6 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ እስካሁን ከተፈጸሙት ሁሉ እጅግ የከፋ የተባለለትን የአየር ድብደባ ለማካሄድ እቅድ ማውጣታቸውን ሲቢኤስ ኒውስ ዘገበ። ጥቃቱ በዚህ የሳምንቱ መጨረሻ ሊፈጸም እንደሚችል በርካታ ምንጮች ጠቁመዋል።
የአየር ድብደባው በአሜሪካ እና በዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ገበያ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽዕኖ በመስጋት፣ ሰኞ የፋይናንስ ገበያዎች ክፍት ከመሆናቸው በፊት ዘመቻውን ለማጠናቀቅ ውይይቶች መደረጋቸው ተገልጿል። ሆኖም የዘመቻው ማብቂያ ጊዜ ገና በግልጽ አልጸደቀም። የአሜሪካ ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ለእስራኤል ማሳወቂያ የተሰጠ ሲሆን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ። ነገር ግን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጥቃቱ የመጨረሻውን የትዕዛዝ ማረጋገጫ ገና አልሰጡም።
የጥቃቱ እቅድ አርብ ዕለት በካምፕ ዴቪድ በተካሄደው የፕሬዝዳንት ትራምፕ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ አንዳንድ የዋይት ሀውስ የፖለቲካ አማካሪዎች ሀሳቡን አጥብቀው ቢቃወሙም፤ ትራምፕ በስብሰባው ላይ ለጋዜጠኞች "በጣም በኃይል እንመታቸዋለን። በአንድ ወቅት፣ 'ከዚህ በላይ መቋቋም አንችልም' ማለት ይጀምራሉ" ሲሉ ተደምጠዋል። የኃይል ማመንጫዎችን እና የነዳጅ ማጣሪያዎችን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ዋነኛ ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተጠቆመ ሲሆን፣ በመላው ቴህራን መብራት ስለማቋረጥ በከፍተኛ ደረጃ ውይይት የተደረገ ቢሆንም እስካሁን የተላለፈ የመጨረሻ ውሳኔ የለም።
የዋይት ሀውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮላይን ሌቪት ለሲቢኤስ ኒውስ በሰጡት መግለጫ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካቢኔ ስብሰባቸው ላይ እንዳሉት፣ አሜሪካ እንደምታሸንፍና በእሳቸው የሥልጣን ዘመንም ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንደማይኖራት አረጋግጠዋል። የፔንታጎን ዋና ቃል አቀባይ ሾን ፓርኔል በበኩላቸው፣ ፕሬዝዳንቱ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጡ ድረስ ፔንታጎን ስለ ኢላማዎቹ አስተያየት እንደማይሰጥ ገልጸው፣ የጦርነት መምሪያው በማንኛውም ሰዓት የፕሬዝዳንቱን ትዕዛዝ ለመፈጸም ሙሉ ዝግጁነት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። በሌላ በኩል አንድ የእስራኤል ባለስልጣን ለእስራኤል በኢራን ላይ በሚደረግ ወታደራዊ እርምጃ እንድትቀላቀል ጥያቄ እንዳልቀረበላትና ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ ስለመጀመሩ መረጃ እንደሌላት ተናግረዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በተገናኙበት ወቅት፣ የአቅርቦት መስመሮች ላይ ያተኮሩትን ጨምሮ ሦስት የጦርነት አማራጮችን ማቅረባቸው ይታወሳል። ኔታንያሁ ከአሜሪካው የመከላከያ ጸሃፊ ሄግሴት (Hegseth) ጋርም ተወያይተዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በሚጓዙ መርከቦች ላይ ለሚሰነዘር እያንዳንዱ ጥቃት የኢራንን የኃይል ማመንጫ ወይም ድልድይ አጋያለሁ ሲሉ በ‘ትሩዝ ሶሻል’ (Truth Social) ገጻቸው መጻፋቸው አይዘነጋም። የቀድሞ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣን እንዳብራሩት፣ የኃይል መሰረተ ልማቶችን መምታት የኢራን ጦር አገልግሎት የመስጠት እና አገሪቱን የማስተዳደር አቅም ክፉኛ ያሽመደምደዋል።

24 days ago
የድኅረ-እውነት ፈተና፦ እውነት ዋጋ ባጣበት ዘመን ኢትዮጵያን ማዳን
**********************
በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕዝብ አስተያየት አወቃቀር እና የፖለቲካ ንግግሮች ምኅዳር በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጧል።
ለዚህም ዋነኛው ማሳያ፥ ተጨባጭ እና ሳይንሳዊ ሐቆች ለሕዝባዊ ውሳኔዎች መሠረት መሆን ሲገባቸው፣ ከእውነት ይልቅ ለሰዎች ስሜት እና ቀድሞ ለተነገሩ የግል እምነቶች የሚቀርቡ የማሳመን ሙከራዎች ከፍተኛውን ተፅዕኖ መፍጠራቸው ነው።
ምሁራን ይህን ጽንሰ-ሐሳብ "ድኅረ-እውነት" (post-truth) በማለት ይገልጹታል። ይህ ጽንሰ-ሐሳብ ሰዎች እውነትን ስለመቃወማቸው ሳይሆን፣ እውነት ራሱ ዋጋ ቢስ ወደሚሆንበት እና ከጉዳይ ወደማይቆጠርበት ደረጃ መድረሱን የሚያሳይ ነው።
ጀርመናዊው ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ ይህን ሀሳብ ሲገልጽ፣ "ተጨባጭ የሆኑ ፍፁማዊ እውነታዎች የሉም፤ ያለው የሰው ልጅ የሥልጣን ፍላጎት የሚፈጥረው ትርጓሜ ብቻ ነው" ይላል።
ዛሬ ላይ እውነታን ከፈጠራ የመለየት አቅም ማጣት ማኅበረሰብን ወደ አጠቃላይ አምባገነናዊነት እና ትርምስ እየመራው ይገኛል።
የድኅረ-እውነት ፖለቲካ መፈጠር እና መስፋፋት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዴሞክራሲያዊ ተቋማት፣ በሕዝብ አመኔታ እና በብሔራዊ ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ውድቀቶችን አስከትሏል።
እ.አ.አ በ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ እና በእንግሊዝ የ‘ብሬግዚት' ውሳኔ ወቅት፣ ፖለቲከኞች የሕዝቡን የኢኮኖሚ ስጋት እና ብሔራዊ ስሜት የሚቀሰቅሱ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የምርጫውን ውጤት መለወጥ ችለዋል።
በተመሳሳይ እ.አ.አ በ2017 በሚያንማር በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ የጥላቻ እና የሐሰት ዘገባዎች በሀገሪቱ ለተፈጸመው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ዋነኛ መንስኤ እንደነበሩ የተባበሩት መንግሥታት መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለዚህ የመረጃ ሥነ-ምህዳር መዛባት ግንባር ቀደም መደላድል የፈጠሩት በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ ያሉት የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ናቸው።
የነዚህ መድረኮች የውሳኔ ሰጪ ስልተ-ቀመሮች (Algorithms) የተገነቡት የመረጃን እውነትነት ለማረጋገጥ ሳይሆን፣ የተጠቃሚዎችን ቀልብ በመሳብ መድረኩ ላይ ረጅም ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማድረግ ነው።
በዚህም የተነሳ ስሜት ቀስቃሽ፣ ጽንፈኛ እና አስደንጋጭ የሐሰት መረጃዎች በፍጥነት ይሰራጫሉ።
በተጨማሪም ተጠቃሚዎች የራሳቸውን አመለካከት ብቻ ከሚያስተጋቡ ሰዎች ጋር እንዲገናኙ በማድረግ፣ "Echo Chambers" ውስጥ እንዲዘፈቁ እና ከተቃራኒ እውነታዎች እንዲገለሉ ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ፈተና እና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ
በኢትዮጵያ ያለው የድኅረ-እውነት ፈተና ከምዕራባውያን ሀገራት በተለየ መልኩ እጅግ አደገኛ እና የሰዎች ሕይወት ላይ አደጋ የሚፈጥር እየሆነ ነው።
በጥቂት ጽንፈኞች የሚነዙ ስሜት ቀስቃሽ የፈጠራ ትርክቶች ሀገራችንን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈሏት፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንደ ጦር መሣሪያ ያገለገለው የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ምስክር ነው።
መንግሥት መረጃ የማጣራት ሥራ ቢሠራም፣ የቴክኖሎጂው ፍጥነት ለቁጥጥር ፈተና ሲሆን አስተውለናል።
በአሁኑ ወቅትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረኩ እና ከሃይማኖት እንዲሁም ከብሔር ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ የሤራ ትንተናዎች ማኅበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀውታል።
ይህ የመረጃ መዛባት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተካሄደ ካለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት አንጻር ሲታይ አሳሳቢ ነው።
ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ ሊሆን እና የዘመናት ቁስሎቻችንን ሊያክም የሚችለው፣ በሐሰተኛ ትርክቶች ያልተመረዘ፣ ለእውነት እና ለምክንያታዊነት የቆመ የሕዝብ ተሳትፎ ሲኖር ነው።
ነገር ግን የድኅረ-እውነት ፖለቲካ አራማጆች የሕዝቡን ስሜት በመኮርኮር፣ መተማመንን ለማሳጣት እና ልዩነቶችን ለማስፋት የሐሰት መረጃን በስፋት እየተጠቀሙ ይገኛሉ።
በመሆኑም እውነተኛ ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የምክክር ሂደቱ ከሐሰተኛ የመረጃ ዘመቻዎች ሊጠበቅ ይገባል።
አሁን እያንዳንዱ ዜጋ ሀገሩን ከዚህ ፈተና የማዳን ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። ማንኛውንም መረጃ ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት "መረጃው ከየት መጣ? ምንጩስ ታማኝ ነው ወይ?" ብለን መጠየቅ ዘመኑ የሚጠይቀው ዋነኛ የዜግነት ግዴታችን ነው።
ስሜትን ከሚኮረኩሩ እና ሀገርን ወደ ግጭት ከሚመሩ የሐሰት ትርክቶች ራሳችንን በማራቅ፣ ሀገራችንን ከድኅረ-እውነት አደጋ በጋራ እንታደግ!
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #posttruth #disinformation #factcheck #socialmedia #ebc

