚዳንት የሥራ ኃላፊ ፌሊክስ ኬ ኮስኬይ እንደገለጹት፣ ባለሥልጣናቱ በሀገር ውስጥ ያለውን የነዳጅ ክምችት አስመልክቶ የተሳሳተ መረጃ ሆን ብለው በማሰራጨት ህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት እንዲፈጠር አድርገዋል። ይህ "የኢኮኖሚ አሻጥር" በታክስ ከፋዩ ህዝብ ላይ ከ500 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ በላይ ኪሳራ ማስከተሉ ተረጋግጧል።
ወቅታዊው እርምጃ መንግስት በስትራቴጂካዊ የሀብት አቅርቦቶች ላይ የሚታዩ ብክነቶችንና ሌብነቶችን ለመከላከል የጀመረው ዘመቻ አካል መሆኑ ተመላክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #kenyanews #oilscandal #economicsabotage #eastafricaupdate #energysector #accountability

Comments