Logo
YenetaTube
ተወዳጇ አርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ በነፃ ለSUSU HUMAN HAIR አምባሳደር ሆነች!!!

በህይወቴ ብዙ ፈተናዎችን እና ተስፋ የሚያስቆርጡ ውጣ ውረዶችን አሳልፌያለሁ። ነገር ግን ከልጅነቴ ጀምሮ ያሰብኩትን ነገር ከማሳካት የሚያስቆመኝ ምንም አይነት ችግር ሆነ ፈተና አልነበረም።

በስደት ሀገር እንደማንኛውም ስደተኛ ሰው ቤት ተቀጥሬ እሰራ ነበር። ከዛ በመውጣት የራሴን ስራ ለመስራት ሞከርኩ። በትንሽዬ የሴቶች የውበት ሳሎን በመጀመር፣ በሊባኖስ ዋና ከተማ ታዋቂ የሂውማን ሄር (Human Hair) አስመጪ እስከመሆን ደረስኩ። ህይወቴ እየተለወጠ፣ እያደግኩ እና እየተሳካልኝ ሲመጣ በማህበራዊ ሚዲያ (በቲክቶክ) ብቅ አልኩ በሀቢባ ቤት LIVE በመግባት እውቅናንም ማግኘት ጀመርኩ ሀቢባ ታዋቂ ለመሆኔ ምክንያት ሆነችኝ። ያኔም ነው ቬሮኒካ አዳነ ያወቀችኝ እንደምወዳት እና አድናቂዋ እንደሆንኩኝ በሷ ሙዚቃ በምሰራቸው ቪድዎች አየች ኮሜንት ለመጀርያ ጊዜ ስትፅፍልኝ የነበረውን ስሜት አልረሳውም። በቬሮኒካም ምክንያት በደንብ ታዋቂ መሆን ጀመርኩ፤

በዚያም ብዙ ወዳጆችን በማፍራት ስሜ በሀገሬ በኢትዮጵያም መታወቅ ጀመረ፤ ተደራሽነቴ እየሰፋ ሄዶ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ያሉ ደንበኞችን ማፈራት ቻልኩ። የመጀመሪያ ልጄንም በዚህ ስራ ላይ እያለሁ ወለድኩ፤ ይህም ይበልጥ ጠንካራ አደረገኝ።

ነገር ግን፣ ምንም በማላውቀው ምክንያት
ሁለት ወር እስራት ገጠመኝ ከዛ በኋላ ከእስር ቤት ወጥቼ ወደ ሀገሬ ገባው በህይወቴ ትልቁን ፈተና የተፈተንኩት ያኔ ነበር ለአስር ዓመታት የለፋሁበትን ህይወት፣ ስራዬን እና ከልጄ ጋር የነበረኝን አንድነት እንደ ቀልድ አጣሁት።

እውነት ለመናገር ያኔ ተስፋዬ ተሟጦ አልቆ ነበር። ነገር ግን ፈጣሪ ሁሌም አለ፤ አይተወኝም። ጠንካራ ሴት ነኝና በህይወቴ እንደ ሀቢባ እና ቬሮኒካ አዳነ ያሉ ጠንካራ ሴቶችን ላከልኝ። ልወድቅ ስል ደገፉኝ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉ ውድ የኢትዮጵያ ህዝቦችና የሚወዱኝ ሰዎች ትልቅ ድጋፍ ሆኑኝ።

ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በኋላ፣ የምወዳት እና የማደንቃት አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ በህይወቴ የማልረሳውን ትልቅ ውለታ ውላልኛለች፤ *«የሁለት ዓመት በነፃ ያለ ምንም ክፍያ የ’ሱሱ ሂውማን ሄር’ (Susu Human Hair) አምባሳደር ነኝ»* ብላ ሰርፕራይዝ አደረገችኝ። ይህ የህይወቴ ትልቁ ሰርፕራይዝ ነበር! ልጄም ወደ ሀገሩ ተመለሰ። በሀቢባ፣ በወዳጆቿ እና በአድናቂዎቼ አማካኝነትም የገንዘብ ድጋፍ ተደረገልኝ።

አሁን የህይወቴ ትልቁ ምዕራፍ ላይ እገኛለሁ። የሂውማን ሄር መሸጫዬን እና የውበት ሳሎኔን እዚሁ ሀገሬ ላይ ልከፍት ነው። ቬሮኒካ አዳነ የ2 ዓመት አምባሳደሬ ሆና በነፃ ትሰራለች፤ ከቻይና ሂውማን ሄር ኩባንያ ጋርም አብሬ እየሰራሁ እገኛለሁ።

አሁን ማንም ሊያስቆመኝ አይችልም! ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላም ከፍ እንድል ምክንያት ሆነውኛል

ከፈተናዎች ማዶ የተገነባ ስኬት:- የሱመያ ዋሪስ የህይወት ጉዞ
እኔ SUSU HUMAN HAIR ነኝ።

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.