2 months ago
ሪያሊቲ ፒያዛ ፓላስ ቪው ፕሮጀክት
REALITY PIAZZA PALACE VIEW PROJECT
በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ከፍተኛ የጥራት መስፈርት እየተገነባ ነው!
#ethiopia | ሪያሊቲ ሪል እስቴት “ሪያሊቲ ይለያል - THE DIFFERENCE IS IN DETAILS” በሚለው መርሁ የሚታወቀው ድርጅት፣ በአዲስ አበባ የታሪክ፣ የንግድ እና የመዝናኛ ማዕከላት በሆኑ ቦታዎች አቅራቢያ የሚገኘውን “ሪያሊቲ ፒያዛ ፓላስ ቪው” ፕሮጀክት በዘመናዊ የአርክቴክቸር ዲዛይንና ዘላቂ የኑሮ ፅንሰ ሀሳብ እያለማ መሆኑን የሪያሊቲ ሪል እስቴት ባለቤትና CEO አቶ ዮሐንስ ገመዳ አስታወቁ።
አቶ ዮሐንስ አያይዘው እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ በ4,000 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን ከ70,000 ሜትር ኪዩብ ወይም 16 ሜትር ( አራት ቤዝመንት) በላይ የቁፋሮ ሥራ ተከናውኗል። በድርጅቱ የፋይናንስ አቅም ፕሮጀክቱን 300 ሚሊዮን ብር በማውጣት መጠነሰፊ ሰፊና የመሠረት ሥራዎቹ በብቃት መጠናቀቃቸውን አስረድተዋል።
ፕሮጀክቱ በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል የሚገኝ ሲሆን፣ ከአድዋ ሙዚየም 853 ሜትር፣ ከቸርችል ጎዳና 465 ሜትር፣ ከፍሬንድሺፕ ፓርክ 240 ሜትር፣ ከዩኒቲ ፓርክ 770 ሜትር እንዲሁም ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 955 ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ አቶ ፍጹም ገብሩ የኮንስትራክሽ ቺፍ ኮንስትራክሰሸ ኦፕሬሽኝ ኦፊሰር
ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ከሼራተን ሆቴል እና ከሊሴ ገብረ ማርያም ትምህርት ቤት አቅራቢያ መገኘቱ ለነዋሪዎችና ለባለሀብቶች ልዩ የቦታ ጥቅም እንደሚሰጥ አቶ ፍጹም አብራርተዋል።
የ“ፖላስ ቪው” ፕሮጀክቱ በቴክኒካል ጥራት፣ በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ እና በከተማ ገጽታ ላይ በሚያመጣው አዎንታዊ ተፅዕኖ ተለይቶ የሚታይ ፕሮጀክት ነው ያሉት ደግሞ ቴክኒካል ማናጀሩ አቶ ዳርዮስ ፍቃዱ ናቸው።
በፕሮጀክቱ ውስጥ አራት ቤዝመንቶች የታቀዱ ሲሆን፣ 8 ሜትር ስፓን ያላቸው የኮለም አቀማመጦች እና 7 በመቶ የራምፕ ተዳፋት በመጠቀም ሰፊና ምቹ የፓርኪንግ ሥርዓት እንዲኖር መደረጉ ገልጸዋል።
እንዲሁም 10 ሊፍቶች እና 4 የአደጋ መውጫ ደረጃዎች የታቀዱ ሲሆን፣ ሕንጻው የእሳት ደህንነት መስፈርቶችን በሙሉ የሚያሟላ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።
በሜካኒካል፣ ኤሌክትሪካል እና ሳኒተሪ ሥርዓቶች ዘርፍም የኤሌክትሪክ እና የሳኒተሪ ዳክቶች ለየብቻቸው መዘጋጀታቸው፣ ዘመናዊ የካሜራና የኢንተርኮም ሥርዓት መካተቱ እና በቂ የአየር ዝውውር የሚያቀርብ የሜካኒካል ቬንቲሌሽን ሲስተም መዘርጋቱ ተጠቅሷል።
የሪያሊቲ ሪል እስቴት ባለቤትና CEO አቶ ዮሐንስ ገመዳ ፕሮጀክቱ በዘመናዊው Post-Tension (PT) Slab System ቴክኖሎጂ የተቀየሰ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ሰፊ ስፓን ለመፍጠር፣ የግንባታ ፍጥነትን ለማሳደግ እና የስትራክቸር ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑ ገልጸዋል።
ከከተማ ገጽታ አንፃርም፣ ሕንጻዎቹ ከ5ኛ ወለል ጀምሮ በመንታ ቅርጽ የሚይዙ ሲሆን ለአካባቢው ዘመናዊ የአርክቴክቸር ገጽታ እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ሰፊ የአረንጓዴ ልማት፣ በዛፎች የተሸፈነ ቴራስ እና ሁለቱን ሕንጻዎች የሚያገናኝ ድልድይ ለፕሮጀክቱ ልዩ የውበት እሴት እንደሚጨምሩ ጠቁመዋል።
ሪያሊቲ ሪል እስቴት ፖላስ ቪው ፕሮጀክት ለመኖሪያ ቤት ፍላጎት መፍትሔ ከመስጠቱ ባሻገር ለከተማው አዲስ ገጽታ የሚያበረክት፣ የዘመናዊ ግንባታ መለኪያ የሚሆን እና የድርጅቱን የጥራት ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው።****
ሪያሊቲ ፒያዛ ፓላስ ቪው ፕሮጀክት ዘመናዊ የኑሮ ፍላጎቶችን በማሟላት 24 ሰዓት የጥበቃ አገልግሎት፣ ስታንድባይ ጄኔሬተር፣ ሰፊ ፓርኪንግ፣ የቆሻሻ ማስወገጃ ሥርዓት፣ ዘመናዊ ሊፍቶች፣ ጂምናዚየም፣ የመቀበያ አዳራሽ፣ ባለብዙ ዓላማ አዳራሽ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎች እና የውጭ አትክልት ስፍራዎችን ያካትታል።
የመኖሪያ እና የንግድ አገልግሎቶች መግቢያዎች ለየብቻ ናቸው። ከመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎቶች አንፃርም ከ200 በላይ ሱቆች፣ ከ1 እስከ 3 መኝታ ቤት ያላቸው አፓርታማዎች፣ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ ሰፊ የፓርኪንግ ቦታዎች እና በሩፍቶፕ የመዝናኛ ስፍራዎችን ይዟል።
የሪያሊቲ ሪል እስቴት የማርኬቲንግ ዳይሬተር
አቶ ሙሉቀን ሽፈራው እንደተናገሩት "መሸጥ ማስረከብ አይደለም። እኛ - (ሪያሊቲ ሪል እስቴት) ግን የሸጥነውን እያስረከብን ነው። ... ማስረከብ ተክነንበታል። ይህ የደንበኞቻችን የምስክርነት ድምፅ ነው" ብለዋል።
አቶ ሙሉቀን ሪያሊቲ ሪል እስቴት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ የንግድ ኤክስፖ ይዘን መጥተናል። ለ 30 ቤቶችን ብቻ በ 90,200 ብር እንዲሁም በ 102 ሺህ ብር ደግሞ የተለያዩ ቤቶችን ለሽያጭ አቅርበናል። ይህ በ48 ወራት የሚጠናቀው ለቤት ፈላጊዎች ትልቅ የምሥራች፤ ትልቅ ዜና ነው"ብለዋል።
“ሰማችን እውነት ነው፣ ሥራችንም የእውነት ነው - DELIVERING THE TRUTH ” በሚል መርህ የሚሰራው ሪያሊቲ ሪል እስቴት፣ ይህ ፕሮጀክት ዘመናዊ አርክቴክቸር፣ ዘላቂ የኑሮ ዘይቤ እና ምርጥ የቦታ ምርጫን በአንድ ላይ ያጣመረ የልህቀት ምሳሌ፤ መሪ ኩባንያ ( Leading Company ) ሆኖ እየሠራ፤ እየታተረ ይገኛል።
በ10 ዓመታት የሪል እስቴት ጉዞ 14 ፕሮጀክቶቾ፤ በ2018ዓም 4 ፕሮጀክቶች የሪያሊቲ ሪል እስቴት ሕያው ቋሚ ሥራዎቹ ናቸው።
ይህ ሪያሊቲ ሪል እስቴት ጉዞ ይቀጥላል ...
“ሪያሊቲ ይለያል!
- THE DIFFERENCE IS IN DETAILS”
+251-977-292929
+251-948-233333

ጥቂት ስለ ግጥምና ገጣምያን!
ደረጀ በላይነህ
ገጣሚና ሐያሲ
#ethiopia | ግጥም እንደ ቋንቋ ጥንታዊና ሁለንታዊና መግባቢያ ስለሆነ፣ጥንታውያኑ ተጠቅመውበታል፤ዘመናውያኑ ደግሞ ኮትኩተውታል ይላሉ-ፕሮፌሰር ሎረነስ ፐሪኔ።
ግጥም ከሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ተወዳጅና አክሊል የሚባለውም እንደ ጥንቅሽ እየተላጠ ተበልቶ ትዝታው ስለማይጠፋ፣የዋሽንቱ ዜማ ከልብ ስለማይገሠሥ ነው።
ዜማዊነቱ ለአይረሴነቱ ሰበብ ሲሆን፣ እምቅነቱ፣ምናባዊነቱ፣ተውኔታዊነት፣ቁጥብነት ወዘተ መለያ ባህርያቱ ናቸው።
ሌላው ብርቅ ከሚያሰኙት አንዱ ደግሞ አተያዩና ፍካሬው ነው። እንደ አልማዝ የተለያዩ ነጸብራቆች ስላሉት የዚያ ብርቅርቅታና ቀለም የገጣሚውን ምናብ ይለካዋል።
ግጥም ይፈላሰፋል፤ግን ፍልስፍና አይደለም። ገጠመኝን አሳምሮ፣በምናብ ወልውሎ ያመጣል እንጂ!
Its primary concern is not with beauty,not philosophical truth,not eith percuation,but with experience. ይላሉ።
ፊትን በመስታወት እንደማየት ይመስላል፤ ጥሬ ምስል አይደለም። ብዙ ቀለም በርካታ ቅርጾች አሉት። ምናልባትም በተሰባበረ መስተዋት እንደማየት ሊሆን ይችላል።.
በቅርጹም ወይ ተራኪ፣ተውኔታዊ፣አሊያም ሌሪክ ይሆንና እንደገና በየፈርጁ ይሸነሸናል።...በተለይ ስሜት ንክር፣ሙዚቃዊ የሆነው ሌሪክ የስሜት ዳንሶች ይዞ በሙሾ ሊያላዝን፣በፍቅር እስክስታ ሊመታ፣በትዝታ ቆርፍዶ እንባው በረዶ ሊሆን ይችላል።...እንጉርጉሮ ቢሆን፣ ጸሎትና ምሕላ፣ሽለላና ቀረርቶም እንደዚሁ።
ቃላት ለግጥም አንዱ መታበያው፣የቁመናው ጌጥ፣የመጋረጃው ዘርፍ ነው።...በተለይ ዘይቤያዊ ቃላት ደመና ላይ ሰቅለው ቼ! በለው የሚሉበት የከፍታው ጉልላት ነው።
ቃላቱንም እማሬያዊና ፍካሬያዊ ብለን ብንለያቸው፣በአብዛኛው ከዘወትራዊው ይልቅ በተምሳሌታዊና አምሳያዊ ትዕምርቶች በወደድነው ሥፍራ ብንዶላቸው ጣማቸው ይጨምራል።
ወይም ስሜት የነሸጠውን ያየንበት ትዝብት ውል ሲልብን፣እንደ መንግሥቱ ለማ፦
በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዓይኖቿ እያበሩ እንደክዋክብት
"ሳማት ሳማት"አሉት"ዕቀፍ ዕቀፋት"
አላወላወለም፤ወጣቱ ታዘዘ፤
ወገቧን አንገቷን፤በእጅና እጁ ያዘ፤
ከንፈሩ በረአድ ወዳፏ ተጠጋ።
-ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የበረዶ አለንጋ፤
ጆሮግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
በጠራው ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዋ ጀማሪ መሆን ፤ዋ ተማሪነት፣
ዋ ትዕዛዝ መፈጸም፣ዋ ምክር መስማት።
እንግዲህ ተራኪው ግጥም እንዲህ ያለ መልዕክት፣ሲያስላልፍ ሥዕሉ ደምቋል። ጣቶቿ አለንጋ፤ጡቶቿ ሹል፣ሲል የልጅቷ ዕድሜ ከውስጥ ፤ቁመናው ከላይ ይታዩናል። ከዚህም አልፎ ደግሞ የምንበረብረው ሳጥን አለ። ከንፈሩ ለምን ቀዘቀዘ?...ፈርቷል። የፈራው ለምንድነው?...ልጅቷ እንዳትቆጣ!...ያኔ በዘመኑ ዐውድ ልጃገረ በእጅ መንካት ሽጉጥ ያስመዝዛል። ግን ተማሪ ጓደኞቹ አሳሳቱትና ጥፊ ቀመሰ።ቅምሻ ብቻ አይደለም ተናጋ። ሲናጋ ድምፅ አለው።
እዚህ ጋ ምሰላ ይመጣል- ድምፅ፣እላይ አጎጠጎጤ- ምስል፤ዐይኖችዋ መጉላት-ዕይታ።
ግጥም እንዲህና እንዲያ ነው። ሙዚቃው ያግባባል፤ሐሳቡ ሆድ ይገባል።
ግጥም የየዘመኑን ዳና ያስቀራል ስንል፥ ፖለቲካው፣ሥነ ልቦናው፣ፍልስፍናው ባሕሉ ወዘተ ቀለሙ ውስጥ ታትሞ ይኖራል። የረሃብ ይሆን ጥጋብ፤የጸብ ይሁን ፍቅር የትውልዱን ትዝብት፣ የነውጡን ንፋስ ፈትል ሰማይ ላይ ረጭቶ፣ የትካዜው ፉጨት፣የሳቁን ዜማ፣የትዝታውን ጥላ፤ ሻካራና እሾሁን፣ ሕመምና ጥዝጣዜውን፣ሳቅና ፍካቱን፣...
የአማርኛ ግጥሞች ዕድሜ ብዙ ሩቅ አይደለም።በዚያ ላይ አዳዲስ ፈርጆችን ይዞ አላስደነቀም። ከፖለቲካው ሥርዐትና ርዕዮት ጋር የቀየረው ቅርጽ የለም።ርዕዮቶችን በአንቀልባ እያዘሉ ከማውረድ የተለየ ሚናም አልነበረው። እንደ ፈረንጆቹ፣ወይም እንደላቲኖቹ፣ካልሆነም እንደመካከለኛ ምሥራቋ እሰራኤል የቤት ዐመታት ላይ የመጣው ለውጥ አልተመዘገበም።
ዘውጉን ሳይለቅ የቁመና ለውጥ ያመጣው ባለፉት አርባ ዐመታት ይመስለኛል። ያም ከፖለቲካዊና አገዛዛዊ ሸምቀቆ ጋር ተያይዞ የመጣ መጉበጥ ይመስላል።
አጫጭር ግጥሞች መብዛታቸውም፣የመታከት፣ብዙ ለመተንተን ሰሚ በማጣት የተፈጠረ መሰልቸት ይመስላል፤ዝም ብሎ ለመተንፈስ ብቻ። ቢጨንቀውና ሰሚ ቢያጣ መሬት ቆፍሮ ለመሬት እንዳወራው ሰው ዓይነት።
በዚሁ ተመሳሳይ ዘመን ሌላም ነገር ታይቷል። በግጥሙ መዝጊያ ላይ አንድ መገረሚያ ማምጣት። ትንሽ ቆይቶም፣
የአዳራሽ ግጥሞች በሙዚቃ እየታጀቡ መቅረብ መጀመራቸው ዘለግ ያሉና መድረክ ላይ የሚያቆዩትን አመጣ። እነዚህ የተንዛዙ ግጥሞችን ወደ ኅትመት ሰፈር ሲመጡ ዘልዛላ ሆኑ።
የመጀመሪያ መጻሕፍታቸው ያማሩላቸው ገጣምያን ሳይቀሩ ግጥሞቻቸው ለዛቸውንና እምቅነታቸውን ነጠቋቸው።
ከዚህ ዘመን ገጣምያን አንዷ ሜሮን ጌትነት ነበረች። ሜሮን ነገሮችን የምታይበትና የምትፈትልበት መንገድ ግሩም ነው። "ዙረት" በሚለው የግጥም መጽሐፏ አንገት በሚያስነቀንቁ፣ልብ በሚንጡ ግጥሞቿ አስመሰከረች።
መድረኮች ላይ ስትወጣ ግን፣እንደነምሥራቅ፣እንደነ ዶክተር በድሉ፣አረዘመቻቸው። ከነርዝመቱ ለዛውን ጠብቆ የሚሄደው አሳየኸኝ ረጋሳ ይመስለኛል። ትዕግሥት ማሞም አንዳች የማይረግብ ገሞራ አላት።
በግጥም ኅትመት ዓለም ብዙዎቹ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውና ቀጣዮቹ እኩል አይደምቁም። ስስነትና እርግበት ይታይባቸዋል። በዚህ ፈተና ያልወደቀው ጋዜጠኛ ዲበኩሉ ጌታ ነው፤የእነ ደበበ ሰይፉን ደጅ እያንኳኳ ይመስላል።እነ አበረ አያሌው ገና አልተፈተኑም። ትዕግሥት ዓለምነህም ወደፊት በመጀመሪያ ግጥሟ ልክ ከመጣች፣ተዐምር ነው።ቋንቋ፣አተያይዋና Allusion አጠቃቀሟ ድንቅ ነው።
ወደ ሜሮን አዲሱ መጽሐፍ ልምጣ ። ስሜት የሚያሞቁት ከበሮ ድብደባዎች፣በቀጭን የሚመጡት ሳቆቿ ፣አንገት የሚያወዛውዙት ግርምቶች፣በአጫጭር ግጥሞቿ የምታደርጋቸው ተዐምራት የቀነሱ ይመስላል።
ቆንጆ ግጥሞች አሏት?...አዎ። ግን እንደድሮ አይደሉም። አዳዲስ ውበቶችና የቃላት ውበት ጨምራለች።
ግጥሞቿ፣ይስበኩን አይባልም። poetry does not teach:but it inspires.ይላሉ የዘርፉ ሰዎች።...ለነገሩ በዚህ የሚያምኑት ሊቃውንት በርካታ ናቸው።
እስቲ ከሜሮን ልምዘዝ፦
መተላለፍ 2
ሐቀኛ ነጋዴ በአመድ ገበያ ላይ ዱቄት ይዟል ማልዶ፣
የታይታ ሀብታም ሰው በሥጋ ወረፋ ይሰለፋል ማዶ።
ዘመን ሰውነትን ሸቀጥ አርጎ አውጥቶ ዐየን እንደዋዛ፣
የወረቀት ገንዘብ ወርቅ ሕልም እየገዛ።
ይህ ግጥሟ ሐሳቡ ብቻ ሳይሆን የቤት መምቻው ድምፅ ደማቅ ነው። ይህን ያደረጉት አናባቢዎቿ ናቸው። ሐሳቡም ግዙፍና የነፋሱን ዘመን በእፍኝ የሰፈረ ነው። ወርቅ ሕልም ፣በወረቀት እየሸጠ፤ዕንቁ በእሪያዎች ፊት እየተጣለ።
ልበ...
የአንተም ልብ ድንጋይ...
የእኔም ልብ ድንጋይ...
(ለዚያ ነው መሰለኝ)
በተጋጨን ቁጥር በፍቅር የምንጋይ።
ግጥም ሙዚቃ፣ ሥዕልም የተካተቱበት የሥነ ጽሑፍ ዘውግ ሰለሆነ፣ነፍስ ያፍነከንካል ፤ትርዒት ያሳያል።
ጋሽ ጸጋዬ በዘይቤዎቹ መዐዛ፣ በምሰላዎቹ ምትሐት ቀልብ ሲስብ፣ ገብረክርስቶስ በሜሎዲዎቹ ብብት ይኮረኩራል። ደበበ ሐሳብ እንደሽንኩርት እየላጠ ያስደምማል። ሁሉም በየራሳቸው ድንኳን የሚሰጡን ጣ'ም አለ።
ላምቦርን("ዶ/ር)ስለዚህ ሲጽፉ፦ Since every one likes pictures and most find pleasure in music,the common indifference to poetry must be due to a failure to realize that poetry is really both.

