1 day ago
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት 118.91 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት አስመዝግቦት የነበረውን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን አብዛኞቹን ዋና ዋና ግቦች በላቀ ደረጃ ማሳካት መቻሉን እና በተለይም በአዳዲስ ደንበኞች ትስስር ረገድ በተቋሙ ታሪክም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ውጤት ማስመዝገቡን ይፋ አድርገዋል።
በበጀት ዓመቱ 800 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ 664 ሺህ 505 አባወራዎችን በማገናኘት የ83.1 በመቶ ስኬት ተመዝግቧል።
ይህም አፈጻጸም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ32.5 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ ተቋሙን በዓይነቱ ከአፍሪካ መሰል የኃይል አቅርቦት ኩባንያዎች የመሪነት ደረጃ ላይ አሰልፎታል።
በተጨማሪም የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሙን በማጠናከር ከዋናው ግሪድ እና ከኦፍ-ግሪድ የፀሐይ ኃይል አማራጮች 205 አዳዲስ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም በአገሪቱ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ተደራሽ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን ቁጥር ወደ 7 ሺህ 908 አድርሶታል።
በፋይናንስና በገቢ አሰባሰብ ረገድም ተቋሙ አስደናቂ ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን፣ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዳዲስ ደንበኞች መስተንግዶና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 115.86 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 118.91 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የ103 በመቶ አፈጻጸም አሳይቷል።
ይህ የገቢ መጠን ከቀደመው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ88.4 በመቶ ከፍተኛ እድገት ያሳየ ነው። ለዚህ አፈጻጸም መሻሻል የዲጂታል ክፍያ አማራጮች መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ክፍያ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር 95.3 በመቶ ደርሷል።
በተጨማሪም ተቋሙ ከስርቆትና ከኃይል ብክነት የመከላከል ሥራዎችን በማጠናከር ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ለተቋሙ ገቢ ማድረግ ችሏል።
ተቋሙ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማሻሻያ፣ የትራንስፎርመር ጥገናና የአቅም ማሳደግ ሥራዎችን ያከናወነ ቢሆንም፣ አሁንም የመሰረተ ልማት እርጅና፣ የግብዓትና የነዳጅ እጥረት እንዲሁም የመሰረተ ልማቶች ስርቆትና ውድመት ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተገልጿል።
ሆኖም ተቋሙ የተደቀኑበትን ተግዳሮቶች በመቋቋም የቴክኖሎጂ ትግበራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬት የሚጠበቅበትን የላቀ ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
ጌትነት ተመስገን
#ethiopianelectricutility #eeu #ethiopia #energysector #ethiopianeconomy #digitalethiopia2030 #ruralelectrification #offgridenergy #performancereport #africaenergy

Comments