Logo
YenetaTube
ትራምፕ ዩናይትድ ኪንግደም እና ቻይና የጦር መርከቦችን ወደ ሆርሙዝ ስትሬት እንደሚልኩ ተስፋ አደርጋለሁ አሉ።

የኔታ ሚዲያ

ዶናልድ ትራምፕ በ "Truth Social" ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የሆርሙዝ ስትሬትን ለመጠበቅ በርካታ ሀገራት የጦር መርከቦችን እንደሚልኩ ገልጸዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ከእነዚህ ሀገራት መካከል እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

እስከዚያው ድረስ ግን ዩናይትድ ስቴትስ የባህር ዳርቻውን በቦምብ ትደበድባለች እንዲሁም የኢራን ጀልባዎችንና መርከቦችን በየተራ ከውሃው ላይ እየመታች ታሰጥማለች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በቅርቡ የሆርሙዝ ስትሬትን በእጃችን እናስገባለን ሲሉ ገልፀዋል

ዩናይትድ ኪንግደም ግን ወደ የውሃ መስመሩ መርከቦችን እንደምትልክ እስካሁን የሰጠችው ፍንጭ የለም።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.