Sponsored by
Surafel
3 months ago
ዶናልድ ትራምፕ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ የ"መጻተኛ" ምስል በማህበራዊ ገጻቸው አጋሩ
#ethiopia | አሜሪካ— የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አንድ በሰንሰለት የታሰረ "መጻተኛ" (Alien) ከሳቸውና ከደህንነት አባላት ጋር ሲጓዝ የሚያሳይ ምስል በገዛ ማህበራዊ ሚዲያቸው "ትሩዝ ሶሻል" (Truth Social) ላይ በማጋራታቸው መነጋገሪያ ሆነዋል።
ምስሉ ዶናልድ ትራምፕን ከጥቁር መጻተኛ ጋር ጎን ለጎን ሲራመዱ የሚያሳይ ሲሆን፣ መጻተኛው እጁ በካቴና ታስሮ ይታያል።
ምስሉ በገሃድ የሚታይ እውነታ ሳይሆን በ AI (Artificial Intelligence) ቴክኖሎጂ የተቀናበረ መሆኑ ተረጋግጧል።
ምስሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት የተሰራጨ ሲሆን፣ ብዙዎች እንደ ቀልድ ቢመለከቱትም ሌሎች ደግሞ የቀድሞው ፕሬዝዳንት እንዲህ አይነት ምስሎችን ማጋራታቸው ለምን አስፈለገ? የሚል ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ።
"ይህ ምስል የቴክኖሎጂ ውጤት እንጂ እውነተኛ ክስተት አይደለም።"
የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ምስሉን ለምን ለማጋራት እንደመረጠ እስካሁን በይፋ የሰጠው ማብራሪያ የለም። ይሁን እንጂ ትራምፕ ከዚህ ቀደም መሰል አነጋጋሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዙ ምስሎችን ለፖለቲካዊ መልዕክቶች እና ለደጋፊዎቻቸው መዝናኛነት ሲጠቀሙ ታይተዋል።
**#donaldtrump #truthsocial #ai #alien #uspolitics #fakeimage **

