በስሜታችሁ ላይ ብቻ አትመኩ!
ብዙዎቻችን "ልብህ የሚልህን ስማ" የሚለውን ምክር እንደ ወርቅ እንቆጥረዋለን። ግን ስነ-ልቦና ባለሙያው ሳቻ ባቺም በአዲሱ መጽሐፉ ላይ እንደሚለው ከሆነ፣ ስሜቶቻችን ሁልጊዜ እውነተኞች አይደሉም፤ አንዳንዴም ክፉኛ ያታልሉናል።
ስለ ስነ-ልቦና የምናምናቸውን 4 የተሳሳቱ አመለካከቶች እስቲ እንያቸው፡
"ስሜት አይዋሽም"
ለምሳሌ አስፈሪ ፊልም ስታዩ ልባችሁ ይመታል፣ ትፈራላችሁ። ምንም እንኳን አደጋ እንደሌለ ብታውቁም ስሜታችሁ ግን "አደጋ አለ" ይላችኋል። ስሜት እንደ አየር ሁኔታ ተለዋዋጭ ስለሆነ ሁልጊዜ እውነት ነው ብላችሁ አትደምድሙ።
መፍትሄ፡ የሚሰማችሁን ስሜትና ምክንያቱን ለይታችሁ እወቁ። "አሁን የሚሰማኝ ፍርሃት/ጭንቀት ከእውነታው ጋር ይገጥማል?" ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ።
2. "ውጥረት ስራ ያቀላጥፋል"
አንዳንዴ ለጥቂት ጊዜ መወጠር ንቁ ሊያደርገን ይችላል። ነገር ግን "ውጥረት ውስጥ ስሆን በደንብ እሰራለሁ" ብሎ ማመን ስህተት ነው። በሂደት አቅማችን እንዲደክም እና እንድንዝል ያደርገናል።
መፍትሄ፡ ከመጠን በላይ መልፋት ውጤታማ እንደማያደርግ ተረድታችሁ፣ አቅማችሁ ሲዝል እረፍት ውሰዱ።
3. "መጨነቅ አስፈላጊ ነው"
ስለ ነገው አየር ንብረትም ይሁን ስለ ጤናችን መጨነቅ ውጤቱን አይለውጠውም። እንዲያውም አብዛኛው የምንጨነቅላቸው ነገሮች በጭራሽ አይከሰቱም።
መፍትሄ፡ "የጭንቀት ጊዜ" መድቡ (ለምሳሌ በቀን 15 ደቂቃ)። ከዚያ ውጭ ጭንቀት ሲመጣ "አቁም!" በማለት ለሌላ ስራ ትኩረት ስጡ።
4. "ሁኔታዎችን መቀበል እጅ መስጠት ነው"
የማይለወጥን ነገር (ለምሳሌ የፍቅር ግንኙነት ማብቃቱን ወይም አቅምህን የሚበልጥ ስራን) አምኖ መቀበል መሸነፍ አይደለም። ይልቁንም ለውስጥ ሰላም እና ወደፊት ለመራመድ ትልቁ መንገድ ነው።
ማጠቃለያ፡ ስሜታችሁን መርምሩ እንጂ በጭፍን አትከተሉት!
👉ይህ ጽሁፍ የተወሰደው "The Truth About Feelings" (በጀርመንኛ "Gefühle sind keine Tatsachen") ከተሰኘው የስነ-ልቦና ባለሙያው ሳቻ ባቺም መጽሐፍ ነው።

6 months ago