2 months ago
''በ48 ሰዓታት ውስጥ ሆርሙዝን ካልከፈታችሁ የኃይል ማመንጫዎቻችሁን አመድ እናደርጋቸዋለን"
#ethiopia | ፕሬዝዳንት ትራምፕ በራሳቸው የትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገፅ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኢራን የዓለም የነዳጅ መስመር የሆነውን የሆርሙዝ ባህርን በ48 ሰዓታት ውስጥ ለትራንስፖርት ክፍት ካላደረገች፣ የአሜሪካ ጦር በሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል።
"ኢራን በ48 ሰዓታት ውስጥ የሆርሙዝ የባህር በርን ካልከፈተች፣ የአሜሪካ ጦር የኢራንን የኃይል ማመንጫዎች በመምታት ከጥቅም ውጭ ያደርጋቸዋል" — ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ጥቃቱ የሚጀምረው በሀገሪቱ ካለው ትልቁ የኃይል ማመንጫ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ይህ እርምጃ የዓለምን የነዳጅ ገበያ ለማረጋጋትና የአሜሪካን ጥቅም ለማስከበር የሚወሰድ እንደሆነ አመልክተዋል።
የተተነበዩ የጥቃት ኢላማዎች
ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚገምቱት፣ ትራምፕ "ትልቁ ማመንጫ" ሲሉ የጠቀሱት፦
* የቡሼህር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ወይም
* በቴህራን አቅራቢያ የሚገኘውን ግዙፉን የዳማቫንድ የኃይል ጣቢያን ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢራን ምላሽና የዓለም ስጋት
በሌላ በኩል ቴህራን ለአሜሪካ ማስፈራሪያ ምላሽ ለመስጠት አልዘገየችም። ማንኛውም ዓይነት ጥቃት በአሜሪካ በኩል ከተሰነዘረ፣ በአካባቢው በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችና ጥቅሞች ላይ "ፈጣንና ከባድ" አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።
ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው የቃላት ጦርነትና ወታደራዊ ዝግጅት፣ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ከማድረጉም በላይ ቀጣናውን ወደ ለየለት ጦርነት ሊከተው ይችላል በሚል ዓለም በከፍተኛ ስጋት ሰኞ ምሽት የሚጠናቀቀውን የጊዜ ገደብ እየተጠባበቀ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #trump #iran #middleeasttension #hormuzstrait #breakingnews #globaloilmarket #usa #geopolitics