በኦርዌል "1984" እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምንና ምን ናቸው?
(ቃልኪዳን ኃይሉ)
ጆርጅ ኦርዌል ማነው?
#ethiopia | ጆርጅ ኦርዌል (ትክክለኛ ስሙ ኤሪክ አርተር ብሌየር) እ.ኤ.አ. በ1903 ሕንድ ውስጥ ተወለደ። ጆርጅ ኦርዌክ በሕይወቱ ለጽሑፎቹ ትልቅ ግብዓት የሆኑ ሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች ነበሩት፦ እነሱም የፖሊስነት ተሞክሮ፣ በአውሮፓ የነበረው የድህነት ኑሮ እና የስፔን የእርስ በርስ ጦርነት፡ በፋሺዝም ላይ ለመዋጋት ወደ ስፔን ሄዶ በጦርነቱ መሳተፉ አስተሳሰቡን እና መጻሕፍቱን በዚያ ልምድና ተሞክሮው ላይ እንዲያጠነጥን አድርጎታል።
ኦርዌል በተለይ በሁለት ዝነኛ መጻሕፍቱ ይበልጥ ይታወቃል፦Animal Farm (የእንስሳት እርሻ) እና 1984 ነው።
Animal Farm የራሺያን አብዮት መነሻ በማድረግ የተጻፈ ተምሳሌታዊ (Allegory) ድርሰት ነው። "ሁሉም እንስሳት እኩል ናቸው፤ ነገር ግን አንዳንዶቹ ከሌሎቹ ይበልጥ እኩል ናቸው" የሚለው ዝነኛ ጥቅሱ ሥልጣን እንዴት አብዮተኞችን ወደ ጨቋኝነታቸው እንደሚቀይር ያሳያል።
ሌላው 1984 ይህ ደግሞ የግለሰብ ነፃነት ሙሉ በሙሉ በጠፋበት ዓለም ውስጥ የሚኖርን ሰው ሕይወት የሚተነብይ የ"ዳይስቶፒያ" (Dystopia) ልብ-ወለድ ነው።
የመከራከሪያ ነጥቦቹ (Core Ideas)
ኦርዌል በሥራዎቹ ውስጥ ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን በጽኑ ይቃወማል፦
1.የእውነት መጥፋት (The Erosion of Truth)፦ ኦርዌል በጣም የሚፈራው "እውነት" የሚባል ነገር ጠፍቶ፣ ገዢዎች የሚሉትን ብቻ ሕዝቡ እንዲያምን የሚደረግበትን ሥርዓት ነው። "በሁለንተናዊ የማታለል ዘመን እውነትን መናገር አብዮታዊ ተግባር ነው" የሚል እምነት ነበረው።
2.የቋንቋ መበላሸት (Corruption of Language)፦ ፖለቲከኞች መጥፎ ተግባራቸውን ለመሸፈን ቋንቋን እንደሚጠቀሙ ይከራከራል። ለምሳሌ "ሰላም ማስከበር" የሚለው ቃል ጦርነትን ለመሸፈን፣ "ማስተካከል" የሚለው ቃል ደግሞ ግድያን ለመሸፈን ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ያሳያል።
3. የግለሰብ ነፃነት (Individual Autonomy)፦ ሥልጣን የሰውን ልጅ አካል ብቻ ሳይሆን አእምሮውንና ትውስታውን ጭምር እንዲቆጣጠር ኦርዌል አይፈልግም።
"ኦርዌሊያን" (Orwellian) የሚለው ቃል
በአሁኑ ጊዜ ይህ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ቅጽል ጥቅም ላይ ይውላል። አንድን ሁኔታ "ኦርዌሊያን" ስንለው፣ ያ ሁኔታ መንግሥት የሰዎችን የግል ሕይወት የሚቆጣጠርበት፣ መረጃን የሚያዛባበትና ዜጎችን በውሸት ፕሮፓጋንዳ የሚያደነዝዝበት መሆኑን ለመግለጽ ነው።
1984 Vs ኢትይጵያ
"1984" እስካሁን ድረስ ጸንቶ የቆየው እንደ ተራ የአምባገነንነት ማስጠንቀቂያ ሳይሆን፣ ሥልጣን ከተራ የተግባር ቁጥጥር ባለፈ የአረዳድ (Perception) የበላይነትን ለመያዝ በሚሻበት ጊዜ እንዴት እንደሚሠራ የሚያሳይ ጥቁር ትንታኔ በመሆኑ ነው።
በጥልቅ ሲታይ፣ ሥርዓቱ በእውቀት ቁጥጥር (Epistemic Control)፣ በቋንቋ ምህንድስና እና በሥነ-ልቦናዊ ተገዥነት ላይ የተገነባ መሆኑን እንረዳለን።
1. ሥልጣን እንደ እውነት የማምረቻ መሣሪያ
የኦርዌል ዋነኛ መከራከሪያ ፍጹም ፖለቲካዊ ሥልጣን የሚገኘው እውነታን የመተርጎም አቅም ላይ ነው የሚል ነው። "ፓርቲው" ነባራዊ እውነታዎች ለፖለቲካዊ ፍላጎት ተገዥ መሆን አለባቸው ብሎ መሟገቱ እንዲሁ ለንግግር ያህል የመጣ ሳይሆን መዋቅራዊ መርህ ነው። የሚጋጩ እውነታዎችን በግዴታ አምኖ መቀበል (Doublethink) ዜጎችን የማላመጃ ዘዴ ሲሆን፣ በእውነትና በሥልጣን መካከል ያለውን ድንበር ያጠፋዋል።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውድድር በዋነኝነት የሚካሄደው በትርክት ግንባታ (Narrative Construction) ነው።
የመንግሥት ተቋማት፣ የተቃዋሚ ንቅናቄዎች እና የሚዲያ ተዋናዮች ስለ ግጭት፣ ስለ ሪፎርም እና ስለ ቅቡልነት የተራራቁ ትርክቶችን ያቀርባሉ። እዚህ ላይ ችግሩ የፕሮፓጋንዳ መኖር ብቻ ሳይሆን፣ "ትክክለኛውን የታሪክ ስሪት" የማጽደቅ ፍልሚያ ነው። የጋራ የሆነ የእውነታ መሠረት በሌለበት ሁኔታ፣ ፖለቲካዊ ፍርድ በቀላሉ የሚለዋወጥና ለማጭበርበር የተጋለጠ ይሆናል።
2. የቋንቋ ቅነሳና ፖለቲካዊ ቅርጻ (Linguistic Compression and Framing)
"ኒውስፒክ" (Newspeak) ቋንቋ የሐሳብ መሠረት (Infrastructure) መሆኑን በሚገባ የተረዳ ስልት ነው። የቃላት ግምጃ ቤትን በዘዴ በመቀነስ፣ ፓርቲው ተቃውሞን ለማሰብ የሚያስፈልጉ የግንዛቤ መሣሪያዎችን ያጠፋል።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ ምንም እንኳ አተገባበሩ እንደ መጽሐፉ የተማከለ ባይሆንም፣ ውጤቱ ግን ተመሳሳይ ነው። ከማንነት፣ ከፌዴራሊዝም፣ ከሉዓላዊነትና ከደኅንነት ጋር የተያያዙ ቃላት በጽንፍ በተራራቁ መንገዶች ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ትንታኔዎች በታፔላዎች (Labels) ይተካሉ። ውስብስብ የሆኑ ነባራዊ ሁኔታዎች በስሜት ወደተሞሉ ምድቦች ይጠቅለላሉ። ይህ ሐሳብን ባያጠፋውም እንኳ፣ አስቀድሞ ወደ ተወሰኑ የፖለቲካ አሰላለፎች እንዲፈስ ያደርገዋል። ውጤቱም ውይይቶች ገና ሳይጀመሩ በቋንቋ አጠቃቀም ብቻ ውጤታቸው እንዲወሰን ያደርጋል።
3. የታሪክ ትርክትና የማስታወስ ፖለቲካ
ፓርቲው ያለፈውን ታሪክ በመቆጣጠር፣ ከሥርዓቱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ነፃ የማጣቀሻ ነጥብ እንዳይኖር ያደርጋል። ታሪክ ለወቅታዊው ሥልጣን ቅቡልነት ሲባል በየጊዜው የሚስተካከል ተለዋዋጭ ነገር ይሆናል።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ በኢትዮጵያም እርስ በርሳቸው የሚጋጩ የታሪክ ትርክቶች ለወቅታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ድጋፍ እንዲሆኑ ተደርገው ይቀርባሉ።
ስለ ሀገር ምስረታ፣ ስለ ማንነትና ስለ ታሪካዊ በደሎች የሚደረጉ ክርክሮች የትምህርት ዘርፍ ብቻ ሳይሆኑ የፖለቲካ መሣሪያዎች ናቸው። በታሪክ ትርጓሜ ላይ ስምምነት አለመኖሩ፣ ለጋራ ሀገራዊ ትርክት መፈጠር እንቅፋት ከመሆኑም በላይ ተጠያቂነትንና እርቅን የማምጣት ሂደትን ያወሳስበዋል።
4. ቁጥጥር፣ ራስን መገደብና የሕዝብ ውይይት
"ቴሌስክሪን" (Telescreen) የማያቋርጥ ክትትልን ያመለክታል፤ ሆኖም ዋናው ተግባሩ ግለሰቡ "እየታየሁ ነው" የሚለውን ስሜት ውስጣዊ አድርጎ ራሱን እንዲቆጣጠር ማድረግ ነው።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ ክትትል በተቋማዊ፣ በዲጂታልና በማኅበራዊ መዋቅሮች አማካኝነት ይከናወናል። ምንም እንኳ ቁጥጥሩ ፍጹም ባይሆንም፣ ዜጎች የሚናገሩትን ነገር እንዲመጥኑ (Calibrate) እና ራሳዊ ቅድም ምርመራ (Self censorship) ያደርጋል።
የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ተንታኞችና ተራ ዜጎች በሕግ፣ በፖለቲካዊ ተጋላጭነትና በማኅበራዊ ጫናዎች የሚወሰኑ ድንበሮችን እያጤኑ ይንቀሳቀሳሉ
(Self censorship)። ውጤቱም ፍጹም ዝምታ ሳይሆን፣ ያልተባለው ነገር ከተባለው እኩል ትርጉም የሚሰጥበት "ስልታዊ የሐሳብ ልውውጥ" (Strategic Communication) መፈጠሩ ነው።
5. ማስገደድና የውዴታ ግዴታን ማምረት (Coercion and Consent)
በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኘው የኦብራይን (O'Brien) ገጸ-ባህሪ ዓላማው ተቃውሞን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን፣ የሰውን እምነትና አስተሳሰብ ጭምር እንደ አዲስ መቅረጽ ነው።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ የፖለቲካው ምኅዳር የተለያየና ብዙ ተዋናዮች የሚሳተፉበት በመሆኑ፣ ጫናው እንደ ኦርዌል ዓለም ወጥና ፍጹም አይደለም። ይሁን እንጂ የሕዝብን ድጋፍ በትርክት የማምረት ፍላጎት ማዕከላዊ ነው። የሚዲያ ሥነ-ምህዳሩ (መደበኛም ሆነ ማኅበራዊ) የተወሰኑ ትርክቶችን በማግነንና ሌሎችን በማዳከም ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
ትግሉ አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብን ከመጫን ይልቅ፣ በተሰባበረ የመረጃ አውድ ውስጥ የትርክት የበላይነትን (Narrative Dominance) የመያዝ ትግል ነው።
ማጠቃለያ
የ"1984" ፋይዳ ያለው በፅንሰ-ሐሳብ ግልጽነቱ ላይ ነው። ሥልጣን ግንዛቤን፣ ቋንቋንና ትውስታን በመቆጣጠር ራሱን እንዴት እንደሚያደላድል ነጥሎ ያሳየናል።
ኢትዮጵያ የኦርዌልን ዝግ የአምባገነንነት፣ የፖለቲካው ሜዳ ተለዋዋጭና የተለያየ ተፅዕኖ ያላቸው ኃይሎች የሚጋጩበት ነው።
ኦርዌል የለያቸው መሠረታዊ መዋቅሮች መልክ ቀይረው ይታያሉ። መረጃን መቆጣጠር፣ ቋንቋን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀምና ታሪክን ፖለቲካዊ ማድረግ እስካሁንም የሥልጣን ትግሉ ማዕከል ናቸው።

በዋይት ሃውስ የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ ተሰማ
* ፕሬዝዳንት ትራምፕ በድንገት ተወሰዱ
#ethiopia | ዛሬ ሌሊት በዋሽንግተን ሒልተን ሆቴል በተካሄደው የዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች የእራት ግብዣ (White House Correspondents' Dinner) ላይ ያልተጠበቀ የተኩስ ድምፅ በመሰማቱ ከፍተኛ ግርግር ተፈጥሯል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደህንነት አካላት ጥበቃ ተደርጎላቸው በአስቸኳይ ከቦታው እንዲወጡ ተደርጓል።
እንደ የጸጥታ አካላት ገለፃ ከ7 እስከ 8 የሚደርሱ የጥይት ድምፆች ተሰምተዋል። በወቅቱ የነበሩ ታዳሚዎች በድንጋጤ ከጠረጴዛ ስር ተሸሽገው ነበር።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በራሳቸው የትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገፃቸው ላይ "ተኳሹ በቁጥጥር ስር ውሏል" ሲሉ አረጋግጠዋል። የደህንነት መስሪያ ቤቱም አንድ ግለሰብ መያዙን ገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ፣ ቀዳማዊት እመቤቷና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት (የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴልን ጨምሮ) በሰላም ከቦታው መውጣታቸው ታውቋል።
ትራምፕ "ዝግጅቱ መቀጠል አለበት" (Let the show go on) የሚል አስተያየት የሰጡ ቢሆንም፣ የጸጥታ አካላት ግን ጥብቅ ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።
ይህ ክስተት አሜሪካ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ውጥረትና የደህንነት ስጋት ዳግም ያሳየ ነው። የጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት ሙከራ መደረጉ አፍን በእጅ አስከድኗል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰላም ቢወጡም የደህንነት አካላቱ እንዴት እንዲህ ያለ ክፍተት እንደተፈጠረ ትልቅ ምርመራ ይጠብቃቸዋል።
ዲፕሎማሲውና ፖለቲካው በጥይት ድምፅ ታውኳል!
የዓለም ዓይኖች ወደ አሜሪካ ዞሯል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getu #trumpnews #breakingnews #whitehousedinner #washingtondc #trumpsafety #secretservice #globalnews #ትራምፕ #ሰበርመረጃ #ዋሽንግተን #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
ትራምፕ ለኢራን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፦ "ስምምነቱ እስኪከበር ጦራችን ከቀጠናው አይወጣም!"
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የጦር መርከቦች፣ አውሮፕላኖች እና ወታደራዊ አባላት በኢራን እና በዙሪያዋ ባለበት እንደሚቀጥሉ በዛሬው ዕለት አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መግለጫ ኢራን በቅርቡ የተደረሰውን "እውነተኛ ስምምነት" ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጓ እስኪረጋገጥ ድረስ ወታደራዊ ኃይሉ ከቀጠናው እንደማይነቃነቅ በግልጽ አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው ላይ አሜሪካ አስፈላጊ የሆኑ ጥይቶችን፣ የጦር መሣሪያዎችን እና ቀደም ሲል በከፍተኛ ሁኔታ የተዳከመውን ጠላት ዳግም ለመደምሰስ የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ወታደራዊ ግብዓቶች ዝግጁ አድርጋ እንደምትቆይ ገልጸዋል። ይህ እርምጃ ስምምነቱ በተገቢው ሁኔታ መከበሩን ለመከታተልና ቁጥጥር ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ፕሬዝዳንት ትራምፕ አክለው አስረድተዋል።
በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ በሰጡት ማስጠንቀቂያ ኢራን የተደረሰውን ስምምነት የማታከብር ከሆነና የማታስከብር ከሆነ አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ሁኔታ እና በከፍተኛ ደረጃ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቀዋል። ይህ መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረበት ወቅት የወጣ መሆኑ አሳሳቢ አድርጎታል፡፡
seledadotio

