ዶናልድ ትራምፕ ዝነኛውንና አስፈሪውን የአልካትራዝ እስር ቤት በቢሊዮኖች በሚቆጠር ወጪ ዳግም ሊያስከፍቱ ነው
የኔታ ሚዲያ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሁኑ ወቅት የቱሪስት መስህብ ሆኖ እያገለገለ የሚገኘውን ዝነኛውን "አልካትራዝ" (Alcatraz) እስር ቤት በዘመናዊ መልኩ ዳግም ስራ ለማስጀመር የ152 ሚሊዮን ዶላር በጀት ጠየቁ።
ትራምፕ በ Truth Social ገጻቸው እንደገለጹት እስር ቤቱ ዳግም የሚከፈተው የአሜሪካ እጅግ ጨካኝና አደገኛ ወንጀለኞችን ለማሰር ታስቦ ነው።
ይህ የ152 ሚሊዮን ዶላር ጥያቄ ለ2027 የፈረንጆች በጀት ዓመት የቀረበ ሲሆን እስር ቤቱን እጅግ ዘመናዊና አስተማማኝ ለማድረግ የሚውል ነው።
ይህም በአጠቃላይ ለማረሚያ ቤቶች ቢሮ ከተመደበው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የሚካተት ነው።
ዘ ሮክ" (The Rock) በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀውና በሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ላይ የሚገኘው ይህ እስር ቤትንእንደ አል ካፖን ያሉ ዝነኛ ወንጀለኞች የታሰሩበትና በፊልሞችም ጭምር የሚታወቅ አስፈሪ ስፍራ ነው።
ይህ የትራምፕ እቅድ በካሊፎርኒያ ፖለቲከኞች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እየቀረበበት ነው። የቀድሞዋ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ እቅዱን የማይረባና የህዝብን ገንዘብ ማባከን ስትል ነቅፋዋለች።
ደሴቱ ላይ በአሁኑ ወቅት የቧንቧ ውሃና የፍሳሽ ማስወገጃ የሌለ ሲሆን ማንኛውም አቅርቦት በጀልባ መጓጓዝ ይኖርበታል።
እስር ቤቱ እ.ኤ.አ በ1963 ከመዘጋቱ በፊት ከማንኛውም የፌደራል እስር ቤት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ወጪ ይጠይቅ ነበር።
በአሁኑ ወቅት በብሔራዊ ፓርክ አገልግሎት ስር የሚገኘው አልካትራዝ በዓመት 60 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለሀገሪቱ ያስገኛል።
ይህ አወዛጋቢ የፕሬዝዳንቱ እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን በአሜሪካ ኮንግረስ መፅደቅ ይኖርበታል።

2 months ago