ትራምፕ ለኢራን መሳሪያ መሸጥ ክልክል ነው አሉ
#ethiopia | የቀድሞውና ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በለመዱትና በወደዱት “የታሪፍ ጦርነት”ስልታቸው ዳግም ብቅ ብለዋል። ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ለማንኛውም ለኢራን የጦር መሳሪያ ለምታቀርብ አገር የአሜሪካ ገበያ ደጃፍ እንደሚዘጋባት በግልጽ አስታውቀዋል።
ማንኛቸውም የኢራን ወዳጅ ወይም አጋር የሆኑ አገራት ለቴህራን ወታደራዊ ድጋፍ ካደረጉ፣ ወደ አሜሪካ በሚልኩት ማናቸውም ምርት ላይ 50% ታሪፍ ይጣልባቸዋል።
ትራምፕ ማስጠንቀቂያው ሁሉንም የንግድ ዘርፎች እንደሚያካትትና ከአሜሪካ ቀረጥ የሚያመልጥ ምንም ዓይነት ምርት እንደማይኖር አስገንዝበዋል።
አሜሪካ እና ኢራን ለረጅም ጊዜ “የሰላም መንገድ” ሲጓዙ መቆየታቸውን የጠቀሱት ትራምፕ፣ ይህ እርምጃቸው ግን የዋሽንግተንን ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል።
ይህ የትራምፕ ጠንካራ ዛቻ የመጣው ቀጣናው በሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ውስጥ ባለበት ወቅት መሆኑ፣ ስምምነቱን አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። በተለይም ከቴህራን ጋር የንግድና የወታደራዊ ትብብር ያላቸው አገራት በአሜሪካ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እና በኢራን ወዳጅነት መካከል እንዲወዛገቡ የሚያደርግ ነው።
“ይህንን እያወቁ ያድርጉት” ሲሉ ያስጠነቀቁት ትራምፕ፣ በቀጣይ የንግድ ግንኙነቶች ላይ የፖለቲካ ታማኝነት ዋነኛው መስፈርት እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ትራምፕ #ኢራን #የንግድጦርነት #ታሪፍ #አሜሪካ #ዓለምአቀፍዜና #trump #iran #tariffs

ትራምፕ ኢራንን የእሳት ምድጃ መሆኗ ነው አሉ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥን ዝግ ያደረገችው ኢራን በአስቸኳይ ሰርጡን እንድትከፍት እጅግ ጥብቅ የሆነ የጊዜ ገደብ አስቀመጡ። ፕሬዝዳንቱ ይህ ካልሆነ ግን በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት እንደሚሰነዘር ዝተዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በራሳቸው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ (Truth Social) ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኢራን እስከ ረቡዕ መንፈቀ ሌሊት 9፡30 (በቴህራን ሰዓት አቆጣጠር) ድረስ ሰርጡን ክፍት ማድረግ እንዳለባት ገልጸዋል። ይህ ቀነ-ገደብ የታለፈው የዲፕሎማሲ ጥረት ውጤት ካላመጣ አሜሪካ ወደ ወታደራዊ አማራጭ እንደምትገባ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
"የቆመ ድልድይም ሆነ የኃይል ማመንጫ አይኖራችሁም"
ትራምፕ ቀደም ብለው ለዎልስትሪት ጆርናል በሰጡት ቃል፣ ማስጠንቀቂያቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ ወደኋላ እንደማይሉ አስታውቀዋል።
"እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ ሰርጡ ካልተከፈተ፣ በኢራን ምድር ምንም ዓይነት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችም ሆኑ የቆሙ ድልድዮች አይኖሯቸውም"
ሲሉ የዛቱት ፕሬዝዳንቱ፣ ጥቃቱ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረገ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ የትራምፕ አስተዳደር የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋትን እንደ "ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ጦርነት" ነው የፈረጀው። በዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ይህ የባሕር መስመር መዘጋቱ፣ አሜሪካ ወታደራዊ ኃይል እንድትጠቀም ገፍቷታል ተብሏል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው ወታደራዊ ዝግጁነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ተመልክቷል።
የዓለም መገናኛ ብዙኃን ትኩረት አሁን ቴህራን ለዚህ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ በምትሰጠው ምላሽ ላይ አርፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #አሜሪካ #ኢራን #ትራምፕ #የሆርሙዝሰርጥ #የዓለምዜና #ውጥረት #trump #iran #hormuzstrait #breakingnews

ዶናልድ ትራምፕ ዝነኛውንና አስፈሪውን የአልካትራዝ እስር ቤት በቢሊዮኖች በሚቆጠር ወጪ ዳግም ሊያስከፍቱ ነው
የኔታ ሚዲያ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሁኑ ወቅት የቱሪስት መስህብ ሆኖ እያገለገለ የሚገኘውን ዝነኛውን "አልካትራዝ" (Alcatraz) እስር ቤት በዘመናዊ መልኩ ዳግም ስራ ለማስጀመር የ152 ሚሊዮን ዶላር በጀት ጠየቁ።
ትራምፕ በ Truth Social ገጻቸው እንደገለጹት እስር ቤቱ ዳግም የሚከፈተው የአሜሪካ እጅግ ጨካኝና አደገኛ ወንጀለኞችን ለማሰር ታስቦ ነው።
ይህ የ152 ሚሊዮን ዶላር ጥያቄ ለ2027 የፈረንጆች በጀት ዓመት የቀረበ ሲሆን እስር ቤቱን እጅግ ዘመናዊና አስተማማኝ ለማድረግ የሚውል ነው።
ይህም በአጠቃላይ ለማረሚያ ቤቶች ቢሮ ከተመደበው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የሚካተት ነው።
ዘ ሮክ" (The Rock) በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀውና በሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ላይ የሚገኘው ይህ እስር ቤትንእንደ አል ካፖን ያሉ ዝነኛ ወንጀለኞች የታሰሩበትና በፊልሞችም ጭምር የሚታወቅ አስፈሪ ስፍራ ነው።
ይህ የትራምፕ እቅድ በካሊፎርኒያ ፖለቲከኞች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እየቀረበበት ነው። የቀድሞዋ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ እቅዱን የማይረባና የህዝብን ገንዘብ ማባከን ስትል ነቅፋዋለች።
ደሴቱ ላይ በአሁኑ ወቅት የቧንቧ ውሃና የፍሳሽ ማስወገጃ የሌለ ሲሆን ማንኛውም አቅርቦት በጀልባ መጓጓዝ ይኖርበታል።
እስር ቤቱ እ.ኤ.አ በ1963 ከመዘጋቱ በፊት ከማንኛውም የፌደራል እስር ቤት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ወጪ ይጠይቅ ነበር።
በአሁኑ ወቅት በብሔራዊ ፓርክ አገልግሎት ስር የሚገኘው አልካትራዝ በዓመት 60 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለሀገሪቱ ያስገኛል።
ይህ አወዛጋቢ የፕሬዝዳንቱ እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን በአሜሪካ ኮንግረስ መፅደቅ ይኖርበታል።

5 months ago
''በ48 ሰዓታት ውስጥ ሆርሙዝን ካልከፈታችሁ የኃይል ማመንጫዎቻችሁን አመድ እናደርጋቸዋለን"
#ethiopia | ፕሬዝዳንት ትራምፕ በራሳቸው የትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገፅ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኢራን የዓለም የነዳጅ መስመር የሆነውን የሆርሙዝ ባህርን በ48 ሰዓታት ውስጥ ለትራንስፖርት ክፍት ካላደረገች፣ የአሜሪካ ጦር በሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል።
"ኢራን በ48 ሰዓታት ውስጥ የሆርሙዝ የባህር በርን ካልከፈተች፣ የአሜሪካ ጦር የኢራንን የኃይል ማመንጫዎች በመምታት ከጥቅም ውጭ ያደርጋቸዋል" — ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ጥቃቱ የሚጀምረው በሀገሪቱ ካለው ትልቁ የኃይል ማመንጫ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ይህ እርምጃ የዓለምን የነዳጅ ገበያ ለማረጋጋትና የአሜሪካን ጥቅም ለማስከበር የሚወሰድ እንደሆነ አመልክተዋል።
የተተነበዩ የጥቃት ኢላማዎች
ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚገምቱት፣ ትራምፕ "ትልቁ ማመንጫ" ሲሉ የጠቀሱት፦
* የቡሼህር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ወይም
* በቴህራን አቅራቢያ የሚገኘውን ግዙፉን የዳማቫንድ የኃይል ጣቢያን ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢራን ምላሽና የዓለም ስጋት
በሌላ በኩል ቴህራን ለአሜሪካ ማስፈራሪያ ምላሽ ለመስጠት አልዘገየችም። ማንኛውም ዓይነት ጥቃት በአሜሪካ በኩል ከተሰነዘረ፣ በአካባቢው በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችና ጥቅሞች ላይ "ፈጣንና ከባድ" አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።
ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው የቃላት ጦርነትና ወታደራዊ ዝግጅት፣ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ከማድረጉም በላይ ቀጣናውን ወደ ለየለት ጦርነት ሊከተው ይችላል በሚል ዓለም በከፍተኛ ስጋት ሰኞ ምሽት የሚጠናቀቀውን የጊዜ ገደብ እየተጠባበቀ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #trump #iran #middleeasttension #hormuzstrait #breakingnews #globaloilmarket #usa #geopolitics

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን ጦርነት የአጋሮቿ ወታደራዊ ድጋፍ እንደማያስፈልጋት ገለጹ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ ጦር ኃይል በኢራን ጦርነት ውስጥ "ከእንግዲህ ወታደራዊ እርዳታ አያስፈልገውም" ሲሉ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው "ትሩዝ ሶሻል" (Truth Social) ማህበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፤ የአሜሪካ ጦር ኃይሎች በኢራን ጦርነት ውስጥ ከማንም ወገን ወታደራዊ እገዛ እንደማይሹ ገልጸዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ የወጣው፣ ለነዳጅ ዝውውር ቁልፍ የሆነውን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ (Strait of Hormuz) ክፍት ለማድረግ እና ደህንነቱን ለመጠበቅ አጋር ሀገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ቀደም ሲል ያቀረቡት ጥሪ በአብዛኞቹ ተቀባይነት ካጣ በኋላ ነው።
ቀደም ሲል አሜሪካ ከሌሎች የአውሮፓ እና የቀጣናው ሀገራት ጋር በመተባበር በባህር ሰርጡ ላይ ያለውን ስጋት ለመመከት ጥሪ ስታቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ አጋሮቿ ለጥሪው አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሁን ባወጡት መግለጫ ግን አሜሪካ ብቻዋን የጥቃቱን እርምጃ ለመቀጠል ሙሉ ወታደራዊ አቅም እንዳላት አመልክተዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ አቋም አሜሪካ በቀጣናው በምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ላይ ያላትን የግል ውሳኔ ሰጪነት የሚያጠናክር እንደሆነ ተገምቷል ሲል የዘገበው አል አረብያ ነው ።
ልዑል ወልዴ

ጂጂ ዩቶጵያ በሚለው ዘፈኗ ጊዜያችን ሳያልቅ "ልዕለ-ሰው" እንድንሆን ትመክረናለች!!
👉 እውነትን ከውሸት ለይቶ ለትውልዱ መንገር አስቸጋሪ እንደሆነም ታስረዳለች
ዘፈንን ለሰላም ፣ለሀገር ፍቅር እና ለሰው ፍቅር ካዋሉ ኢትዮጵያዊ አቀንቃኞቻችን መሀል እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ ) ትጠቀሳለች።
የዘፈኑ ርዕስ ከግሪክ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም በፖለቲካ፣ በህግ እና በማህበራዊ ኑሮ ረገድ ምንም ዓይነት እንከን የሌለበት፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት ምናባዊ ዓለም የሰፈነበት ፍጹም የሆነ ማህበረሰብ ማለት ነው።
ትልቁ ጥያቄ ግን በሰው ልጅ ፀብ አጫሪነት እና ስግብግብ ባህሪ እንደዚህ ዓይነት ማህብረሰብ መፍጠር ይቻላል ወይ የሚለው ነው?
ግጥሙ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ለአለም የሚተርፍ ፍቅርን ይሰብካል።ዩቶጵያ የምትገኘው በደመና ላይ ሳይሆን፣ "በልብ ውስጥ" እና "በእውነት መሰረት" ላይ በመመስረት ነው ይለናል።
ጂጂ "አንድነትን የሰው ልጅ መዋደድ" በማለት ሰላም የሚገኘው በፖለቲካ ስምምነት ሳይሆን በሰው ልጅ የልብ መለወጥ ነው ትለናለች። ሰው ልቡ ካልተለወጠ ፖለቲካው ቢለዋወጥም ሰላም እንደማይመጣ በመንገር ሰላም በግዳጅ ሳይሆን በፍቅር እንደሚመጣ በመንገር ስለ አንድነት ትሰብካለች።
ጂጂ "ሰው አይርሳ የሰላምን መንገድ" ስትል የተለመደ ምክር እየመከረችን ሳይሆን ፍጹም የሆነ ትዕዛዝ እያዘዘችን ነው። ሰላም ለሰው ልጅ አማራጭ ሳይሆን የሰውነት መገለጫ ግዴታ መሆኑን ትናገራለች።
"መሰረቱን ያጽናልን በእውነት" ስትል ጂጂ ለ"እውነት" የሰጠችውን ከፍተኛ ቦታ ያሳያል። ውሸት ባለበት ሰላም ሊኖር አይችልም፤ ሰላም በእውነት ላይ ካልተመሰረተ "የመቃብር ሰላም" እንደሆነም ዘፈኑ ያስረዳል።
ጂጂ "Sing, sing, children of the world" በማለት የአለም ልጆች ሰላም ለጠማት አለም ስለ ሰላም እንዲዘፍኑ ትጠይቃለች።
ጂጂ "I believe we can survive in Uthopia" በማለት የሰው ልጅ ካለበት መከራ ወጥቶ ወደ ተሻለ ዓለም ሲሸጋገር ለማየት እንደናፈቀች እናያለን።
"ኢትዮጵያ"ን እንደ ሀገር ብቻ ሳይሆን እንደ ቀዳማይ ምስል ጂጂ ስላታለች። ኢትዮጵያ በግጥሙ ውስጥ "የደስታችን ቤት" በማለት ዜጎች ወደ እናታቸው ቤት ወደ ሰላማዊው መሠረታቸው የመመለስ ፍላጎታቸውን ታንፀባርቃለች።
ግጥሙ "አንድነትን የሰው ልጅ መዋደድ" ግለሰባዊ ፍላጎት ወደ ማህበራዊ አንድነት፣ ማህበራዊ አንድነት ደግሞ ወደ አለም አቀፋዊ ፍቅር የሚያድግበትን " ሂደት ያሳያል።
ዩቶጵያ ማለት ለጂጂ የሰው ልጅ ግጭቶችን ጨርሶ፣ እውነትና ነፃነት ተዋህደው የሚኖሩበት የታሪክ ፍፃሜ ነው። ግጥሙ ተስፋን መሰረት በማድረግ፣ መንፈስ ሁሌም ወደ ተሻለ ብርሃን እንደሚገሰግስ የሚያሳይ የጂጂ ፍልስፍና ነጸብራቅ ነው።
ጂጂ What’s the truth and what are lies በማለት እወነትና ውሸትን ለይቶ ለትውልድ ማስረዳት ከባድ እንደሆነ ትነግረናለች። እዚጋ ለጂጂ እውነት"ጭምብል" ናት። ጂጂ "Signal spake between the stations" በማለት የሰው ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በሃሰት መረጃዎች መካከል ያለውን ግራ መጋባት ትገልፃለች።
ጂጂ "ፍቅራችን ነው መዋደድ አይጥፋ" በሚለው ጥሪዋ ሰላም የሰው ልጅ በራሱ ፍቃድ የሚፈጥረው እሴት እንደሆነ ትናገራለች ።
A hundred years from now / Who'll be left to stay" የሚለው የግጥሙ ክፍል የሰው ልጅ ሟች መሆኑን ሲረዳ ነው ህይወቱን በትክክለኛ መንገድ መምራት እንደሚጀምር ይሰብካል።
ግጥሙ "ጊዜ ለዘላለም አይቆይም" በማለት የሰላምን መንገድ አሁኑኑ እንድንይዝ መገፋፋቱ ህልውናዊ ጥሪ ነው።
"ልጅ ተወልዶ ወተትም ይጠጣ" የሚለው መስመር ሰላም ማለት ረቂቅ ቃላት ሳይሆኑ፣ አንድ ህጻን ወተት የሚጠጣበት፣ ምድር ፍሬዋን የምትሰጥበት "መኖር" እንደሆነ እንረዳለን።
ባጠቃላይ ይህ ዘፈን በልባችን ውስጥ ያለውን ብርሃን ተከትለን በመጓዝ ከግለሰብ አልፎ ለአለም የሚተርፍ ሰላም ማምጣት እንደምንችል ይሰብካል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ለማድረግ አሁን ላይ ፍላጎት እንደሌላቸው ገለጹ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሁኑ ወቅት ከኢራን ጋር ያለውን ጦርነት ለማቆም የሚያስችል ድርድር ለማድረግ ዝግጁ እንዳልሆኑ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ኢራን በወታደራዊ ዘመቻው "ሙሉ በሙሉ ተሸንፋለች" ባሉበት ወቅት መሆኑን አል አራቢያ ዘግቧል።
የአሜሪካ እና እስራኤል ጥምር ኃይል በኢራን ላይ የጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በሁለተኛ ሳምንቱ ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገጽ (Truth Social) ላይ ባሰፈሩት መረጃ "ኢራን ሙሉ በሙሉ ተሸንፋለች" ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የቴህራን ባለስልጣናት ጦርነቱን ለማቆም ስምምነት ቢፈልጉም፣ እሳቸው ግን አሁን የቀረበውን አይነት ስምምነት ለመቀበል ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ትራምፕ "የሀሰት ሚዲያዎች የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ ያስመዘገበውን ድል መዘገብ አይፈልጉም፤ ኢራን ስምምነት ትፈልጋለች፤ ነገር ግን እኔ የምቀበለው አይነት ስምምነት አይደለም" በማለት አቋማቸውን በግልጽ አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ስማቸው ያልተጠቀሰ የዋይት ሃውስ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደገለጹት፣ የመካከለኛው ምስራቅ አጋር ሀገራት የተኩስ አቁም ድርድር እንዲጀመር ጥረት ቢያደርጉም ትራምፕ ግን ጥረቱን ውድቅ አድርገውታል።
ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ ትኩረታቸው የኢራንን ወታደራዊ አቅም የበለጠ ማዳከም ላይ እንደሆነና "ምናልባት ሌላ ቀን እንጂ አሁን የድርድር ጊዜ አይደለም" ማለታቸው ተነግሯል።
በሌላ በኩል ኢራን በበኩሏ የአሜሪካ እና የእስራኤል የአየር ድብደባ ካልቆመ ምንም አይነት የተኩስ አቁም ድርድር እንደማታደርግ አስታውቃለች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ ከዚህ ቀደም ከአሜሪካ ጋር በነበራቸው ድርድር "መጥፎ ልምድ" እንዳላቸው በመጥቀስ፣ ከአሜሪካ ጋር መነጋገር በአሁኑ ወቅት በአጀንዳቸው ውስጥ እንደሌለ ገልጸዋል።[2][4]
በአሜሪካ "Epic Fury" (ታላቅ ቁጣ) በሚል ስያሜ በሚመራው በዚህ ጦርነት፣ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ባለፈው አርብ በኢራን ዋነኛ የነዳጅ ማከፋፈያ በሆነችው ካርግ ደሴት (Kharg Island) ላይ ከፍተኛ የአየር ድብደባ መፈጸሙ ይታወሳል።
ይህም በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ መናወጥ መፍጠሩ ተዘግቧል።
ጦርነቱ እስካሁን ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉንና በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ይበልጥ እያባባሰው መሆኑ ተመልክቷል።

ትራምፕ ዩናይትድ ኪንግደም እና ቻይና የጦር መርከቦችን ወደ ሆርሙዝ ስትሬት እንደሚልኩ ተስፋ አደርጋለሁ አሉ።
የኔታ ሚዲያ
ዶናልድ ትራምፕ በ "Truth Social" ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የሆርሙዝ ስትሬትን ለመጠበቅ በርካታ ሀገራት የጦር መርከቦችን እንደሚልኩ ገልጸዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ከእነዚህ ሀገራት መካከል እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
እስከዚያው ድረስ ግን ዩናይትድ ስቴትስ የባህር ዳርቻውን በቦምብ ትደበድባለች እንዲሁም የኢራን ጀልባዎችንና መርከቦችን በየተራ ከውሃው ላይ እየመታች ታሰጥማለች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በቅርቡ የሆርሙዝ ስትሬትን በእጃችን እናስገባለን ሲሉ ገልፀዋል
ዩናይትድ ኪንግደም ግን ወደ የውሃ መስመሩ መርከቦችን እንደምትልክ እስካሁን የሰጠችው ፍንጭ የለም።

ፈንጂ ወይስ ድርድር? በሆርሙዝ ሰርጥ እየመጣ ያለው ወታደራዊ ውጥረት
👉የባህር ላይ ፈንጂዎች ስምሪት፦ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ተቋማት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የንግድ መርከቦች ማለፊያ መስመር ላይ የባህር ውስጥ ፈንጂዎችን (Naval Mines) ለማሰማራት እየተንቀሳቀሰች መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ማየታቸውን CBS ዘግቧል።
👉የአሰራር ዘዴ፦ ኢራን ፈንጂዎቹን ለማጓጓዝ አነስተኛ ጀልባዎችን እየተጠቀመች ሲሆን፣ እያንዳንዱ ጀልባ ከ2 እስከ 3 የሚደርሱ ፈንጂዎችን የመጫን አቅም እንዳለው Investing Live ጠቅሷል።
👉የኢራን የፈንጂ ክምችት፦ ኢራን በክምችቷ ውስጥ ከ2,000 እስከ 6,000 የሚደርሱ የራሷ፣ የቻይና እና የሩሲያ ሰራሽ የባህር ውስጥ ፈንጂዎች እንዳሏት ይገመታል።
👉የዶናልድ ትራምፕ ማስጠንቀቂያ፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ፈንጂዎቹን በአስቸኳይ እንድታነሳ ካልሆነ ግን "ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ" ወታደራዊ እርምጃ እንደሚጠብቃት በ TruthSocial ገጻቸው አስጠንቅቀዋል።
👉የአሜሪካ የባህር ኃይል ሚና፦ የአሜሪካ የባህር ኃይል በወሽመጡ የሚያልፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ጥበቃ እንደሚያደርግ ትራምፕ የአስቸኳይ ጊዜ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
👉የእስራኤል እና አሜሪካ ግንኙነት፦ አሜሪካ እስራኤል የኢራንን የኢነርጂ እና የነዳጅ መሰረተ ልማቶች ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም መጠየቋን Axios ዘግቧል።
የነዳጅ ገበያ ስጋት፦ በዚህ ውጥረት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ የታየ ሲሆን፣ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ (WTI) ዋጋ እስከ 87 ዶላር ደርሶ ነበር።
👉የጎልድማን ሳክስ ግምት፦ ውጥረቱ ካልረገበ በ2026 አራተኛ ሩብ ዓመት የነዳጅ ዋጋ እንደ ሁኔታው አስከፊነት እስከ 93 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል።
👉የዲፕሎማሲ ጥረት፦ የአሜሪካ ልዩ ተወካይ ዊትኮፍ (Vitkoff) ወደ እስራኤል በመጓዝ ኢራን ለንግግር ፈቃደኛ መሆኗንና የዲፕሎማሲ መፍትሄ የመኖሩን ሁኔታ እንደሚመረምሩ ተገልጿል።
👉የኢራን አጸፋዊ ምላሽ፦ ኢራን በበኩሏ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ለሚደረገው እገዳ ምላሽ በሚመስል መልኩ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የዛቻ መልእክት ማስተላለፏ ተጠቅሷል።
ምንጮች፦ CBS News, Axios, Investing Live, Goldman Sachs Internal Note እና የዶናልድ ትራምፕ ማህበራዊ ገጽ

ኢራን ይፋ ያደረገችው "ኦፕሬሽን አል-ቫድ አል-ሳዲቅ 4" ( እውነተኛ ቃል ኪዳን 4 )(Operation True Promise 4)
ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም የኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን ይፋ ያደረገው "ኦፕሬሽን አል-ቫድ አል-ሳዲቅ 4" (Operation True Promise 4) በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀያየረ ያለና ቀጣናዊ ጦርነት የመቀስቀስ ዕድሉ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ እርምጃ ነው።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) "እውነተኛ ቃል ኪዳን 4" (Truthful Promise 4) በሚል የሰየመውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ መጀመሩን አስታወቀ ይህ ጥቃት የተሰነዘረው ዛሬ ማለዳ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸሙትን የአየር ጥቃት ተከትሎ የተወሰደ የአጸፋ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
1. የኦፕሬሽኑ ዋና ዓላማዎች
ኢራን ይህንን ጥቃት የጀመረችው እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር እና የሚሳይል ጣቢያዎች ላይ ለሰነዘሩት ጥቃት አጸፋ ለመስጠት ነው። እንደ ኢራን መንግስት ገለጻ ጥቃቱ ያነጣጠረው በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ነው
* በእስራኤል ግዛት ላይ፦ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሳይሎች እና ድሮኖች ወደ እስራኤል መተኮሳቸው ተዘግቧል።
* በአረብ ሀገራት በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ፦ ጥቃቱ ከዚህ ቀደም ከነበሩት በተለየ መልኩ የአሜሪካ ጦር በሚገኝባቸው የአረብ ሀገራት (UAE፣ ኳታር፣ ባህሬን እና ኩዌት) ላይ ያነጣጠረ ነው።
የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) የሚከተሉትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎች መምታቱን አስታውቋል
* አል ዳፍራ (Al Dhafra) የጦር ሰፈር -
UAE:
አቡ ዳቢ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ዋና ኢላማ ነበር። በደረሰው የሚሳይል ስብርባሪ በአቡ ዳቢ አንድ ሰው መሞቱ ተረጋግጧል።
* አል ኡዴይድ (Al Udeid) - ኳታር:
በመካከለኛው ምስራቅ ትልቁ የአሜሪካ የጦር ሰፈር የሚገኝበት ቦታ።
* ባህሬን (5ኛው የባህር ኃይል ክፍለ ጦር): የአሜሪካ ባህር ኃይል ጠንካራ ይዞታ።
* ሃይፋ እና ቴል አቪቭ - እስራኤል: በእስራኤል የነዳጅ ማጣሪያዎች እና ወታደራዊ ማዕከላት ላይ ጥቃት መሞከሩ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፍተኛ ወታደራዊ እርምጃ (Major combat operation) መጀመሩን ገልጸዋል ይህ ጥቃት ኢራን ከአሜሪካ ጋር በኒውክሌር ጉዳይ ላይ በኦማን በኩል ድርድር በጀመረችበት ዋዜማ መከሰቱ ድርድሩን ሙሉ በሙሉ አክሽፎታል።
ሩሲያ (በዲሚትሪ ሜድቬዴቭ በኩል) አሜሪካ ድርድሩን እንደ ሽፋን በመጠቀም ጥቃት ፈጽማለች ስትል ወቅሳለች ይሁን እንጂ ሩሲያ ከትራምፕ ጋር ያላትን ግንኙነት ላለማበላሸት በቀጥታ ጦርነቱ ውስጥ ከመግባት ልትቆጠብ እንደምትችል ይገመታል።
UAE፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች የባህረ ሰላጤው ሀገራት የአየር ክልላቸውን ዘግተዋል ጥቃቱ በእነሱ ግዛት ላይ ባሉ የአሜሪካ ሰፈሮች ላይ መነጣጠሩ ሀገራቱን ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ ጥሏቸዋል።
የኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን የዚህን የአፀፋ ኦፕሬሽን ጥቃት ከማብሰሩ ጥቂት ቀናት በፊት የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናትን (ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትር ካትዝን ጨምሮ) "የግድያ ዝርዝር" (Hit list) ይፋ አድርጎ ነበር።
ይህም ኢራን ወደፊት ያልተገደበ ጦርነት ውስጥ ለመግባት መዘጋጀቷን የሚያሳይ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል።

6 months ago
በስሜታችሁ ላይ ብቻ አትመኩ!
ብዙዎቻችን "ልብህ የሚልህን ስማ" የሚለውን ምክር እንደ ወርቅ እንቆጥረዋለን። ግን ስነ-ልቦና ባለሙያው ሳቻ ባቺም በአዲሱ መጽሐፉ ላይ እንደሚለው ከሆነ፣ ስሜቶቻችን ሁልጊዜ እውነተኞች አይደሉም፤ አንዳንዴም ክፉኛ ያታልሉናል።
ስለ ስነ-ልቦና የምናምናቸውን 4 የተሳሳቱ አመለካከቶች እስቲ እንያቸው፡
"ስሜት አይዋሽም"
ለምሳሌ አስፈሪ ፊልም ስታዩ ልባችሁ ይመታል፣ ትፈራላችሁ። ምንም እንኳን አደጋ እንደሌለ ብታውቁም ስሜታችሁ ግን "አደጋ አለ" ይላችኋል። ስሜት እንደ አየር ሁኔታ ተለዋዋጭ ስለሆነ ሁልጊዜ እውነት ነው ብላችሁ አትደምድሙ።
መፍትሄ፡ የሚሰማችሁን ስሜትና ምክንያቱን ለይታችሁ እወቁ። "አሁን የሚሰማኝ ፍርሃት/ጭንቀት ከእውነታው ጋር ይገጥማል?" ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ።
2. "ውጥረት ስራ ያቀላጥፋል"
አንዳንዴ ለጥቂት ጊዜ መወጠር ንቁ ሊያደርገን ይችላል። ነገር ግን "ውጥረት ውስጥ ስሆን በደንብ እሰራለሁ" ብሎ ማመን ስህተት ነው። በሂደት አቅማችን እንዲደክም እና እንድንዝል ያደርገናል።
መፍትሄ፡ ከመጠን በላይ መልፋት ውጤታማ እንደማያደርግ ተረድታችሁ፣ አቅማችሁ ሲዝል እረፍት ውሰዱ።
3. "መጨነቅ አስፈላጊ ነው"
ስለ ነገው አየር ንብረትም ይሁን ስለ ጤናችን መጨነቅ ውጤቱን አይለውጠውም። እንዲያውም አብዛኛው የምንጨነቅላቸው ነገሮች በጭራሽ አይከሰቱም።
መፍትሄ፡ "የጭንቀት ጊዜ" መድቡ (ለምሳሌ በቀን 15 ደቂቃ)። ከዚያ ውጭ ጭንቀት ሲመጣ "አቁም!" በማለት ለሌላ ስራ ትኩረት ስጡ።
4. "ሁኔታዎችን መቀበል እጅ መስጠት ነው"
የማይለወጥን ነገር (ለምሳሌ የፍቅር ግንኙነት ማብቃቱን ወይም አቅምህን የሚበልጥ ስራን) አምኖ መቀበል መሸነፍ አይደለም። ይልቁንም ለውስጥ ሰላም እና ወደፊት ለመራመድ ትልቁ መንገድ ነው።
ማጠቃለያ፡ ስሜታችሁን መርምሩ እንጂ በጭፍን አትከተሉት!
👉ይህ ጽሁፍ የተወሰደው "The Truth About Feelings" (በጀርመንኛ "Gefühle sind keine Tatsachen") ከተሰኘው የስነ-ልቦና ባለሙያው ሳቻ ባቺም መጽሐፍ ነው።

ኦባማ ትራምፕ እኔና ባለቤቴ ላይ መሳለቁ አደገኛ ነገር ነው አሉ
#ethiopia | የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ፣ ዶናልድ ትራምፕ እሳቸውን እና ባለቤታቸውን ሚሼል ኦባማን ዝንጀሮ አስመስሎ በሚያሳይ ምስል ላይ የሰጡትን ጠንከር ያለ ምላሽ ይፋ አደረጉ። ኦባማ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ድርጊቱ የአሜሪካን ፖለቲካዊ ስርዓት እና የንግግር ባህል በእጅጉ የሚያሽቆለቁል መሆኑን ገልጸዋል።
የውዝግቡ መነሻ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስሉን በራሳቸው የትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገጽ ላይ ያጋሩት ሲሆን፣ ምስሉ ኦባማን እና ባለቤታቸውን ሚሼልን የሚያንቋሽሽና የዘረኝነት ይዘት ያለው ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር። ቪዲዮው ከፍተኛ ውዝግብ ከፈጠረ በኋላ ከገጹ ላይ እንዲጠፋ ተደርጓል።
የኦባማ ምላሽ እና የትራምፕ መከላከያ
* ባራክ ኦባማ፦ "የሀገሪቱ የፖለቲካ ንግግር ወደ ጭካኔ ደረጃ ወርዷል" ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ለፕሬዝዳንታዊ ቢሮ (Oval Office) ሊኖር የሚገባው ክብር እና ስርዓት እየጠፋ መምጣቱ እንደሚያሳዝናቸው ገልጸው፣ አብዛኛው አሜሪካዊ እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት "እጅግ አሳሳቢ" ሆኖ እንደሚያገኘው ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።
* ዶናልድ ትራምፕ፦ በበኩላቸው ምስሉን ያጋሩት የክለቡ ሰራተኛ መሆናቸውን እና እሳቸው ቪዲዮውን ሙሉ በሙሉ እንዳልተመለከቱት በመግለጽ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ፖለቲካዊ አንድምታው
ይህ ድርጊት በዲሞክራቶች ዘንድ ብቻ ሳይሆን በሪፐብሊካን ወገኖችም ጭምር ትችት እየቀረበበት ይገኛል። ኦባማ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፣ አሜሪካውያን አሁንም ቢሆን ጨዋነትን፣ ቅንነትን እና እርስ በእርስ መከባበርን እንደሚያስቀድሙ ያላቸውን ተስፋ አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #barackobama #donaldtrump #uspolitics #truthsocial #politicsnews #ethionews #የአሜሪካፖለቲካ #ዘረኝነትን_እንቃወማለን

✒️ በብዕር የተገነባ ጀግንነት - ሙጅብ አሚኖ! 🦁
#ethiopua | የዲጂታል ዘመኑ ፋና ወጊ... አጀንዳ ተቀባይ ሳይሆን አጀንዳ ሰጪ!
በዘመናዊው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ሙጅብ አሚኖ ተራ ተሳታፊ አይደለም፤ የሀሳብ የበላይነትን የጨበጠ እና የማህበረሰቡን ስነ-ልቦና የሚመራ የዘመኑ የብዕር ጀግና ነው።
ለምን ይለያል?
✅ አጀንዳ ሰጪነት:
ብዙዎች በሚወረወሩ አጀንዳዎች ሲነዱ፤ እርሱ ግን የሙስሊሙን ማህበረሰብ የልብ ትርታ በመረዳት አጀንዳ በመቅረጽ ቀዳሚ ነው።
✅ አመክንዮአዊ ምላሽ:
የጠላቶቹን የሀሳብ ምሽግ የሚያፈርሰው በጩኸት ሳይሆን፤ አመክንዮአዊ በሆነና በማያወላዳ የብዕር ምት ነው።
✅ ፅናት:
ለእምነቱና ለማንነቱ ያለው ፍቅር ከግል ጥቅሙና ከደህንነቱ በላይ ነው። ስሙንና ዝናውን ለቆመለት ዓላማ ጋሻ አድርጎ የጥላቻ ናዳዎችን በብቃት ይመክታል።
የሙጅብ ብዕር ለተገፉት አይንና ጆሮ፣ ለዲኑ ጠበቃ፣ ለተሳሳቱት ደግሞ የማረሚያ መውጊያ ነው። ስኬቱ የሚለካው በተቃዋሚዎቹ ብዛት ሳይሆን፤ በፈጠረው የንቃተ-ህሊና ለውጥ ነው።
ክብር ለእውነት ዘቦች! 🙌
Via የሙስሊም ወጣቶች ድምፅ በደሴ
#mujibamino #penhero #truth #digitalinfluencer #ethiopianmuslims #respect #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

ዶናልድ ትራምፕ የቭላድሚር ፑቲንን የኒውክሌር ስምምነት ማራዘሚያ ጥያቄ ውድቅ አደረጉ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን የስትራቴጂክ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ገደብ ለማራዘም ያቀረቡትን ጥያቄ ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ውሳኔ ያሳወቁት በሁለቱ ኃያላን አገራት መካከል የነበረው "ኒው ስታርት" (New START) የተሰኘው
የመጨረሻው የኒውክሌር መሣሪያ ቁጥጥር ስምምነት በይፋ ማብቃቱን ተከትሎ ነው።
የፕሬዝዳንት ትራምፕ አቋም
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦
* አሜሪካ የቀድሞውን ስምምነት ከማራዘም ይልቅ ለወደፊቱ ዘላቂ የሚሆን አዲስ እና ዘመናዊ ስምምነት ላይ ትኩረት ታደርጋለች።
* የኒውክሌር ባለሙያዎች ተቀናጅተው የተሻለና የተሻሻለ አዲስ ስምምነት እንዲያረቁ መመሪያ ሰጥተዋል።
የሩሲያ ጥያቄና ምላሽ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በስምምነቱ ቀድሞ የተቀመጠውን የ1,550 የስትራቴጂክ የኒውክሌር አረር (warheads) ገደብ በፈቃደኝነት ለማክበር ጥያቄ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ ከአሜሪካ ወገን ግን አዎንታዊ ምላሽ አላገኙም። ክሬምሊን በበኩሉ አሜሪካ ገንቢ ምላሽ የምትሰጥ ከሆነ አሁንም ለውይይት ክፍት መሆኑን ገልጿል።
የ"ኒው ስታርት" ስምምነት ታሪክና ስጋት
* እ.ኤ.አ. በ2010 ተፈርሞ በ2021 የተራዘመው ይህ ስምምነት፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የኒውክሌር ክምችት የሚገታ ብቸኛው ሕጋዊ ሰነድ ነበር።
* አሁን ላይ ስምምነቱ መቋረጡ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ የጦር መሣሪያ እሽቅድምድም ሊያስነሳ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት በብዙኃኑ ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አሜሪካ #ሩሲያ #ዶናልድትራምፕ #ቭላድሚርፑቲን #ኒውክሌር #ኒውስታርት #ዓለምአቀፍዜና

ዶናልድ ትራምፕ ኦባማን ዝንጀሮ አድርጎ የሚያሳይ ቪዲዮ በመልቀቃቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን እና ባለቤታቸውን ሚሼል ኦባማን እንደ ዝንጀሮ አድርጎ የሚያሳይ አወዛጋቢ ቪዲዮ በTruth Social ገጻቸው ላይ በመልቀቃቸው ከፍተኛ የዘረኝነት ውንጀላ እና ተቃውሞ እየደረሰባቸው ይገኛል።
በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተሰራው ይህ ቪዲዮ የኦባማን ጥንዶች ፊት በዝንጀሮዎች ላይ በመለጠፍ በጫካ ውስጥ ሲወዛወዙ ያሳያል። በቪዲዮው ላይ "The Lion Sleeps Tonight" የሚለው ዘፈን በስተጀርባ ይሰማል።
መጀመሪያ ላይ የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ጉዳዩን እንደ "የኢንተርኔት ቀልድ (Meme)" በመቁጠር ተቃውሞውን "የሐሰት ቁጣ" ስትል አጣጥላው ነበር። ሆኖም ከሁለቱም ወገን (ሪፐብሊካን እና ዲሞክራት) ጠንካራ ተቃውሞ በመነሳቱ ቪዲዮው ከገጹ እንዲጠፋ ተደርጓል።
ኋይት ሃውስ ቪዲዮው የተለቀቀው በሰራተኛ ስህተት መሆኑን ቢገልጽም፣ ትራምፕ ግን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ቪዲዮው እንዲለቀቅ መፍቀዳቸውን ገልጸው "የመጀመሪያውን ክፍል እንጂ መጨረሻውን አላየሁም" ብለዋል።
ሀኪም ጄፍሪስ (የዲሞክራቶች መሪ)፦ ትራምፕን "አደገኛ እና ዘረኛ" ሲሉ የገለጹ ሲሆን፣ ድርጊቱ የአሜሪካን ክብር የሚቀንስ መሆኑን ተናግረዋል።
የካሊፎርኒያ ገዢ ጋቪን ኒውሰም፦ "አስጸያፊ ድርጊት! እያንዳንዱ ሪፐብሊካን ይህንን ድርጊት ማውገዝ አለበት" ብለዋል።
ትራምፕ በቪዲዮው መጨረሻ ላይ ስላለው ምስል "ባውቅ ኖሮ ደስ አይለኝም ነበር" ቢሉም፣ ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ለመጠየቅ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም።

📌 በቪዲዮው ዙሪያ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ይዘቱ፦ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተሰራው ይህ ቪዲዮ የኦባማን ጥንዶች ፊት በዝንጀሮዎች ላይ በመለጠፍ በጫካ ውስጥ ሲወዛወዙ ያሳያል። በቪዲዮው ላይ "The Lion Sleeps Tonight" የሚለው ዘፈን በስተጀርባ ይሰማል።
የኋይት ሃውስ ምላሽ፦ መጀመሪያ ላይ የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ጉዳዩን እንደ "የኢንተርኔት ቀልድ (Meme)" በመቁጠር ተቃውሞውን "የሐሰት ቁጣ" ስትል አጣጥላው ነበር። ሆኖም ከሁለቱም ወገን (ሪፐብሊካን እና ዲሞክራት) ጠንካራ ተቃውሞ በመነሳቱ ቪዲዮው ከገጹ እንዲጠፋ ተደርጓል።
የጥፋተኝነት ውንጀላ፦ ኋይት ሃውስ ቪዲዮው የተለቀቀው በሰራተኛ ስህተት መሆኑን ቢገልጽም፣ ትራምፕ ግን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ቪዲዮው እንዲለቀቅ መፍቀዳቸውን ገልጸው "የመጀመሪያውን ክፍል እንጂ መጨረሻውን አላየሁም" ብለዋል።
🗣️ የተሰጡ አስተያየቶች፦
ሴናተር ቲም ስኮት (ሪፐብሊካን)፦ "ይህ ከዚህ ኋይት ሃውስ ያየሁት እጅግ የከፋ የዘረኝነት ድርጊት ነው።"

ትራምፕ ካናዳ ከቻይና ጋር የንግድ ስምምነት የምታደርግ ከሆነ፣ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ማናቸውም የካናዳ ምርቶች ላይ የ100 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ አስታወቁ
የቁጣው መንስኤ፦ ካናዳ ቻይናን እንደ "መሸጋገሪያ ወደብ" (transshipment port) በመጠቀም የቻይና ምርቶች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ካደረገች ከፍተኛ ዋጋ እንደምትከፍል ትራምፕ አስጠንቅቀዋል።
"ቻይና ካናዳን ትውጣለች"፦ ትራምፕ በTruth Social ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ "ቻይና ካናዳን ሙሉ በሙሉ ትውጣለች፤ የንግድ ተቋሞቿንና ማህበራዊ መሰረቷንም ታፈርሳለች" ብለዋል።
የመሪዎች ፍጥጫ፦ በትራምፕ እና በካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ መካከል ያለው ግንኙነት እየተሻከረ መጥቷል። ትራምፕ ካናዳ "የምትኖረው በአሜሪካ እርዳታ ነው" በማለት ተናግረዋል።
የግሪንላንድ ጉዳይ፦ ትራምፕ ግሪንላንድን የአሜሪካ ግዛት ለማድረግ ያላቸው ፍላጎትና ካናዳ የአሜሪካ 51ኛ ክፍለ ሀገር እንድትሆን ያቀረቡት ሀሳብ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ አክሮታል።

7 months ago
ትራምፕ ለኢራን ተቃዋሚዎች፦ "እርዳታ በመንገድ ላይ ነው፤ ተቋማቱን ተቆጣጠሩ!"
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ አስመልክቶ ለተቃዋሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ እርዳታ በመንገድ ላይ መሆኑን በመግለጽ የኢራን ዜጎች የመንግስት ተቋማትን እንዲቆጣጠሩ ጥሪ አቀረቡ።
ፕሬዝዳንቱ ማክሰኞ እለት የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው (Truth Social) ባስተላለፉት መልዕክት፣ "የኢራን የሀገር ፍቅር ስሜት ያላችሁ ዜጎች ሆይ፤ ተቃውሞአችሁን ቀጥሉ፣ ተቋማቶቻችሁንም ተቆጣጠሩ - እርዳታ በመንገድ ላይ ነው!" ብለዋል።
ትራምፕ ቀደም ሲል ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንዳላቸው ሲገልጹ የቆዩ ቢሆንም፣ አሁን ግን በዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ ተከትሎ ሃሳባቸውን የቀየሩ ይመስላል።
ፕሬዝዳንቱ በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለው "ትርጉም የለሽ ግድያ" እስካልቆመ ድረስ፣ ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ማንኛውንም አይነት ስብሰባ መሰረዛቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
ትራምፕ በሰልፈኞች ላይ ጥቃት የሚያደርሱ የመንግስት አካላትን አስመልክቶ ባስተላለፉት ማስጠንቀቂያ፣ "የገዳዮችንና የአንገላታቾችን ስም መዝግባችሁ ያዙ፤ ከፍተኛ ዋጋ ይከፍላሉ" ሲሉ ዝተዋል።
ዋሽንግተን ለኢራን ተቃዋሚዎች የምትልከው እርዳታ ምን እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ በዝርዝር ባይገልጹም፣ ንግግራቸው ግን አሜሪካ በኢራን ጉዳይ ላይ ያላትን አቋም ወደ ጠንካራ እርምጃ እየቀየረች መሆኑን አመላካች ነው ተብሏል።

ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸውን የቬንዙዌላ "ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት" አድርገው ሰየሙ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገጽ (Truth Social) ላይ ባሰፈሩት መረጃ፣ ራሳቸውን የቬንዙዌላ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን ገለጹ።
ትራምፕ የተጠቀሙት ምስል በዊኪፔዲያ (Wikipedia) ገጽ ላይ የተደረገ የሚመስል ኤዲቲንግ ሲሆን፣ በውስጡም ከ45ኛው እና 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንትነታቸው በተጨማሪ፦ "የቬንዙዌላ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት - ከጃንዋሪ 2026 ጀምሮ በስልጣን ላይ ያሉ" የሚል ማዕረግ ተቀምጦባቸዋል።
ይህ ያልተጠበቀ እርምጃ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያና መላምት ፈጥሯል። ሆኖም የሕግ ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት፣ ይህ ማዕረግ በዓለም አቀፍ ሕግም ሆነ በቬንዙዌላ ሕገ-መንግሥታዊ ሰነዶች ውስጥ ምንም ዓይነት ሕጋዊ መሠረት የለውም።

ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸውን የቬንዙዌላ "ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት" አድርገው ሰየሙ
#ethiopia | የቀድሞው (ወይም ተመራጩ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገጽ "ትሩዝ ሶሻል" (Truth Social) ላይ ራሳቸውን የቬንዙዌላ ጊዜያዊ መሪ አድርገው የሚያሳይ ምስል መለጠፋቸው በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ላይ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
🇻🇪 የዋሽንግተን እና የካራካስ ፍጥጫ
ይህ የትራምፕ እርምጃ ዋሽንግተን በቬንዙዌላ (ካራካስ) ፖለቲካ ላይ ያላትን ጥልቅ ጣልቃ ገብነት በግልጽ የሚያሳይ ነው ተብሏል። አሜሪካ ከሳምንት በፊት በኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዷ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የላቲን አሜሪካን የነዳጅ ፖለቲካ በቀጥታ ለመቆጣጠር ፍላጎት እንዳላት እየታየ ነው።
⚠️ አዲስ የፖለቲካ ስጋት
ምንም እንኳን የማዱሮ ምክትል የነበሩት ዴልሲ ሮድሪጌዝ የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ተደርገው ቢሾሙም፣ ትራምፕ ራሳቸውን እንደ መሪ አድርገው ማቅረባቸው በሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል። ይህ ድርጊት አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የራሷን አሻንጉሊት መንግስት ለመመሥረት ወይም ቀጥተኛ ቁጥጥር ለማድረግ እያሰበች እንደሆነ አመላካች ነው ተብሏል።
🗺️ የላቲን አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ጫና
ትራምፕ በቬንዙዌላ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በጎረቤት ሀገራት ላይም የሚከተሉትን እርምጃዎች እየወሰዱ ይገኛሉ ተብሏል፦
* ኩባ እና ኮሎምቢያ፦ በእነዚህ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በማድረግ የቀጠናውን ፖለቲካ ለመቀየር እየሰሩ መሆኑ ይነገራል።
* የነዳጅ የበላይነት፦ የቬንዙዌላን ግዙፍ የነዳጅ ክምችት ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት የአሜሪካ የኢኮኖሚ ስትራቴጂ አካል ተደርጎ ተወስዷል።
ይህ ያልተለመደ የትራምፕ ፖለቲካዊ "ቪዲዮና ምስል" በዓለም አቀፍ መሪዎች ዘንድ ምን ዓይነት ምላሽ ሊያስከትል እንደሚችል በጉጉት እየተጠበቀ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ትራምፕ #ቬንዙዌላ #ማዱሮ #ነዳጅ #አሜሪካ #ላቲንአሜሪካ #የዓለምፖለቲካ #trump #venezuela #breakingnews

በአሜሪካ በድጎማ የሚኖሩ ብዙ ስደተኞች ያሏቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት
1)- ሶማሊያ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 71.9%
2)- ኮንጎ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 66.0%
3)- ጊኒ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 65.8%
4)-ቶጎ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 52.9%
5)- ኤርትራ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 52.7%
6)- ደቡብ ሱዳን - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 52.0%
7)- ላይቤሪያ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 48.9%
8)- አልጄሪያ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 48.1%
9)- ሊቢያ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 47.8%
10)- ኢትዮጵያ - ድጎማ የሚቀበሉ የስደተኛ ቤተሰቦች፡ 47.6%
ምንጭ፡ ዶናልድ ትራምፕ (Truth Social)

Comments